በ” ጋዲሳ ሆገንሳ ኦሮሞ ” በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

“ጋዲሳ ሆገንሳ ኦሮሞ ” በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ አውጥቷል።

በአንድ ጥላ ስር የተሰባሰበው የኦሮሞ አመራር በትናንትናው እለት ያካሄደው ስብሰባ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በግልፅና በስፋት በመምከር በስኬት መጠናቀቁን በመግለጫው አስታውቋል።

በውይይቱም በኦሮሞ የፖለቲካ ሀይሎች መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ በውይይት ከመፍታት ባለፈ አንዱ በአንዱ ላይ ዘመቻ መክፈት ለማንም እንደማይጠቅም ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል።

“አሁን ያለንበት ወቅት በጣም ወሳኝ በመሆኑ እያንዳንዱ እርምጃ የኦሮሞን ህዝብም ሆነ የሀገሪቱን ብሄር ብሄረሰቦች የነገ ተስፋ ወደ ብርሃን የሚያሻግር አልያም ለከፍተኛ አደጋ ሊዳርግ የሚችል” መሆኑን መመልከቱንም ገልጿል።

በስብሰባው ከዚህ ቀደም እንደዚህ አይነት በአንድ ጥላ ስር የተሰባሰበው የኦሮሞ አመራር ቢኖር ኖሮ በመካከላቸው ያለው ጥርጣሬ ዛሬ ያለበት ደረጃ ላይ እንደማይደርስም ነው ያስታወቀው።

ካሁን በኋላ ግን በአንድ ጥላ ስር የተሰባሰበው የኦሮሞ አመራርን በማጠናከር በመካከላቸው ለተፈጠሩ እና ለሚፈጠሩ ችግሮች በጋራ በመሆን መፍትሄ የማፈላለግ ስራ እንደሚሰራም አንስቷል።

በተጨማሪም ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲ አንድ የሚያደርገው ጉዳይ የኦሮሞን ህዝብ እና የሀገሪቱን ብሄር ብሄረሰቦች ጥቅም ማስጠበቅ እንደመሆኑ አሁን ያለውን ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝም ስርዓት ለማጠናከር እና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ መስራት ይጠበቃልም ብሏል።

እኩልነት፣ ነፃነት እና የህዝቦች ወንድማማችነት የተረጋገጠበት እንዲሁም ዴሞክራሲ ያበበበት እውነተኛ ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝም ስርዓት እንዲተገበር ለማድረግ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በመስማማት አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።

በአጠቃላይ በኦሮሚያ ክልል የሚስተዋሉ የሰላም ችግሮችን እንዲሁም ከሰሞኑ በክልሉ ለተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች መንስኤ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግም፤ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የስራ ክፍፍል አድርጓል።

እንዲሁም መጭው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ እንዲሆን ምን አይነት መንገድ መከተል እንዳለባቸው የሚያሳይ አጭር ጥናት ከተካሄደ በኋላ ሰፊ እና ጥልቅ ውይይቶችን በማካሄድ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በጋራ ለማስቀመጥም ውሳኔ አሳልፏል።

እንደ ሀገር የተጀመረውን ለውጥ በጠንካራ እና አስተማማኝ መሰረት ላይ ለማቆም ከሁሉም የሀገሪቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ቀጣይነት ያለው ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማመንም፥ በሀገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ ከሁሉም የፖለቲካ ሀይሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር በጋራ መስራት የሚቻልባቸውን ሁኔታዎች መፍጠር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር ለማድረግም ተስማምተዋል።

ጋዲሳ ሆገንሳ ኦሮሞ

(ኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ)

2 Responses to በ” ጋዲሳ ሆገንሳ ኦሮሞ ” በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ

 1. OLF ( Oromo Liberation Front) is defeating Abiy’s military since many of Abiy’s soldiers deserted rather than fight against OLF .

  OLF is heading to the Capital of Oromia regional state , city of Addis Ababa which also at the same time happens to be the Capital of the country of Ethiopia , Addis Ababa .

  Abiy’s military is begging Amara districts military militias to help him but they seem to be non cooperating. The Amara militias are not willing to fight against OLF , Amara are saying no to Abiy’s call for help to fight OLF . It is expected for Abiy to swallow his pride and call on TPLF for help next. Abiy is in dire need of a quick reinforcement if he don’t get it he might loose this war with not having another chance to fight again.

  Avatar for MeG

  MeG
  November 5, 2019 at 11:20 pm
  Reply

 2. ስለሀገር ያስባሉ የተባሉት ስለሰፈር አንድነት እያወሩልን ነው ጀለሶቼ ለዛውም ከነ ጀዊ ጋር !! ይቺናት ኢትዮጵያ !! እርፍ አሉ እማማ አስካሉ ሞባይላቸው የተሰረቀባቸው እለት !!!!

  Avatar for pitohu bucher

  pitohu bucher
  November 6, 2019 at 1:08 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.