ተቀምጠው የሰቀሉት…………! ከታምራት ይገዙ

1 min read

ሰሞኑን የጠቅላይ ሚንስትራችንን የሰላም ኖቤል ሽልማትና የፓርላማው ንግግራቸው የኦሮሞ አክራሪ አክ ቲቭስቶችንና የድርጅት መሪዮችን ከማስቆጣት አልፎ አቶ ታዪ ደንደአ እንዳስነበቡን ሆነ የተለያዩ የአለም ሚዲያዎች እንደ ዘገቡት “ህይወታቸው በጨካኖችና በአረመኔዎች የጠፋው 67 ሰባት ሲሆን በከባድ ሁኔታ የተጎዱት ደሞ 218 ናቸው ይህ አሳዛኝ ወንጀል ባለቤት ሊያገኝ ይገባዋል።

” በማለ ዝምታቸውን አቶ ታዪ ደንደአ ሰብረዋል፡፡

ስሰማ ያደኩት “በጥቅምት አንድ አጥንት” የሚል የወላጆች አባባል ነበር በዘንድሮ የጥቅምት ወር ግን ከአገ ራችን ከኢትዮጵያ እየተሰማና እየታየ ያለው የእልቂት ከበሮ ሲጎሰመና የሰላማዊ ኢትዮጵያኑች ደም እንደ ጎር ፍ ሲፈስ ነው የዚህም ዋናው ተጠያቂ ማን እንደሆነ አቶ ታዪ ደንደአ በፊስ ቡካቸው ላይ ለጠፋውህይወ ትለተጎዳውለቆሰለውወገንለጠፋውንብረትተጠያቂውጀዋርነው የሚልአስነብበዋል፡፡

በአገራችን እየሆነ ያለው የህዝባችን ደም መፍሰስ አቶ ጀዋርም ይሁኑ የእርሳቸው የቅርብ ሰዎች ውክልና ሳ ይሰጣቸው የወከለንና የምንወክለው ህዝባችን እያሉ የራሳቸውን የስልጣንና የጥቅም አራራቸውን ለማሳካ

 • በወጉ እሳት የመታው ሽሮ ጠግቦ ያልበላውን የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን በአጠቃላይ ተመች ቶት ያላደገውን ኢትዮጵያዊ ወጣት የእሳት እራት እያደረጉት ይገኛል ይህ ደሞ እየተደረገ ያለው ጠቅላይ ሚ ንስትራችን ዶ/ር አብይ አህመድ የሰላም ተሸላሚ በሆኑ በቀናት ውስጥ መሆኑ የሀገራችን ህዝብ ሆነ ሽልማ ቱን የሰጣቸውንም ክፍል አጀብ የሚያስብል ነው ብል መሳሳት አይሆንም፡፡ ለአርስት የመረጥኩት “ተቀምጠው የሰቀሉት ቆመው ለማውረድ ይቸግራል” የሚለውን የአበው አባባል ያ ስታወሰኝ አቶ ጀዋር ከየት ተነስተው አሁን የት እንደደረሱ ስመለከት ነው::

መጀመሪያ “እዚ ሀገር ሁለት መንግስት ነው ያለው የአብይና የቄሮ(የኔ) አለ ይህን ግዜ ከጠቅላይ ሚንስትራችንም ሆነ ከጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰማነው ነገር ሳይኖር በዝምታ ታለፈ፡፡ ሲቀጥል ሀገ መንግስት በዝምታ ያገነነው ኢመደበኛው የጀዋር መንግስት በንግግር ብቻ ሳይወሰን ውሳኔዎችን መሻርና ማሳለፍ የርሱ ድርሻ ሆኖ ሲቀጥል ጠቅላይ ሚንስትራችንም ሆኑ አቃቤ ህጉ አሁንም ዝምታን መረጡ፡፡ ያን ግዜ አቶ ጀዋርም መንግስትነቱ ተርጋገጠለት፡፡ እነሆ ባሳለፍነው ሳምንት ለውጡ በመጣባቸው ጥቅመኛ የምንግስት ሰዎችና የህወሀት ባለስልጣኖችና እንዲሁም በአኩራፊዎች በተቀነባበረ ሴራ ኢመደበኛው መንግስታችሁ ሊገረሰስ ነው ተባለ በተጨማሪም የመግደል ሙከራ ሊደረግብኝ ነው በሚል የፈጠራ ወሬ ስልሳ ሰባት ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን ላልተገራው ኢመደበኛ ስልጣኑ ይደላደል ምሽጉም ይጠንክር ዘንድ ምንም የማያቁት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን መስዋዐት ሆነው ቀረቡለት፡፡ በነዚህ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ አገዳደል በአሁኑ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን በአገራችን ሊደረግ አይደለም ሊታሰብ የማይገባ አስቀያሚ ድርጊት ነው፡፡ ይህን ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር አብይም ሆኑ አቃቤ ህጉ ዝም አይሉም ብለን ስናስብ ሁለቱም የጋን ውስጥ መብራት ሆነው አረፉት፡፡

እኔ እንድ አንድ ኢትዮጵያዊ መንግስትንም ሆነ አሊያም ኢትዮጵያዊ ነን የሚሉ የኦሮሞ ልሂቃን፤ ኢትዮጵያዊ ነን የሚሉ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና ተከታዮቻቸው እንዲመልሱልኝ የምጠይቃቸው

ይህ የመርህ መጣስ መቼ ነው የሚቆመው እናንተ ባላቹሁበት አገር ይህን አይነት አሰቃቂ እልቂት እንዴት ደረስ? ከደረሰም ባሃላ ምን እርምጃ ልትወስዱ አሰባችሁ? ለግል ስልጣኑ፡ ለግል ንብረቱ እና ለግል እውቅና በመቆመጥ በአገራችን የርስ በርስ ጦርነት እንዲጀመር ሌት ተቀን የሚሰራውን አቶ ጀዋር መቋጫ ልታበጁለት አይገባም ወይ?፡፡ ያ ሳይሆን ቀርቶ ወደ አላስፈላጊ ችግር ውስጥ ከተገባ በአገራችን አሸናፊና ተሸናፊ ወደ ሌለው ብጥብጥ የምንገባ አልመሰላችሁም ወይ?፡፡

በሌላ በኩል የክብር ጠቅላይ ሚንስትር አብይ መንግስት መደበኛ መንግስትነቱን ያረጋግጥ ካላረጋገጠ የምንገዛው ተጠያቂነት በሌለው ኢ- መንግስታዊ ክፍል ስለሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱንና ሀገራችንን ለመከላከል በአስቸኮይ ይደራጅ ያን ግዜ ለራሱ አይደለም ለሌሎች የሚተርፍ አቅምና ጉልበት ይኖረዋል፡፡ ያ ግን ለማንም አይበጅም፡፡

በአጠቃላይ ይህ እንዳይሆን የህግ የበላይነት ይከበር ጠቅላይ ሚንስትር አብይም የመንግስትነትን ሃላፊኖቶትን የመወጣት ግዴታዎት ነውና የአገራችን የኢትዮጵያ እንዲሁም የህዝቦቾን ድህንነት በስርአቱ ያስከብሩ ዘንድ በአክብሮት አሳስባለው!

በተጨማሪ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ የተሾሙት የአቃቤ ህግ ወንጀለኛ እና ዘረኞችን አገር በጥባጮችን ለህግ የማያቀርቡ ከሆነ የወንጀሎችና የዝረኞች ተባባሪ ነው መባሉ አይቀሬ ነው። በአቃቤ ህጉ ስህተት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከትችትና ከወቀሳ እንደማያልፉ ሊገነዘቡ ይገባል።

በኔ እምነት የጠቅላይ ሚንስትራችን የዶ/ር አብይ መንግስት ሰላም ለማስፈን ቁርጠኝነቱ እንጂ የጎደለው አቅም የሚያንሰው አይመስለኝም። የሀገራችን ሰላም መሆን ለሁላችንም ነው። መንግስት ፍላጎቱ ካለው የዘረኞችን እና አገር በጥባጮችን ለመኮነን በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ፀረ ዘረኞች የሆነ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፎችን ማዘጋጀት ይችላል። በውጪም ሀገራት የምንኖር ኢትዮጵያውያን ከወትሮው ለየት ባለ መንግድ የውጪ አገር የመኖሪያ ፍቃድ ይዘው አገራችን ውስጥ የማያባራ እልቂት እንዲጀመር የሚያደርጉትን በሚኖሩብርት ሀገር ህግና ደንብ እንዲዳኙ ለህግ ፊት ማቅረብ ይቻላል የሚል እምነቱ አለኝ።

ከአንድ አመት በፊት ለትግሉ ትልቅ ድጋፍ የነበረው “ቄሮ” በአክራሪ የኦሮሞ ግለሰቦችና ድርጅቶች ተጠልፎል ቢባል ከእውነታው መራቅ አይሆንም። ከአመት በፊት በ“ቄሮ” ስም ፀረ ሰላም የሆነ ሀይል ይነሳል ብሎ ያሰበ አልነበረም አሁን አሁን ግን ነገሩ ግልፅ እየሆነ እንደሚታየው በቄሮ ስም የሚነግደው አቶ ጀዋር የኦሮሞ ወንድሞቻችንን ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ወንድሙ ጋ የማያባራ ግጭት ውስጥ ሊያስገባው ዳር ዳር እያለ ነው። በአሁን ሰዓት መንግስት ሰላሙ የታወከበትን ህዝቡን ካላስተባበረውና በዘረኞች አደጋ እንዳይደርስበት ዋስትና ካልሰጠው ህዝቡ ራሱ ተደራጅቶ ወደ አደባባይ መትመሙ እይቀሬ ይሆናል።

ሁላችንም እንደምናስታውሰው ከመንፈቅ በፊት ከተለያዩ የኦሮምያ ክፍሎች ያሉ ወንድሞቻችን ደረሰባቸው በተባለው የተለያየ ምክንያቶች ወደ አዲሳባ መጥተው በተለያዩ ክፍሎች እንዲሰፍሩ ሲደረግና መታወቅያ ሲታደላቸው የተለያዩ ክፍሎች በተለይ የባልደራሱ በለአደራ ምክር ቤት ይህ ትክክል አይደለ ም የማታ የማታ ዋጋ ያስከፍላል ሲሉ አድማጭ አላገኙም ነበር::

ያሉት አልቀረም ይህው ጠቅላይ ሚንስትራችን የሰላም ተሸላሚ በሆኑ በቀናት ውስጥ ችግሩ አይን አፍጥጦ መጣ በዛ ወቅት የተባለው ቁጠር ተጋኖል አሊያም እናንተ ፈቃዳችሁ ነው ይህን ያህል ህዝብ የሰፈረው በ ማለት ነገሩን ከማጣጣል እነዚህን የኦሮሞ ወንድሞቻችን ከየትኛው ክፍል ነው የመጡት የት የት ቦታ ነው እንዲሰፍሩ የተደረጉት ከኖሪዎቹ ጋር ምን ኣይነት ስነ ልቦና አላቸው ይህንንስ የሚዘውረውና መመሪያ የሚ ሰጣቸው ክፍል ማነው ብሎ ማሳብ ተገቢ ነበር ምክንያቱም በሰሞኑ የይድረሱልኝ ጥሪ ከየአካባቢያቸው

ተሰባስበው የተግናኙትና በሰውና በንብረት ላይ አደጋ ያደረሱት ባብዝኛዎቹ እነዚህ በአቶ ጀዋር መዋቅር ው ስጥ የሚገኙት የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ነቸው መልዕክትም የሚቀበሉት ከመንግስት ሳይሆን የ ተሳሳተ መንገድ እየመራቸው ካለው ከአቶ ጀዋር ነው ብል መዋሸት አይደለም፡፡

መካሪ የሌለው ንጉስ ያለ ኣመት አይነግስይሉ ዘንድ ጠቅላይ ሚንስትር አማካሪ ያጡ ይመስል አቶ ጀዋርን የግላቸው አማካሪ አድርገው ማስቀመጣቸው በሬ ከአራጁ ይውላል የሚለውን የአበውን አባባ

 • የሚያስታውሰን ስንቶቻችንን ይሆን? እኔ እንደ አንድ ተራ ኢትዪጵያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን በምክ ንያት እደግፋለው በምክንያት ደሞ ከመውቀስ ወደኾላ የሚያደርገኝ አንዳችም ሃይ የለም ብዪ አምናለው፡፡

እንደማንኛውም ሀገር እና ህዝብ ወዳድ ኢትዮጵያዊ ለጠቅላይ ሚንስትር ያለኝ ጥያቄ እንደሚከተው ነው፡፡

 • ክብር ጠቅላይ ሚንስትር አብይ

ምን ያህል የአገራችን ህጻናትና ታዳጊ ልጆች መሞት አለባቸ እርሶ ከህግ በላይ የሆኑትን ግለሰቦች ህግ ፊት እ ንዲቀርቡ ለማደረግ? ምን ያህል ያገራችን ወጣቶች መሞት አለባቸው እርሶ ወንጀሎኞችን ህግ ፊት ለማቅረ ብ? ምን ያህል ህረገውያን አባቶቻችንና እናቶቻችን መሞት አለባቸ በአገራችን በኢትዮጵያ የህግ የበላይነትን ለማስከበ? ምን ያህል የኢትዮጵያ ህዝብ ማለቅ አለበት “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ” ብለው የተናገሩትን ቃሎትን ለመጠበቅ?

 • የአገራችን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትርና የጦር ሀይሎች

ጠቅላይ አዛዥ በመሆኖት አርሶ በአሁኑ ሰኣት በአገሮትና በአገራችን ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም የከፋ አደ

ጋ በታሪክም ሆነ በትውልድ ተወቃሽ እንዳይሆኑ ስጋቴ ነው፡፡

ስለሆነም የህግ የበላይነትን ለማስከበርና የተገደሉት ኢትዮጵያኖች ደማቸው ደመ ከልብ ሆኖ

እንዳይቀር ይህ አሰቃቂ አደጋ እንዲነሳና እንዲደርስ ያደረጉ ግለሰቦችም ይሁኑ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዋች በአስቸኮይ በህግ ፊት እንዲቀርቡ ማድረግ ይጠበቅቦታል ያ ሳይሆን ቢቀር ከላይ ለማለት አንደፈለኩት በታ ሪክና በትውልድ እርሶ ብቻ ሳይሆኑ ከአብራኮት የተፈጠሩት ልጆቾትም ጭምር ያለጠፋታቸው ሲወቀሱና በ የትኛውም ኣለም ቢኖሩ የፖለቲካ እስረኛ ሆነው እንደሚኖሩ አይጠራጠሩ ስለ ሆነም መቼ ነው የህግ የበላይነትን ለመስከበር ቆርጠው የሚነሱት? የሚል ጥያቄ በአክብሮት አቀርባለው፡፡

በሌላ በኩል ደሞ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እርሶን የአገራችን ጠቅላይ ሚንስቴርና የጦር ሃይሎች አዛዥ መሆኖትን እንጂ አምኖ የተቀበለው የማህበራዊ ህይወት አማካሪ (social worker counsellors’) ኖት ብሎ እንዳይደለ ጠንቅቀው ሊያውቁ ይገባል ባይ ነኝ ይህን ያልኩበት ምክንያት እየሰሩትና እየተመለከትን ያለው የማህበራዊ ህይወት አማካሪ ስራተኛ (social worker counsellors) እየሆንብን ስለተቸገርን ነው።

በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የህግ የበላይነትን በአገራችን በኢትዮጵያ የማያስከብሩ ከሆነ በኦሮሞ አክራሪዎችና በእስልምና አክራሪዎች መዳፍ ስር የመውደቅ እጣ ፋንታቸው ከፍ ያለ ነው የሚል የግል ግምት አለኝ ምክንያቴም

(ሀ) ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ሲመጡ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ” የሚለው አነጋገራቸው ለሃያ ሰባት ኣመት ኢትዮጵያዊነቱ ሲያስቀጣው ለነበረ የአገራችን ህዝብ ዳግ

 • በኢትዮጵያዊነቱ እንዲያምን ያደረገ ንግግር ሲሆን በሌላ በኩል ደሞ ኢትዮጵያ እድትጠፋና እን ድትበታተን ሲሰሩ ለነበሩ አክራሪ ኦሮሞዎችና አክራሪ የእስልምና እምነት ተከታዮች እና ለህወሀት ባለስልጣኖች መርዶ ከመሆኑ ባለፈ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በነዚህ ሐይሎች ጥርስ ውስጥ የገቡበት ሰኣት ነው፡፡

(ለ) ሌላው ደሞ ትውልዳቸው ከኦሮሞ ቤተሰብ ሆኖ ኢትዮጵያውነትን በመስበካቸው እንደ አቶ ጀ ዋር ያሉት አክራሪ የኦሮሞ ተወላጆችና አክራሪ የእስልምና ኢምነት ተከታዮች እንዲሁም የህወሀት ባለስልጣኖች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ህይወታቸውን ለማጥፋት ሌት ተቀን ሲያልሙ ነው የሚይድሩት የሚል ህሳበ አለኝ።

(ሐ) በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትር የተወለዱት ከእስልምና እምነት ተከታይ አባታቸው ሲሆን እርሳ ቸው ግን የክርስትና እምነት ተከታይ በመሆናቸው በአክራሪ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ይ ህድርጊታቸው ሀጢያት ነው ስለ ሆነም ሀይማኖታቸውን በመለወጣቸው የሞት ቅጣት ሊቀጦቸው ሲያሴሩ ነው የሚያድሩት ምክንያቱም አክራሪ የእስልምና ተከታዪች ገነት እንገባለን ብለው የሚያ ስቡት ክርስቲያን በማስለም አሊያም አልሰልምም ያለውን ሰሞኑን በአገራችን ህዝብ ላይ እንደደረ ሰው በካራ አንገቱን በመስላት መሆኑን የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡

በመጨረሻም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የህግ የበላይነት ይከበር ስንል የህግ የበላይነት ይኑር ማለታችን ነው ይህም ማለት በዚህ የሰ ሞኑ የድረሱልኝ ጥሪ በማስተላለፍ ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት ለከተሰተው የህይወት መጥፋት የ ተጠረጠሩት አቶ ጀዋር በአቃቤ ህጉ ክስ ተመስርቶባቸው በማረፍያ ቤት ግብተው ክሳቸውን መከ ታተል አለባቸው ብለን የምናስብ ቡዙዎች ነን፡፡ ይህ ሲሆን ግን ሰባዊ መፍታቸው ተጠብቆላቸው ጥፋተኛ አይደለሁም ሲሉ መከራከር ይችሉ ዘንድ መፍታቸው ሊጠበቅ ይገባል፡፡ ከዚህ ውጪ መፍታቸውን እና ስበዕናቸውን መግፈፍ አግባብ አይደለም ምክንያቱም ህግ ይከበር እያልን መንግስት የመንጋ ፍትህ እንዲያመጣ መገፋፋትም ሆነ እኛ የምንፈልገው ቅጣት ብቻ ነው ትክክል ብሎ ማሰብም ትክክል አይደለም። ምክንያቱም የምንጠይቀው የህግ የበላይነት ይከበር እያልን ስለሆነ፡፡

ልዑለ እግዚአብሄር አገራችንን ኢትዮጵያን ከመጣው ፈተና የጠብቃት!

ታምራት ይገዙ

1 Comment

 1. I am starting to think most of us Ethiopians need to be checked for bipolar disorder . A foreign citizen who swore under oath that he is a United States Citizen would not in a right mind be offended because an Ethiopian reminded him he is a foreign country citizen , if he was not a foreign citizen maybe he can feel offended even then not too offended to this extent unless ( Bipolar disorder ) took effect.

  Ethiopians liked PM Abiy as if he was the answer not only to all of their prayers they prayed but also as if he was the answer to all the prayers they will ever pray , that was just a year and some months ago – a manic episode.

  Now all that went down the drain and the depressive episode is going on among almost all of us wishing we never knew Abiy in the first place or we never cheered for him – depressive episode.

  All the khat users especially need to be checked for bipolar disorder since we be best of friends now then just a few times later they be worst of enemies. In Ethiopia bipolarism is getting way too common .

  Many pretend to be happy by day and turn into monsters by late afternoon in the same day, that’s why Ethiopians are known to be the best fit for the service industry works allover the world, they be cheering smiling all the way at work then off finishing work from the customer service jobs their other episode comes out with them being evil at each other.

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.