የኢትዮጵያውያኖችን አንገት ያስደፋ፤ ልባችንን ያሳዘነ አሳዛኝ ገጽታ – በኮሎራዶ ኢትዮጵያን ማህበረሰብ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |
የሁላችንንም ፤ እምባችንን ይስፈሰሰ፤ የምንወዳቸውን ሰዎች ከጎናችን የነጠቀ፤ ክስተት ከተፈፀመ ቀናቶች አልፈዋል፥ የወደፊት የኢትዮጵያ እጣ ምን ይሆን፤ በሚል ህሳቤ አብዛኞቻችንን እንድንሰጋ ሆነናል::
ባሳለፍናቸው ወራቶች ውስጥም ብሔርን ባማከለ ሁኔታ ኢትዮጵያውያኖች ወልደው ከከበዱበት ስፍራ በስርኣት አልበኞች ተፈናቅለዋል፥ ተሰደዋል፥ አልፎ ተርፎም ሞተዋል፤ ይህንን የሰብኣዊ ጥሰት እንዲቆም አለመጮህ እንዳሻቸው የሚፈነጩ ጥቂቶች ለፍርድ እንዲቀርቡ አለመጠየቅ የሕግ የበላይነት እንዳይሆን ማድረግ ነው፡፡
ሰሞኑን የተከሰተውን አሳዛኝ ገጽታ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደ ራሱ አድርጎ መውሰድ ካልቻለ፣ ፅንፈኝነትና ጀብደኝነት የተሞላው የአገሪቱ ፖለቲካ የንፁኃንን ደም ማፍሰስ ይቀጥላል፡፡ ይህ እንዳይሆን መንግስት ለማሳሰብ ያዘኑትን ለማጽናናት ድምፃችንን ማሰማታችንን መቀጠል አለበት፡፡
በዛሬው የጸሎትና የሻማ ማብራት የጀማ ስብሰባ ላይ የሚከተሉት የመንግስት ባለስልጣኖች ተገኝተዋል፡፡ ኮንግረስማን ጀሰን ክሮው የቀድሞው ኮንግረስማን ማይክ ኮፍማን የአውሮራ ሜየር እጩ ተወዳዳሪዎች ሚር ርያን ፍሬዘር ሚር ኦማር ሞንትጎመሪ ፅንዲሁም የኮሎራሶ ዲሞክራት ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ተገኝተዋል እንዲሁም የእምነት አባቶች ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና ከወንጌላውያን በቴ ክርስቲያን ተገኝተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ጠንካራ አገር ሆና ለዜጎች ሰላም፣ ልማት፣ ዴሞክራሲና ፍትሕ በእኩልነት ተደራሽ እንዲሆኑ ተባብሮ መሥራት እጅግ ያስፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመንግሥታዊ ሥልጣንም ሆነ የአገር ሀብት ሉዓላዊ ባለቤት መሆኑን በተግባር ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡
ጥቂቶች እንዳሻቸው የሚፈነጩበት ሳይሆን፣ ብዙኃን በነፃነት የሚኖሩበት ሥርዓት ማረጋገጥ የኢትዮጵያውያን የማይታለፍ ግዴታም ኃላፊነትም ነው፡፡
በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን አክብራችሁ ለተገኛችሁ ምስጋናችን እጅግ የበዛ ነው፡፡
የኮሎራዶ ኢትዮጵያን ማህበረሰብ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.