አዲሱ መፈንቅለ መንግስት! – አበባ ተካልኝ

1 min read

ህወሓት በህዝባዊ አመፅ ከስልጣን ከተገፈተረች በሗላ መቀሌ በመመሸግ ሀገሪቱን እንዳትረጋጋ በርካታ ስራዎችን ስትሰራ እንደነበር በተደጋጋሚ ተገልፁዋል:: በዚሁ የህወሓት ከፍተኛ ሰዎች ያስቀመጡት ግብ ዶ/ር አብይን ቢበዛ እስከ 2013 ወይም በስደት ወይም በእብደት አሊያም በኩዴታ ካልሆነም የመጨረሻ ሙከራ በማድረግ በምርጫም ቢሆን ማስወገድ እንደሚችሉ ከመግባባት ደርሰው የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ነበሩ።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተፈጠረ ያለውን መልካም አጋጣሚ እንደጥሩ ግብዓት በመውሰድ ዕቅዳቸውን በማሻሻል የጥድፊያ ስራ ውስጥ ገብተዋል። እንደ መልካም ዕድል ያዩት ነጥቦች ሶስት ሲሆኑ: አንደኛው የመደመር ፍልስፍናው ተቃውሞ ገጥሞታል የሚል ሲሆን ሁለተኛው ኢህአዴግን አፍርሶ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ምስረታውም ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል የሚል ነው። ሶስተኛው በቅርብ ጊዜ በኦሮሚያ ሀረርና ድሬዳዋ የተፈጠረውን ነገር ስርዓቱ ቤዝ ባደረገው ኦሮሞ ዘንድ ራሱ ተቀባይነት አጥቶ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል የሚሉ ናቸው።

እነዚህን መነሻ በማድረግ የተለያዩ ሀይሎችን በማሰባሰብ ለአንድ ግብ በማሰለፍ ላይ ናቸው። እነዚህ ሀይሎች ትግራይን ቤዝ ካደረጉ ኃይሎች በተጨማሪ ከኦሮሚያ ሁለት ፓርቲዎችን ከአማራ ከሞላ ጎደል አብዛኛውን ሀይል ያሳተፈ ከደቡብ የተወሰኑ ብሄረሰቦችን ያጣመረ ሲሆን ከፖለቲካ ድርጅቶች በተጨማሪ ታዋቂ ግለሰቦችንና ሚዲያዎችን አካቷል። ለሁሉም ያስቀመጡት አጀንዳ የተለያየ ሲሆን ለኦሮሞዎች የኦሮሞ ጥያቄ አንድም አልተመለሰም የሚል ሲሆን የአማራ ሀይሎችን ደግሞ ኦሮሞ አዲስ ገዥ መደብ በመሆን ሁሉንም ጨፍልቆ ለመሄድ እየተንቀሳቀሰ ነውና ምን ትጠብቃላችሁ እያሉ ነው።

ይህንን የዶክተር አብይን መንግስት ለማስወገድ አሁን ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ከህዝብ ተቆራርጧል ቀሪው ነገር ገፍትሮ በመጣል የሽግግር መንግስት ማቋቋም የሚል ግብ የተቀመጠ ሲሆን የመጨረሻ መረማመጃ የሚሆነው በህዝቡ ውስጥ በተለያየ ሚዲያ የህዝቡን ብሶት የሚያባብሱ ስራዎችን በመስራት ላይ ስለሚገኙ ይህንኑ አጠናክሮ በመቀጠል ህዝቡን ወደ አደባባይ የሚያስወጣ አንድ ክስተት (event) በመፍጠር ከፍተኛ ሁከት በመላው ሃገሪቱ በመፍጠር ከዚሁ ጎን ለጎን ቀደም ሲል አንድ ዓመት ላለፈ ጊዜ በተለያየ አቅጣጫ አዲስ አበባ ገብቶ እንዲከማች ለተደረገው ጦር-መሣሪያ: በስልጣን ላይ ያለውን ሀይል እያንጠባጠቡ ወደ አዲስ አበባ በማስገባት ህዝባዊ አመፁ ሲቀጣጠል በቀጥታ ኩዴታ (መፈንቅለ መንግስትን) በማካሄድ ጠበቅ ያለ እርምጃ በመውሰድ የሽግግር መንግስት ለመመስረት ነው።

እስከአሁን ሁሉም የተወሻሸውና በፉገራ የተግባቡት የአመራር ጉዳይ ነው። ቀደም ባለው ዕቅድ የሽግግር መንግስቱ መሪ የኦሮሞ ድርጅት ሊ/መንበር ሆኖ በረጅም ገመድ በመልቀቅ ከሗላ ሆኖ ለመዘወር ታቅዶ ነበር ይሁንና ህወሓቶች በውስጣቸው አዲስ ሀሳብ ማቀንቀን ጀምረዋል። ኦሮሞ ዕድሉን አግኝቶ በአንድ ዓመት ሀገሪቱን መቀመቅ ከቷል ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ህዝብ የትግሬ ጊዜ ይሻላል ማለት ጀምሯልና በቀጥታ ብንይዝም ችግር የለውም ማለት ጀምረዋል። የአማራ ሀይሎች ሞተን እንገኛለን እንጂ አሁን የመምራቱን ኃላፊነት ሊሰጠን ይገባል ይህ ካልሆነ ይህች ሀገር አትረጋጋም በማለት ጠንካራ አቋም ይዘዋል። ትግሬዎች በበኩላቸው አማራ ተመልሶ መሪ ከሚሆንብን ወይ ከደቡብ ይህ ካልሆነ ከፈለገ ይቅር የሚል አቋም በውስጣቸው እያራመዱ ነው። በዚህ አጀንዳ ላይ መሸዋወድ ስላለ የኦሮሞ ሰውም ቀጣዩ መሪ ነኝ ብሎ የፕሮቶኮል ልምምድ እያደረገ ነው።

2 Comments

  1. “የአማራ ሀይሎች ሞተን እንገኛለን እንጂ አሁን የመምራቱን ኃላፊነት ሊሰጠን ይገባል ይህ ካልሆነ ይህች ሀገር አትረጋጋም በማለት ጠንካራ አቋም ይዘዋል። ትግሬዎች በበኩላቸው አማራ ተመልሶ መሪ ከሚሆንብን ወይ ከደቡብ ይህ ካልሆነ ከፈለገ ይቅር የሚል አቋም በውስጣቸው እያራመዱ ነው። በዚህ አጀንዳ ላይ መሸዋወድ ስላለ የኦሮሞ ሰውም ቀጣዩ መሪ ነኝ ብሎ የፕሮቶኮል ልምምድ እያደረገ ነው።”
    ምን ዓይነት ትንታኔ ነው? በምን ማስረጃ ልይስ የተመሠረተ ነው? በስሜት የምንጽፋቸው ይህን መሰል አስተያየቶች ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ይበልጣልና አንዳንዴ ዝም ማለትም ሀገርን እንደሚጠቅም መረዳት ጥሩ ነው። መናገር ወይ መጽፍ ስለተቻለ ብቻ እየተነሱ በዜጎች ቁሥል ጨው መነስነስ ዐዋቂነት አይደለም። አንዱ የችግራችን ቆስቋሽ ወያኔ ቢሆንም መሠረታዊ ችግራችን ግን በአቢይና ጃዋር የሚነዳውና በተረኝነት ሥሜት ያበደው ሥልጣን ብርቁው የጽንፈኛና አክራሪ ኦሮሞ ነው፦ የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ እንዲያውም ይህን ሃቅ ለመሸፋፈን የተውተፈተፈ የእንዝህላል አጥር ይመሥለኛል። የሚያሳክከን ቦታ ሌላ ጸሓፊው የሚቦጫጭረን ቦታ ሌላ። ያሣዝናል።

  2. Both my friend and I recognized the face of this person who is said to be suspected of killing two military generals just few months back, we recognized him to be that he was Arena Tigrai political party member from long time ago that was believed to be in prisoned then went to join the freedom fighters in Eritrea, during the late PM Meles Zenawis time. He lost so much weight since then but his face has not changed.

    If not mistaken his name was either Tekleab , Mehreteab , Gebreab or similar to those ,definitely not Mesafint..

    https://borkena.com/2019/11/06/ethiopian-defense-chief-of-staff-alleged-killer-appeared-in-closed-court-hearing/

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.