ሰኔ 15 ጀነራል ሰአረ መኮንን ላይ ግድያ እንደፈፀመ የተጠረጠረው ጠባቂ ህክምናውን ጨርሶ ከጦር ሀይሎች ከሆስፒታል እንደወጣ መረጃ ደርሶኛል!

1 min read

መረጃው እንደሚጠቁመው ተጠርጣሪው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ቅዳሜ ምሽት ከሆስፒታል የወጣ ሲሆን ወዴት እንደተወሰደ ግን አልታወቀም። የመረጃው ምንጮች ግምት የሆነው ወደ እስር ቤት ሳይወሰድ እንዳልቀረ ሲሆን የፌደራል ፖሊስ መረጃው እንደሌለው አሳውቆኛል። የፌደራል ማረሚያ ቤቶችን ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ እስካሁን አልተሳካም።

ግለሰቡ በአራት የፌደራል እና አራት መከላከያ አባላት ጥበቃ ተደርጎለት ህክምና እየተከታተለ እንደነበር ከዚህ በፊት ፅፌ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ንግግር እና እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሯል ተብሎ ተገልፆልኝ ነበር።

ኤልያስ መሰረት