የእብድ ገላጋይ ………..…! ከታምራት ይገዙ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

ሰሞኑን የአቶ ጀዋርን የይድረሱልኝ ጥሪ ሰምተው ኩሩውን የኦሮሞን ህዝብ የማይወክሉ “ቄሮ”ዎች በንጹሃን ኢትዮጵያውን ላይ ባደረሱት አሰቃቂ አገዳደል ያላዘነና ያልተቆጨ ቢኖር ያ አስከፊና ሰቅጣጭ አገዳደል በንጹሃን ኢትዮጵያውን ላይ እንዲደርስ ምክንያት የሆኑት አክራሪው የኦሮሞ ተወላጅ አቶ ጀዋር፤ የህወሃት አመራሮች፤ እንዲሁም አክራሪ የእስልምና ተከታዮችና ድርጊቱን የፈጸሙት ህልናቢስ እና እንደ እንሰሳ የሚያስቡ ክፉንና ደጉን የማያስተውሉት የአቶ ጀዋር ተከታዮች እና የእውሸትna Asmesay  “ቄሮ”ዎች ናቸው ብል መሳሳት አይሆንም።

እንደ እውነቱ ከሆነ አቶ ጀዋር እንደዚህ ዓይነት አስናዋሪ እልቂት በኢትዮጵያዊያ ላይ እንዲሆንና እንዲከሰት ያደረጉት ለስልጣንና ለግል ጥቅማቸው አስበው ቢሆንም እንዲ ዓይነት እልቂት በአሁኑ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ይደርሳል ብሎ ማሰብ ፈጽሞ አይታሰበም። ይህን ዓይነት የንጹሃን ኢትዮጵያውያን እልቂት በድሮ ዘመን ግራኝ ማህመድ ወይንም አስቴር ጉዲት ፈጸሙት ተብሎ በታሪካችን ስንሰማ ለነበርነው ኢትዮጵያውያን በአሁን ዘመን በህይወት እያለን ታሪክ ራሱን ስደግም መመልከታችን ቡዙ ሊያበሳጭ ከመጠን በላይ ሊያስቆጣን ቢያደርገን ቢያንስ እንጂ አይበዛም ባይ ነኝ።

ይህንን ዓይነት ጭካናዊና ኢ- ሰባዊ ድርጊት እንድንበሳጭ ቢገፋፋንም ቅሉ ሳይማሩ ያስተማሩን አባቶቻችን እና አያቶቻችን የሰው ልጅ ሲበሳጭና ሲከፋው የሚያደርገውን ስለማያውቅ ጎጂውን የጎዳ መስለሎት በሚያጅብበት ወቅት የእብደ ገላጋይ ድንጋይ ያቀበላል የሚለውን ብህላዊ ምክር የያዘች ቃላት እንደ ዘበት ወርወር ያደርጋሉ።

ሰሞኑን በደረሰው አስከፊ እልቂት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያዘነ ሲሆን ሃዘኑንም በተለያየ መንግድ ሲገልጽ ሰንብቶል በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ላይ በመጻፍ፤ ምስሉንና ድምጹን በመቅራጽ፤ በተጨማሪም በሰላማዊ ሰልፍ በያለበት አገር ሆኖ ድምጽ ለሌለው ድምጽ ለመሆን ሞክሮል እኔም አንዱ ነበርኩ።

በዚህ ግዜ ነው የአባቶቻአችንን አባባል ያስታወስኩትና እንደ መግቢያ ልጠቀምበት የገፋፋኝ። እኔም በተሳተፍኩበት የሰላማዊ ሰልፍም ላይ ይሁን በተለያዩ መድረኮች ላይ ሲተላለፍ የሰማሁት በተለይ በተለይ ታዋቂ ግለሰቦች በጹሁፍና ብቃላቸው ጭምር ጠ/ሚ አብይ አቅም ስለሌለው ከስልጣን ይውረድ የሚሉ ጽሁፎችንና ንግግሮችን አድምጫለው። እንደ እውነቱ ከሆነ እኔም በግሌ በተወሰነ ደረጃ ጠ/ሚ አብይ ላይ ቅሬታ ቢኖረኝም qlu በሳቸው ላይ ግን ተስፋዪ እንዲህ ሙሉ በሙሉ አልተሞጠጠም ባይ ነኝ።

እንደውም በኔ እይታ ትላልቅ ሰዎችና የኢትዮጵያን ፖለቲካ አዋቂዎች ናቸው የምላቸው ሰዎች ቢያንስ እንዴትና በምን ጠ/ሚ አብይን እንርዳቸው ማለት ሲገባቸው አቅም አንሶቸዋል ቦታውን ይልቀቁ ብለው ሢናገሩና ሲተቹ ሥሰማ አባቶቻችን የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል የሚሎቸው እንደነዚ አይነቶቹን ሰዎች መሆን አለበት ብዪ አሰብኩ ምክንያቱም አክራሪ የኦሮሞ ሰዎችና ድርጅቶች እንዲሁም የህወሃት ሰዎች የሚሉትና የሚፈልጉትም ጠ/ሚ አብይን ከስልጣን ይውረዱ ነው።  እነርሱ አውርደው ያመለጣቸውን ስልጣን ለሁለት ተካፍለው የራሳቸውን መንግስት ማቆቆም መሆኑን እንዴት ሊገነዘቡት አልቻሉም የሚለው ሃሳብ ነው በአይምሮዪ ሲመላለስ የሰነበተው።

በመጨረሻም በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ የምንኖር ኢትዮጵያውያን “ለምጣዱ ሲባል አይጦ ትለፍ” የሚለውን አባባል በማጤን ጠ/ሚ አብይ የተጋረጣቸውን ጋሬጣ ከፊታቸው ገለል እንዲል በእንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነን በስንት መሰዋትነት የተገኘው ለውጥ በአክራሪ የኦሮሞዎች ሰዎችና ድርጅቶች እንዲሁም በህወሃት እንዳይጠለፍ ከመቸውም ግዜ በበለጠ ጠ/ሚ አብይ ጎን ሆነን መደገፍ ያለብን ይመስለኛል። በለላ በኩል ደሞ “ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም” የሚለውን አባባል ጠ/ሚ አብይ አጽኖት ስጥተው እንዲመለከቱት በትህተና አሳስባለው ምክንያቱም ብ/ጄ ከማል ገልቹ ከፍራቻ ይሆን ከጀግንነት አይታወቅም omn ላይ ወጥተው የተናገሩትን አዳምጠው የሚበጀቶን በአስቸኮይ መምረጥ ለነገ የሚሉት የቤት ስራ አይደለም ለምን ቢሉን ምናልባት ነገ የርሶ ላትሆን ትችላለችና።https://www.facebook.com/100009762090628/videos/1000544163614311/?t=2 የጀ/ል ከማልን ንግግር ለማድመጥ ሊንኩን ይጫኑት።

ሌሎቻችንም በኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት የምናምን ሁላችን “የእብድ ገላጋይ” የሚለውን አባባል ፈጻሚ ሆነን እንዳንገኝ ዘመኑን በብልሃት መዋጀት ብልህነት መሆኑን መረዳት አለብን እያልኩ የዛሬውን ጹሁፊን ልደምደም።

አምላከ አቦው አገራችንን ኢትዮጵያ ይጠብቁልን አሜን!

3 Responses to የእብድ ገላጋይ ………..…! ከታምራት ይገዙ

 1. Somebody please find a wife for Jawar , his lonely night gave not only him but all of us a nightmare to remember.

  Avatar for Jadesa

  Jadesa
  November 6, 2019 at 11:31 pm
  Reply

 2. “አስቴር” የተባለው “ዮዲት” ለማለት ታስቦ መሆን አለበት!

  ይህ ሁሉ አሰቃቂ ወንጀል ሲከናወን መንግሥት የት ነው?!!!!

  Avatar for Hibret Selamu

  Hibret Selamu
  November 7, 2019 at 2:03 am
  Reply

 3. Somali , Oromia , Amara and Tigrai regions are about to be covered by locust infestation. The planes deployed to spray chemical got called off the next day for cost budget shortage reasons.

  The emergency reserve disaster fund of the country is almost empty with the man made disasters the country experienced in the last two years, not to mention the fight with OLF right now.

  Avatar for Yoseph

  Yoseph
  November 7, 2019 at 3:17 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.