ግልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓቢይ አሕመድ – የዳላስ ቴክሳስ ኢትዮጵያውያን ማሕበረሠብ መድረክ ፅሕፈት ቤት

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

ግልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓቢይ አሕመድ::

አዲስ አበባ:
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር::

በመጋቢት 2018 ማብቂያ በኢሕአዴግ አውራ ፓርቲ ትህነግ የመዝቀጥ አደጋ በተደረገው የስልጣን ሽግሽግ ፓርቲዎን ወክለው ወደ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት ሲወጡ ዝቅ ብለው ኢትዮጵያን ከፍ በማድረግዎ በግዜው የኢትዮጵያን ሕዝብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ በሚያሰኝ ሁኔታ አግኝተዋል::

በአስከአሁኑ ሁለት አመት ባልሞላ ቆይታዎ ለሀገርዎ ላበረከቷቸው ታላላቅ አስተዋፅኦዎች ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው አብዛኛው ሀገር ወዳዱ ኢትዮጵያዊ አንደ አይኑ ብሌን የሳሳልዎት የወደድዎትና የተከተልዎት በአነጋገርዎ ረክቶ ተስፋ ሠንቆ በድርጊትዎ ኮርቶ ሃገራችንም ካለችበት የተወሳሰበና ዘርፈ ብዙiችግር ባነሰ መስዋአትነት ሊያሻግር የሚችል በአሁኑ ግዜ ከርስዎ የተሻለ መሪ የለም ብሎ ፈጥጠው የሚታዩ ችግሮችን በድጋፍና በወገንተኛነት እንዳላየ ሆኖ ሊያልፍ ቢሞክርም ዛሬ በየአግጣጫው በሚሰማው የሕዝብ አልቂት መገፋፋትና ጉዳት ደጋፊዎ ሕዝብ በሀዘንና በተስፋ መቁረጥ መሃከል ሲባዝን ይስተዋላል::

በቀደሙት ሶስት አስርተ አመታት የዘር ፖለቲካ ሲያራምድ ትውልድ ሲገድል ሀገርን በጎሳና በቁአንቁአ ሲሸነሽን ሲገርፍ ሲያሠድድና ሐገሪቱን በጭካኔ ሲዘርፍ የነበረ ዛሬ መውጫው የጠበበበት መቀሌ የተሸነቆረው የወንጀለኛ መንጋ ምንም ይቅርታ ቢደረግለት ሐጥያቱ ስለሚያባንነው ከገባበት አጣብቂኝ ማእዘን ለመውጣት የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደማይኖር አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚረዳው ነው::

የኢትዮጵያን አንድነት ጥንካሬ የምስራቅ አፍሪካን ቀጠና ውሕደትና የኤኮኖሚ ትብብር: ፍቅርና ይቅር ባይነትን መስበክዎ መደመር ብለው አዲስ ጥምር የፖለቲካ ፓርቲ ማሠብዎ አክራሪ ብሔረተኞችንና ፅንፍ የረገጡ የመገንጠል አባዜ የተጠናወታቸውን የትንንሽ መንደር መሪ ናፋቂዎችን ሊያስነሳብዎ እንደሚችል በሐዘንና በጉዳት አንገታቸውን የሰበሩት አያሌ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወገንዎችዎ ይረዳሉ::

 

ክቡር ጠ/ሚኒስትር ::

ታድያ እነዚሕ ሁለት የኢትዮጵያ ጠላቶች በግዚያዊ ወዳጅነት ተጣምረው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያ የሚልን ሁሉ ለማጥፋት አምርረው እየታገሉ ይገኛሉ:: በየግዜውም የሚታየው የጅምላ ግድያ ሕዝብን ማፈናቀል ማሠደድ የጥላቻ የሃሠት ዜና ማሠራጨት ሕዝብን ሕዝብ ላይ በማስነሳት አብያተ ክርስትያናትን ማቃጠል የሐይማኖት አባቶችን መግደል መስጊዶችን ማቃጠል እኩይ ተግባራቸው በርስዎ የተለሳለሠ የፍቅርና የይቅርታ ሠበካ ሊሸነፍና ሊከስም ቀርቶ ያተረፈልዎ ከሠሞኑ የታየውን በአምቦ ከተማ ወጣቶች “አቢይ ነፍጠኛ” ነው ጫጫታና ከፍተኛ ተቃውሞን ነው:: ያተረፈልዎ በትሕነግ አመራሮችና አንድም ጥይት ሳይተኩሱ በየ ሐገሩ ተሰደው ታጋይ ነበርን በሚሉ ደካማ ሠዎች መገሰፅን ነው:: ያተረፈልዎ በራስዎ ላይ ከተደረገው የግድያ ሙከራ ጀምሮ በኢንጂነር ስመኘው በአማራ ክልል በወንድማማችዎች በነ ዶ/ ር አምባቸው መሐከልና አዲስ አበባ በነ ጄነራል ሠአረ የተደረገውን ግድያ የትሕነግ ረጅም እጅ በደም የተለወሠ ሆኖ ራሳቸው ባቀናበሩት ወንጀል እርስዎ የሚመሩትን መንግስት ደካማ ከማሠኘት ባለፈ በነዚሕ ሁሉ ወንጀሎች ጀርባ እንዳሉበት በከፈቱት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ አነስተኛ ቁጥር የማይባል የዋሕ ሕዝብ ማሳሳትን ነው :: ያተረፈልዎ የአጋርዎን የለማ መገርሳና በዙሪያዎ የሚገኙትን የኦሮሞ ኢሊቶችን በመከፋፈልና አርስዎን ከሕዝብ የመነጠል ስራ ተሠርቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ መሪው ደካማ መሆኑን በድርጊት እንዲያምን ማድረግን ነው::

 

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር::

ያንድ ሐገር ዜጎች ወይም ማሕበረሰብ ወይ ቡድን በሕግ መገዛትን በጋራ ሊያከብሩት የሚገባ ጉዳይ ሆኖ ማንኛውም መንግስት እንደ መንግስት ተቁአማቱን አጠናክሮ ባለው መንገድ ሁሉ ፍትሕን ለዜጎቹ በእኩልነት ሲያስከብር የሐገርንም ሰላም ማረጋጋትና እድገት የተመቻቸ ሁኔታን መፍጠር ዋነኛ ግዴታውና ሐላፊነቱ ነው::

ሕጉን በሚጥሱ ሕዝብን ወደጅምላ ጭፍጨፋ የሚያነሳሱትን የሐሠት ወሬ በመንዛት የሐይማኖት ግጭቶችን የሚፈጥሩትን 78 የንፁህ ዜጎችን ሕይወት በአሠቃቂ ሁኔታ የሚያስገድሉትን 26 ባንኮች የሚያዘርፉትን በረጅም እጃቸው መቀሌ ተቀምጠው ሐገር ለማፍረስ ሕዝብ ለማጫረስ ሌት ተቀን የሚሠሩትን ወንጀለኞችን ማባበልና ሕግን ተከትለን እርምጃ እንወስዳለን አካሄድ በአንድ በኩል: እንደ እስክንድር ያሉ አክትቪስቶችን ማስፈራራት የአብን አመራርን ጋዜጠኞችንና የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ሕግ በማስከበር ስም ቀለል ያለውን እየመረጡ እርምጃ መውሰድ የተሄደበት ፍርደ ገምድል አካሄድ በሌላ በኩል ሲታይ አሳዛኝ የፍትሕ ውርጃ ከመሆኑም በላይ የመንግስትን አቅም ማጣት የሚያሳይ አለያም ሠብአዊ መብት በማክበር ስም የፖለቲካ ምህዳር በማስፋት ስም ሕዝብ ሲያልቅ የመንግስት ድፍረትና ቁርጠኝነት ማጣት ያለ መምሠሉ አሳዝኖናል::

በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የኢትዮጵያውያን ማሕበረሠብ መድረክ (ኢትዮጵያንስ ኮሚይኒቲ ፎረም) አባሎች ከማናቸውም የፖለቲካ ድርጅት ነጻ የሆንን በጋራ የሐገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሠላምና ደሕንነቱ በጥልቅ የሚያሳስበን ወገኖች ውስብስብ የሆነውን የሀገራችንን ማሕበራዊ ፖለቲካና ኤኮኖሚያዊ አካሄድ ስንመረምር በሌሊት ከሚያባንኑን በቀን ከሚያስጨንቁን የሀገራችን አስከፊ ጉዳዮች መሃከል ጥቂቶቹን እናንሳ

 • አሁንም ግዜው የመሸ አይመስልም ቁርጠኝነቱ ካለ:: ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ ይላል የሀገራችን ሰው::

ሐገር እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከታሰበ በአስቸኩአይ የዚሕ ሁሉ ችግር ጠንሳሽ የሆነው መቀሌ የከተመው የዘራፊው ትህነግ ቡድን ላይ

መንግስት አቅሙን አሠባስቦ ሁሉን አቀፍ ጠንካራ እርምጃ መውሠድ ችግሩን ከምንጩ ማድረቅ ነው ብለን እናምናለን:: ባንድም ይሁን በሌላ መንገድ ይሕን ማድረግ መንግስት ከተሳነው ግን የተሰነቀልንን የርስ በርስ ዕልቂትና የሀገር መፍረስ ዕጣ ቆመን እየጠበቅን ቀስ አያልን እየሞትን ወንድሞቻችንን ዛሬ በአስር ነገ በመቶ ከነገ ወዲያ በሺህዎች እየቀበርን የሐገራችንን መበተን እያየን ወደ ውድቀት እንደምንጉአዝ የሚያሳይ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው::

 • ባለፈ ታሪካችን ላይ ተመርኩዞ በየጊዜዉ ለሚከሰተዉ ጭቅጭቅ መፍትሄ ይሆን ዘንድ ከሁሉም ብሄር ብሄረሰብ የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች፣የሃይማኖት አባቶች፣አባገዳዎች፣የጎሳ መሪዎች፣ምሁሮች እና ፖለቲከኞች ያሉበት አገር አቀፍ ጉባኤ እንዲቋቋም እና ለታሪካችን

የመዝጊያ ምዕራፍ (Closure) እንዲኖረው ማድረግ ያስፈልጋል። በ100 ቀን ዉስጥ 800ሺ ዜጎችን ካጣችው ሩዋንዳ ትልቅ ትምህርት መውሰድ ይቻላል።

 • በህገ መንግስቱ አንቀጽ 52 ንኡስ አንቀፅ ሰ ላይ የተጠቀሰው “የክልሉን የፖሊስ ሐይል ያደራጃል ይመራል የክልሉን ሰላምና ፀጥታ

ያስጠብቃል” የሚለው ንዑስ ክፍል በትግራይና በአንዳንድ ሌሎች ክልሎች ከሚገባው በላይ ትርጉሙ ተለጥጦ የተደራጀው የልዩ ሃይልና የሚሊሺያ ሰራዊት አደረጃጀት ፖሊስ ከመሆን ባለፈ የፌደራሉን መከላከያ አቅም የሚገዳደር አቅም ያጎለበተ በፌዴራል መከላከያ ውስጥ ሌላ መከላከያ መፈጠሩ የከፍተኛ ስጋትና የአርስ በርስ ብጥብጥ መንስዔ ስለሚሆን መንግስት ሊያተኩርበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ለማሳሠብ እንወዳለን::

 • ዛሬ በሐገራችን እየታየ ያለው የሕግ የበላይነት መጥፋት እንደዚህ ዓይነት ኢሰብ አዊ ድርጊት በአገራችን ተፈጽሞ ማየት በጣም የሚያሳዝን እና በታሪካችንም እጅግ የሚያሳፍር እኩይ ተግባር ነው። በተለይም ደግሞ በጉዲፈቻ እና በሞጋሳ ባህሉ በአቃፊነቱ በሚታወቀው በታላቁ የኦሮሞ ህዝብ ክልል ውስጥ መፈጸሙ ብዙዎቻችንን ያስደነገጠ እና እስክ አሁን ለማመን ያቃተን ጉዳይ ነው። በፍጹም የኦሮሞን ህዝብ የሚመጥን አይደለም። የዚሕም ኢሠብአዊ ድርጊት መንስኤው ከስር መሰረቱ መመርመር አለበት ። ምርመራውን የሚመራ ገለልተኛ አካል እንዲቋቋም ፣ ተጠሪነቱም ለፓርላማ እንዲሆንና ዉጤቱን ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ እንጠይቃለን::
 • ሀገርንና ህዝብን ወደማያስፈልግ አግጣጫ አየገፋ ያለው የወንጀለኞች ሴራ አያያዙን አይተሕ ዳቦውን ቀማው ጦርነት አውጀው ለአያሌ

የሀገራችን ሕዝብ ሞት ስቃይ ከቀዬው መፈናቀል ስደትና ሰላም መደፍረስ የማያባራ ምክንያት ሆኗል:: ይሕ በትሕነግና በኦሮሞ አክራሪ ቡድኖች ለኢትዮጵያ የተደገሰው እኩይ ድርጊት አግጣጫውና መዳረሻው ሩዋንዳ ወይ የመን ወይ ሶርያ አለመሆኑን መንግስት በተለሳለሠ ስብከትና መግለጫ ሳይሆን በተጠናከረ ተግባር ሊያረጋግጥ ይገባል::

 • ) ዛሬ የሚታየዉን ቅጥ ያጣ የሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ተከትሎ ሀገር ቀውስ ውስጥ ከገባችና ሕግን ማስከበር በመንግስታዊ ተቁዋማት ሳይሆን በጎበዝ አለቃና በሰዎች መዳፍ ስር ከወደቀ የሚቀረው አንሽራታች ቁልቁለት በቅፅበት ሕዝብንና ሃገርን እንደ ሰደድ እሳት የሚያዳርስ የከፋ አደጋ ያለው መሆኑን መንግስት በመገንዘብ ከሚቀጥለው ምርጫ በፊት የሕዝብን ተሳትፎ ያማከለ ዘመቻ አድርጎ ያለውን የጦር መሳሪያ በአዋጅ ወይም መልሶ በመግዛት ይሕን እሳት ከሕዝቡ ጉያ ውስጥ ለማውጣት ከፍተኛ ሥራ ያስፈልጋል::

 

 • ዛሬ የሚታየውን የጅምላ ፍጅት ወደሚቀጥለው ላቅ ያለ ደረጃ ለማሸጋገር በውጭ የሐገራችን ጠላቶች በሚታገዙ አሸባሪዎች ታላላቅ ተፅእኖ ፈጣሪዎችን ለማስገደል የስናይፐር መሳርያ አካሎችን ወደሐገር ለማስገባት ሙከራው ሕግ በሌለበት በሕግ አካሄድ ማለት ተገቢ አይመስልም:: ተቀድሞ ምክንያት ከመደርደርና ሙሾ ከማውረድ ጠንክር ያለ መከላከልና ማጥቃት መጀመር ሐገር ያድናል ስርአትም ያስከብራል ዜጎቻችንም ካላስፈላጊ መቀጠፍ ያድናል ብለን እናምናለን:: አሁን እጅን አጣጥፎ ከዛሬ ነገ ይሻል ይሆን ተስፋ መሰነቅ ከሩዋንዳ ክሶማሊያ ከየመንና ከሶርያ ላለመማር ቤታችን አሳቱ እስኪገባ የመጠበቅ ያክል ሆኖ ይሰማናል:: አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ባሰብሽ የቅደመ ጥንቃቄ ሃገራዊ ብሂል ላለንበት ሁኔታ ጥሩ ማሳያ ነው::

 

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር::

በመላው አፍሪካ ተወዳጅ የሆነችዉ ዶ/ር ሙምቢ ሴራኪ ኦክቶበር 30/2019 ለ 11 ደቂቃ በ“Dr.Mumbi Show” ስለ እርስዎ ባዘጋጅችዉ ፕሮግራም ላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተከሰተዉን መጥፎ አጋጣሚ “የኖቤል እርግማን” (The Curse of Nobel) ካለች በኋላ ምናልባትም አገራችን ላይ የሚካሄድ የዉጭ ሴራ ሊኖር እንደሚችል ገምታ በእርስዎ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያ እንዳትበታተን ስጋቷን በሃዘን በመግለጽ ህዝቡ ወደ ፈጣሪ እንዲጸልይ መክራለች ።

በታሪክ አጋጣሚ ሃገራችን አሁን ባለችበት የመበታተን አደጋ ወቅት የእግዚአብሄር ፈቃድ ሆኖ በያዙት ሃላፊነት የኢትዮጵያ ዕጣ በእጅዎ ላይ ወድቋል፡፡ በዚህ ስጋትና ተስፋ በተቀላቀለበት ስሜት ዉስጥ ስላለ ነዉ ህዝባችን “ሙሴ” እና “ነቢይ” እያለ እርስዎን እስክማምለክ የደረሰው፡፡ይህን እድል ከተጠቀሙበት ኢትዮጵያን ከውድቀት ሊያድኗት ይችላሉ፡፡ አለበለዚያ ግን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ኢትዮጵያ ወደ 10 እና ከዛ በላይ ባሉ ትናንሽ አገሮች ከተከፋፈለች በታሪክ ተወቃሽ በመሆን የጎርባቾቭን ቦታ ይወስዳሉ።እንዲህ ዓይነቱ መበታተን ደግሞ መጨረሻዉ በበርካታ ትናንሽ መንግስታት መካከል በሚነሳ የድንበር ጥያቄ ማለቅያ ወደሌለው ጦርነት ማምራት ነው ። ደቡብ ሱዳንና ኤርትራ ለዚህ ምሳሌ ናቸው።

በመጨረሻም ፀጥ ያለው ብዙሃን የኢትዮጵያ ህዝብ እስከዛሬ ለሀገርዎ ያበረከቱትን በአድናቆት የሚከታተልና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምና ደህንነት ለሀገራችንም እንደሀገር በሰላም ለመቀጠል ለሚያደርጉት ሁሉን ስለምንረዳ ኢትዮጵያውያን ከጎንዎ እንደምንቆም በአፅንዎት ልንገልፅልዎ አንወዳለን::

 

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ::

የኢትዮጵያውያን ማሕበረሠብ መድረክ ፅሕፈት ቤት

ዳላስ ቴክሳስ

7 ኖቬምበር 2019

 

 

 

 

8 Responses to ግልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓቢይ አሕመድ – የዳላስ ቴክሳስ ኢትዮጵያውያን ማሕበረሠብ መድረክ ፅሕፈት ቤት

 1. እግዚአብሄር ይባርካችሁ:: ገንቢ ሚዛናዊና ሀቀኛ ምክር ነው:: ፍሬ ነገሩን ተረድታችሗል:: የህውሀትና ኦነግ ፀረ ኢትዮጵያ ዘመቻ በአንድ ቡድን ተሰልፏል:: ዐቢይ ነፍጠኛ ነው ብሎ የኦሮሞውን መንጋ አሳምኗል:: ሌላው ኢትዮጵያዊ ዐቢይ ኦነግ እንደሆነ ይህ ጥምር ፀረ ኢትዮጵያ ሀይል ዐቢይንለማዳከም እጅግ ብዙ ሰርቷል:: ኢትዮጵያውያን ያለን ምርጫ ዐቢይን አጠናክረን አብሮ መቆም ነው:: በዚህ ወቅት አማራጭ የለንም:: አረንጏዴ ቢጫ ቀይ የሚያውለበልቡ ተቃዋሚ ድርጅቶች የጋራ ግንባር የሚፈጥሩበት ወቅት ቢኖር እሁን ነው:: ፀረ ኢትዮጵያዊ ሀገር አጥፊ መንጋ እጅግ በጣም ትንሽ ናቸው:: እንዲሰመርበት የሚፈለገው ኦሮሞ ሁሉ ጃዋር አይደለም:: እንደ ጃዋር ያለ ደላላ ወንጀለኛ የኦሮሞ ከለላን ይፈልጋል:: እኛ ኢትዮጵያውያን ከኦሮሞ ወገኖቻችን ጋር ሆነን ኢትዮጵያን ከፀረ ኢትዮጵያ ሀይሎች መታደግ ነው

  Avatar for እውነቱ

  እውነቱ
  November 7, 2019 at 9:11 am
  Reply

 2. It is so sad for us to continue the very stupid way of doing the politics of cry and decry . Here we agin begging hard the Prime Minister and his chronically spoilt ruling party and government that will never get out if the deadly politics of ethno-centerism and parochialism . It is quite clear that the Prime Minister is overwhelmingly consumed by his narcissist or excessive self-love or self- aggrandizement political mentality and behavior . This behavior always cynically try hard to win if possible all sides of the political actors and if this doesn’t work , it goes with the side that he believes has more power or strength than any other actor regardless of the objective that side holds. That is why we see the Prime Minster swinging among various actors and dancing a very ugly twist dance .
  Nowadays, the actors those actors if bad politics are making the balance of power tilted towards the ethino-centrists and parochialism and the PM is playing this dirty and dangerous political game by alleging himself with them in practical terms, but on the other hand fooling the majority of the people who truly believe in the politics of democratic Ethiopia of not the mutually deadly politics of ethno-centrism and parochialism .
  So, if we have to get out of this very dirty and destructive political game , there is a need to tell and make the people aware so that they can to get organized in a much broader and effective manner, not keep producing and posting extremely monotonous and self- defeating statement or meglecha !
  Let us do politics in a different way that brings about a different result! Aren’t we sicken and tired of begging and praising those politicians of EORDF who are out of and creative ideas of politics ? I strongly argue we are ! So, why not we learn and change the course of our idiotic way of doing politics that we came through a quarter of a century ?

  Avatar for Tegenaw Goshu

  Tegenaw Goshu
  November 7, 2019 at 10:01 am
  Reply

 3. በታሪክ አጋጣሚ ሃገራችን አሁን ባለችበት የመበታተን አደጋ ወቅት የእግዚአብሄር ፈቃድ ሆኖ በያዙት ሃላፊነት የኢትዮጵያ ዕጣ በእጅዎ ላይ ወድቋል፡ False narrative!!!!
  I am not sure how Abiy is expected,and “begged” to save Ethiopia, a country on the verge of collapse, when he, Abiy himself is the coordinator, enabler and at times supporter of the evil doings that his elected officials have done to our fellow Ethiopians.
  How dare you go and ask Abiy to “save Ethiopia” when he has told us in so many words that he is on the side of Jawar Mohammed.
  What kind of prove are you waiting for this so called Ethiopian Organization to realize the ONLY THE PEOPLE OF ETHIOPIA CAN SAVE ETHIOPIA
  Not an OLF member and supporter who brought OLF back to our country and continue the destruction of our country.
  SHAME ON YOU TO NOT EVEN REALIZE WHO ABIY REALLY IS EVEN AFTER ALL THESE MASSACARE!!!

  Avatar for Samuel Abebe

  Samuel Abebe
  November 7, 2019 at 10:36 am
  Reply

 4. በመጀመሪያ ፅሁፉን ላቀረቡት ክፍተኛ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ:: ይበል የሚያሰኝ ነው::
  በመቀጠል ጠገናው ጎሹ ሰባራ የተንሸዋረረና የወረደ ሐሳቡን በደከመ እንግሊዝኛ የሚቀጥለውን አስፍሯል:: “It is so sad for us to continue the very stupid way of doing the politics of cry and decry . Here we agin begging hard the Prime Minister and his chronically spoilt ruling party and government that will never get out if the deadly politics of ethno-centeri..” ጠገናው በጥላቻና በቅናት የሚናውዝ የቀድሞ ኢሕአፓ አባል የነ ጌታቸው ረዳ ተከታይ እድሜውን በሙሉ የረባ ሕይወት ያልመራ እኔ ካልበላሁት ጭሬ ልበትነው እንዳለችው ዶሮ የዶሮ ጭንቅላት የያዘ ደካማ ፖለቲካ ያልገባው ወሬኛ ነው:: ሌላው ኢሕአፓ ሳሙኤል ነው:: አሳዛኙ የፓርት ታይም የኢትዮጵያ ፖለትከኛ ካስተመሩን በመጠበቅ ላይ እያለ በሚያየው ፌስቡክ ተወስውሶ በምቀኝነት ተንገብግቦ ግራና ቀኝ መቃወም:: ጠቅላይ ሚኒስተር ስለተቃወመ ካለበት ጉድጉአድ ውስጥ ከፍ ያለ የሚመስለው በሽተኛ የሞላበት ነው:: ምን ይደረግ አማራጭ ምንድነው ብለሕ ይሕን የመንደር ወሬኛ ብትጠይቀው ምንም አያቀርብም :: እንዲሁ የተለቀ የሚመስለው ተንጠራርቶ ጭቃ ሲወረውር ብቻ ነው:: ለጠገናው አይነቶች የምለው ከጌታቸው ረዳ ስር ተወሽቀሕ ሳይሆን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን አስበህ የጥላቻ ወሬሕን ልክ አበጅለት:: ራስሕን ገዝግዞ ሳይጥልሕ::

  Avatar for እጅጉ ዮሐንስ

  እጅጉ ዮሐንስ
  November 7, 2019 at 7:20 pm
  Reply

 5. እኔ በጣም ከሚገርመኝ ነገር ከጎጠኝነት ከዘርኝነት ከፖለቲካ ነፃ እንደሆናችሁ የምትፅፉትን ነገር ነው እንደ አማራ ጎጠኛ ዘረኛ የለም እኔ ብቻ ነኝ ኢትዮጵያ የእኔ ብቻ ናት ኢትዮጵያ የሚል የድሮ የአባቶችሁ አግላይ ኋላቀር አስተሳሰብ ያለው እናንተው ጋር ነው፡፡ እናውቃለን በዚች ሀገር የእናንተ ጠላት ህወሀት እና የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው ይባስ ብሎ ከሳምንት በፊት በኦሮሚያ የነበረው ግድያ እና ግጭት በህወሀት ማሳበባችሁ እንደ አንዱ ምሳሌ ነው ምን ያህል በህወሀት ጭፍን ጥላቻ እንዳላችሁ ያስታውቃል ቢሆንም እኔ በዚህ ጭፍን ጠጥላቻችሁ አልፈርድባችሁም ለምን ቢባል በደርግ ውድቀት ተሸናፊ ነበራችሁ ሁለቴ ሶስቴ ተማርካችሁ ስትለቁ ኮብልላችሁ ሀገር የወጣቹ ናችሁ ስለዚህ ከእናንተ ብዙም አልጠብቅም ገግር ግን ሀገር እንደ ሀገር ለማስቀጠል ሁላችንም ተቻችለን ተከባብረን አንዱ የአንዱን ባህል፤ እሴት፤ ቋንቃውን አክብረን ጣት ሳንቀሳሰር የአንዱም የሌላው ፖለቲካ ድርጅት ሳናጥላላ ለምን ያ ድርጅት ብዙ ደጋፈ ተከታይ አለው እና መንግስተም ህገ መንግስቱ በማከበር የዜጎቹ ሂወት ሲጠብቅ ነው፡፡ የእናንተ ፉከራ እና ሽለላ የትም አያደረስም

  Avatar for Tom

  Tom
  November 8, 2019 at 12:08 am
  Reply

 6. ስንሰማው የኖርነው ስለሆነ ብዙም አዲስ ነገር የለውም።ይልቁንስ ለሆዳቸው ያላደሩ እውነተኛ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ካሉ የሚከተለውን አንብበው ሀገራቸውን እና ወገናቸውን ከጥፋት ያድኑ።እውነቱ ያለው እስከዛሬ የተወራውና የተፃፈው ላይ ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ እውነተኛ ዘላቂ ለውጥ ይመጣ ነበር።እውነቱ ያለው እስከዛሬ በአግባቡ ካልተወራው ከሚከተለው ጥቅስ ላይ ነው።
  “The Jews rule this world by proxies.They get others to fight and die for them” By Malaysian Prime Minister October 2003.
  Source
  From the heading of Synagogue Of Satan found on the follwing website. http://www.Antichristconcy.ኮም

  other websites to visit

  ከላይ ያለውን የጠቆምኩት እራሳችንን ከተጠያቂነት ነፃ አድርገን ጣታችንን ሙሉ በሙሉ ወደሌላ አካል ለመጠቆም ሳይሆን እራሳችንንም ጭምር ተጠያቂ እንድናደርግ ነው።ምክንያቱም ማንኛውም ሰይጣናዊ እኩይ ሃይል ከፍተኛ ጥፋት ለማድረስ እንዲችል በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በየደረጃው እና በየአይነቱ ሌላ የጥፋት ተባባሪ አጋዥ ሃይል ይፈልጋል።ዶ/ ር አብይ ለሁሉም ነገር ሃላፊነት ሊወስድልን አይችልም።ከላይ የተጠቀሱትን ከሞላ ጎደል አንብበን ስንጨርስ የዚህ አለም ሁኔታ በተወሰነ ይገለፅልናል።የአክቲቪስቶች የፓለቲከኞች የምሁራን የልሂቃኑ የሃይማኖት አባቶች እና የእነ አብይ አቅም እስከየት ድረስ እንደሆነ ይገባናል።ስንሰማው ስናነበው ስንፅፈው በኖርነው ተመሳሳይ ነገር ጊዜያችንን አናባክን።እርግጥ ነው እንደዚህ አይነት ነገር ጭራሽ እንዳይነሳ አጥብቀው የሚከታተሉና የሚሰሩ በጥቅም የተገዙ የአይሁዶቹ ተላላኪዎች ውዥንብር እና ግራ መጋባት ለመፍጠር ውሻ በበላበት እንደሚባለው በየሚዲያው እንደውሻ ይጮሃሉ።በሌላው አለም ይፋ የወጣ ሆኖ ሳለ በኢትዮጵያ ውስጥ ለብዙ አመታት ክርስቶስን የሰቀሉት የአይሁዶቹ አለም አቀፍ ሴራ ፈፅሞ እንዳይነሳ ለምን ሆነ?
  አሁን መወራት ያለበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ነን።
  ያለበለዚያ መደመር የሚባለው ሁሉ መሬት ላይ ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ባዶ ቲዎሪ ሆኖ ይቀራል።

  Avatar for እናት ሀገር

  እናት ሀገር
  November 8, 2019 at 1:26 am
  Reply

 7. Dear Ejigu Yohannes, I am writing this piece not to provoke unnecessary dialogue or conversation but to make the very purpose of having exchange of ideas and views more clear and straight-forward.
  1.Let me first say that regardless of the differences we may have, the very purpose of exchanging our ideas and views is if possible to convince each other and to find a common ground and move forward accordingly; and if not, to disagree with a real sense of civility. This is possible in a situation where we remain focused on issues, not on very personal affairs and way of lives of people. I have to say that it would have been good if your comment was expressed with this kind of desirable attitude and purpose. I honestly want to tell you that I am neither surprised nor disappointed with your wrong approach to challenge my points of view. This is because I adequately understand the political culture of the society you and me belong to (assuming that you grew up in Ethiopia). I do understand that this very undesirable political attitude and behavior will take fairly long time and tremendous effort to be dealt with effectively. Any way, it is your right to express your comment about mine in any way you believe and you want to do so. But focusing on personal attack to the extent of insulting my own way of life is terribly wrong and it does not serve any purpose at all. I want to assure you that I am not a person of disappointment and discouragement because of the people who talk or discuss about people, not about ideas and issues; or the people who think small, not big.
  2. I thank you for your comment regarding the grammatical error that I was supposed to carefully edit it before I posted it. Even if the way you perceived and expressed it is exaggerated, I thank you for your teachable comment.
  3. As I mentioned in the first paragraph, I would like to stress that;
  . The way you tried to make a connection between Getachew Asefa and me is absolutely wrong. It is wrong not because I am afraid of being attached to his name, but it has no any grain of truth in it; and this kind of categorization for the simple reason I disagree with the very political mentality and behavior of EPRDF’s reformists who replaced TPLF’S hegemony by ODP/OLF/Jawar’s hegemony is totally absurd, to say the least. The politics of blaming and condemning TPLF and its ruthless cadres whereas evil-minded individuals such as Jawar Mehmed are causing an unprecedented chaos and horror but are protected by security guards at the expense of the people of Ethiopia who are languishing in abject poverty does not make sense at all. By the way, do you really understand what the very essence of justice is? Justice cannot be described as a quarter or half or almost! It is described and explained with its complete meaning. I am not defending those who committed politically motivated crime. What I am saying is that it is terribly wrong to make justice an instrument to hold some alleged criminals accountable but not others on the very basis of political favorite.
  . I really do not understand why you tried hard to go all the back to the story of EPRP. With all its mistakes that should be judged by the very reality of the time, that generation had done what it had believed was good for the country that was badly lagging behind both in terms of political reform and socio-economic betterment because of the refusal of the monarchy to do so. That generation had no choice but to look around for a solution to break the deadlock of political progress and socio-economic betterment, and it was at that very critical moment that socialist camp of the world made itself available as a choice better than the camp of the capitalist world. Yes, as there was neither prior experience nor the willingness of the monarchy to undertake necessary reform, the young generation of the time got emotionally motivated by the very misleading theory of socialism/communism and did what it did. I wonder how we blame and condemn what that generation did almost half a century ago whereas we are doing extremely horrible things in this 21st century. Yes, that generation did serious mistakes almost half century ago ; but it did not burn down religious institutions and peoples ‘homes together with innocent compatriots , it did not deliberately killed and mutilated innocent citizens who were outside very circle of the political fight , it did not killed innocent citizens and hanged them upside down in an open place where a lot of people stood round and watched as if they were watching kind of funny sport ,it did not killed innocent citizens by stoning , it did not pock the eyes and cut off the arms of the elderly , and above all, it did not stupidly dishonor and put the very essence and value of Ethiopia and Ethhiopiawinet at risk, and so on and so forth. So, what is the moral, ethical and political rationality and capacity of this generation to squarely blame and condemn that generation of the second half of the 20th century?
  . I do write or express my opinion with the observation and knowledge I draw from the very hard reality on the ground on the one hand and a very voracious and flowery words (rhetoric) by politicians on the other hand. I do not think the political reality in our country is something difficult to understand as it is reflected under the very roof of each and every innocent citizen. So, I do not think your argument that I am ignorant of Ethiopian politics does make sense at all.
  . With regard to your comment that I am a person of your analogy of “chicken and food” story. As ordinary citizen with a genuine sense of concern about our country, I have nothing either be jealous or ambitious about the palace politics that cannot produce and deliver meaningful, effective, sustainable and timely solutions. I have nothing to envy the palace politics that has become a very disappointing and outrageous political theater.
  Let me conclude with the following:
  Whether EPRDF continues as a front ruling circle or as a united party, it will never be the trustworthy or credible locomotive force of genuine democratic transition to a sustainable democratic system. This is because the very gist of the matter is the very political mindset that holds and produces the very content of what is to be done or what is good for the common good which is essentially intertwined with the genuine democratic transition to a well-founded democratic system. That is why the very idea of creating some sort of transitional body consisting of relatively credible and genuine stake holders through a national conference of how to move forward. To this end, there is a need to create a country-wide mass movement that can produce a truly patriotic leadership with the power and purpose of making democracy a reality with a new and young members of this generation with its political blood that is not badly contaminated like politicians and cadres of EPRDF.

  Avatar for Tegenaw Goshu

  Tegenaw Goshu
  November 8, 2019 at 10:26 pm
  Reply

 8. የዚህ ጽሁፍ ይዘት ጠ/ሚኒስትር አብይ የጸጥታና የፍትህ አካላትን ተጠቅመው በኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋትን መፍጠር ሲችሉ በሚከተሉት የማባበል(appeasement) ፖሊሲ ምክንያት ሀገሪቱ አደጋ ላይ መውደቋን በመጠቆም ሊወስዱት የሚገባቸውን እርምጃዎች ጨዋነት በተሞላበት ኢትዮጵያዊ ባህል ለመጠቆም ነው።

  ለዚህም መነሻ የሆነው በሶማሌ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ፣ በቤንሻንጉል እና በአማራ ክልሎች የጸጥታ ችግር ሲያጋጥም የነበራቸው ፈጣን እና ቆራጥ አመራር በትግራይ እና በኦሮሚያ ላይ ሲሆን የሚያሳዩት ዳተኝነት አሁን ለተከሰተው ጭፍጨፋ ምክንያት ሆኗል። እነዚህን ጉልበተኞች ሃይ የሚላቸው በመጥፋቱ 86 ዜጎች በገጀራ ታርደው፣ በድንጋይ ተቀጥቅጠው፣ ቤታቸው እላያቸው ላይ ተቃጥሎ፣ ሴቶች ጡታቸው ተቆርጦ እንዲሞቱ ሆኗል። ይህ ጭፍጨፋ ክሩዋንዳ የሚለየው በቁጥር ካልሆነ በስተቀር በአገዳደል የኛው ይብሳል ።

  እንግሊዝና ፈረንሳይ የተከተሉት ሙሶሊኒ እና ሂትለርን የማባበል ፖሊሲ ለ67 ሚሊዮን ህዝብ መሞት ምክኛት ሆነ እንጂ 2ኛ የአለም ጦርነትን አላቆመም። እኛም የዚህ ሰለባ ሆነን በጣሊያን ተወረርን።

  “በታሪክ አጋጣሚ ሀገራችን ባለችበት የመበታተን አደጋ ወቅት የእግዚአበሄር ፈቃድ ሆኖ በያዙት ሃላፊነት የእትዮጵያ ዕጣ በእጅዎ ላይ ወድቋል።”ማለት የዉሸት ትርክት ሳይሆን በመሬት ላይ ያለ እውነታ ነው። እሳቸው በሚወስዱት ዉሳኔ ላይ ተመርኩዞ የሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ ወይ ባለንበት መቀጠል አለበለዚያ ደግሞ መበታተን ሊሆን ይችላል።የሶቭየት ህብረቱ ሚካኤል ገርበቾቭ ልፍስፍስ በመሆኑ እነ ዬልሲን አገሪቷን ወደ 15 መንግስታት ተበታተኑ።

  አላማው ከላይ የተጠቀሰው ሆኖ ሳለ በቃላት ስንጠቃ እሰጥ አገባ ውስጥ መግባቱ አስፈላጊ አይደለም።

  Avatar for ሰለሞን ታደሰ

  ሰለሞን ታደሰ
  November 10, 2019 at 4:15 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.