ጽንፈኞችን ለሕግ ማስገዛት ካልቻሉ ዶ/ር አብይ ቢለቁ ይሻላል #ግርማካሳ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

ሰሞኑን በአገራችን የመጀመሪያው ያልሆነ ዘግናኝና አንገት የሚያስደፋ የሽብር ተግባራት በዜጎች ላይ ተፈጽሟል፡፡ ጠ/ሚ አብይ አህመድ 83 ኢትዮጵያዉያን ሕይወታቸው እንደተቀጠፈ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም የተገደሉ ዜጎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ብዙዎች ይናገራሉ፡፡

ራሱን ቄሮ ብሎ የሚጠራው ቡድን ፣ የጃዋር መሀመድን “ተከብቢያለሁ” ጩኸት ተከትሎ በዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት ግድያ፣ ድብደባ፣ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችንና የእምንት ተቋማትን የማውደም፣ የማቃጠል ተግባር የፈጸመ ሲሆን፣ ፣ ዜጎች ራሳቸውን ለመመከት በወሰዱት እርምጃና በአንዳንድ አካባቢዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በተደረገ ግጭት የተወሰኑት ቄሮዎች ተገድለዋል፡፡

በዶዶላ ፣ በሕመም ሲሰቃዩ የነበሩ፣ የ80 አመት አዛዉንት ነበሩ፡፡ አቶ ኃይሉ አማረ፡፡ አንገታቸው ታርዶ፣ ራሳቸው በድንጋይና በስለት ተፈጥፍጦ፣ አይናቸውን ወጥቶ፣ ምላሳቸው ተቆርጦ፣ አገጫቸው ተከፍሎ፣ቀኝ እጃቸውን ተቆርጦ፣ ሆዳቸውን በስለት ተቀድዶ…በዘግናኝ ሁኔታ ነበር የተገደሉት፡፡ በኦሮሞ ቄሮዎች፡፡

ዘምሼ ሲሳይ ትባል ነበር፡፡ እህታችን፡፡የሁለት ሕጻን እናት፡፡ ጡቷን ቆርጠውና አርደው ነበር የገደሏት፡፡

ከድረዳዋ ቀርብ ብላ ባለች የምስራቅ ሃረርጌ ዞን አካባቢ፣ ከነበረው ግርግር በመሸሽ ተደብቀው የነበሩ አንዲት እናትና ሴት ልጃቸው በቤታቸው እንዳሉ፣ በር ተዘግቶባቸው ፣ ቤታቸው ላይ እሳት በቄሮዎች ተለኩሶ ነው የተገደሉት፡፡

አሁንም በምስራቅ ሀረርጌ በሮዳ በሚባል ቦታ አቶ ደረጀ ኃይሉና አቶ ደመና የተባሉ በንግድ የሚተዳደሩ ሁለት ወንድማማቾች፣ የአቶ ደመና ባለቤት ወ/ሮ ወላንሳ ፍቅሬ በቄሮዎች ታርደዋል፡፡ በተለይም አቶ ደረጄ ለማምለጥ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢገቡም፣ ፖሊስ ጣቢያዉን ሰብረው በመግባት፣ የኦሮሞ ክልል የአካባቢው ፖሊስ እየተመለከተ፣ በዱላ ቀጥቅጠው፣ ብልታቸውን ቆርጠው አፉቸው ውስጥ በመክተት ነበር አሰቃይተው የገደሏቸው፡፡ በፊታቸው ይሄ ሁሉ ሲፈጸም የኦሮሞ ክልል ፖሊስ ዝም ማለቱ፣ የክልሉ ፖሊሶች ዩኒፎርም የለበሱ ቈሮዎች ናቸው ለሚለው አባባል አንድ ማሳያ ነው፡፡

የጃዋር መሐመድን ጥሪ ሰምተው የጭካኔ ተግባር የፈጸሙ ቄሮዎች ብዙ ጥፋት የፈጸሙት በዋናነት ከሃያ የኦሮሞ ክልል ዞኖች በአራቱ ሲሆን ( ምእራብ አርሲ ፣ ባሌና ምስራቅና ምእራብ ሃረርጌ ዞኖች) እንደ ሁሩታና አሰላ ያሉ ከተሞች ባሉባት የአርሲ ዞን አካባቢዎች ተመሳሳይ ጥቃት ለመፈጸም ሞከረው ነበር፡፡ ሆኖም ነዋሪዎች ራሳቸውን ለመከላከል በመቻላቸው እንደ ምእራብ አርሲና ባሌ ዞኖች እንደታየው ዜጎች ብዙ አልተገደሉም፡፡

በሸዋ የአዲስ አበባና የአዲስ አበባን ዙሪያ ዲሞግራፊ ለመቀየር በሚል፣ በኦሮሞ ክልል መንግስት ከሃረርጌ፣ ባሌና አርሲ መጥተው የሰፈሩ፣ በአካባቢው ባሉ ኦህዴድ ሃላፊዎች የተደራጁ፣ የሚደገፉና ጥበቃ የሚደረግላቸው ቄሮዎችም፣ የጃዋርን ጥሪ ተከትለው ብዙ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በናዝሬት፣ በደብረ ዘይት፣ በሞጆ፣ በዱከም፣ በሰበታ/ወለቴ እንዲሁም እንደ ጀሞ ባሉ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ሜንጫና የተሳለ መሳሪያዎች በመያዝ ብዙ ሰዎችን ገድለዋል፤ አቁስለዋለዋል፡፤ ንብረትም አውድመዋል፡፡

ነዋሪነቱ በደብረ ዘይት የሆነ አንድ ወዳጅ አለኝ፡፡ እናቱ አማራ ሲሆኑ አባቱ ኦሮሞ ናቸው፡፡ “ወደ ቢሾፍቱ ስገባ ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው የመጡ ቄሮዎች አስቆሙኝ፡፡ በእጃቸው ሜንጫና የተሳለ መሳሪያ ይዘዋል፡፡ በኦሮምኛ አናገርኳቸው፡፡ ጃዋርን አውቀዋለሁ አልኳቸው፡፡ ያኔ እለፍ ብለው አሳለፉኝ፡፡ ኦሮምኛ ባልናገር ኖሮ አልቆልኝ ነበር” ሲል ነው፣ ከአዲስ አበባ ወደ ቤቱ ሲመለስ ያጋጠመውን በፌስ ቡክ ገጹ የገለጸው፡፡

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገው ደግሞ፣ በአዳማ ቄሮዎች አንድ ወጣትን ያገኙታል፡፡ ተመስገን ቶሎሳ ይባላል፡፡ ኦሮሞ ነው፡፡ ኦሮምኛ ተናጋሪ ነው፡፡ ተቀላቀለን አሉት፡፡ እምቢ ሲላቸው ደበደቡት፡፡ በስለት ቆራረጡት፡፡

በወለቴ/ሰበታ የሆነው ሌላ የሚሰቀጥጥ አሳዛኝ እልቂት ነበር፡፡ ወደ ስምንት የሚሆኑ በሰበታ ይኖሩ የነበሩ የጋሞ ወንድሞች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፡፡ ከሞቱት መካከል የፕሮቴስታንት እምነት ሰባኪያን የነበሩ 2 ዜጎች ይገኙበታል። ከሁለቱ ወንጌላዊያን መካከል አንደኛው ቤተክርስትያን ውስጥ እያለ ድንገት በመጡ ቄሮዎች “አንገቱ ታርዶ” ሲሞት ሁለተኛው ከቤተክርስትያን ወደቤት ሲሄድ አግኝተዉት በተመሳሳይ የአገዳደል መንገድ ነበር የገደሉት፡፡

የጋሞ ሜዲያ ኔትዎርክ እንደዘገበው፣ ባለቤቷን በፊቷ ላይ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በቄሮዎች የገደሉባት የሁለት መንታ ልጆች እናት ስለነበርወው ሁኔታ ይሄንን ብላለች፡

“ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ቄሮ መጣ እያሉ ሰዎች እየጮኹ ወደየቤታቸው መግባት ጀመሩ። እኛም ቤታችን ገብተን በር ዘግተን ተቀመጥን። ቄሮዎቹም እንደደረሱ የእኛ ቤት ላይ ድንጋይ መወርወር ጀመሩ። እኛ ምንም አላሰብንም፤ ደነገጥን። ከዝያም አጥራችንን አፍርሰው ወደጊቢያችን እንደገቡ በመጀመርያ ስድብ መስደብ ጀመሩ። መሬቱም የኛ ነው፤ መንግስትም የኛ ነው እናንተ ጋሞዎች ኑ ውጡ አሉን። ከነርሱም መካከል ሁለቱ ቤት ገብተው እኔና ባለቤቴን ይዘውን ወጡ። ባለቤቴም ከቄሮዎቹ መካከል የሚያውቀውን አንድ ጋዲሳ የተባለ የሰፈር ልጅን ‘አንተ ጋዲሣ እንዴት እንዲህ አይነት ነገር በእኛ ላይ ታደርጋለህ እባክህን ተው፤ ለነዚህ ህፃናት ስትል ተው ባክህ’ ይለዋል። እነርሱ ግን እንጨርሳለን፤ ገና እንጨርሳቹኋለን እያሉ ባለቤቴን በድንጋይ መደብደብ፣ በስለት መውጋት ጀመሩ። ባለቤቴ ብዙ ከደበደቡት በኋላ ሞተ። እሱ እንደሞተ እኔ መጨው ስጀምር ‘ለምን ትጮዄለሽ አፍሽን ዝጊ እያሉ እኔንም መምታት ጀመሩ። ከዝያንም የሰፈራችን ሰው 5 ሌትር ጅሪካን እና ክብሪት ሲሰጣቸው አየሁ። ‘ጨርሱ ካለቀ እኔ ጨምራለው’ አላቸው። ባመጡት ጋዝ ቤታችንን አቃጠሉ። አብዝቼ ብጮህም የደረሰልኝ የለም። የፖሊስ ልብስ የለበሱ ሰዎችን የባሌን አስክሬን አንሱልኝ ስላቸው እየሳቁ አይተውኝ ሄዱ።”

በአገራችን ያለው የዘር ፖለቲካ ዜጎች አጥበው እንዲያዩ ያደረገ ፖለቲካ ነው፡፡ ለስብእናትና ለዜግነት ቦታና ክብር የሚሰጥ ሳይሆን ለዘርና ለጎጥ ቦታ የሚሰጥ ነው፡፡

በዚህ ሳምንት የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት፣ ምን እንኳን አሁን አለም አቀፍ ሽፋንና ወገዛ ቢያስከትልም፣ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ከሁለት አመት በፊት አሁን የኦሮሞ ሜዲያ ኔትዎርክና የኦሮሞ ጽንፈኞች ሲያራግቡት በነበረው ጸረ ሶማሌ ዘመቻ ሰለባ የሆኑ ኦሮሞዎች፣ በአወዳይ ከተማ በአንድ ቀን ብቻ ከስልሳ በላይ ሰላማዊ የሶማሌ ወገኖች አርደው መጨረሳቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ከአንድ አመት በፊት በቡራዩ በተለይም የጋሞ ተወላጆች ላይ በቄሮዎች እጅግ አሰቃቂ ግድያና እልቂት ተፈጽሞ ነበር፡፡ ያንን እልቂት ተከትሎም እርቅ በሚል በጋሞ ሽማግሌዎችና በኦሮሞ አባገዳዎች መካከል ተደርጎ የነበረ ቢሆንም፣ እርቁ የአንድ ቀን የፎቶና የፕሮፖጋንዳ ዜና ከመሆን ውጭ የፈየደው ነገር አልነበረም፡፡ ይኸው በአመሩ ጋሞዎች እንደገሰና በኦሮሞ ቄሮዎች ተጨፈጨፉ፡፡

ከአንድ አመት በፊት በቡራዩ፣ ከሁለት አመት በፊት በአወዳይ እንዲሁም ሰሞኑን የተከሰተው ዘር፣ኃይማኖትና ማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት አሁን ባለው ህግ መንግስት፣ አሁን ባለው ዘር ተኮር ፖለቲካ እንደውም የበለጠ እየከፋ ይመጣል እንጂ በምንም መልኩ አይሻሻልም፡፡

ይሄ ሁሉ ግፍና ሰቆቃ በአገራችን እየሆነ ያለው መንግስት አለ በተባለበት አገር ነው፡፡ ሆኖም መንግስት ቀዳሚ ስራውን መወጣት ባለመቻሉ ነው፡፡ የዶ/ር አብይ አስተዳደር እንደ ጲላጦስ ከደሙ ንጹህ ነኝ ማለት አይችልም፡፡ ለሞቱት ፣ ለተገደሉት፣ ለተፈናቀሉት ተጠያቂ ነው፡፡ አገር ወደ ዚህ ደረጃ ልትደርስ እንደምትችል ብዙዎች አስጠንቅቀዋል፣ ጽፈዋል፡፡ ሆኖም አስተዳደሩ ከወዲሁ ችግሮች እንዳይከተሉ ማድረግ ባለመቻሉ ዜጎች እየሞቱ ነው፡፡

አሁን በአስቸኳይ መሰራት ያለበት የሚከተሉት ናቸው፡

1) አገርን ትልቅ አደጋ ላይ የጣለው የኦሮሞ ጽንፈኝነት እንደመሆኑ በኦሮሞ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ፣ የፌዴራል መከላከያ ሙሉ በሙሉ ከክልል እክሰ ቀበሌ ሕግን የማስክበር ስራ እንዲሰራ ማድረግ

2) የኦሮሞ ሜዲያ ኔትዎርክ ያሉ የዘር ጥላቻ ፕሮፖጋንዳ የሚትያሰራጩ የሜዱኢያ ተቋማትን መዝጋትና እንደ ጃዋር መሐመድ ያሉ ለዜጎች መሞት ምክንያት የሆኑትን በአስቸኳይ ለፍርድ ማቅረብ

በቀጣይነት ችግሩን ከስር ለመንቀል ፣ ስር ነቀል ስራ መሰራት አለበት፡፡

በሕግ የዘር ፖለቲካ ካልታገደ፣  “ሀ” ወይም አንድ ብለው ተከባብረው፣ ዘርና ኃይማኖት ልዩነት ሳይደረግ እንደ አገር መኖር የሚችሉበት ስርዓት መገንባት ካልጀመሩ፣  ከፍተኛ እልቂት ነው የሚሆነው፡፡ በዘር ተደራጅቶ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ መታገድ አለበት፡፡ ያ ብቻ አይደለም በዘር ላይ የተመሰረተውን የፌዴራል አወቃቀር መፍረስ አለበት፡፡ ዜጎች በሁሉም የአገሪቷ ክፍል ኃይማኖታቸውና ዘራቸው ሳይጠየቅ መኖር፣ መስራት፣ መነገድ፣ መውጣት፣  መግባት፣ መመረጥ፣ መምረጥ መቻል አለባቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ ማእዘናት ዶ/ር አብይ አህመድ ከብዙዎች ተማጽኖ እየቀረበላቸው ነው፡፡ ሆኖም እስከ አሁን ዜግችን በማረጋጋት ረገድ ምንም ያደረጉት ነገር የለም፡፡ በቃልም ሆነ በጽሁፍ የሰጧቸው መግለጫዎች እንኳን ሊጠቅሙ እንደውም ባይሰጡ ይሻል ነበር የሚያስብሎ መግለጫዎች ሆነው ነው የተገኙት፡፡ እነ ጃዋርን ለፍርድ አለማቅረባቸው  ብዙዎች ዶ/ር አብይ ራሳቸው ከነጃዋር ጋር አብረው የሚሰሩ ሳይሆኑ አልቀረም ብለው ወደ ማሰብ እየወሰዳቸው ነው፡፡

በኔ እይታ ዶ/ር አብይ በቶሎ ትልቅ እርምጃ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከኦሮሞ ጽንፈኞች ጋር ያላቸው ገመድ በጥሰው ከአብዝኝዐእ ሰላም ወዳድ የኦሮሞ ማህበረሰብ፣ ከአብዛኝዐው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን መቆሙ ይሻላቸዋል፡፡ከነ አቶ ለማ መገርሳ ጋር ያላቸው ጓደኝነት ይዟቸው መደረግ ያለበትን ማድረግ ካልቻሉ፣ መድፈር ካቃጣቸው ግን  እንደ አቶ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ  ስልጣቸውን ቢለቁ፣ እርሳቸው መስራት ያልቻሉትን ሊሰሩ ለሚችሉ ቢያስረክቡ ጥሩ ነው፡፡

14 Responses to ጽንፈኞችን ለሕግ ማስገዛት ካልቻሉ ዶ/ር አብይ ቢለቁ ይሻላል #ግርማካሳ

 1. አንተ ወራዳ እናት ትነፋ! ቀዳዳ። ዶክቶር አብይን ቄሮ እያለ ከወንባራቸዉ የሚነቀንቃቸዉ የለም። እርሳቸዉን ለማንሳት መጀምሪያ ቄሮን ማጥፋት አለብህ። እርሱን ደግሞ እንኳንስ በዉንህ በህልምህም ማድረግ አትችልም። የነፍጠኛ ነገር አበቃ። ዶክቶር አብይ መነጋገር ያለባቸዉ ከንዳንተ ዓይነቱ ነፍጠኛ ጋር ሳይሆን በእኩልነት በሚያምኑ ሀቀኛ አማሮች ጋር ነዉ። አንተማ ስንት ዓመት አላዘንክ፤ ግን የትም አልደረስክም።

  Avatar for kefelegn

  kefelegn
  November 7, 2019 at 2:53 pm
  Reply

  • Zehabesha:

   Shame on you to post comments by these wild animals.

   Avatar for meseret

   meseret
   November 8, 2019 at 10:39 am
   Reply

   • I absolutely agree with Meseret. Such comment shouldn’t be posted here. It is not a matter of stifling ideas or being undemocratic to expression of ideas; it is a matter of avoiding vulgarism. If anyone can forward such insults, there is no need to say “your comment is awaiting moderation”. What is moderation then? Why don’t you simply let it go automatically as soon as the comment is written by anyone? I hope there is no moderation, if there is, we wouldn’t have seen such immorality on this beloved website. Am really sorry.

    Avatar for Germame

    Germame
    November 11, 2019 at 3:11 am
    Reply

    • He spoiled our language, better if he did not learn it so that he would remain the rest of his life an uncivilized Galla.

     Avatar for Kibret

     Kibret
     November 11, 2019 at 2:46 pm
     Reply

 2. በዚህ ቀውጢ ወቅት ማንነቱ የማይታወቅ መሪ ከመመኘት እስክችግራቸውም ቢሆን በብዙ በጎ ሥራቸው በሀገር ብቻ በአለምአቀፍ መድረክ እውቅና የተቸራቸውን አብይን እየደገፉ: እየወቀሱ: እያስተማሩ: አዳንዴም ቆንጣጭ ተፅእኖችን እየፈጠሩ መሄዱ ይበጃል:: እሣቸውን ማስደንበርና ማስበርገግ ለፅንፈኞች ጉልበት ከመጨመር ውጭ ለኢትዮጵያ የሚፈይደው ነገር የለም:: በሽግግር ጊዜ ለዛውም የኢትዬጽያ የውስጥና የውጭ ጠላቶች አሰፍስፈው ሀገሪቷን ለመበተን በሚሠሩበት ሰአት ትንሽ ትንሽ እንኳን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በአለም አቀፍ መድረክ አንገቷን ቀና እንድታደርግ ያቅማቸውን የሞከሩ ደፋርና ወጣት መሪን ለሀገሩ ምንም እንዳልሠራ ሰው write-off ማድረግ እግዚአብሔርም አይወደውም:: ማን እንደሚመጣ በማይታወቅበት ሁኔታ የሌለን መመኘት ያለውን አደጋ የሀገሬ ሰው ሲገልፅው “ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሠይጣን ይሻላል” ይላልና!! እንረጋጋ!! ሆደሰፊ እንሁን:: ይህን ችግር እንሻገራለን…አብይ አሻጋሪ ህልምና እግዚአብሔር አላቸው!!

  Avatar for Serbessa

  Serbessa
  November 7, 2019 at 9:17 pm
  Reply

 3. It is like giving him an award to name just one reason mentioned above while not mentioning the other reasons PM Abiy’s should resign. He probably feels good about his administration now after reading your letter since the list of reasons why he should resign is endless but only one reason is written in the letter.

  International media such as the Washinton Post , New York Times , Reuteurs , BBC , Al Jazeera , VOA and DW would very much be interested in the story on the ground about the Sidama Referendum and other human rights issues so they can write it in a journalistically proven way . I suggest for WOLAITA COMMITTEE FOR HUMAN RIGHTS ( WCHR ) to contact the medias I mentioned above and tell them what is really taking place on the ground , since the local medias are not permitted or are not willing to fully investigate and write a full coverage .

  Just not too long ago the Washington Post report came out titled ” After years of repression, Ethiopia’s media is free ” .

  Amnesty international and the Human Rights Watch need to be contacted also with every detail taking place in regards to this referendum of Hawassa and other human rights issues in the country before it is too late , documenting the validity of the WCHR version of what is happening need to be done by as many entities as possible quickly.
  .

  Avatar for Bejrond Y. Astatqe

  Bejrond Y. Astatqe
  November 7, 2019 at 9:58 pm
  Reply

 4. አይ መሬት ላይ ያለ ሰዉ አለ ሰዉየዉ- ግርማ ካሳ ከመጻፍ ዉጭ የኢትዮጵያ ፖለቲካ መቼ እንደሚገባህ ማወቅ አፈልጋለሁ- አባክህ መቼ ነዉ ነዉ ፖለቲካል ማቹሪቲ የሚኖርህ? ለመሆኑ በህይለማሪያም መልቀቅና በአቢይ መልቀቅ መካከል ያለዉ ትልቅ ልዩነት ይታይሃል ወይስ ዝም ብለህ ነዉ ሰዉየዉን እንደ ሃይለማሪያም ልቀቅ የምትለዉ? ይህንን ነዉ ፖለቲካል ኢማቹሪቲ የምለዉ! ሃይለማሪያም ሲለቅ በስንት መከራ አቢይ መጣ- ያኔ ህወሓት ነበር- አሁን ህወሓት የለም- ግን ጠንካራ ኦሮሞ ናሽናሊዝምና ጀዋርን የመሰለ አዉሬ አለ- ሞደሬት የሆነዉን አቢይን ልቀቅ ያልክ ለታ የሚመጣዉኮ ያዉ ኦሮሞ ነዉ ግን ምን አይነት ኦሮሞ? የጀዋር እዉቅና የሌለዉ ኦሮሞ የሚመጣ ይመስልሃል? ከመጣስ ለኛ የሚበጅ ይመስልሃል? እባክህ ግርማም ሆንክ ዳይስፖራ ቁጭ ብለሽ የኢትዮጵያን ፖለቲካ እንደ ፒሳ የምትገምጪ ሹል አፍ ሁሉ የአገራችንን ችግር ተረዱ- አቢይ ተገፍቶ ቢወጣ የሚመጣዉ አማራጭ ምን ሊሆን ይችላል ብላችሁ አስቡ- ይህንን ሳትረዱ ዝም ብላችሁ የምትጭሩት ጭረት ሌላ ነግር ይጭራል እኒ መፍትሄ አይሆንም- በተለይ ግርማ ካሳ ከዚህ በፊትም ዝም ብለህ ሰዎችና ድርግቶች ላይ ቦምብ ስታወርድ ነበር- እነዚያ ሰዎች ዛሬ አገር ገብተዉ ይቺን አገር ለማዳን ጎንበስ ቀና እያሉ ነዉ- አንተ ቦምብ አዉራጁ ግን አሁንም እዚያዉ የችካጎን ኡኖ ፒሳ እየገመጥክ ነዉ

  Avatar for Kassa Arona

  Kassa Arona
  November 7, 2019 at 10:46 pm
  Reply

 5. this is site is like isat waging and insiting violence
  lulu you are not right. This is the most common national agenda. It is this kind of attitude that drags ethiopia behind other countries . We tend to critise and blame eachother other than working together. He just shared his comment and idea. You can simply say it is wrong but not calling names and saying TPLF , Neftegna etc it is not necessary here.

  When someone get promoted , we donot like that . We love watching our own people dying and then planning to take thier properties and land. We habesha are always envious, suffering from jealousy.

  We steal ideas, books, researches and other resarch outcomes. We also go futher to detsroy the lives of hardworking and smart people.

  That is why most of us prefer to lead a miserable life in an alien country.

  Stop doing that . This is what we develop as a part of our culture and identity. It manifest itself in various ways such as cultivating civil war at home in an attepmt t gain profit in the arena of politics and other sectors.
  Shame on you

  Avatar for Gemechu

  Gemechu
  November 8, 2019 at 6:25 am
  Reply

 6. Muktar Kedir orchestrated this recent attacks that killed 86 people’s lives.

  Avatar for Yenita A.

  Yenita A.
  November 8, 2019 at 10:40 am
  Reply

 7. Girma,I totally agree with you. With the current constitution and Ethnic federalism,there will never be peace in Ethiopia.That is the main goal of Egypt and other foreign powers. Abiy has to choose between the ODP extremists and the people of Ethiopia before it is too late. His silence during the recent genocide is unbelievable.Sometimes I really doubt if Abiy is in control.

  Avatar for Ahmed

  Ahmed
  November 8, 2019 at 11:33 am
  Reply

 8. ዶ/ር አብይ ኖረ አልኖረ ለኢትዮጵያ ምን ያደርጋል! የኢትዮጵያ ህዝብ ትናንትም ይሞቱ ይገደሉ ነበር ዛሬ ደሞ ከበፊቱ በከፋ መንገድ በዘር በሀይማኖት እየተለዩ እየተገደሉ ነው! ሀይለስላሴ ፈርጥጠው እንግሊዝ ሲገቡ እኮ ኢትዮጵያ ሀገረ መሪ አልነበራትም ለ5ዓመት! ምንም አልሆነች! መንግስት ተብየወች ሁሌ እራሳቸውን ለማግዘፍ ኢትዬጵያ ትፈርሳለች ትበታተናለች ወዘተ እያሉ ይደሰኩራሉ! ያወራሉ ኢትዬጵያ እንድሆነች ምንም አትሆኑም! በቀልቡ ያልሆነ ግን ሁሌም ዋጋውን ያገኛል! በመንግስት ሳይሆን በእውነተኛ ዳኛው! ስለዚህ ወረደ ኖረ ተቀየረ በእውነት ሀገሩን ቢያገለግል ጥሩ ነበር! ከዚያ ውጭ ሚያስፈራ ነገር ቅንጣትም የለ!

  Avatar for Babillon Jutass

  Babillon Jutass
  November 8, 2019 at 5:09 pm
  Reply

 9. አስተያየት የምትስጡ በድን ቅል እራሶች ታስዝናላችሁ ብትስተውሉ መልካም ነበር ግና ያቅማችሁን ቢሆንም አልፈርድባችሁም !የተከበሩ ግርማ ካሳ ያልቱን እኔም እስማማለሁ!!በጥቂቱ አብይ ምን አይነት አደንዛዥ ውስጠ ኦሮሞ ጽንፋኛና ክብር ወዳድ መሆኑን በቅርብ አራት ወር አብይ ያሳሰራቸውና የፈታቸው የህሊና እስረኞችን አድምጡ ምድር ላይ አብይ ምን እየስራ እንደሆነ ብንፅህ ህሊና ተመልከቱ የኢትዮጵያን ዝብ በተለይም ደሀው አርሶ አደር ምን እየተሰራ እንደሆን ያልገባውን ደግ ህዝብ አስቡ
  ችግሩ ያለው ጥቂት የኦሮሞ ፅንፈኞች እራሳቸውን በውሽት ፕሮፖግንዳ ራሳቸውን አብልጠው ከቦታ ቦታ በአይሱዚ እየጫኑ የሚበጠብጡት አቅም ኖሮአቸው ሳይሆን አብይ ራሱ ስለሚፈልገው እየሰራውም ስለሆነ እንጅ በእርግጠኝነት እንድ ሙስጠፋ ያሉ የሱማሌ ክልል ቢመጣ መንግስት በአለው አቅም አስቸኮይ ግዜ አውጆ ቄሮ የሚባሉትን ፈሪ መሳርያ ድምፅ ሲስሙ እንደ ኤሬቻው ደብረዘይት ገደል የሚገቡ ናቸው ስው መሆናቸውን አንርሳ!
  ጁሀር በጣም ቀላል ነው ለአሜሪካ መንግስት ዜጋችሁ እየበጠበጠን ነው ቢላቸው በደቂቃ ወህኒ አሜሪካ ይወስዱታል!ቄሮ ቄሮ ብለን እንደ ውሽታም ስኬት አመታዊ ሪፖርት ቄሮን ስማይ ጥግ አደረስ ነው ሜንጫ የያዘ ከመሳርያ ጋር የሚታገል ሮቦት አደረጋችሁት !ቄሮን ለዚህ ድፍረት ያበቃቸው ኦነጉ አብይ ነው አማራ ክልል ላይ የበረታ ክንድ እስክንድር ላይ የበረታ ክንድ ለህሊና እስረኞች ላይ የበረታ ክንድ ቆሮ ላይ ምንም ባለመኖሩና በውስጥ መስመር ስለሚረዳቸው ብቻ ነው እነርሱም እንደ አማራ ክል ሰው ናቸው
  መፍትሄው አብይ ከስልጣን መልቀቅና ለወታደሩ መልቀቅ እስከ ሽግግር መንግስት
  በኢትዮጵያ ስው እንደ እንደ እንሰሳ የታረደው በእርሱ ስልጣን ዘመን ነው አለም ህዝብና ታሪክ ለዘላለም ይዘክሩታል!አብይ ማለት አደንዛዥ ዕፅ ማለት ነው! ይወገድ!

  Avatar for በፍቃዱ ጃለታ

  በፍቃዱ ጃለታ
  November 8, 2019 at 10:28 pm
  Reply

 10. Menlik II and his army known as Neftegna policies were driven by a racist mindset and was responsible for hand and breast mutilation, the slave trade, genocide, and ethnic cleansing. These extremists openly claim “restoring the past Ethiopian glory” – “the good old days.” 

  The revived ultranationalists of the Amhara are now organized as the Fanno and Satenawu and act like Menelik II, and they are engaged in collective acts of violence, i.e., burning houses, looting and killing the 

  Qimanti, Agaw, Oromo and Gumuz people. In the manner the Nazis characterized the Jewish as “alien race” and indiscriminately killed them, the Amhara ultranationalists are bluntly calling the Gumuz people as “chimpanzees” and indiscriminately gunning them down in the Matakal region.

  The amharic private and public Media  outlets have been airing hate speech, prejudices and make racist terms acceptable. Those media describe the Oromo cultural values as irrelevant. On the one hand, they attempted to categorize the Oromo people as outsiders, and on the other hand, they delegalized the Oromo religion and dehumanized them. 

  But the malicious politics of the hatemongers will not work in the new Ethiopia any more. The scramble for Oromia like the Menilik’s era is no more possible. But the ultranationalists can keep on their making noises in the coming years. But it will not keep back the democratization process in Ethiopia. The main problems with the offsprings of the ex-neftengas are their greediness and selfishness. They are still dreaming for the “golden” time of the their forefathers. 

  Avatar for Gamadaa

  Gamadaa
  November 9, 2019 at 12:17 am
  Reply

 11. ሔኖክ፤ አፈር ብላ ልልህ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው በገዛ ሜዳህ ያሻህን ጋላ ማስጋለብ፥ ያሻህን ፌክ ዜና መለፈፍ ትችላለህ። ስለዚህ ላንተና መሰሎችህ ማፈሪያዎች ልቡና ይስጣችሁ እላለሁ።

  Avatar for ትዝብት

  ትዝብት
  November 10, 2019 at 8:10 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.