በኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች ዙሪያ፥ ወደ ዴሞክራሲ መዳረሻ ፍኖተ ካርታ የፓለቲካ ልሂቃን፣ የብሄርም የህብረብሄር የሚመክሩበት ብሄራዊ የውይይትና የመግባባት መድረኮች አስፈላጊነት – ነአምን ዘለቀ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፦

በኢትዮጵያ ዋና ዋና የፖለቲካ ችግሮች ዙሪያ እንድሁም ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት መዳረሻ ባለድርሻዎች፣ የፓለቲካ ልሂቃን፣ የብሄርም የህብረብሄር የፓለቲካ ሃይሎች የሚሳተፉበት የሚመክሩበት ብሄራዊ ውይይትና የመግባባት መድረኮች አስፈላጊነት (ይህ ማለት የሽግግር መንግስት ማለት አይደለም) በተከታታይ ከቀረቡት የቀጠለ

ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበት፣ ማንም ተሸናፊ የማይሆንበት በሀገሪቱ ዋና ዋና ችግሮች ዙሪያ መፍትሔ ተኮር ውይይቶች በየደረጃው የሚደረጉበት ሁኔታዎች መፈለግ አስፈላጊ ይሆናል። ሁሉም ባለድርሻዎች አገሪቷን እሁን ላይ ከገጠማት የህልውና አደጋ ለመታደግ ከለውጡ መሪዎች ጋር በመነጋገር ፣ በለውጡ መሪዎችም በኩል ጉልህ ድምጽ ያላቸውን ባለድርሻዎች፣ የየብሄሩን ልሂቃንና የፓለቲካ ሃይሎች ሁሉ ፍላጎታቸውን በግልጽ ወደ ጠረጴዛው እንዲያቀርቡ ፣ ውይይቶች እንዲደረጉ፣ ሰጥቶ የመቀበል፣ ብሎም ሀገራዊና ብሄራዊ መግባባት ላይ መድረስ እንዲቻል መድረኮችን የማመቻቸት ጊዜው አሁን ነው የሚል የሚል ሃሳብ አቀርባለሁ።

የሁሉም ዜጎችና የቋንቋና የባህል ማሕበሰቦች ጥቅምና መብቶች ያልተከበሩባት ኢትዮጵያ የማንም የየትኛውም ብቸኛ ማህበረሰብ/ወይንም ብሔር መብት፣ ፍትህና ጥቅም ለዘለቄታው ሊከበርባት እይችልም። የአማራ ፣ የኦሮሞ፣ የሌሎም ማህበሰቦች ልሂቃንና የፓለቲካ ሃይሎች ቆም ብለው የማንም የማትሆን አገር ሁላችንም ወደ ምድራዊ ሲኦል የሚወስድ መንገድ ከመግፋት እጅግ የተሻለው አመራጭ ለሁሉም ጥቅም፣ ለሁሉም እኩልነት፣ መብቶች፣ ለሁሉም ድምጽና ክብር ፡ ለሁሉም የምትመች ኢትዮጵያን እንድትሆን ተነጋግሮ፣ ተግባብቶ ፣ ፍኖተ ካርታውን፣ የጨዋታውን ህግ ፣ ሂደቱን ፣ የስነ መግባር ደንቡን ፣ ወዘተ የሚመለከቱ እንዲሁም ዋና ዋና ፓለቲካዊ ልዪነቶች ላይ ዉይይቶች በማድረግ፣ ወደ መግባባት ላይ ለመድረስ ማሰብ ያለባቸው ጊዜ አሁን የመስለኛል። ይህ ጥሪ ለኦሮሞ፣ ለአማራ፣ ለሶማሌ፣ ለአፋር፣ ለትግራይ ለሌሎችም ማህበሰቦች ልሂቃን፣ የፓለቲካ ሃይሎች፣ እንዲሁም የሕብረ ብሔር የኢትዮጵያዊነት የዜግነት የፓለቲካ ሃይሎች በሙሉ ለህሊናም፣ ለታሪካችሁም እጅግ የተሻለው አማራጭ መሆኑን በአንክሮ ማሰብ ወቅቱ አሁን ይመስለኛል።

በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ ሕብረ ብሔር ኢትዮጵያውያን የዜግነት መብቶችና ጥቅሞች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲስተናገድ፣ እንዲከበሩ ፣ እንዲረጋገጡ የሚያስችል ሂደት መጀመርም አለበት። የየትኛውም ብሔር የበላይነት/ ወይንም ሄጀመኒ፣ በየትኛውም አካባቢ ይህ የኔ ለእኔ ብሔር ብቻ ነው ሌላው ዜጋ መጤ ነው፣ ሰፋሪ ነው ወዘተ የሚሉ የተዛቡና ብዙ ሚሊዮን ዜጎችን በገዛ አገራቸው ባይተዋር ያደረጉ፣ ስጋትን፣ የነገን ተስፋ አለማየት ፣ ከሰሞኑ ደግሞ በንጹሃን ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ሕይወት ያስቀጠፉ አስተሳሰቦችና ስነ ልቦናዎች የሚለወጡበት ሁኔታ በቅጡ መታሰብ ፣ መፍትሔም ማግኘት አለባቸው። በተጨማሪም ይሄ “የኔ ብሔር፣ ይሄ የኔ አካባቢ ብቻ ነው”፣ የሚሉ ኢ-ፍትሃዊ የሆኑ- ጸረ ዴሞክራሲያዊ አመለካከቶች “የኔ” ለተባለውም ብሔር ሕዝብ ጥቅምንም መብቶችንም ለዘላቂው ሊያስከብርና ሊያስቀጥል አይችልም፡፡ ዴሞክራሲያዊ ስርአት በሌለበት፣ የህግ የበላይነት ባልተረጋገጠበት፣ ተጠያቂነትና ግልጽነት የሌሉዋቸው የፓለቲካ ስርአቶች በስመ ብሄር፣ ወይንም በሀገራዊ ብሄርተኝነት ስም ወደ ስልጣን የመጡ ፈላጭ ቆራጭ አምባገነኖች ብሄሬ በሚሉት ህዝብ ላይ ያደረሱትን መከራ፣ ስቃይና፣ እልቂት በታሪክም አሁን ላይ በዘመናችንም ከበቂ በላይ ሁላችንም የታዘብን፣ ያየን ይመስለኛል።

በአንድ ሀገር ውስጥ ግማሹ የበኩር ልጅና አንደኛ ዜጋ ፣ ገሚሱ የአገሪቱ ሕዝብ ደግሞ የእንጀራ ልጅና ሁለተኛ ዜጋ ፣ ከዚያም ወረድ ብሎ በስጋት በፍርሃት፣ ያለዋስትና እየኖረ የሚቀጥልባት ኢትዮጵያ እንደ እንድ የጋራ አገር፣ በጋራ አብሮ ለመኖር ሊያዘልቁ የሚያስችሉ አይሆኑም ። ይህን እስከፊና ለ26 አመታት የተንሰራፋ፣ ዛሬም ሊደገም፣ ተጠናክሮ ሊቀጠልበት የሚሞከርበት፣ ብዙ ሚሊዮኖች አማርኛ ተናጋሪ ይሁኑ እንጂ ከኦሮሞ፣ ከጉራጌ፣ ከወላይታ፣ ከትግሬ፣ ከከንባታ፣ ጋሞ፣ ከሶማሌ አፋር፣ ከሌሎችም ማሕበረሰቦች ቅይጥና ቅልቅል የሆኑ፣ ወይንም በስነ ልቦናም፣ በአመለካከትም፣ የትኛውም ብሔር ሳጥን ውስጥ ሊገፉና ሊከተቱ የማይችሉ ፣ ነገር ግን ሁሉንም ብሔሮች/ማሕበረሰቦች የሚወዱ፣ አብሮ የኖሩ፣ አፍቅሮ፣ ተጋብቶና ተዋልዶ፣ በልዩ ልዩ ማህበራዊና ሰዋዊ ገመዶች የተሳሰረ፣ በደም በአጥንት የተለሰነ የልዩ ልዩ ማህበረሰቦች የተገኙ “ከአስገባሪነት”፣ “ከነፍጠኝነት፣ ከሰባሪነት” ጋር ምንም ግኙነት የሌላቸው፣ ከኢትዮጵያዊነት ሌላ ቤት የሌላቸው፣ ብዙ ሚሊዮን ዜጎቻችን በአዲስ አበባ አካባቢዎች፣ በሐረር፣ በድሬ ዳዋ፣ በባሌ፣ በአዳማ፣ በአሰላ ፣ በአዋሳ፣ በልዪ ልዪ ሌሎች የሀገሪቱ የከተማ፣ ከተማ ቀመስና የገጠር አካባቢዎች ሁሉ ሙሉ መበቶቻቸው፣ ደህነታቸው ፣ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሞ፣ በደቡብ በሌሎችም አካባቢዎች መከበር፣ መረጋገጥ የሚቻልበት ሁኔታዎች ፣ ውይይቶች፣ ድርድሮች ፣ መግባባቶች መደረስ ይኖርበታል።

በሀገርም ውስጥ በውጭም የምትገኙ የምታውቁኝም የማታውቁኝም ወድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፦

ታላቁ የአሜሪካን ፕሬዝደንት አብረሃም ሊንከን የአሜሪካ ጥቁ ር ሕዝቦችን ከባርነት ለማላቀቅ በተደረገው የደቡብ ባሪያ አሳዳሪ ኮንፌደሬት ሰራዊትና የስሜኑ የአንድነት ሰራዊቶች ከዛሬ 160 አመታት በፊት ባድረጉት የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት እንደተናገረው እርስ በእርሱ ተከፋፈለ ቤት ሊቆም/ሊዘልቅ አይችልም “A house divided against itself cannot stand” ። አሁን እየታየ ባለው በህዝብ ውስጥ የሚገኝ ቅሬኔና ትላልቅ ህመሞችና ስንጥቆች ሳቢያ የሁላችንም የጋራ ቤት የሆነችው ሀገረ ኢትዮጵያ በዚህ ሁኔታ ህልውናዋ መቀጠል አይችልም። ፍትሃዊነትና ልከኝነትን (just and fair) ማዕከል አድርገን አገራዊ የፓለቲካ ችግሮቻችንን ካልፈታን፣ ይህ ብዙ ሚሊዮን ዜጎቻችንን መብት አልባና እንገት እስደፊ ያደረገ፣ እስከፊና አሳፋሪ ሁኔታ እንደ አገር አብሮ ለመኖር አያስችለንም፡፡ይህን አስከፊና ከሀገሪቱ ችግሮች አንዱ የሆነ አስተሳሰብና ሕጎች ለመለወጥ ሂደቶች መጀመር አለባቸው። ተጠያቂነት፣ ግልጽነት፣ ስልጣን የተገደበበት፣ ሕዝብ በርካታ አማራጮች ቀርበውለት በነጻ ርዕቱአዊ ምርጫ ሊወስን የሚችልበት የሕግ የበላይነትና ለአገራችን ውስብስብ ችግሮች መድህን ሊሆን የሚችል ፌደራላዊም ዴሞክራሲያዊም የሆነ የፓለቲካ ስርአት ለዘላቂው ለሁሉም የቋንቋና የባህል ማሕበሰቦች፣ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜጎች ሊበጅና ሊጠቅም የሚችለው። በአንድ ጎን በየአካባቢው የሚገኙ የማሕበረሰቦች የስልጣን ምንጭነት፣ የባህል ቋንቋቸው እኩልነት የሚረጋገጥበት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ሙሉ መብቶች የሚከበሩበት፣ የሚረጋገጡበት ምንትዮሽ ግብ ሊያጣጥም፣ ሊያስታርቅ የሚችሉ የመፍትሔ ሃሳቦች ፣ ሌሎች መሰል አመራጮችንም ማፈላለግ የአገሪቱ የፓለቲካ ልሂቃንና የተደራጁ ሃይሎች በጥልቀት ሊያስቡበት የሚገባ እንገብጋቢና ከቀዳሚዎቹ የፓለቲካ ችግሮቻችን አንዱ ይመስለኛል።

የ20ኛ ክፍለ ዘመ ን ታላቁ የስይንስ ጄኒ አልበርት አንስታይን ከእምሮዋዊ አቅምና እውቀት፣ የወደፊቱን የማለም ምናባዊ ህይል የበለጠ ነው” “Imagination is more important than Knowledge” እንዳለው ወቅቱ እውቀት እለን የምትሉ ልሂቃን ምናባዊ አቅማችሁን በመጠቀም የሀገችንን የፓለቲካ ችግሮችና ተግዳሮቶች በውይይት፣ በድርድር፣ ለመፍታት ማሰብን በረጅሙ ማለምን ይጠይቃችሁሃል። ፓለቲካ የእድሎች ጥበብ ወይንም “Politics the Art of the possible” ጭምር ነው ይባላል። ይህ አሻግሮ ማይትን፣ ተግዳሮቶችን ወደ መልካም እድሎች፣ አደጋዎችን ወደ ጥሩ አጋጣሚዎች ለመለወጥ ምናባዊ እቅምን መጠቀምንም የሚጠይቅም ጭምር ስለሆነ ይመስለኛል። ዊኒስን ቸርችል ታላቅ ከመሆን ጋር ታላቅ ሃፊነትነትም እብሮ ይመጣል፣ ትልቅ ዋጋም ያስከፍላል እንዳለው የብሄርና የህበረ ብሄር የፓለቲካ ልሂቃን የሀገራችን የፓለቲካ ሃይሎች ለሀገራዊ ስላም፣ ለህዝብ መረጋጋት ፣ለፍትሃዊ የፓለቲካ ስርአት ምስረታ ፣ እናንም ትልቅ ለመሆን ለምትችሉበት ፣ በርእቱዊ ነጻ ምርጫ አማራጽ የፓለቲካ ፕሮግራሞቻችሁን አቅርባችሁ ካሸነፋችሁ 105 ሚልዮን ህዝብ ለመምራት ለምትችሉበት ዴሞክራሲያዊ የፓለቲካ ስርአት በጋራ መስርቱ። ቆምንለት ለምትሉት ብሄር/ብሄረሰብም ደህነትና ሰላም፣ ጥቅምና መብቶች ፣ እንዲሁ ለመላው ህዝብ፣ ለሁሉም ኢትዮጵያውን ዜጎች፣ ለሁላችንም የጋራ ሃገር በታላቅ ሀላፊነት መንገድ ለመንቀሳቀስ መወሰን ብልህነትና አስተውሎ ነው። በታሪክ ፊት፣ በህግም ፊት ፣ በሂሊናችሁም ተጠያቂ አያደርጋችሁም። በሰማይም እንዲሁ። ሀገር ከሌለ፣ ሀገር ውስጥ ሰላም መረጋጋት ከጠፉ ስልጣንም ፣ ጥቅምም፣ ታላቅነትም፣ ማንም ምንም የሚያገኝበት ሁኔታ ሊኖር እንደማይችል፣ ሁሉም ሊጠፋፋ የሚችልበት ሀገራዊ ትርምስ ውስጥ እንደ ዋዛ ፈዛዛ ሊገባ እንደሚቻል በዛሬ ዘመን የተወለዱ የሊቢያን፣ የሶርያን፣ የመንን ህዝቦች መከራና ስቆቃ እያዩ ያደጉ ታዳጊ ወጣቶች እንኳን የሚገነዘቡት እውነታ ነው።

አገራችን ኢትዮጵያ የምትገኝበት አጠቃላይ ሁኔታ እጅግ እንደሚያሳስበው እንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ፣ ሰሞኑን በተከሰተው የንጹሃን ዚጎቻችን ሕይወት መቀጠፍ፣ መቁሰልና መፈናቀል እንደሚያሳዝነው አንድ ሰብአዊ ፍጡር፣ ለአማራ ወይንም ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የቋንቋና የባሕል ማሕበረሰቦች፣ ዜጎች በፍትሕ፣በሕግ የበላይነት ፣ በማህበራዊ ፍትህ፣ በዴሞክራሲ ፌደራላዊ የፓለቲካ ስርአት የሚኖሩባት ኢትዮጵያ እውን እንድትሆን የበኩሉን አስተዋጽኦና ትግል እንዳደረገ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለጠ/ሚኒስትሩ ዶ/ር አብይ እህመድ፣ ለም/ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፣ ለአቶ ለማ መገርሳ፣ ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ ሌሎችም ለውጡን የመሩና በመምራት ላይ የሚገኙ የኢህአዴግ አመራሮች ይህን ጉዳይ በጥብቅ እንዲያስቡበት ከሀገሪቱ ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት፣ የብሔርም/ዘውግም ፣ የሕብረ ብሔራዊ የፓለቲካ አመለካከትና ፕሮግራም ያላቸው ልሂቃንና ተጽእኖ ፈጣሪ ባለድርሻዎች ሁሉ በአግባቡ የሚሳተፉበት ብሄራዊ የውይይት፣ የምክክር መድረኮች ማመቻቸት ሰ-ሰአቱ የድረሰ ይመስለኛል። መግባባትና እርቅ የሚደረስበት ፣ እንዲሁም ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ሊያራምዱ የሚችሉ ፍኖተ ካርታ በሁሉም ባለድርሻዎች ተሳትፎ ወደ ስምምነት የሚያደርሱ መድረኮች የማመቻቸት ሂደት እንዲጀመር የግሌን ሃሳብ እንደ
እንድ ኢትዮጵያዊ ለማቅረብ እወዳለሁ።

የአገራችንን ችግሮችና ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት በማዘጋጀት ላይ ያለሁትን የግሌን ሰፋ ያለ ምልከታ በቀጣይ አቀርባለሁ። ፍትህ፣ ሰላም፣ የሕግ የበላይነት፣ የሕዝብና የአገርን ጥቅም ማስቀደም በአገራችን እንዲሰፍን ፣ መቻቻልና አብሮ መኖር እንዲለመልም ቸሩ አምላክ ይርዳን!!

ነአምን ዘለቀ
ቨርጂኒያ፡ አሜሪካ

FACEBOOK.COM

9 Responses to በኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች ዙሪያ፥ ወደ ዴሞክራሲ መዳረሻ ፍኖተ ካርታ የፓለቲካ ልሂቃን፣ የብሄርም የህብረብሄር የሚመክሩበት ብሄራዊ የውይይትና የመግባባት መድረኮች አስፈላጊነት – ነአምን ዘለቀ

 1. Dear Neamin,

  You are one of the best liberal politicians of Ethiopia. Even though I am not agree with the some of your political views, I couldn’t often withhold my appreciations for your personal stands and positions on some crucial matters. You have tried always to find a middle ground in most of the controversial cases. I like and appreciate a person with such stands. I hope, you will continue helping the rebirth of the new multinational democratic Ethiopia by bridging the cliffs between the backward ultranationalists und the progressive democratic thinkers.  

  The rights of the minorities must be respected all over Ethiopia. But the minorities must change also their mindset in order to understand the aspirations of their respective host peoples. Besides that they must respect the law and order the respective reginal states. They must change their racist and chauvinist mindset in order to learn the languages of the reginal states in which they live and integrate themselves in the communities of the majorityaround them.

  There is nobody without national background and heritages in this planet. All human beings have ethnic backgrounds regardless of the composition of their ethnicity. Those who try to nullify their ethnic backgrounds are claiming Amhara ethnicity by default under the mask of Ethiopianism. They speak amharic and claim the cultures from north as their culture. They try to impose their default identity (Amaharaism as Ethiopianism) on the others. But it is not more acceptable! Therefore, the current Ethiopian nationalism is equivalent to the Amahara nationalism. Which will be voided soon. It will be replaced by the multinationalism of all Ethiopians.

  Narrow nationalists and racists are those who are against the democratic rights of the differet nations in Ethiopia. They have been using always derogatory terminologies in order to undermine the demands of the Oromo, the Sidama and all other nations. Such efforts are futile and a sign of desperation and hopelessness. No more business as a usual. You should have to swallow these naked realities. 

  Finally, I wish all Ethiopian peoples mutual understanding and respect. Besides that I wish a democratic based and true unity, peace and prosperity for all of our peoples in our homeland Ethiopia.

  Avatar for Gamadaa

  Gamadaa
  November 9, 2019 at 4:01 am
  Reply

 2. Tsinfenya, xebab, nafxanya, timkhitenya,……yemilu werada qalatochin zim bilen kemeqebaxer (inde ESAToch malet new)yalewun chigir bemeqerareb menegager bicha new meftihew. Oromoo babetu iyeteregexe, iyeteshenabet…..le 150+ ametat tagisoal. Ahun yibeqal. Mebtachinin babetachin infeligalen. Bura karayu yetim ayadersim, aladeresem. Oromo babetu tewardo min ayinet Itiyophiyaa indemitnafiqu gira yigebal. Impayeruwa wayi yehulum tihonalech, way tifersalech…That is all.

  Avatar for Gurbattii Namaa

  Gurbattii Namaa
  November 9, 2019 at 7:05 am
  Reply

 3. ይህ ከቅን ዜጎች የሚፈልቅ ሃሳብ ነው፡፡ ተመሳሳይ ሃሳብ በኢዜማም ተነስቶአል፡፡ ኢትዮጵያ ጠል የሆኑ አገር እንዲረጋጋ የማይሹ ከዛሬ ጀምሮ ሃሳቡን ከማጣጣል አንስቶ የአሃዳዊ ስርዓት አራማጆች በሚል በሚታወቁት የጃዋርና የወያኔ ሚዲያዎች መሰራጨት እንደሚጀምሩ ያለምንም ጥርጥር እንገምታለን፡፡
  እነሱ ሰላም ወርዶ በኢትዮጵያ ስም ምንም አይነት ውይይት እንዲካሄድ አይሹም፡፡ ቢፈልጉ እነኳን በነሱ ጠንሳሽነት አንድነትን የሚሰብክ ሳይሆን ከፋፋይ ከመሆን አይዘልም፡፡ ልብ በሉ አገር እገንጣለለሁ ብሎ የተነሳ የፖለቲካ ፓርቲ ፍቃድ ተሰጥቶት በአገር ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ በሌላ በኩል ስልጣን ላይ ለመመለስ ከህግ በላይ በመሆን ወያኔ እየሰራ ነው፡፡
  አንድ ፓርቲ እገነጥላለሁ ግቤም እሱ ነው ብሎ የሚሰራ ፓርቲ በምንም አይነት ኢትዮጵያ ተረጋግታ እንድትኖር ይሰራል ብሎ ማሰብ አይቻልም–ግቡ አገርን ማመስ ነውና፡፡ ስለዚህም ነው የሲዳማን አመጽ፣ የወላይታ፣ የቅማንትን አመጽ በተለያዩ መንገዶች ሲደግፉ የምናየው፡፡ አንድ ሉአላዊ አገር በስሩ የሚገኝ አንድ ክልል መገንጠል ለሚታገል ፓርቲ ጭራሽ መረጃ ስሰጥ ነበር ብለው ጠ/ሚሩ ሲናገሩ መስማታችንም የችግራችንን ስፋት ያሳያል፡፡ ዛሬስ ከገንጣዮች ጋር አለመሆናቸውን በምን እናውቃለን፡፡
  ልብ በሉ እርሰዎም ሆኑ ኢዜማ ሰሞኑን ለመፍጠር ያሰባችሁትን የውይይት መድረክ መጠነ ሰፊ የሆነ አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ የኢትዮጵያን አንድነት ማፈራረስ ከሚሹ ሚዲያዎች፣ ግለሰቦችና አክቲቪስት ነን ባዮች ይጠብቋችኋል፡፡ አላማቸው የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት በማናጋት የራሳቸውን ድብቅ አላማ ማሳካት ነውና፡፡

  Avatar for Nazrawi

  Nazrawi
  November 9, 2019 at 8:18 am
  Reply

 4. Nazrawi; ናዝራዊ ሆነህ እንዴት ስለኢትዮጵያ አንድነት ከኢትዮጵያ de facto ዜጎች በላይ እንደምታስብ አይገባኝም! De facto ዜጎች ያልኩበት፣ በዚያ በአለም እንደ አንድ ሃገር በካርታ በታወቀው ክልል የሚኖሩ ሁሉ እንደዜጎች መቆጠር ሲገባቸው፣ እንዳንተ አይነቶቹ ከሌላው የበለጠ ኢትዮጵያውያን (more Ethiopians than others) እነዚህን ህዝቦች እንካሁን እንደዜጋ ስለማትቆጥሩት ነው። እንደዜጋ ካልተቆጠርን፣ እኩል መብት ያለው ዜጋ የምንሆንበትን የራስችንን ሃገር እንመስርት ሲሉ ደግሞ “ግቡ አገርን ማመስ ነው” ብላችሁ ጦርነት ታዉጁበታላችሁ።

  መገንጠል ከጭቆናና ከመንግስታዊ ሽብር መላቀቂያ ሌላ የፖለቲካ መንገድ ሁሉ ስለተዘጋ አንድ ህዝብ እንደመጨረሻው አማራጭ የሚወስደው መንገድ መሆኑን ክደው (ልክ ደርግ እስከዕለተ ሞቱ ሲደሰኩር እንደነበረው) “አካኪ ዘራፍ፣ ተገንጣይ ወንበዴ!” ብለው ያቅራራሉ! ምን ስህተት ሰርተን ነው ህዝብ እንከመገንጠል የቆረጠው ብለው የሚያስቡበት አዕምሮ የላቸውም! አንተም ያንኑን ያደግህበትን ቀረርቶ እዚህ ትደግማለህ። 40% የሆነው ኦሮሞ እና ሌሎችም ህዝቦች በኢሰብዐዊ ጭቆና ስር እንዲማቀቁ እየተደረጉ “ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ” ተብሎ የሚሰጋው ለነማን ድሎት እንደሆነ እናንተው ታውቁት ይሆናል። ለሰፊው ህዝብ ግን ኢትዮጵያ አንድ ሃገር ሆና ልትዘልቅ የሚትችለው የእያንዳንድዱ ብሄር ብሄረሰብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት ያለገደብ ሲከበርለት ብቻ ነው። የግዴታ ፍቅር እንደማይኖር ሁሉ፣ የግዴታ አንድነትም ሊሳካ አይችልም። ራስችሁን የኢትዮጵያ አንድነት ዋስትና አድርጋችሁ የምትቆጥሩ ሁሉ እንደምታስቡት፣ የኢትዮጵያ አንድነት ባረጀ ባፈጀው የ”አንድ ቋንቋ፣ አንድ ባህል፣ አንድ ሃይማኖት፣ ወዘተ” ፍልስፍና የሚጠበቅ አይደለም። መገንጠልን እንደመነሻና ግቡ አድርጎ የተነሳ የፖሊቲካ ቡድን የለም፣ መነሻው የአንድን ህዝብ ከጭቆናና ሽብር ማላቀቅ ነው። መገንጠል ደግሞ ሌላ መፍትሄ ሲጠፋ የሚወሰድ የመጨረሻ አማራጭ ነው።

  ስለሆነም፣ በኤርትራ ጉዳይ እንደታየው፣ የተቀረችውን ኢትዮጵያም በዚያው ጎዳና እንዳታስቀጥሉ፣ “የጎሳ ፌደራሊዝም ካልፈረሰ” የምትሉትን ቡራ ከረዩ ወደ ጎን ትታችሁ፣ ሃገሪቱ ወደእውነተኛ ፌደራላዊ ዴሞክራሲ ለማሸጋገር የበኩላችሁን ተወጡ! የአንዱ መሰረታዊ መብት ተረግጦ ሌላው የበላይ የሚሆንባት ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ልትኖር አትችልም!

  Avatar for Abba Caala

  Abba Caala
  November 9, 2019 at 4:25 pm
  Reply

  • ናዝራዊ መጠሪያዬ እንጂ ዜግነቴ አይደለም፡፡ ግን የቱ ጋ ነው De facto ዜጎች ያልኩበት፣ በዚያ በአለም እንደ አንድ ሃገር በካርታ በታወቀው ክልል የሚኖሩ ሁሉ እንደዜጎች መቆጠር ሲገባቸው፣ እንዳንተ አይነቶቹ ከሌላው የበለጠ ኢትዮጵያውያን የሚል ሃሳብ ያነበብከው፡፡ የፈለከውን ሃሳብ መሰንዘር መብትህ ቢሆንም እኔ ያላልኩትን መተቸት ግን ተገቢ አይደለም፡፡ እኔን ሳታነሳ ሃሳብህን መተንፈስ ግን ተፈጥሮአዊ መብትህ ነው፡፡
   አባ ጫላ እርስዎ ሲደረግ የነበረው ትግል ከሲስተም ጋር ሳይሆን ከዘር ጋር እንደሆነ ከሚያቀነቅኑ ሰዎች መካከል ይመስሉኛል፡፡ ዘርን አስመልክቶ ቢያንስ ከ27 አመታት በፊት ፋይሉ ተዘግቶ ወያኔና ኦነግ ባዘጋጁት ህገመንግስት ብሄሮች ብ/ህ ኢትዮጵያ የምትባል አዲስ አገር በሙሉ ስምምነት የመሰረቱ ስለመሆናቸው ይደነግጋል፡፡ ህገመንግስቱ መነካት እንደሌለበት የእርስዎ ወዳጆች ኪንግ ጃዋርና (ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ) እና ፐሮሰፈር (እልቂት ወዳጅ ስለሆነ)ህዝቅኤል ደጋግመው ሲሟገቱ ሰምተናል፡፡ የሚገርመው ህገ-መንግስቱን ሲንዱና ሲያስንዱ ደግሞ የምናያቸው እነሱን ነው፡፡ ሌሎችም አሉ ምን አለፋዎት አብዛኛው የኢህአዴግ አባላት የሚኖርት ከህገ-መንግስቱ ተቃርነው እንጂ ተወዳጅተው አይደለም፡፡
   የትኛውም ፓርቲም ሆነ ግለሰብ በህግ አግባብ የፈለጉት አመለካከት ማራመድ መብታቸው ነው፡፡ ይሁንና ህዝብን/ዜጋውን ማፈናቀል፣ መደብደብ፣ መግደል በፍጹም መብት የላቸውም፡፡ ከሰልፍ ጀምሮ ድግሪትንም ሆነ ሃሳብን በህግና በህግ ብቻ፡፡ የፈለገ አካል በዚህ መንገድ ከተቀረው ህዝብ መለየት ይችላል ግን ህዝብን መለያየት የሌለ ታሪክ መተረክ፣ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ማንቋሽሽ አይቻልም፡፡ ይህን ጸያፍ ድርጊት የሚፈጽም ህሊናውን የሳተ ግለሰብ ወይም ለህግ የማይገዛ መንጋ ብቻ ነው፡፡
   አባ ጫላ መገንጠል እንደአማራጭ ሲሉ ከማነው የሚገኘጠሉት፤ ማንን ነው የጠሉት፡፡ አገዛዙን ከሆነ በጋራ ታግለን እሱን ከስልጣኑ ማንሳት እንጂ ህዝብን ከህዝብ ለመለየት ሲበዛ የተሳሳተ መንገድ ነው፡፡ እርስዎ የሚሉትን ጠቅሰው ነው አንቀጽ 39 ወረቀት ላይ የሰፈረችው፡፡ ጠላታችን አሰራርና አገዛዝ እንጂ ህዝብ አይደለም፡፡
   ይህን ሃሳብ ከተቃወሙ እርስዎም የመንጋው አካል ይሆናሉ ብዬ ስለማምን ብጤዎን ይፈልጉ እንጂ ከእንግዲህ ከኔ ምላሽ አያገኙም፡፡

   Avatar for Nazrawi

   Nazrawi
   November 11, 2019 at 8:33 am
   Reply

   • በመጀመሪያ፣ ለተቃወምከው ሁሉ የቅጽል ስም እየለጠፍክ አትሂድ! “መንጋ” የምትለውስ ማንን ነው?? ድሮ “ጠባብ” ነበር ቃሉ፣ ዛሬ ሲበዙ “መንጋ” ተባሉ?? እንዲህ እንዲህ ከቀጠለ አብሮ ያኖረናል?
    ህገ መንግስት ተቀዶ ይጣል እና ይሻሻል በሚሉት መካከል ሰፊ ልዩነት አለ! አይሻሻልም ያለ የለም። ክርክሩ ያለው ይቀደድ፣ አይቀደድም በሚሉት መካከል ነው።
    “ከማነው የሚገነጠሉት? ጠላታችን አሰራርና አገዛዝ እንጂ ህዝብ አይደለም” ትላለህ። አንተ የምትወደው እና የምትሞትለት “አሰራርና አገዛዝ” የሌላውን መሰረታዊ መብት የሚገፍ ከሆነስ? መብትን የሚገፍ ስርዐት ባይኖርማ ኖሮ፣ የሚያጣላና ወደ ትግል የሚወስድ ምክንያት አልነበረም።

    Avatar for Abba Caala

    Abba Caala
    November 13, 2019 at 7:38 pm
    Reply

    • ወንድሜ ጫላ
     የመገንጠል ጥያቄ የሚያቀርቡ ቡድኖች መገንጠል የሚፈልጉት ከህዝቡ ነው ከስርዓቱ/ከአገዛዝ? ከህዝቡ ከሆነ ህዝቡ ምን አጠፋ? ከስርዓት ከሆነ መገርሰስ ያለብን በጋራ ከጭቁን ህዝቡ ጋር በመሆን ስርአቱን/አገዛዙን ነው፡፡ ምርጫው ያንተ ነው፡፡ አይ አልጣመኝም ብቻዬን ኖሬ ማየት ነው የምፈልገው ከተባለም ያን በግልጽ ተነገሮን በሰላማዊ መንገድ አንተና ወዳጆችህ ብቻ ሳትሆኑ እኛም መንገዱን እናግዛችኋለን፡፡
     “አሰራርና አገዛዝ” የሌላውን መሰረታዊ መብት የሚገፍ ከሆነስ? ላልከው ይህ ነው እኮ Nazrawi የሚልህ፡፡ ስርዓት በአንድ አካል ሳይሆን በሁላቻንም በጋራ የሚወሰን ነው፡፡ የሌላውን መሰረታዊ መብት የሚገፍ ከሆነማ እሱ ስርዓት መፍረስ አለበት–ህዝቡ ግን አብሮ ይኖራል፡፡ ንጉሱ፣ ደርግ፣ ወያኔም ሄዱ ህዝብ ግን ለዘለአለም ይኖራል፡፡ አብረን አንኖርም ካልክ ጸብህ ከስርዓት ሳይሆን ከህዝቡ ነው፡፡ ይህም መብትህ ነው ህገ-መንግስቱ ለመገነጣጠል ምክንያት አይጠይቅምና፡፡
     ጫላ ይቺን መልሺ–መገንጠሉ ከህዝብ ወይስ ከአገዛዝ

     Avatar for Zeberga

     Zeberga
     November 14, 2019 at 6:01 am
     Reply

 5. ነአምን ምናለ የሰራሀውን ወንጀል ሰርተህ ዝም ብትል? ህዝብን ሁሌ ማሞኘት የምትችል ይመስልሃል? እዚያው ጌታህ ሻቢያ ጉያ ተሟሟቅ።

  Avatar for nahom

  nahom
  November 9, 2019 at 7:27 pm
  Reply

 6. This is not a new idea, and has been tried by different groups. The conclusion we derive from all trials is, a few interested groups and self appointed individuals as well as people who think they represent a certain group without the peoples consent by talking with each other will not be able to accomplish anything in the Ethiopian context. Especially now when certain portion of the population is benefiting from the current situation and believes this is their chance not only to take the lions share but also to eliminate other Ethiopians. Appeasement, begging and sacrificing some of the population is not a solution as we already can see and have seen. The solution is not in nursing the states quo but completely dismantling it and creating a just system based on merit and merit alone. We need to move away from the wrong so called socialist analysis of the children of the 60’s. Any one country is a nation and is logically impossible to have a nation within a nation.

  Avatar for Enqoqo

  Enqoqo
  November 11, 2019 at 11:24 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.