የአንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ (ኢትዮጵያችን) ልሳን

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

 ኢትዮጵያችን ቅጽ 4 ቁጥር 2                                                     ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም.

እኛ ኢትዮጵያውያን ብሔር ሁነን ኖረን ብሔር ሁነን እንሞታለን

የድምጽ ቅጂውን ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ (https://www.youtube.com/watch?v=HmCGE9Y5tMQ)

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የህዳር 03 ቀን 2012 ዓ.ም. የዘር ቆጠራን ንግግር መሠረት አድርጎ የተወሰደ ርዕስ፡፡

ኢሕአዴግ ሥልጣን እርከን ላይ እንደተቆናጠጠ በአርባ ጉጉና በደኖ አማሮች ላይ በተካሄደው ዕልቂት እንዳልጮህን፤ የ1997 ዓ.ም. የታዳጊ ወጣት ሽብሬ ደሳለኝና በመቶ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን እልቂት በመደመር ፖለቲካ “አታንሱት” ሲባል ዳግም ቤተሰብን፣ ወዳጅ ዘመድን ሲያስተክዝ፣ ስለ ሰው ልጅ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ሊሰማቸው በተገባ ነበር፡፡ የትላንቱ ገዳይ፣ ገራፊ፣ አሳዳች፣ አካል አጉዳይ ፍትህ አለማግኘት ብቻ ሳይሆን ከሥልጣናቸው ፈቀቅም ሳይሉ ለተመለከተ፤ አምባገነን ገዳይና አረመኔዎች “አትጨነቅ! ግደል! ዝረፍ! ነገ ብሄራዊ ዕርቅ ይባልልሃል” ቢሉ ምን ያስደንቃል? ወንጀል፣ ግድያ፣ ዝርፊያ “ፍትህ” ሲመለከተው ነው አስተማሪነቱ፡፡ “የፍትህ ያለ!” ሲባልለት ነው ለነገው ተረኛ አገዛዝ አስተማሪነቱ፡፡ “ፍትህ” ለተበደሉ ስትቆም ነው ያለአግባብ ግድያ ዳግም እንዳይደገም አስተማሪነቷ፡፡ በሕዝባችን ሰቆቃና እልቂት ስለ ተዘነጋችው “ፍትህ” የጠ/ሚ ዐቢይ አገዛዝ “የሞቱት እኮ ከሁሉም ዘር ነው” ሲሉን፣ ጥቃቱን የእርስ በርስ ግጭት ሲያደርጉት፣ አሸባሪውን ጀዋር መሐመድ መጠለያ ሰጥተው ሲያስጠብቁት፣ አይሰማም ብለው በኦሮምኛ ከጓደኛቸው ለማ መገርሳ ጋር “ጀዋር ወንድማችን” ሲሉን ነው ምላሽ ያገኘነው፡፡ ይህን እያደመጥን የጠ/ሚሩን አካሄድ እውነት “ብልሃትና ዘዴ” ነው ማለት በሙታን ወገኖቻችን መቀለድ፤ ቤተሰቦቻቸውን ብቻ ሳይሆን ሀገርን ዳግም ማስለቀስ ነው፡፡

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በሥልጣን ርክክብ ወቅት በንግግራቸው “ኢትዮጵያውያን ሁነን ኖረን ኢትዮጵያ ሁነን እንሞታለን” እንዳላሉ የጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ሟቾችን በዘር በመሸንሸን ያቀረቡት ጥናት ያስገኘላቸው ቢኖር መነጋገሪያ መሆንን ነው፡፡ በሚልዮን የሚቆጠር አድማጭ እንደሚታዘባቸው፣ የሚሉትን እንደሚረዳ ቢገባቸው ጥሩ ነበር፡፡

አዎ! ዛሬ በሀገራችን እየተካሄደ ያለው የእርስ በርስ ግጭት ሳይሆን ከአንድ ወገን የሚሠነዘር ጥቃትነት ተሻግሮ የአሸባሪ ድርጊት ነው ቢባል ሚዛን ይደፋል፡፡ በአክራሪ እስላሞች በዓለም ደረጃ የተደረገው አሸባሪነት እኮ እስላም ወገኖችን አልማረም፡፡ አሸባሪ የሰውን ዘር በማጥፋት ሊነግሥ ብቻ ሳይሆን “ገነት ሊገባ” የሚያልም ኃይል ነው፡፡ ለዚህም ነው አሸባሪዎች በመስጊድ ሳይቀር ቦምብ እየታጠቁ አጥፍቶ መጥፋት ተግባራቸው ሙስሊም ወገኖቻቸውን የሚፈጁት፡፡ ጀዋር መሐመድ “በለውጥ አራማጁ” በጎ ፈቃድ ወደ ሀገር ከመግባቱ በፊት ለአለፉት 10 ዓመት የሚያደርጋቸው ቅስቀሳዎች ከብሔር ተኮርነቱ ይልቅ ሃይማኖታዊ ይዘት እንዳለው በYou Tubeና በተለያዩ ማህበረሰብ ገጾች ተቀምጠውልናል፡፡ በመሆኑም ጠ/ሚሩ ስሙን በክፉ ሊያነሱ አልፈቀዱምና የጀዋር አሸባሪነት ኢትዮጵያ ሀገራችንን መበታተንና ማዳከም በመሆኑ ቄሮዎቹ ዘር፣ ሃይማኖት፣ ዕድሜና ፆታ ሳይመርጡ እንደቅጠል የሰው ልጅ ሕይወት ይቀጥፋሉ፡፡

የእርስ በርስ ግጭት ለማስመሰል ከሰጡት የዘር አደላደል እጅጉን የሚያሳፍረው ባይናገሩትም እንደውም የሞተው ኦሮሞና እስላም ለማስመሰል ይረዳኛል በሚል የለቀቁት የዘረኝነት ትንታኔ እጅጉን ወደ ሌላ ግጭት የሚጋብዝ አስተዛዛቢ አባባል ነው፡፡ ትክክለኛ መረጃነቱ አጠያያቂነቱ እንደተጠበቀ በጥቅሉ የታረዱት፣ የተውገሩት፣ የተቆራረጡት ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ በቃ!

ለአሸባሪው ጀዋር የጥቃቱ ዒላማ ቤተ ክርስቲያን፣ አማራና የምኒልክ ታሪክ ብቻ እንዳልሆኑ መናገር ይቻላል፡፡ ለጀዋር የኦሮሞ ክርስቲያን፣ የአማራ ሙስሊም አይታሰበውም፡፡ ይህን በግልጽ እንናገረው ከተባለ እንቅስቃሴው እስላማዊ ሳይሆን በእስልምና ስም እንደሌሎቹ አክራሪ ሽብርተኞች የሚመደብ ነው፡፡ ለዚህ የሽብር ድርጊቱ እስካመቸው ድረስ ኦሮሞ ወገኖችን ጥያቄውን የሁሉም ኦሮሞ በማስመሰል ሊጠቀምባቸው ሞክሮ ነበር፡፡ አልተሳካለትም፣ አይሳካለትምም እንጂ ሙስሊሙን ኅብረተሰብ የድርጊቱ ተካፋይ ቢያደርግ አይጠላም፡፡

የኢትዮጵያ እስልምናና ክርስትና ታሪክ፣ አንድነትና ጥንካሬ ተረት ብለው ለአለፉት 27 ዓመታት መርዘኛ ድልድይ በሠሩለት ህወሓት/ኢሕአዴግ እና አሁንም ሽፋንና ከለላ እየሰጡት ባሉት የመንግሥት አውታሮች ሲዳክር ይኖራል እንጂ ኢትዮጵያን ሊበትናት ከቶም አይችልም፡፡ እርግጥ ለሰው ልጅ አይጨነቅምና አሁንም ዘግናኝ እልቂት ሊገጥመን ይችላል፡፡ የአሸባሪው ጀዋር ቅዥትን የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት፣ በእምነትና በጽናት መመከት አይደለም ዳግም ለሚያስቡም ትምህርት በመስጠት ድባቅ ይከተዋል፡፡ ችግሩ እስካፍንጫው የታጠቀው የወያኔ ጦርና የአሁንም የኢሕአዴግ ሠራዊት ለጀዋር ቄሮዎች ዱላ አቀባይ፣ ሜንጫና ገጀራ ሞራጅ፣ ድንጋይ ደርዳሪ የመሆን አዝማሚያ በረሀብና በሕክምና የተጎሳቀለውን ሕዝባችንና ወጣቱን ቢፈታተንም፤ ዛሬም እንደጥንቱ በጀግኖች አባቶቹና እናቶቹ፣ በማያወላውል እምነቱ፣ በሀገርና ሰንደቅ ዓላማ ፍቅሩ፣ በወደፊት ተስፋው የማያወላውል ጽናቱን አክሎበት የሀገራችንና የሕዝባችንን አንድነት በማስከበር ዳር እስከ ዳር ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማዋ እንደሚውለበለብ በእርግጥኝነት መናገር ይቻላል፡፡

እኛ አንድ ሀገር! ስንል አንድ ሕዝብ! ስንል አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቃችንን፣ 14ቱን ክፍለ ሀገራት፣ ሁሉንም ዘርና/ቋንቋ፣ እስልምናና ክርስትና ሃይማኖታችንን፣ ታሪካዊ ቅርሶቻችንን ይዘን ነው፡፡ ይችን ነው ኢትዮጵያዬ/ኢትዮጵያችን የምንላት፡፡ የአክሱም ሃውልትን እንደገነደሰችው፣ አብያተ ክርስቲያን እንዳወደመችው ዮዲት ጉዲት ዘመንና እንደ ግራኝ አሕመድ ወረራ በዛሬው ክፍለዘመን አንገት ለሚቆርጥ ጨካኝ፣ ቤተ ክርስቲያን ለሚያቃጥል አረመኔ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከበሮ ለሚደልቅ አሸባሪ የሚሰጥ ከለላና ጥበቃ ኢትዮጵያዊ ከሆነ እሥር ቤት ሲሆን፣ የውጭ ዜጋም ከተሆነ በ24 ሰዓት ከሀገር ማባረር ነው፡፡ እውን ይህ ለዶር ዐቢይ አሕመድ የሚሰጥ ምክር መሆን አልነበረበትም፡፡

ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብና ወጣቶች ሆይ!

ጠ/ሚሩ ሥልጣን ከያዙበት 2010 መጋቢት ወር ጀምሮ መፈናቀል፣ መሰደድ፣ አካለ ስንኩል መሆን፣ መገደል የዕለት ተለት ተግባር ነበር፣ ነውም፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተገድለዋል፡፡ በሕይወት የተረፉትም እትብታቸው ከተቀበረበት ወይም ለበርካታ አሥርተ ዓመታት ከኖሩበት ቀዬ ተፈናቅለው በምግብና ሕክምና እጦት እየተሰቃዩ እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በድንጋይ ወገራው፣ በሜንጫ አንገት መቅላቱ፣ በዱላ መደብደቡ የየዕለት ሂደት ሆነና ለሞቱት ስናዝን አውላላ ሜዳ ላይ ተጥለው የተራቡትን ሕጻናት፣ እናትና አባቶችን ዘነጋናቸው፡፡

ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ ወያኔ/ህወሀት/ኢሕአዴግ ለ27 ዓመት ኢትዮጵያን በዘርና ቋንቋ ከፋፍሎ፣ የሕዝባችንን አንድነት ሸርሽሮ፣ አኩሪ ባህላችንን በርዞ፣ ሰንደቅ ዓላማችንን አስረግጦ፣ ተተኪ ትውልድ እንዳይበቅልባት በተለያየ ሱስ የተቻለውን ጥሮ ሰጠኋችሁ ያለው የ100 ዓመት የቤት ሥራ ዛሬ “ለውጥ አራማጅ ነኝ” ያለው የኢሕአዴግ ተቀጥላ አገዛዝ ጀዋር አሕመድ የተባለን አሸባሪ ጥበቃና ከለላ መስጠት በመንግሥት ደረጃ ያሉትን አካላት በሙሉ ከተጠያቂነት እንደማያድን ልናስገነዝብ እንወዳለን፡፡

“እየዬም ሲዳላ ነው” እንደተባለው እራሳቸውን ከሚጋፈጣቸው እርድ ለማምለጥ እግሬ አውጪኝ በማለት የሞተባቸውን የቤተሰብ አካል አፈር ማልበስ ያልቻሉ ቤተሰቦችን በለውጥ ስም ማየት እጅጉን ይዘገንናል፡፡ አባቶች በዱላ ተጨፍጭፈው፣ አካላቸው ተቆራርጦ ያዩ ልጆች በዶር ዐቢይ አገዛዝ ድምጻቸውን በሚዲያ ማድመጥ እንዴት “ጀዋር ወንድሜ” ያሰኛል? በ1997 ዓ.ም. ፍጅት በአጋዚ ጦር ጥይት በራፏ ላይ ልጇ የተደፋባት እናት “አርጩሜ እንኳ ሲበዛበት ነው” ያለችው ልቅሶ ከውስጣችን ሳይጠፋ ዛሬም “ረዳቴን፣ ልጄን” ብላ ምታነባ እናት በዐቢይ “ኢትዮጵያ” መስማት ምንኛ ያቆስላል? ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ አንድ ቤተሰብ በእሳት ሲጋይ፣ “መከላከያ አልደረሰልንም፣ ፌደራል ፖሊስ ቆሞ ነው የሚያየው፣ ለመንግሥት ድምጻችንን አሰሙልን፣ መንግሥት ይድረስልን” የሚል በሞትና በሕይወት መሃል ያለ የጣር ጩኸት የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑት ጠ/ሚር ምላሽ ሲነፈግ ተቃውሟችንን ብናሰማ አግባብ አይደለምን?

እስቲ ለአብነት ያህል ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓ.ም. (December 05, 2019)  የአሜሪካን ድምጽ የአማርኛው ክፍል የዘገበውን ጽዮን ግርማ እንዳቀናበረችው እንስማ፦

“ፋንታሁን ኃይሉ ከ14 ቀናት በፊት በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች በተቀሰቀስ ግጭትና ጥቃት ምክንያት ዶዶላ ከተማ ውስጥ ወላጅ አባቱን አቶ ኃይሉ አስማረን አጥቷል፡፡ የሟች ቤተሰቦችም ተፈናቅለው ዶዶላ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የ6 ልጆች አባት የሆኑት አቶ ኃይሉ ዶዶላ ውስጥ ከ1980 ዓ.ም. ጀምሮ ኖረው 6 ልጆች አፍርተዋል፡፡ ቤቱ ውስጥ ታመው በተኙበት ዱላና ስለታማ ነገር በያዙ ወጣቶች ጥቃት ደርሶባቸው ሕይወታቸው እንዳለፈ ገልጾልናል፡፡ “ቤታችን ውስጥ በተኙበት ታርደው እጃቸው ተቆራርጦ፣ አንገታቸው ታርዶና ሆዳቸው በቢላ ተቀዶ ነው የተደረገው ድርጊት፡፡ የአባታችን ደም፣ የአባታችን ሕይወት ይፋረድልን ለኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንን የአባታችንን አሰቃቂ ግድያ፣ ይሄ በቃ አንገት መታረድ፣ እጃቸውን ተቆርጦ፣ እጃቸውን እኮ ከነአካላቸው አይደለም የቀበርናቸው፡፡ አንድ እጃቸውን እኮ አጥተን እስካሁን አላገኘነውም እኮ፣ ካለ አንድ እጅ ነው የቀበርናቸው አባታችንን፡፡ ይህንን ፍርድ ለእግዚአብሔርና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰጥተናል፡፡” ፋንታሁን እንዲህ ያሉ ነገሮች ተመልሰው እንዳይከሰቱ ማድረግ የሚችለው መንግሥት እንደሆነ ያምናል፡፡ የሰሞኑን ሁኔታ በማስመልከትም ጠ/ሚር ዐቢይ የሰጡትን መግለጫ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠልለውና ሀዘን ላይ በመሆናቸው እንዳልሰሙ ገልጾ ነገር ግን ከመንግሥት መግለጫ ባሻገር የሕግ የበላይነትን ማስከበር የዜጎችን ደህንነት ያረጋግጣል የሚል ሀሳብ አለው፡፡ “ይህንን ነገር ማስተካከል የሚችለው መንግሥት ነው፡፡ እኛ አሁን አባታችን ተገሎብናል፣ ንብረታችን ተዘርፏል፣ ሱቃችን ተዘርፏል፣ መጋዘናችን ተዘርፏል፣ መኖሪያ ቤታችን እንዳለ ተዘርፏል፣ ኧ ከብቶቻችን ተወስደውብናል፣ አማራና ክርስቲያን በመሆናችን ነው፤ የሰው ሀገር ሰው ነን፡፡ እና ይህንን መንግሥት ካልደረሰልን በስተቀር ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ ይህንን ከመንግሥት ነው የምንጠብቀው፡፡ አሁንም ቢሆን ተደራጅተው እንትን እያሉ ነው ያሉት፡፡ ምንም የተረጋጋ ነገር የለም እኛ ጋ አሁን፡፡ የመንግሥት የሕግ የበላይነት ካልተከበረ በጣም አስቸጋሪ ጉዳይ ነው፡፡ ካለንበት ለመውጣት እግዚአብሔር ይርዳን እንግዲህ ያው መንግሥት ካለ ያውጣን፡፡ እንግዲህ ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ እስከመቼ ነው? ቤተክርስቲያን ተቀምጠን የምንኖረው፡፡ እኛ እኮ ለሰው እረጂ፣ ለሰው እረጂ የሆን ነን ዛሬ ተረጂ የሆነው፡፡ እኛ ለስንቱ እየረዳን ነበረ፤ ዛሬ ካለምንም በአንድ ቲሸርት ነው የወጣነው እኮ ካለምንም እንትን፤ ስለዚህ ፈጣሪ እንግዲህ እንትን ይበለን፡፡” ገለልተኛ የሆነ የጸጥታ አካል በሀገሪቱ ላይ ቢኖር መፍትሄ ይኖራል ብሏል፡፡” ሥርዝ የተጨመረበት፡፡

“ቢቂላ ሲርና የተባለ የ18 ዓመት ወንድ ልጃቸው በዚሁ ግጭት በአምቦ በታጣቂዎች የተገደለባቸው እናት ወ/ሮ አበቡ ሰፈራ ከነበሯቸው አራት ልጆች አንዱ እንደነበር ይናገራሉ፡፡  የኦሮምኛ ትርጉምየመጀመሪያው ወንድ ልጄ ነበር፤ የተቀሩት ሦስቱ ሴቶች ናቸው፡፡ የሞተበትን ምክንያት አላወኩም ግን ፖሊስ ነው በጥይት የመታው አሉኝ፤ ሁሉም ነገር አልፎ በተረጋጋበት ነው፡፡ ከምሽን ዝቅ ብሎ በአለው ሥፍራ ላይ የገደሉት፡፡” ልጃቸው በጥይት ከተመታ በኋላ ሕይወቱ ስላላለፈ ወደ ሌላ ሆስፒታል ተወሰዶ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን አይናገርም ነበር፡፡ ጥይቱ በግምባሩ ገብቶ ከበስተኋላ ወጥቷል፡፡ ሐሙስ ቀን ከተመታ በኋላ የዚያን ቀን ለሊት ሆስፒታል አድሮ አርብ ቀን ነው ያረፈው ይላሉ፡፡ ስለ ልጃቸው ሲናገሩ የኦሮምኛ ትርጉምበፊትም እርሱ ነበር የተለያየ ነገር እየሠራ የሚያኖረን እኔ ታማሚ ነኝ አባቱም በሕይወት የሉም፡፡ እሱ ነበር ታላቅ፤ ኪራይ ቤት ውስጥ ነው ያለነው፤ እሱንም ይኸው ገደሉት፤ መውደቂያዬን አጥቼ እየተቸገርኩ ነው” እናቱ ወ/ሮ አበቡ አያይዘው “አባቱ በ2006 ዓ.ም. ነው ያረፉት የተቀሩት ሌሎቹ ሴት ልጆች ደግሞ እራሳቸውን የቻሉ አይደሉም፡፡ ቢቂላ ሸንኮራ እየነገደ አንዳንድ ነገሮችንም እየሠራ ያኖረን ነበር፡፡ የወደፊቱን እንግዲህ እግዚአብሔር ያውቃል፤ እኔ ምን አውቃለሁ” ይላሉ፡፡ “አሁን ስለ ኑሮ ምንም አላስብም፤ ምን እየሆነ እንዳለም አይገባኝም፤ ዞሮብናል አንድ ያለኝን ወንድ ልጄን አጥቼ ምን ኑሮ ነው? ዝም ብለው ምንም ያላደረገ ሕጻን ልጅ እየገደሉ፤ ምንም ነገር ሳይኖር መሣሪያ በመተኮስ መግደል ምን ማለት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ነገር አለ?” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ እህቱንም አነጋግረናት ነበር፡፡ በሕጻን አንደበት እኔ ግን በጣም ሀዘን ተሰምቶኛል፤ ከዚያ በቃ ለምን ዝምብሎ እኛ ዘመዳችን ለምን ይሞታል ብለን እሱ ወንድማችን ነው፡፡ ከዛ ደግሞ ዝም ብሎ ነው ተመቶ በቃ! እሱ ደግሞ የኦሮሚያ ፖሊስ ነው የመታው ደሙ በጣም ነው የፈሰሰ በቃ!” ግድያው ተጠንቶ ለምን እንደተመታ፤ ኦሮሞ ያለምንም ሰበብ ለምን ያልቃል? የኦሮሚያ ፖሊስ ለምን ይመታዋል?” ስትል ትጠይቃለች፡፡ የኦሮምኛ ትርጉምጥሩ ውሻ እንኳን ግልገሎቿን ተንከባክባ በሥርዓት ታሳድጋለች፤ መጥፎ ውሻ ግን መልሳ ግልገሎቿን ትበላለች ለምን ገደሉት? አባታችን ከሞተ በኋላ እሱ ነው ከእናቴ ጋር የሚረዳን፡፡ ትምህርቱን እየተከታተለ ማለቴ ነው፡፡ እኔም ሽንኩርት እየነገድኩ እናቴም ፊልተር ጠላ እየሸጠች ነው የምንኖረው፡፡” ሥርዝ የተጨመረበት፤ የአሜሪካ ድምጽ አማርኛ ዝግጅት ጽዮን ግርማ እንደዘገበችው፡፡

እስቲ ለንጽጽር የዛሬ 15 ዓመት ግንቦት 1997 ዓ.ም. ምርጫ አስታኮ ኢሕአዴግ በአዲስ አበባ ያፈሰሰውን ደም VOA የአሜሪካን ድምጽ አማርኛው ሬድዮ ክፍል ዝግጅት በወቅቱ የዘገበውን እናድምጥና ያለፈው ደም ሳይሽር ዛሬም የመጣብንን መከራ እናዛምደው፡፡

ልጄ ልጅ አልነበረም፤ ልጄ ማለት እናቴ ነው፡፡ አባትና እናት የሚያስቡትን ያህል ነው ጭንቅላቱ የሚያስበው፡፡ እኔ አረብ ሀገር በነበርኩበት ጊዜ የሚጽፋቸው ደብዳቤዎች ያስለቅሳሉ፣ ሁለተኛ እኔ አረብ ሀገር በነበርኩበት ጊዜ በሠራተኛ አይደለም የኖረው፡፡ ሽንኩርት ከትፎ፣ ወጥ ሠርቶ፣ ሻይ አፍልቶ ጠጥቶ፣ ታናሹን አጥቦ፣ ልብሱን አጥቦ፣ እንደዚህ ያለ ልጅ ነው፡፡ እንጀራ መጋገር ብቻ ነው የሚቀረው ልጄ፡፡ የአካባቢ የሀገሩ ሕዝብ ሁሉ ሊመሰክር ይችላል፡፡ ልጄ ኳስ ሜዳ እንኳን አይሄድም፤ ኳስ ጨዋታ እንኳ አያምረውም ልጄ፡፡ ለእኔ ማገዶ እየለቀመ፣ እንጀራ ስጋግር ማገዶ የሚለቅምልኝ ልጄ ነው:: ከዚያ በኋላ አሁን እንኳ ካደገ ወዲያ ልጄ ለእኔ ታዛዤ ነው፡፡ አንድም ጨዋታ የሚያምረው ልጅ አይደለም ውጪ የሚያምረው ልጅ አይደለም፡፡ ሁል ጊዜ “እኔ አድጌ አሳርፍሻለሁኝ”፤ አሁን በሚማረው ትምህርት፣ መካኒክ ነው የሚማረው፣ ጄነራል መካኒክ ነው የሚማረው፤ “እናቴ አሁን ይኸውልሽ ደረስኩኝ በቃ! ይችን ዓመት ነው አይዞሽ!” እያለ የሚለኝ ጨዋ ልጅ ነው፡፡ ቤቴ፣ ልጄ፣ እናቴ፣ ትዳሬ ነው ልጄ፣ ቤቴ ነው ልጄ በቃ! ያጣሁት ሁሉ ነገሬን ነው፤ የመጀመሪያ ልጄ ሁሉን ነገሬን ነው ያጣሁት፡፡ ከእነ ደብተሩ ዝርግፍ አለብኝ በቃ! ምኔም ምኔም ተርፏል በቃ! ምኔም ተርፏል በቃ! በዚህ በሁካታ ወቅት፡፡ ቅር ብዬ እንኳ አላልኩትም እኔ፤ እሱም ልቅር አላለኝም ልማር ብሎኝ ነው፤ “የፈተና ወቅት ነው ልማር ፈተና አያምልጠኝ” ብሎ የሄደው ልጄ ነው እንዲህ የቀረብኝ፡፡ የእኔ ልጅ ውጭውን እንኳ አያቅም፣ ውጭውን እንኳ አያቅም፤ እንኳን እንደዚህ ዓይነት ሁካታ ውስጥ ሊገባ ይቅርና፡፡ እሱ መጽሐፍ ቅዱስ ከማንበብ ሌላ፣ ሁልጊዜ ስለ ኑሮ ከማሰብ ሌላ ምንም የሚያቅ ልጅ አይደለም፡፡ እ…እ…እ… እኔ ስለ ልጄ መናገር አልችልም፤ ምን እንደማደርግም አላውቅም፡፡ የለፋሁበት፣ ሰው ሀገር የተንከራተትኩበት ነገሬ ሁሉ ከንቱ ሁኗል፡፡” በ1997 ግንቦት ወር ምርጫ ተስታኮ በተፈጠረው ዕልቂት VOA የአሜሪካ ድምጽ አማርኛው ሬድዮ ክፍል ዝግጅት በወቅቱ እንደዘገበው፡፡ ዛሬ ይህች እናት እውን ፍትህ አግኝታለች?

እጅግ ይዘገንናል በአፓርትይድ ዘመን ነጮች በጥቁሮች ወንድሞቻችን ላይ የፈፀሙት አሰቃቂ ጥቃት ማለት እችላለሁ፡፡ ጥይት ወደላይ መተኮስ ቀርቶ ወደ ሰው ይተኮሳል፤ የሰው እሬሳ እላይ በላዩ ተደራርቧል፡፡ አንዳንዶች መሄድ አቅቷቸው ሲንፏቀቁ ይታያሉ፡፡ ጎጃም በረንዳ ጨው በረንዳ መውረጃ አካባቢ ደግሞ የተወሰኑት በዱላ ይቀጠቀጣሉ፤ የሚሮጡ በጥይት ይመታሉ፡፡ አብዛኛው የሞቱት ሰዎች ጭንቅላታቸው ተመሳሳይ ቦታ በጥይት መመታታቸውንና ይህም በአልሞ ተኳሾች የተገደሉ መሆኑን ለማወቅ ያስችላል፡፡ በአጠቃላይ በአዲስ አበባ የደረሰው ዕልቂት አሳዛኝ ነው፡፡ ዕሮብ ለታ አብነት አካባቢ ሁለት ወንድ ልጆቻቸው የተገደሉባቸው እናት ሐሙስ ዕለት እራሳቸውን አጥፍተዋል፡፡ ይህም የዕልቂቱን መራራነት ተጠቃሽ አድርጎታል ማለት ይቻላል፡፡” በ1997 ግንቦት ወር ምርጫ አስታኮ በተፈጠረው ዕልቂት VOA በውቅቱ እንደዘገበው፡፡ ዛሬስ ታሪክ እራሱን እየደጋገመ አይደለምን?

እኔ ዓለምነሽ እባላለሁ ከአዲስ አበባ ነው እባካችሁ! እባካችሁ! እባካችሁ! ይድረስ ይሄ ቃል ለዓለም መንግሥታት፣ ከኢትዮጵያ ውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዎች ሁሉ! ለአሜሪካን ሕዝብና ለአሜሪካን መንግሥት ሄ…ሎ…ሄ… እያልን ነው እኛ ኢትዮጵያውያኖች፡፡ ልጆቻችን አለቁ! አለቁ! አለቁ! መኖር አልቻልንም፡፡ ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሄዳችሁ ብታዩ ጉድ! ነው፡፡ እዚህ እሱ የሚያወራውንና እኛ የአየነው ምንም አልቻልንም፡፡ እባካችሁ! እባካችሁ! የድረሱልን ጥሪ ነው የምናስተላልፈው እኛ ኢትዮጵያውያኖች፡፡” በ1997 ግንቦት ወር ምርጫ ተስታኮ በተፈጠረው ዕልቂት VOA የአሜሪካ ድምጽ አማርኛው ሬድዮ ክፍል ዝግጅት በወቅቱ እንደዘገበው፡፡ ዛሬስ ድረሱልን! አድኑን! እያሉ የሚጮሁ ወገኖቻችን በመላዋ ሀገራችን እየተደመጡ አይደለምን?

የዶር ዐቢይን ኢትዮጵያዊነትና የመደመር ሰበካ በቴሌቪዝን መስኮት አንጋጠን፣ ሬድዮ ጆራችን ላይ ሰክተን፣ በየሶሻል ሚዲያው አንገታችንን ደፍተን፣ በየድረ ገጹ ተጣብቀን፣ በየመድረኩ አጨብጭበን ስንዘናጋ ሀገር በታኙ፣ ሕዝብ አስለቃሹ፣ አሸባሪ ቡድን ተደራጅቶና ታጥቆ መጥቶብናል፡፡

ዶክተር ዐብይ አሕመድ እንደ ሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው በሀገሪቱ ወሳኝና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በተደጋጋሚ አፋጣኝ ውሳኔና አመራር ሲሰጡ አይስተዋሉም፡፡ ለምሳሌ በሱማሌ ጉዳይ፣ በድንበር ኮሚሽን፣ በሰላምና ዕርቅ ኮሚሽን ጉዳይ እና የመሳሰሉት ተቋማት በእንጥልጥል ተይዘዋል፡፡ የሰው ሕይወትን እየቀጠፈና የሀገር ሉዓላዊነት እየተፈታተነ የመጣው የጀዋር አሕመድ አካሄድ የዴሞክራሲ ጥያቄ ሳይሆን ሲሻው ዘርና ሃይማኖት እያጣመረ፤ ሲያሰኘውም ዘረኝነትን ተገን እያደረገ የተጓዘበት አሸባሪነት አካሄድ ለበርካታ ዜጎቻችን ሕይወት መጥፋትና በሚልዮን ለሚቆጠሩ ወገኖች መፈናቀል ተጠያቂ እንደሆነ ገሃድ በወጣበት በአሁን ወቅት የሕዝብን እሮሮና ድረሱልኝ ጥሪ አድምጦ አፋጣኝ ምላሽና ውሳኔ መስጠት ተስኗቸዋል፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ እንደ ርዕሰ መንግሥትነታቸው የሚያደርጉት ንግግርና የሚወስዱት ውሳኔ የሚያስተላልፈው መልዕክት ከሰላማዊው ሕዝብ አልፎ ለዘርና ሃይማኖት ነክ አመፀኞችም ትርጉም አለው፡፡ ከዚህም አልፎ በሕግ፣ ፀጥታና ሰላም አስከባሪ የመንግሥት አካላት ተግባርም ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አለው፡፡ በተለይ ሕግ፣ ሰላምንና የሕዝብን ደህንነት የማስጠበቅ ተግባር “በሆደ ሰፊነት፣ በትግዕሥት” እያሉ መናገር አመፀኞችን ማበረታታት ነው፡፡ በጥፋታቸው አይቀጡም፣ ለወደፊቱም አይታረሙም፡፡ እንኳንስ የመንጋ አድመኞች የጭካኔ ግድያ፣ ቤትና ቤተክርስቲያን ማቃጠል ይቅርና በማንኛውም ጊዜ ቢሆን ወንጀል የሠራና ሕግ የተላለፈ ሰው ተጠያቂ ነው፡፡ ይህም ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ ሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናት በንግግርም ሆነ በዕዝም ጣልቃ ሳይገቡ ለፖሊስ ደህንነትና ለሎችም ሰላም አስከባሪ ኅይሎች እንዲያስፈፅሙ የተሰጠ ሃላፊነት ነው የሚይስፈልገው፡፡ እነዚህ አካላት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማሳሰብና የሚይስፈልጋቸውን ድግፍ ማቅረብ ተገቢ ሲሆን ይልቅስ ሃላፊነታቸውን በማይወጡት ላይ ተገቢውን አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ የመንግሥት ሃላፊነት ነው፡፡ ይህንን ሲያደርጉ አለመታያቱ ሰላማዊውን ዜጋ ከማሳሰብ አልፎ ወደ ስጋትና እራሱን፣ ቤተሰቡን፣ ንብረቱንና አካባቢውን እንዴት መጠበቅ እንደሚችል እያሰበና እየተወያየ ነው፡፡

በመሆኑም ከሰሞኑ የጠ/ሚሩ መግለጫ አኳያ “መንግሥት ይደርስልናል” ብለን እራሳችንን አናሙኝ፡፡ ዛሬ ጀዋር፣ ኦነግ እና ወያኔ/ኢሕአዴግ አንድም ሦስትም መሆናቸውን በመገንዘብ ትግላችን ይህንን የ28 ዓመት የዘረኛ አገዛዝ ከሥሩ ነቅለን በመጣል ሀገራችንን እና ሕዝባችንን ማዳን ይኖርብናል፡፡ ቀደም ሲል ሚያዝያ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. “ኢትዮጵያችን” ቅጽ 3 ቁጥር 6 እትማችን  (http://www.ethiopiachen.org/images/pdf/Eth_Vol3/072711_1H1H_Ethiopiachin_Vol_3_No_6.pdf)  “በምርጫ ስም ኢትዮጵያ አትከፋፈልም” ብለን እንዳስነበብነው ዛሬ ስለ ምርጫ የምንደሰኩርበት አይደለም፡፡ “መጀመሪያ የመቀመጫዬን” እንዳለችው ሀገራችንን እናድን፡፡ በየሜዳው ለሚሰቃዩት ወገኖቻችን እንድረስ፡፡ የተነጣጠረብንን ዱላና ሜንጫ ለመመከት እንዘጋጅ፡፡ “ያለ ባለቤቱ አይነድም እሳቱ” እንዲሉ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ዘብ እንቁም፡፡ ታሪክ በአግባቡ ተዘግቦ፣ በየትምህርት ቤቱም በሚገባ ተሰጥቶ ባንማረውም የሀገር በቀሎቹን የዮዲት ጉዲትን፣ የግራኝ አሕመድን፤ ከባዕድ ኃይሎች የድርቡሾች፣ የዐድዋ፣ የሶማሊያ፣ የባድሜ ጦርነቶችን የመከቱት፣ በአኩሪ ተጋድሎ የተወጡትና ሀገርን ለትውልድ ያስተላለፉት ጀግኖቻችን ድሉን የተቀዳጁት በሕዝብ ድጋፍ፣ በጸሎት፣ በመንግሥት ትብብር መሆኑን እንገንዘብ፡፡ ዛሬ በመንግሥት ከለላ አሸባሪው ጀዋር መሐመድ የጥፋት ዱላውን ሕዝባችን ላይ ካሳረፈ እነሆ! ሁለት ዓመት ሲያስቆጥር መንግሥት “አዎ! ከለላና ጥበቃ አድርገንለታል” ለማለት ሲደፍር መልሱ ሊገባን፣ ልንረዳው ይገባናል፡፡

በመሆኑም ከዚህ “ዘመነ ጥፋት” ሀገርና ሕዝብን ለማዳን ብሎም ታሪካዊ ቅርሶቻችንን፣ ሃይማኖታችንና ባህላችንን ለመጠበቅ “እምቢኝ ለሀገሬ!” የምንልበት ሰዓት ነውና በየትኛውም አካባቢ ያላችሁ ወገኖች በጎበዝ አለቃ መሰባሰብ የሚገባን ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡ ከአንድ ወገን አራጁ ሥራውን ጀምሯልና የመከላከል ብቻ ሳይሆን የማምከን የሞራል ብቃት አለንና “ክተት!” ምንልበት ወቅት ነው፡፡

ህፃናት፣ አዛውንት እናትና አባት፣ ወጣቶች እየተቀሉ ለራሳችን ደራሽ እራሳችን መሆኑ እየተነገረን ነውና እምነት ያለህ በጸሎትህ ሀገርህን አድን፣ ሕዝብህን ጠብቅ፡፡ አቅም ያለህ በተለይ ወጣቶች “ሰው ሊኖር ሰው ሞቷል” ታሪክን በመድገም፣ ምሁራን ስለ ኢትዮጵያ አንድነትና ስለ ሕዝባችን ሰቆቃ ድምጻችሁን በማሰማትና ብዕራችሁን ከወረቀት በማገናኘት፣ ሠራተኞች ሀገር ለገጠማት መከራ የተቃውሞ ድምጻችሁን በሥራ ማቆም አድማ ድጋፍ በመስጠት፣ መምህራንና ተማሪዎች ሀገር አቀፍ የትምህርት ማቆም አድማ በማድረግ፣ ነጋዴዎች በገንዘብ፣ በቁሳቁስ በመርዳት፣ የብዙሃን ድርጅቶች በያላችሁበት ድምጻችሁን በማሰማት ኢትዮጵያ ከመጣባት መሃት እናድን፡፡ በውጭው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሰሞኑን በሰሜን አሜሪካ፣ አውሮጳ ለሚመለከታቸው አካላት የጀመራችሁት በሀገራችን እየተካሄደ ያለውን ፍጅትና እልቂት የማጋለጥ ዘመቻ ሳትታክቱ ግፉበት እንላለን፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ ክርስትናና እስልምና ተቋማት ቀሳውስት፣ ሼኾች፣ አባቶች፣ በሀገራችን ላይ እየተካሄደ ያለው ጥቃትና እያንዣበበ ያለው አደጋ ውጤቱ ለማንም አይበጅምና በጋራ በመምከር እየተካሄደ ያለውን ጾምና ጸሎት በማጠንከር በተጨማሪ ለሀገርና ሕዝብ አድን ጥሪ ሃይማኖታዊ ግዳጃችሁን ትወጡ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን፡፡ የፖለቲካ ድርጅቶች እስቲ ለዚህ የኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እልቂትና ለሀገር ውድመት ማብቃት ስንል፣ ተግባራዊ የማይሆነውን ምርጫ አንጋጦ ከመጠበቅ ቅድሚያ ለሀገርና ሕዝብ ድምጽ ማሰማቱ አይጎዳምና ለእናት ኢትዮጵያና ለሕዝባችን ደህንነት እንጩህ ስንል “አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ” የእሪታ ድምጽችንን እናሰማለን፡፡

አሸባሪነት በኢትዮጵያ ልጆች ድል ይመታል!

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

“አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ”

ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም. (December 07, 2019)

ዋቢ ማጣቀሻ ፦VOA የአሜሪካ ድምጽ አማርኛው ሬድዮ ክፍል ዝግጅት በተለያየ ወቅት ከዘገባቸው፡፡

ማሳሰቢያ ፡

  • ውድ ወገኖቻችን ይህንን «አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ» «ኢትዮጵያችን» ልሳን በተለይ በሀገር ቤት ኮምፒዩተር የማግኘት ዕድል ለሌላቸው በማባዛት ታሰራጩት ዘንድ ቀና ትብብራችሁን በትህትና እንጠይቃለን።
  • «አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ» መስከረም 8 ቀን 2009 ዓ.ም. እራሱን ይፋ ያደረገ ሕዝባዊ ድርጅት ሲሆን የንቅናቄውን ማንፌስቶና ፕሮግራም ethiopiachen.org ከሚለው ድረ ገጻችን ማግኘት ትችላላችሁ።

 

ኢሜል ፡ ethiopiachen2009@gmail.com

ድረ ገጽ ፡ www.ethiopiachen.org , www.ethiopiachen.com

ምሥለ ገጽ ፡ 1H1H Ethiopiachin

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.