ከባንክ ደንበኞች ላይ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ያጭበረበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

የተሰረቁ ቼኮችን እና ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም ከተለያዩ የመንግስትና የግል ባንክ ደንበኞች ላይ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ያጭበረበሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ ከፌደራልና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተውጣጣ የምርመራና የክትትል ቡድን በማዋቀር ምርመራው መጀመሩን በኮሚሽኑ የከባድ ሌብነትና ዘረፋ ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ያሬድ አለማየሁ ገልፀዋል።

በወንጀሉ ተጠርጥረው የተያዙት ከ70 በላይ ግለሰቦች ከተለያዩ የግል ተቋማት ቼኮችን በመስረቅ እና ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ከተለያዩ የግል ባንክ የደንበኞች የባንክ ሂሳብ ውስጥ 60 ሚሊየን 843 ሺህ 601 ብር ወጪ አድርገው መውሰዳቸው በምርመራ ተረጋግጧል ብለዋል።

በተመሳሳይ መንገድ ወጪ ተደርጎ ሊወሰድ በሂደት ላይ የነበረ ከ28 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን እና ከተጠርጣሪዎቹ እጅ የተለያዩ የባንክ ቼኮች እንዲሁም ለወንጀል መፈፀሚያነት የሚጠቀሙባቸው ቁሳቁሶች መያዛቸውንም ተናግረዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በተጠርጣሪዎቹ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ውስጥ የተገኘ ከ16 ሚሊየን ብር በላይ እንዲታገድ መደረጉን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን የፈፀሙት ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከባንኮች፣ ከወረዳ አስተዳደር፣ ከሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ፅህፈት ቤት እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት መረጃ የሚሰጧቸውን ሰራተኞች በመመልመል መሆኑንም ጠቅሰዋል።

(ኤፍ ቢ ሲ)

One Response to ከባንክ ደንበኞች ላይ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ያጭበረበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

  1. City of Addis Ababa Police Commission stole our condominiums from us giving it to the ethnic Oromo city police officers family members , leaving us honest hard-working poor non Oromos no other choice but to try to get money through crime so we can secure a roof over our head. For the time being Jail is a roof over our head.

    Avatar for Anteneh Girma

    Anteneh Girma
    November 11, 2019 at 1:53 am
    Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.