የህዳሴው ግድብ ድርድር ሂደትና የግብፅ ሴራ!!

1 min read

ራፋኤል አዲሱ

አሜሪካና የአለም ባንክ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በግብፅ ውትወታ በሦስተኛ ወገን አደራዳሪነት/ታዛቢነት መሰየም ግብፅ ጉዳዩን አለም አቀፍ ገፅታ እንዲይዝ ( internationalize) በማድረግ የሦስትዮሽ ድርድሩ ሂደት ከቴክኒካል ይዘት ወደ ፖለቲካዊ ይዘት እንዲሸጋገር የሰራችው ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ውጤት ነው:: አሁን ድርድሩ የደረሰበት ደረጃ ግብፅ የሀያሏን ሀገር አሜሪካ እና አሁን ላይ ዋነኛዎቹን የሀገር ሀብት የሆኑ በመንግስት የሚተዳደሩ ተቋማት (SOEs) ወደ ግሉ ዘርፍ በሽያጭ ለማዞር ( Privatize ለማስደረግ) ለአብይ አስተዳደር ድጋፍ እየሰጠ ያለውን የአለም ባንክ ጫና በመጠቀም በፖለቲካዊ ውሳኔ የኢትዮጵያን ሀገራዊ ጥቅም (national interest) በማሳጣት (compromise በማስድረግ) ለአንድ ምዕተ አመት የቆየ ጥቅሟን ለማስጠበቅ አልማ የሰራችበት የሴራ አካሄድ ነው::

ትላንት በዋሽንግተን ዲሲ በአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በአሜሪካና በራሷ በሚዘወረው የአለም ባንክ አደራዳሪነት በተደረገው ውይይት ወቅት በሦስቱ ሀገሮች (ግብፅ: ሱዳንና ኢትዮጵያ) በተገባው ስምምነት መሰረት እስከ ፈረንጆቹ ጥር 15, 2020 የህዳሴ ግድብን የውሃ አሞላልና ኦፕሬሽን በተመለከተ በውሃ ሚኒስትሮች ደረጃ በሚደረጉ አራት የሦስትዮሽ ቴክኒካል ውይይቶች ስምምነት ላይ ለመድረስ ለመስራት ተስማምተዋል:: በእነዚህም ውይይታቸው ሶስቱ ሀገራት በአውሮፓውያኑ 2015 ላይ በካርቱም የደረሱትን ስምምነት ተፈፃሚ ለማድረግ ግልፅ ሂደትን ለማስቀመጥም ነው የተስማሙት። በተጨማሪም አደራዳሪዎቹ አሜሪካና የአለም ባንክ በታዛቢነት በሚሳተፉበት የስምምነቶቹን አፈፃፀም ለመገምገምና ለመደገፍ በሦስቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ደረጃ የሚደረጉ ሁለት ስብሰባዎችን በዋሽንግተን ለማከናወን ከስምምነት ደርሰዋል።

በዚህ የዋሽንግተን ዲሲ ስምምነት መሰረት እስከ ፈረንጆቹ ጥር 15, 2020 ድረስ ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻሉ በካርቱም የተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት አንቀፅ 10ን ተግባራዊ ወደ ማድረግ ይሸጋገራሉ:: ይሄ አካሄድ ግብፅ እራሷ አስባበት የወጠነችው የድርድር አቅጣጫ በመሆኑ እስከተቀመጠው የጥር 15, 2020 ቀነ ገደብ ድረስ በውሃ ሚንስትሮች ደረጃ የሚደረጉት የሦስትዮሽ ቴክኒካል ውይይቶቹ ግብፅ ቀደም ብላ ባቀረበቻቸው ፕሮፖዛሎች መሰረት ካልሄዱ ባለመቀበል ከስምምነት እንዳይደረስ ለማድረግ እንደምትሰራ ይጠበቃል:: ይህ ደግሞ ለግብፅ በእጅጉ ወደሚጠቅማትና ከቴክኒካል ውይይት ይዘት ወጥቶ ፖለቲካዊ ይዘት ብቻ ወደሚኖረው በሀገራቱ ርዕሰ-ብሔራት (heads of states) [በፕሬዚዳንትና ጠ/ሚር] ደረጃ በአለም አቀፍ የሦስተኛ ወገን አደራዳሪነት ወደሚደረግ ሦስቱ ሀገራት በአውሮፓውያኑ 2015 ላይ በካርቱም በደረሱት ስምምነት በአንቀፅ 10 ወደተቀመጠው የውይይት አግባብ ይሸጋገራል ማለት ነው::

በዚህ አካሄድ ግብፅ አለም አቀፍ የሀያላን ሀገራት አጋሮቿን የፖለቲካ ጫና በመጠቀም በምትፈልገው መልኩ በፖለቲካዊ ውሳኔ እንደ 1959 ዓ.ም.(እ.ኤ.አ.) የናይል ውሃ አጠቃቀም ስምምነት የግብፅን ጥቅም በዋናነት በሚያስጠብቅ መልኩ ውሳኔ እንዲደረስ የማድረግ እቅድ እንዳላት እገምታለው:: ይህ አካሄድ ደግሞ በ1889 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ.) በኢትዮጵያና በኢጣሊያ መሀከል የተደረሰውና ኋላ ላይ ለታላቁ የአድዋ ጦርነት ምክንያት የሆነው የዉጫሌ ስምምነት (The Treaty of Wuchale) አይነት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ያላትን ሉዓላዊና ተፈጥሯዊ መብት (sovereign and natural right) ለሚያሳጣት ታሪካዊና በፖለቲካ ጫና ለተሸረበ ውል እድሉን ይፈጥራል የሚል ስጋት አለኝ::

1 Comment

  1. The GERD dam construction total cost is expected to be over than $6.4 Biliions of USD dollars.

    More than $4 Billions of USD dollars had already been spent so far with 60% of the construction or over a half of the construction being completed so far.

    In the future 40% of the construction is yet to be completed. Ethiopia will most likely need to borrow money from Egypt to finish the remaining 40% of the Construction.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.