ፕ/ት ትራምፕ “አሸባሪዎችን “ቢያስታግሱልን ምን አለበት? – ታምሩ ገዳ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

የአሜሪካው ፕ/ት ዶናል ትራምፕ በአወዛጋቢው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ የሚነታርኩት የኢትዮጵያ፣የግብጽ እና የሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮችን በማነጋገር የህዳሴው ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ ወደ ኢትዮጵያ ብቅ ብለው የምረቃ ማብሰሪያውን ክር (ሪቫን)በመቁረጥ ክብረበአሉን እንደሚያደምቁት መናገራቸውን አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ገልጸዋል ።

ሰሞኑን ዋሽንግተን ከተማ ላይ የተካሄደው ውይይትን የታደሙት የኢትዮጵያ የውሃ እና የመስኖ ሚኒስተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የጉዟቸው ውጤትን በተመለከተ ለአገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃናት እንደተናገሩት”የህዳሴው ግድብ በሰላም እና በስምምነት ተጠናቆ ሲመረቅ ፕ/ት ትራምፕ በስፍራው ተገኝቼ ሪቫን እቆርጣለሁ ብለዋል” ሲሉ ኢንጂነር ስለሺ የትራምፕን ምኞትን ገልጸዋል። ትራምፕ ቃላቸውን ከጠበቁ በስልጣን ላይ ሳሉ ኢትዮጵያን በመጎብኘት ሁለተኛው የአሜሪካ መሪ ይሆናሉ ማለት ነው።

በአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስተር ስቲቨን ማኑቺ አደራዳሪነት ዋሽንግተን ላይ የተሰባሰቡት የኢትዮጵያ፣የሱዳን እና የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚኑስተሮች በመጪው ጥር 15 2020 እኤአ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የመጨረሻውን ፊርማ ይፈራረማሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ከአስራ ሁለት አመት በላይ የተፋሰሱ አገራትን ያወዛገበው ያባይ ወንዝ እና ከአምስት አመት በላይ ግብጽ እና ኢትዮጵያን በእጅጉ ያካረረው የህዳሴው ግድብ ግንባታ አሜሪካ በተለይ ደግሞ በፕ/ት ትራምፕ ዘመን በምን አይነት የዲፕሎማሲ የመጫወት ክህሎቷ እንደምታረግበው ለብዙዎች ለመገመት ከብዷል።

አንዳንድ ታዛቢዎች በበኩላቸው የ ፕ/ት ትራምፕ መልካም ምኞትን በአውንታነት በመደገፍ ” ኢትዮጵያን በተመለከተ ከአፋቸው የወጣው በጎ ቃላት እንደተጠበቀ ሆኖ በሁለት ዛፎች ላይ ተንጠልጥለው(የአሜሪካ ፖስፓርትን እንደማስፈራሪያ እና መሸሸጊያነት እየተጠቀሙ )ለበሬ እና ለትራክተር መግዢያ፣ለት/ቤት ለጤና ኬላ መገንቢያ ሳይሆን ፣ ለቆንጨራ እና ለጥይት መሸመቻ የሚውል ገንዘብን በገፍ በማሰባሰብ እና በመላክ ለዘመናት በሰላም እና ተከባብሮ በኖረው ምስኪን ኢትዮጵያ ደም እና ነፍስ ላይ ተራ የፖለቲካ ችርቻሮ የሚያካሄዱ እና እያካሄዱ ያሉ ግለሰቦችን አርፋችሁ ተቀመጡ፣አሊያም ጓዛችሁን ጠቅላላችሁ ወደ አገራችሁ ሄዳችሁ ችግሩን እዚያው ተጋፈጡ ፣ እሳቱንም አብራችሁ ሙቁ ፣ወደ አሜሪካም ዞር ብላችሁ እንዳታዩ ቢሉልን ከአራት ቢሊዬን ዶላር በላይ የሚፈጀው እና በአመት ስድስት ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው የህዳሴው ግድብን ቱጃሩ ፕ/ት ትራምፕ በሙሉ ወጪያቸው እንዳስገነቡልን ያህል እንቆጥረዋለን።”በማለት በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ እና ልጆቿ የሰላም ፣የአንድነት እና የፍቅር እጦት እንጂ የዲፕሎማሲ እና የእውቀት ደሃዎች አይደሉም ሲሉ ቁም ነገር አዘል አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል።

የ ፕ/ት ትራምፕ የዲፕሎማሲ ጉዞዎች:-:-

የፕ/ት ትራምፕ የእስከ አሁኑ ታሪካቸው የራስን ገጽታ በመገንባት ላይ ብቻ ያተኮረ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ።
ለምሳሌ ያህል ሰላሳ ኢትዮጵያን ክርስቲያኖችን ጨምሮ ለበርካታ ሰላማዊ ወገኖች መገደል ዋንኛ ተጠያቂ የሆነው እና የአክራሪው አይሲስ መሪ የነበረው አቡበከር አል ባግዳዲ ሰሞኑን “እንደ ውሻ እያላዘነ ገደል ነው” በማለት ትራምፕ በቴሌቭዥን መስኮት ሲፎክሩ ተስተውለዋል።

እውነታው ግን ሶሪያ ድንበር ላይ በአሜሪካ ወታደሮች ከበባ ውስጥ መሆኑን የተረዳው አል ባግዳዲ እራሱን እና ሶስት ልጆቹን በታጠቀው ቦንብ አንጉዶ መሞቱን የአሜሪካ ወታደራዊ መረጃዎች ገልጸዋል። የአሜሪካ ጦር ከሶሪያ መሬት እንዲወጣ በትዊተር መልክት ያዘዙት ፕ/ት ትራምፕ አናሳዎቹ ኩርዶችን ለጨፍጫፊዋች በገጸበረከትነት አሳልፈው ሰጥተዋል የሚል የከረረ ወቀሳ ከራሳቸው ከሪፖብሊካን ፓርቲ አባላት ሳይቀር ገጥሟቸዋል።

ከኢራን ጋር እኤአ 2015 ተደርሶ የነበረ የኒኩሌር አጠቃቀም ስምምነትን ፕ/ት ትራምፕ አፍርሰዋል በቴህራንም ላይ ማእቀባቸውን ይበልጥ አጠንክረዋል ፣ከአፍጋኒስታን የታሊባን አማጺያኖች ጋር ጀምረውት የነበረው ምስጢራዊ የእርቀ ስላም ስምምነትን ወዲያውኑ አቋርጠዋል፣ (ባለሮኬቱ ሰውዬ)ከሚሏቸው ከሰሜን ኮሪያው ፕ/ት ኪም ጆንግ ኡን ጋር የጀመሩትን ድርድርን ሁለቱ ኮሪያዎችን የሚያዋስነው ድንበርን በማቋረጥ የመጀመሪያው ምእራባዊ መሪ ቢባሉም ድርድሩን ረግጠው በመውጣት እንደገና እንወያይ በማለት ላይ ይገኛሉ።

አሜሪካ ከትንሿ ጎረቤቷ፣ከ ኩባ ጋር ለሀምሳ አመታት የነበራትን ተቃርኖን በዘመነ ፕ/ት ባራክ ኦባማ እኤአ 2015 ለዘብ ብታደርገውም ፕ/ት ትራምፕ ስልጣን በያዙ ማግስት በኩባ ላይ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ማእቀቡ ጫናው እንዲ በርታ አድርገዋል።

በመሬት ይገባኛል ሳቢያ ከግማሽ ምእተ አመት በላይ እየተዋጉ የሚገኙት ፍልስጤሞች እና እስራኤሎች ብቸኛው መፍትሄ የሁለት መንግስታት ምስረታን ማጽናት እንዲሆን ብዙ አገራት ይስማማሉ።ይሁን እንጂ አወዛጋቢው የእየሩሳሌምን ከተማ ጉዳይን በተናጥል በመወሰን የአሜሪካ ኢምባሲንም ከቴላቪቭ ከተማ ወደ እየሩሳሌም እንዲዛወር ትራምፕ መወሰናችው በእስራኤሎች ዘንድ “ጀግናው መሪ ” ሲሰኙ ፍልስጤሞች በፌናቸው “ከሀዲው መሪ” በማለት ይኮንኑዋቸዋል። በእነዚህ እና መሰል አወዛጋቢ ውሳኔዎቻቸው እና ተለዋዋጭ ባህሪያቸው በርካታ ምእራባዊያን ተንታኞችም ” ፕ/ት ትራምፕ እኮ ያው እንደ ስያሜያቸው ….ማለት ናቸው።”ሲሉ ይወርፏቸዋል።

(በታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)

5 Responses to ፕ/ት ትራምፕ “አሸባሪዎችን “ቢያስታግሱልን ምን አለበት? – ታምሩ ገዳ

 1. Effort conglomerate and METEC. Messobo Cement factory had been putting/burried low quality standard materials some places no material along with dynamite chemical explosives deep in the GERD dam by falsifying records , explosives are put so when the GERD dam collapses due to the low quality sometimes no materials the METEC Effort Conglomerate put starting from deep inside the foundation upto the middle part of the dam by breaching the contract they were hired to do resulting in possible collapse of the entire dam .

  When the collapse happens due to the low quality materials , any of the remaining evidence of the low quality materials are intended to get blown into pieces with the dynamite chemical explosives put burried so no evidence remaining survives to hold the METEC EFFORT CONGLOMERATE liable for the GERD dam collapsing.

  http://www.ginbot7.org/List_of_TPLF_Companies_Under_EFFORT.htm

  Avatar for Sara

  Sara
  November 9, 2019 at 5:56 pm
  Reply

 2. እውነት ነው፣ “ለቆንጨራ እና ለጥይት መሸመቻ የሚውል ገንዘብን በገፍ በማሰባሰብ እና በመላክ ለዘመናት በሰላም እና ተከባብሮ በኖረው ምስኪን ኢትዮጵያ ደም እና ነፍስ ላይ ተራ የፖለቲካ ችርቻሮ የሚያካሄዱ እና እያካሄዱ ያሉ ግለሰቦችን” እና ቡድኖች፣ አንተ ለማመላከት እንደከጀልከው ፎቶውን እዚህ የለጠፋችሁት ሳይሆን፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ በአባቶቻቸው በተዘረፈ ገንዘብና ሃብት አሜሪካ ሃገር ተልከው የተንደላቀቀ ኑሮ የሚኖሩ፣ የቀድሞ ፊውዳሎች ልጆችና የነፍጠኛ ርዝራዦች ናቸው! በሚልኩት ገንዘብ የድሮ የፊውዳል ስርዐትና ጪሰኞቻቸውን የሚያስመልሱ መስሎአቸው ገንዘብ በገፍ በማዋጣት ቅጥረኛ ነብሰበላዎችን ቀጥረው፣ በገዛ ሃገሩ ለመብቱ ለመከራከር የወጣውን ሰላማዊ የኦሮሞ ወጣት ላይ ያስዘመቱ፣ ድርጊቱንም በኦሮሞ ወጣቶች ላይ በማላከክ በሰፊው በተቆጣጠሩት ሚዲያ ሁሉ ሙሉ የኦሮሞን ህዝብ ስም ለማጉደፍ ለት ተቀን ጥሩንባ የሚነፉ ናቸው።

  በመጀመሪያ ደረጃ፣ አንድ ወገን ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ፣ መቃወም ወይም መቆጣጠር ያለበት የመንግስት ፖሊስ ሆኖ እያለ፣ ሌላ የተደራጀና የታጠቀ ሃይል ለምን ሰላማዊ ሰልፍ ታደርጋለህ ብሎ ጥቃት ማድረስ ቀርቶ የመጠየቅም መብት የለውም። የተደረገው ግን እነዚህ በአብንና ኢዜማ የተደራጁና የታጠቁ ወሮበሎች ሰልፍ የወጡትናን ሌላውንም መንገደኛ ከማጥቃት አልፈው፣ ቤተ ክርስቲያናትንና መስጊዶችን በማቃጠል የዘርና የሃይማኖት ብጥብጥ እንዲነሳ ሞከሩ። የተልዕኮው ጠንሳስና መሪዎች ደግሞ፣ የፕሮፓጋንዳ ሽፋን ከመስጠት ሌላ፣ ቄሮን አልፎም የኦሮሞን ህዝብ በጅምላ በአሸባሪነት በአለም ዙሪያ ሲከሱ ይታያሉ! የውሸት እግር አጭር ናትና፣ አላማቸው አይሳካም! ባይሆን ያተረፉልን ነገር ቢኖር፣ ህዝብን በጅምላ ከሚወነጅሉ ወገኖች ጋር አብሮ ለመኖር የወደፊት ተስፋ እንደሌለ አሳይተውናል! የኦሮሞ ህዝብ ያለማወላወል ለፍጻሜው ነጻነቱ በአንድነት ቆርጦ መነሳት እንዳለበት ነው! የጭቆናችሁን ዘመን ለማራዘም ሁሌም የባዕዳንን ዕርዳታ እንደምትጠይቁ በታሪክ የተመዘገበ ነው። አዲዮስ ኢትዮጵያ!

  Avatar for Abba Caala

  Abba Caala
  November 9, 2019 at 6:40 pm
  Reply

 3. Donot use Religion for your political gain . STOP condemning eachother . You could learn from european they were fighting among eachothers for centuries .

  https://en.wikipedia.org/wiki/France%E2%ted_Kingdom_relations#The_Hundred_Years'_War

  Let us say “let bygones be bygones” ,”bury the hatchets, and vow to work together for united Ethiopia. We donot profit from war and violence.

  We donot live for more than 6 decades , let alone for centuries.

  Why are you using religion here to divide people , do you think that your argument will hold water when you engage in religious politics.

  Why did you shit from ethnic based agenda, YOu could also say that peopel who get massacred in Dodola are Amhara .

  Why are you here advocating for Oromos in the name of Orthodox .There are christians in Oromia , Tigray, Gumuz, Kimant , Benshangul.

  When you want to extend your teritorry you massacre Agew, Kimant, Agew, Oromo and others ?

  Why are you changing your face like Chameleon.I understand you are trying to use these innocent people for your political convenience, profit.

  You could learn a lot from Europeans and Rwandans who were killing with one another over 100 years and 100 days respectively and began to befriend with one another and establish a strong bond among themselves.

  I believe Jawar is better than you, your countless victims who fall victim to superstition, poison,voiceless dagger, pen, amhara elites who constantly instigating Amhara to kill Kimant and others

  Stop this dirty ethinic or religious based politics and work together with your fellow brothers and sisters

  Avatar for Biratu

  Biratu
  November 10, 2019 at 5:12 am
  Reply

 4. Obviously if you have the iq of a donkey you will admire Jawar and cry Oromia. Jawar is nothing but the face of Abiy and EPRDF. You should in reality admire Abiy for using Jawar to his ends. But then again one needs to be human first to have any human iq. Anyone who supports murder and mutilation is not human not even an animal. That’s you Biratu and caala and the millions of you.

  Avatar for Enqoqo

  Enqoqo
  November 11, 2019 at 10:51 pm
  Reply

  • you are enqoqo yourself, your face and tongue is bitter than enqoqo, aloevera metetegna

   Avatar for mamito mamo

   mamito mamo
   November 13, 2019 at 7:16 am
   Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.