የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 75ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 75ኛ መደበኛ ስብሰባ በአምስት ረቂቅ አዋጆች እና ደንቦች ላይ ተወያይቶ አዋጆቹ ይፀድቁ ዘንድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

በመከላከያ ሚንስቴር በቀረበ የመከላከያ ሠራዊት መተዳደሪያ ረቂቅ ደንብ እና የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ ደንቦቹ ፀድቀው በስራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል፡፡

የፌደራል የአስተዳደር ስነ-ስርዓትን ለመደንገግ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ፣ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ እና በኢትዮያ እና በጅቡቲ መንግስት መካከል የተፈጥሮ ጋዝ ቧንቧ መስመር ለማስተላለፍ የተደረገውን ስምምነት ለማፅደቅ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ አዋጆቹ ይፀድቁ ዘንድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑን የጠቅላይ ሚንስቴር ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.