ከዓለማቀፋዊ የአማራ ሕብረት የተሰጠ መግለጫ 

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

November 9, 2019

ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል ለሕይዎት መጥፋትና ንብረት መውደም ተጠያቂ የሆኑት እነጅዋር ሙሃመድ ለፍርድ ይቅረቡ

ዶ/ር ዓቢይ አህመድ እንደመጡ በትኩሱ ያደረጓቸውን ሥራዎችና የወሰዷቸውን ዲሞክራሲያዊ የሚመስል እርምጃዎች በማድነቅ፣ ዘራፊና ገዳይ የነበሩት የወያኔ መሪዎች በመወገዳቸው የተሰማውን ደስታ በመግለጽ አማራው ከየሚኖርበት በሰልፍ እየወጣ ድጋፉን መስጠቱ

ይታወሳል፡፡ ነገር ግን፣ እየቆዬን ስንመጣ፣ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ፣ ስንሞት ኢትዮጵያ” በማለት ተስፋ በሰጡት ጠ/ሚ አገዛዝ የተሰነቀው ተስፋው እየጨለመ፣ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ፣ ህዝቡ ከወያኔ ጊዜ በባሰ እየተፈናቀለና እየተገደለ፣ በሜንጫ እየታረደ፣ ዓይኑ በጉጠት እየተጎለጎለ፣ ምላሱ እየተቆረጠ፣ የቤተክርስቲያንና የመስጊድ ማቃጠል፣ እጅግ ዘግናኝ ኢትዮጵያ ታሪክ ወስጥ ተሠርቶ፣ ተሰምቶም በማያውቅ ሁኔታ የብሄርና የሃይማኖት ጦርነት ለመቀስቀስ፣ በተወሰኑ ቅጥረኞችና የተደራጁ አገርበቀል ወንጀለኞች ከፍተኛ ዘመቻ እየተጧጧፈ ይገኛል፡፡

ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ከተሞች የተደረገውን ጭፍጨፋ በተመለከተ፣ የጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መግለጫ፣ በጃዋር መሐመድ የጦር አዝማችነት የቄሮ ወራሪ ሠራዊት በአማሮች ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋ በሁለት ተፎካካሪዎች መካከል እንደሚደረግ

ዕለታዊ ግጭት አድርጎ አሳንሶ በማስመሰል “እርስ በርስ ተቧድነው» የሚል ቃል በማኅበራዊ መገናኛ መናገራቸው እጅግ አስደማሚ ነው፣ ይህ አነጋገራችው የሚያመለክተው ወንጀለኛውን ቄሮን ተጠያቂ ላለማድረግ፣ የተጨፈጨፈው ግፍ የተሠራበት አማራው ለሞቱ ተጠያቂው ራሱ እንደሆነ አድርጎ ለማቅረብ የተቃጣ ነው፡፡ ይሁን እንጅ፣ ዕውነታው ሌላ ነው፡ ቀንደኛ መሪውን ጃዋርንና ተከታይ ሠራዊቱን፣ ቄሮን ከተጠያቂነት ነጻ ለማውጣት የሚደረገው ሙከራ ሁሉ እጅግ አሳዛኝና አሳሳቢ ቢሆንም ቅሉ፣ የሰሞኑ የቄሮ ጭፍጨፋ በአማሮች ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ መሆኑን ሊለውጠው የሚችል ከቶ ምንም ዐይነት ምክንያት ሊቀርብ አይችልም፡፡

በኦነግና በወያኔ ተገንጣይ ቡድኖች ጊዜያዊ ስምምነትና የማያዛልቅ ሴራ፣ የአማራውን ህዝብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ለእነ ጅዋር ሙሃመድ፣ ህዝቅኤል ጋቢሳና በቀለ ገርባ ለመሳሰሉት ከሀዲዎች ቁጥር የሌለው ገንዘብ እያፈሰሱ ድሀውንና ረሃብተኛውን ወጣት ዕውነትነት የሌለውና የተዛባ የሀሰት ታሪክ በመስጠት፣ አዕምሮውን በመበረዝና የጫት መቃሚያ ሣንቲም በማታለል ሥርዓት አልባ የሆነ ሁለተኛ መንግሥት

የሚመስል “ቄሮን” መሥርተው አገር ለማፍረስ በአማራውና በሌላውም፣ ኦሮሞ ባልሆነው ዘር ሁሉ ከፍተኛ ግድያና አሰቃቂ ድርጊት እየፈጸሙ ነው፡፡

ታዲያ የዚህ የቄሮ መንጋ መሪው አቶ ጅዋር ሙሀመድ መሆኑን መንግሥት ጠንቅቆ እያወቀ፣ ጭራሽ እሱን ምንም እንዳይነካው በስፔሻል ፎርስ፣ በሠለጠኑ ወታደሮች እየተጠበቀና በኢሀደግ ውስጥ በሚሠሩ የጦር መኮንኖች ፣ የደህንነት ሠራተኞችና ከፍተኛ ሹማምንት እየተደገፈ የፈለገውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል፡፡

እንግዴህ ኢትዮጵያን መምራት፣ ህዝብን ማስተዳደር ማለት ወንጀለኞችን፣ ያውም የውጭ አገር ዜጋ የሆኑ የዘር ጥላቻ በመርጨት በገሀድ እየሰበኩ ያሉትን ቅጥረኞች አቅፎ ይዞ በየቀኑ ህዝብ እየታረደ፣ ዕትብቱ ከተቀበረበት ቦታው እየተፈናቀለ፣ እየተባረረና እየተገደለ፣ ድረሱልኝ፣ አድኑኝ በማለት እየተማጸነ፣ በገዛ አገሩ የሚደርስለት አጥቶ፣ የመንግሥት ያለህ እያለ ሲጮህ ጆሮ ዳባ ልበስ፣ ዓይኔን ግንባር

ያርገው አላየሁም፣ አልሰማሁም ብሎ ዝም ብሎ የሚቀመጥ ከሆነ በሀገራችን መንግሥት አለ? የለም በሚያስብል ደረጃ የብዙ ህዝብ ጥያቄ እየሆነ መጥቷል፡፡

አማራው፣ ወያኔን የጅአዙር የግፍ አገዛዝ ቀንበር ተሸክሞ ያለምንም ምክንያት አማራ በመሆኑ ብቻ ሲታሠር ሲገረፍ ሲኮላሽና ሲገደል ለ27 ኣመት ቢኖርም በደሉና ሰቆቃው፣ ግፉ ከመጠን

አልፎ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በመሆን ኢሀደግን ያሽከረክር የነበረውን የትግራይ ተገጣይ ቡድን ቁንጮ አባላትን አስወግዷል፡፡ አሁንም፣ አማራው የራሱንና የኢትዮጵያን

የሀገሩን ህልውና ለማረጋገጥ ከሌላው ሀቀኛና ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በመሆን እንደአያት ቀድመአያቱ ከባንዳና ከከሀዲ ጋር በመፋለም፣ በአጥንቱና በደሙ የኢትዮጵያን አንድነትና ህያውነት ለማረጋገጥ እንኳን ሜንጫና ቆንጨራ፤ መድፍና መትረጌስ እንደማይበግረው ሊታወቅ ይገባል፡፡ ይኸ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ግን የኢትዮጵያን ህዝብ ለማተረማመስ በግልጽ እየሠሩ ባሉት በነጅዋር ሙሀመድና ለነርሱም የእኩይ ሥራ አጋር ለሆኑላቸው በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ለተሠገሰጉት ሹማምንት፣ የበታች ሠራተኛ፣ የጦርና የፖሊስ መኮንኖች ምንጊዜም ከንደዚህ ያለ አድላዊና ወገንተኛነተኝነት እንዲቆጠቡ አስፈላጊው ተግሳጽና ምክር ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

በመቀጠል፣ ከዚህ በታች ከተራ ቁጥር 1 – 6 የተዘረዘሩትን በመንግሥት በኩል ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲተገበሩ ቢደረግ ለሀገራችን ደህንነት ይበጃሉ የሚል ፅኑ እምነት አለን፤

1) የመንግሥት ታጣቂ ኃይሎችን ከለላ በማድረግ በቄሮዎችና በተደራጁ የአጥቂ ሀይሎች በጅዋር ሙሃመድ አሳታፊነት በደረሰው አሰቃቂ የሆነ የሰው ዕልቂት ሰለባ ለሆኑት ቀሪ ቤተሰቦች፣ በየቦታው አስቸኳይ የምግብ፣ የዉሃና የመጠለያ ዕርዳታ እንዲደረግላቸው፣

2) ክ84 ቁጥር በላይ በሠላማዊ ሰው ላይ ለደረሰው የህይዎት መጥፋትና ለንብረት መውደም ዋና ተጠያቂው ጅዋር ሙሃመድ ነው፤ ስለሆነም፣ ነገ ዛሬ ሳይባል ባስቸኳይ ተይዞ በሕግ ፊት ለፍርድ እንዲቀርብ መደረግ አለበት፣

3) በኢትዮጵያ የክርስትና አማኞችና ካህናት በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ የደረሰውና እየደረሰ ያለው ያላቋረጠ ጭፍጨፍና እልቂት በአስቸኳይ እንዲቆምና መንግሥት ተገቢውን ጥበቃና መልሶ የማቋቋም ተግባር እንዲያከናውን፣ ቤተሰቦቻቸው የተገደሉባቸው እንደ ሁኔታው አሰቃቂነትና ብዛታቸው መጠንና ንብረታቸው የተዘረፈባቸው፣ ተመጣጣኝ ካሣ መንግሥት እንዲከፍላቸው አበክረን እንጠይቃለን፤

4) በዘር ልዩነት ላይ የተመሠረተውን ህገመንግሥት ተገን በማድረግ በአማራው ላይ “ነፍጠኛ/ትምክህተኛ” የሚል ቅጽል ስም በመስጠት፣ ከአማራ ክልል ውጭም ሆነ በአማራ ክልል ውስጥ የሚካሄደውን ዕልቂትና የዘር ማጥፋት ዘመቻ በመግታት ጸጥታና መረጋጋት እንዲኖር፣ ባስቸኳይ መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ የህዝቡን ደህንነት በሚያረጋግጥ መንገድ በአዋጅ የህግ የበላይነት እንዲከበር ያደርግ ዘንድ አጥብቀን እናሳስባእን፤

5) ሰውን እንደንስሳ የሚያርዱ በነጅዋር የሠለጠኑ ሥራ ፈቶች ተከታታይ የሰብዓዊነትና በዘረኞቹ ቀጣሪዎቻቸው የሚሰጣቸው የሀሰት ትርክቶችን አስመልክቶ ትምህርት እንዲሰጣቸው፣

6) ባልፉት ሣምንታት ውስጥ በሀገራችን የተካሄደው ኢሰባዊ ድርጊት በተለይም በናዝሬት፣ በደብረ ዘይት፣ በድሬ ዳዋና ሀረር፣ በባሌ ሮቢ፣ በአሩሲ – ዶዶላ፡ በተፈጸመው የህዝብ ዕልቂትና የንብረት ውድመት፣ ከሀገር ውስጥና ከተባበሩት መንግሥታት የተወጣጣ ገለልተኛ ቡድን ባስቸኳይ እንዲቋቋምና ከቄሮ በስተጀርባ ሆኖ የጭጨፋው ተካፋይ የነበረው አካል በምርመራ ተጣርቶ ለህዝብ እንዲገለጽ፤

በማጠቃለል እንደማሳሰቢያ የምናቀርበው፦ በውስጥና በውጭ ያለው ያገሪቱ አጠቃላይ ሁኔታ፣ የጸጥታው፣ የኢኮኖሚ፣ የፖሊቲካና የማሕበረሰባዊ አቋም አስተማማኝ ባለመሆኑ፣ ማሕበረሰቡ እችግር ላይ እንደወደቀ አያሌ ምልክቶች ያሳያሉ፤ ይህንን የማኅበራዊ ቀውስ ወደባሰ ደረጃ ከመድረሱ በፊት፣ አሁን በሥራ ላይ ያለው መንግሥት በባላደራ ወይም ጊዜያዊ መንግሥት መተካት የሚችልበትን መንገድ በመቀየስ ከወዲሁ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ሀገሪቱን ካልተጠበቀ ደም መፋሰስና እልቂት ያድናል ብለን በጽኑ እናስባለን፡፡

አማራው ከሌላው ሀቀኛ ኢትዮጵያዊ ወ ገኑ ጋር በመሆን የራሱንና የኢትዮጵያን ህልውና ያስከብራል

 

 

6 Responses to ከዓለማቀፋዊ የአማራ ሕብረት የተሰጠ መግለጫ 

 1. Ethiopia’s institutionalized political reforms and institutionalized economic reforms will sprint forward the human developmental index (HDI) rank of the country .

  Avatar for Manjis

  Manjis
  November 10, 2019 at 8:34 am
  Reply

 2. ከዚህ የተሻለ አስተሳሰብ ያለውና በዕውነት ላይ የተመሰረተ ትንታኔ ማቅረብ የሚችል አማራ በአለም አቀፍ ደረጃ የለም ማለት ነው??? “እነ ጅዋር ሙሃመድ፣ ህዝቅኤል ጋቢሳና በቀለ ገርባ ለመሳሰሉት ከሀዲዎች..” ስትሉ፣ በየትኛው መስክ ምን አይነት ዉል ተዋውላችሁ ኖሮ ነው የተካካዳችሁት?? ወይስ የናንተን የሻገተ የ18ኛው ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ (i.e. መጽሃፍ ቅዱሳችሁን) የተቃወመ ሁሉ “ከሃዲ” ነው??

  Avatar for Abba Caala

  Abba Caala
  November 10, 2019 at 2:57 pm
  Reply

 3. By now all Amharas and Ethiopians should understand Jawar is just doing the dirty work Abiy instructs him to do. He is a kind of voluntary victim of the oromo woyane axis bought by a few dollars. Its time every one realizes instructions to eliminate, cut up amharas come directly from Abiy himself. Stop apologizing for Abiy he with Lema and the rest of EPRDF are doing this with the tacit support of the so called amhara representatives in the EPRDF. Know thy enemy, accept facts and fight for your existence like your fore fathers did. Do understand Abiy and the whole EPRDF is anti Amahara and anti coptic christianity and that is the enemy that needs to be defeated for the Amhara to guarantee its existence. Statements like the one above from an Amhara org is unacceptable as it helps cover up the real architects like Abiy hiding behind Jawar. If an Amhara thinks Abiy is gona save him or her, they just signed there death warrant themselves.

  Avatar for Enqoqo

  Enqoqo
  November 11, 2019 at 10:22 pm
  Reply

  • The Amhara or the orthodox Christian that speaks Amharic is victimized all over Ethiopia for the last three decades. Tefera Walwa said in AAU ‘we are not responsible for the Amhara that lives in Oromo or other non Amhara regions’ BEGEZA IJJU QWANQWA LEMEMAR BALEMEFELEG…and that is still on you tube. Getachew Mamo aka Tamrat Layne’s ugly speech in Jigjiga is recorded too. And yet they wondered why Addis Ababans never voted for them. TEFERA WALWA lost twice in the very neighborhood he was born at and where Lij Iyassu brought his ancestors in chains from GIMIRA.

   Professor Asrat, orphaned son of a patriot, couldn’t take it any more and formed a party politically. I mean, where were the rest? Why should the most hard working professor and surgeon be doing politics at the time when he should enjoy the beautiful sunset with his grand children and reflecting on what he has done for his country? As it turned out even the deputy Qegnazmach was stabbing him on his back.

   None Amhara Ethiopians loved that professor and loved him even more for his slippery slops the TPLF pointed out to make him hated by non Amhara Ethiopians. Everybody knew professor Asrat had very limited experience in politics. He told BBC what DERG said about the death of the last emperor was totally bogus and he went back to his 16 hour a day job of curing and teaching future curers. Professor Asrat was the least Amharized Amhara and was often confused in ethnic politics. “I can’t remember his name but you remember that Gurage guy when we went to Beirut? Can you get his phone number for me?…” and at the other end “you know your phone is jammed and you told me so yourself last week, you should be careful about ethnic name calling…” “…Antedemo it is just because I can’t remember his name but it is him who told me he was Gurage all on the way back. He was trying to get me go to ATATA hospital to celebrate MESQEL that year and he have Muslim name…what do we call Gurage today? Is it offensive?…”

   In short: Ethiopians are aware Amhara is being killed for no reason. The students of the 1960s, at least half of them, might have been ethnically Amhara. And they tried to end the Solomonic empire after 3000 years. The students were looking at a middle class spot after graduation with guaranteed employment. 425 Birr a month was a lot of money back in the days and that was the minimum wage of a graduate. 150 birr for apartment in 4 killo was considred expensive. A cold Meta Bira served by the most beautiful girl was half a birr. An ounce of Yohannes Aramde TIKOOROO was l birr in Genet Hotel.

   Avatar for Ibro

   Ibro
   November 12, 2019 at 9:09 pm
   Reply

 4. when I was but a child I remember one cruel teacher who hated me. He hated the whole class. He told us we were spoiled brats every single day. Some parents of my classmates complained but he was allowed to continue terrorizing kids until the end of the school year of that year. Daniel was like one third of the size of that teacher. Danny couldn’t take the beating and bit on teacher B L’s leg and ran away. The bell rang but teacher B L was not done yet. HULISHIM….YEFIWDAL RIZERAZZZ HULA…’ We were glad we were let go that day and because it was the longest day. ‘HULA!’ we said to each other and laughed it off. To this day, I don’t understand why schools hire such brutal idiots. I met teacher B L again when I went back home the first time. I told him I was one of his students decades ago and his ugly face lit up with happiness. His Amharic was now totally Addis Ababan. Many former students of that school from all over the world came home to thank teacher ME’AZA and teacher Sophia he said. Even that SEKARAM teacher Sultan’s funeral was attended by ‘diaspora’ that came home for FASIKA….

  Avatar for Ibro

  Ibro
  November 12, 2019 at 9:51 pm
  Reply

 5. “Menga”, actually this terms applies to livestock and not humans whatsoever the case might be. Do you also consider the Amhara/MANA Fannos as “menga” because they are killing innocent Oromo students learning in universities in Amhara region? Don’t you know that Jawar is an influential political activities among all Oromos and who contributed the downfall of the tyrannical regime of TPLF that all the Amharas hated. When Jawar was fighting to eliminate the TPLF regime, your Fannos were sitting by their mothers and cooking wat. It was after the movement created by Oromoo Qeerroos eroded the base of the TPLF that your Fannos came to join Qeerroo struggle. Qeerroo sacrifices were immense as compared to that of Fannos in Gondar. If at all those who fought TPLF were to be considered as causes for the destruction of Ethiopia, the Fannoos as they finally joined the Qeerroo struggle have to also condemned. Otherwise, there is no reason the Amhara elites consider Qeerroo as terrorists and the fannoo as freedom fighters. It is more than shame to consider own group as blessed and others as devils. Come to your common sense and try to forward convincing ideas so that the future of the coming generation will be based on equality mutual respect for the rights of each others. Don’t bark as a dog before you critically analyze the existing situation. Cheap popularity as the expense of blaming will not be a solution to peacefully live together.

  Avatar for Badhoo Baraa

  Badhoo Baraa
  November 13, 2019 at 6:51 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.