በዪኒቨርሲቲዎች የብሔር ግጭት እንዲፈጠር የሚሰሩ ሀይሎችን ለመታገል ህብረተሰቡ እንዲተባበር ተጠየቀ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

በዪኒቨርሲቲዎች ውስጥ የብሔር ግጭት እንዲፈጠር አልመው የሚሰሩ ሀይሎችን ለመታገል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እንዲተባበር ተጠየቀ፡፡

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ትናንት በተከሰተው ችግር ዙሪያ የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር እየተካሄደ በሚገኘው 5ኛ ዙር 5ኛ አመት 14 መደበኛ ጉባኤ ላይ ወቅታዊ የክልሉ የጸጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ለክልሉ ምክር ቤቱ በሰጡት ማብራሪያ በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ምሽት ላይ ተማሪዎች እግር ኳስ እየተመለከቱ እያለ በደጋፊዎች መካከል ግጭት ተከስቶ ነበር፡፡

ግጭቱን የሚፈልጉት ሀይሎች ስለነበሩ ግጭቱን ወዲያውኑ የብሔር ግጭት አደረጉት፤ በዚህም ተማሪዎች ተጎድተዋል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰአት የተፈጠረውን ግጭት አረጋግተነዋል፤ በዚህ ወንጀል ላይ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩትንም በቁጥጥር ስር አውለናል በማለት አቶ አገኘሁ ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል በሚገኙ አስሩም ዩኒቨርሲቲዎች ሰላም እንዲደፈርስ አቅደውና አልመው የሚሰሩ ሀይሎችን ለይተን እርምጃ ለመውሰድ እየተንቀሳቀስን ነው ሲሉም ለምክር ቤቱ ገልጸዋል፡፡

በዚህም በግለሰቦች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶችን ወደ ብሔር ግጭት ለመውሰድ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን ለመታገል የምክር ቤት አባላት እና መላው የክልሉ ህዝብ ከጸጥታ ሀይሉ ጎን በመሆን እንዲተባባር ቢሮ ኃላፊው ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

(ኢ.ፕ.ድ)

One Response to በዪኒቨርሲቲዎች የብሔር ግጭት እንዲፈጠር የሚሰሩ ሀይሎችን ለመታገል ህብረተሰቡ እንዲተባበር ተጠየቀ

 1. The cyclone 3A is heading towards the Northern part of Ethiopia, it is notime to turn against one another. All of us need to merge together to prevent damages from this cyclone by being vigilant for the next 3 to 4 days, in the process we will get the much needed training on merging .

  Merging all of EPRDF member parties as one is the solution to move beyond ethnic based politics.

  If not merged the country will be nomore.

  Avatar for Redai

  Redai
  November 10, 2019 at 3:09 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.