ለሲዳማ ህዝበ ውሳኔ እስከአሁን የተመዘገቡ ድምፅ ሰጪዎች ብዛት 1 ሚሊየን 394ሺ 922 መድረሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

ድምፅ ሰጪዎቹ የተመዘገቡት በ1 ሺህ 692 የምዝገባ ጣቢያዎች ነው::

ቦርዱ ከፍተኛና ዝቅተኛ ተመዝጋቢ የታየባቸውን አካባቢዎች ይፋ አድርጏል::

አርቤጎና፣ ሁላ፣ ወንሾ፣ ቦና ዙሪያ፣ ከፍተኛ ተመዝጋቢ የታየባቸው ዝቅተኛ ተመዝጋቢ የታየባቸው አካባቢዎች- ደግሞ ሃዋሳ ከተማ፣ አለታ ወንዶ፣ ዳራ ሆነዋል::

የቦርዱ ስራ ሃላፊዎች እና የማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ አባላት በተለያዩ ወረዳዎች በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው የምዝገባ ሂደቱን ተመልክተዋል፡፡

በሂደቱ የታዩ የአሰራር ክፍተቶች ላይም ግብረ መልስ ሰጥተዋል::

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የካርድ እና የመመዝገቢያ ቁሳቁስ እጥረት ያለባቸው ቦታዎች ላይ ተጨማሪ የቁሳቁስ ስርጭቶችን ያከናወነ ሲሆን በቀሩት ቀናት የድምጽ ሰጪዎች ምዝገባ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ዝቅተኛ ምዝገባ ያለባቸው ቦታዎች ነዋሪዎች እንዲመዘገቡ የተለያዩ መረጃዎችን የመስጠት ስራዎችን እንድሚስራም አስታውቋል፡፡

ምንጭ :-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.