በተማሪዎች መካከል በተከሰተ ግጭት የ2 ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን የወልድያ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ምሽት 5:00 ሰዓት አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የተማሪዎች ሕይወት አልፏል፤ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ ደግሞ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የአካደሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እና ተወካይ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስረስ ንጉሥ ችግሩን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት፣ “ምሽት አካባቢ የተፈጠረው ችግር ምንጩ እስከሚጣራ ድረስ ከመገመት የዘለለ በትክክል አይታወቅም” ማለታቸውን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።

በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ሃይማኖትን ሲሰብኩ እና ወደ ግጭት የሚያመሩ እንቅስቃሴዎችን ሲያካሂዱ የነበሩ ተማሪዎች በሥነ ምግባር ግድፈት ከትምህርት ገበታ መታገዳቸው እና ከሰሞኑ በሀገሪቱ የነበረው የፖለቲካ ችግር ለግጭቱ መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ግምት እንዳላቸው ነው ዶ/ር አስረስ ለአብመድ የገለጹት። ትክክለኛ ችግሩ ተጣርቶ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግም ተናግረዋል።

በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በወልድያ አጠቃላይ ሆስፒታል ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑም ተገልጿል።

ከጉዳቱ በኋላ ከተማሪ ተወካዮች ጋር ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ በመደረሱ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እና ለሕግ ለማቅረብ እንደሚሠራም አስታውቀዋል።

ተማሪዎቹ በተወካዮቻቸው አማካኝነት የፀጥታ እና ደህንነት ስጋት ስላለባቸው ዋስትና እንዲያገኙ በመጠየቃቸው እና የመከላከያ ኃይል ወደ ግቢው እንዲገባ መግባባት ላይ በመደረሱ ዛሬ ማምሻውን የመከላከያ ኃይል ወደ ዩኒቨርሲቲው እየገባ መሆኑን ገልጸዋል።

በደረሰው ጉዳት በዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን የገለጹት ዶክተር አስረስ፣ “ጦማሪያን፣ አክቲቪስቶች እና የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው አካላት በስብጥርና በፍቅር ተሰናስሎ የሚኖረውን ኅብረተሰብ ለማጋጨት የሚያደርጉትን ጥረት ሊያቆሙ ይገባል” ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልዋል።

ምንጭ፦ አብመድ

#etv

#etv በትናንትናው እለት በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ግጭት የሁለት ተማሪዎች ህይወት ማለፉንና 10 ተማሪዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ፡፡

Posted by Ethiopian Broadcasting Corporation on Sunday, November 10, 2019

2 Responses to በተማሪዎች መካከል በተከሰተ ግጭት የ2 ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን የወልድያ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ

 1. The fact is in Ethiopia most of the athiest youth who were born during Meles Zenawi’s time had for all their lives been programmed to act violently towards Orthodox Christians by their surroundings environment , these athiest University students in Ethiopia were told Orthodox is the religion of the lazy who don’t work their fair share of work by claiming each day of the month is a holiday. These athiest youth don’t know any better but to be violent against “LAZY ORTHODOX” who were said to be to follow the religion only to get out of their work duties (currently the locust infestation fighting duties) by claiming everyday of the month is a holiday, the athiest youth were brain washed by the EPRDF five years growth and transformation plan cadres that spread gossip saying most Orthodox followers are not doing their fair share of work even with Meles Zenawi’s world class leadership , because the Orthodox followers tend to call days off saying it is a holiday everyday of the month just to get out of work or school duties , that brought the country to continue being the poorest in the world with such a low Human Developmental Index (HDI) rank.

  More than half of the country’s University students claim to be athiests according to the Universities record across the country.

  Avatar for Ahadu

  Ahadu
  November 10, 2019 at 10:11 pm
  Reply

 2. It is mahibre kiduisuan who always create division among students in an attempt to promote its business in the name of religion. This profitable organisation registered as NGO has political as well as ethnic based propaganda.

  They devise several techniques to deceive the gullible youngeters who are supposed to impart financial support soon after they leave the school and start working.

  It is how they multiply thier staff and enhance thier budget.

  They also collect moeny from the laity in the guise of helping old and burnt churches , and Abinet school, Tradtional school teaching geez poetry, and church hymn.

  To put it in a nut shell, mahibr kidusan and its supporters , including some naive bishops , they are mafias .

  They donot allow to join thier office unless they studied his or her background, ethnicity and relation with other entities with whom they had enemity etc

  Avatar for Biru Andargachew

  Biru Andargachew
  November 11, 2019 at 4:48 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.