ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ወደነበረበት ሠላማዊ ሁኔታ እየተመለሠ መሆኑ ተገልጿል

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ምሽት ተፈጥሮ በነበረ ግጭት ጉዳት ደርሷል፡፡
ትናንት ከምሽቱ 4፡00 እስከ 5፡00 ገደማ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የሁለት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉና ስምንት ተማሪዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንዳጋጠማቸው ተገለጸ፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወልደትንኤ መኮንን ለአብመድ በስልክ እንደገለጹት ምሽት ተማሪዎች ኳስ በቴሌቪዝን በጋራ ሲከታተሉ አምሽተው ሲመለሱ በተፈጠረ ግጭት ነው የተማሪዎች ሕይወት ያለፈውና የአካል ጉዳት ያጋጠመው፡፡
ጉዳት ካጋጠማቸው ስምንት ተማሪዎች ሦስቱ ቀላል ጉዳት ያጋጠማቸው ስለነበር መጠነኛ ሕክምና አግኝተው ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሳቸውንም አቶ ወልደትንሳኤ አስታውቀዋል፡፡

የተወሰኑ ተማሪዎችንና የተማሪ ተወካዮችን በችግሩ ዙሪያ ማወያዬታቸውን ያመለከቱት አቶ ወልደትንሳኤ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ለመያዝና ለሕግ ለማቅረብ እየተሠራ እንደሆነ አስውቀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲውና የአካባቢው አስተዳደር የተማሪዎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ እየሠሩ እንደሚገኙ ያመለከቱት ዋና አስተዳዳሪው ‹‹ከዚህ በፊት የግጭት ምንጭ የሚሆኑ አስተዳደራዊ ጉዳዮች እንዲፈቱ በትኩረት ሠርተናል፤ የውኃ፣ መብራትና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እንዲቀረፉም እየተደረገ ነው፤ ብዙ ውይይቶችም ተደርገዋል፡፡ የአሁኑ ግጭት መንስኤ ምን እንደሆነ ግን ገና እየተጣራ ነው›› ብለዋል፡፡

‹‹የዞን አስተዳደሩና የዞኑ ሕዝብ በልጆቹ መነጠቅ አዝኗል፤ ለሁላችንም መጽናናቱን እንዲሰጠን እመኛለሁ፤ የተጎዱትም በቶሎ አገግመው ወደ ትምርታቸው እንደሚመለሱ ተስፋ አደርጋለሁ›› ብለዋል አቶ ወልደትንሳኤ መኮንን ለአብመድ ሲናገሩ፡፡

የፀጥታ ኃይል በአካቢው መሠማራቱንና ተማሪዎች መረጋጋታቸውንም አስታውቀዋል፤ ተማሪዎች የእርስ በእርስም ሆነ ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጋር የሚኖሯቸውን ልዩነቶች በሰከነ መንገድ እንዲፈቱም አሳስበዋል፡፡

አብመድ ከተማሪዎች እንዳረጋገጠው ዩኒቨርሲቲው አሁን በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ነው፤ ተማሪዎቹ ተረጋግተው በቤተ መጻሕፍትና እና በመኖሪያ ክፍሎቻቸው እንዲሁም በግቢው እየተንቀሳቀሱ እና መደበኛ ተግባራቸውን እየከወኑ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አብመድ ከዩኒቨርሲቲው የሥራ ኃላፊዎች መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረገ ነው፤ መረጃውን እንዳገኘ ያቀርባል፤ ለሟች ተማሪዎች ጓደኞችና ቤተሰቦችም መጽናናትን ይመኛል፡፡

ዘጋቢ፡- አብርሃም በዕውቀት

አብመድ

2 Responses to ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ወደነበረበት ሠላማዊ ሁኔታ እየተመለሠ መሆኑ ተገልጿል

 1. The fact is most of the athiest youth who were born during Meles Zenawi’s time had for all their lives been programmed to act violently towards Orthodox Christians by their surroundings environment , these athiest University students were told Orthodox is the religion of the lazy who don’t work their fair share of work by claiming each day of the month is a holiday. These athiest youth don’t know any better but to be violent against “LAZY ORTHODOX” who follow the religion only to get out of their work duties by claiming everyday of the month is a holiday, The.athiest youth were brain washed by the EPRDF five years growth and transformation plan cadres that spread gossip saying most Orthodox followers are not doing their fair share of work even with Meles Zenawi’s world class leadership.because the Orthodox followers tend to call days off saying it is a holiday everyday of the month just to get out of work or school duties , that brought the country to continue being the poorest in the world.

  More than half of the country’s University students claim to be athiests according to the Universities record across the country.

  Avatar for Ahadu

  Ahadu
  November 10, 2019 at 9:27 pm
  Reply

 2. It is mahibre kiduisuan who always create division among students in an attempt to promote its business in the name of religion. This profitable organisation registered as NGO has political as well as ethnic based propaganda.

  They devise several techniques to deceive the gullible youngeters who are supposed to impart financial support soon after they leave the school and start working.

  It is how they multiply thier staff and enhance thier budget.

  They also collect moeny from the laity in the guise of helping old and burnt churches , and Abinet school, Tradtional school teaching geez poetry, and church hymn.

  To put it in a nut shell, mahibr kidusan and its supporters , including some naive bishops , they are mafias .

  They donot allow to join thier office unless they studied his or her background, ethnicity and relation with other entities with whom they had enemity etc

  Avatar for Biru Andargachew

  Biru Andargachew
  November 11, 2019 at 4:49 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.