ጥረት ኮርፓሬት ተጠሪነቱ ለአማራ ክልል ምክር ቤት እንዲሆን ተወሰነ

1 min read

የአማራ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 14ኛ በመደበኛ ጉባኤ ጥረት ኮርፓሬት ተጠሪነቱ ለክልል ምክር ቤት እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል።

የክልሉ ምክር ቤት የህግ ፍትህ እና አስተዳደር ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አማረ ሰጤ፥ ጥረት ኮርፓሬት ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት እንዲሆን የተባለበትን ዝርዝር ሁኔታዎች አቅርቧል።

በዚህም ጥረት ኮርፓሬት የክልሉ ህዝብ ሃብት መሆኑን፣ የአሰራር ግልፀኝነት ችግር የነበረበት በመሆኑ እና አሁን ባለው ሁኔታ 11 ሺህ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህ መሰረትም ጥረት ኮርፓሬት ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት ቢሆን ከዚህ የተሻለ የስራ ዕድል መፍጠር የሚችል መሆኑን ጠቁመዋል።

የምክር ቤቱ አባለት በበኩላቸው አሁን ጥረት ያለበት ሁኔታንና ከዚህ በፊት በማን ሲመራ እንደነበር ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ጥረት በስሩ የሚስተዳደራቸው ተቋማት፣ ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች በግልፅ ሊታወቁ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።

ተቋሙ ሁሉን ባሳተፈ መልኩ እንደገና ቢዋቀር መልካም መሆኑንም የምክር ቤቱ አባላት መጠቆማቸውን የዘገበው ኤፍቢሲ ነው።

በሌላ በኩል ጥረት ኮርፓሬት አጠቃላይ ያለው ሃብት ኦዲትና ግልፅ ተደርጎ ከቀረበ በኋላ ለምክር ቤቱ መቅረብ ያለበት መሆኑን አንስተዋል።

የጥረት ኮርፓሬት ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር አምላኩ አስረስ በበኩላቸው፥ የተጠቃለለ ሪፓርት የሚቀርበው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የፊታችን ታህሣስ ወር ላይ መሆኑን በመግለጽ በሚቀጥለው የምክር ቤት ጉባኤ ላይ የሚቀርብ መሆኑን ተናግረዋል።

ምክር ቤቱም ጥረት ኮርፓሬት ተጠሪነቱ ለክልል ምክር ቤት እንዲሆን የቀረበወን ሃሳብ በአራት ተቃውሞ እና በአብለጫ ድምፅ አፅድቆታል።

(ኢ.ፕ.ድ)

1 Comment

  1. Eventually EPRDF chairman will own Tiret , when ADP and ODP and the rest of EPRDF member parties become one.

    EFFORT and Tiret and alike will be all one owned by EPRDF chairman.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.