ከተሞቹ ስምምነታቸውን በአዲስ መልክ ለማደስ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

1 min read

አዲስ አበባና ዋሽንግተን ዲሲ የእትማማች ከተማነት ስምምነታቸውን በአዲስ መልክ ለማደስ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን ኢ/ር ታከለ ኡማና የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር የተፈራረሙት ሲሆን ሁለቱ ከተሞች በኢኮኖሚ፣ ጤና፣ የባህል ልውውጥና አረንጓዴ ልማት ላይ በጋራ ለመስራት ተሰማምተዋል፡፡

በኢኮኖሚው ዘርፍ ላይ መረጃ ለመለዋወጥና በጋራ የሚሰሩ የልማት ስራዎች ላይ ለመሳተፍ ተስማምተዋል፡፡

ሀገራዊ የቢዝነስ ሀሳቦች ማደግ በሚችሉበት ዙሪያ በከተማ አስተዳደርና በንግድ ዘርፍ ማህበራት ደረጃ በጋራ መስራትም በስምምነቱ ውስጥ ተካቷል፡፡

በተለያዩ የፈጠራ ሀሳቦችና የቴክኖሎጂ እድገቶች ላይ በጋራ መስራት፤ የፈጠራ ሀሳቦች እንዲተገበሩ ልምድን መለዋወጥም የእህትማማች ከተማነት ስምምነት ውስጥ ተጠቅሷል፡፡

በጤና ዘርፍ ደግሞ ለዘርፉ ማደግ አስተዋጽኦ ካላቸው የጤና ፖሊሲዎች ጀምሮ በሽታን መከላከል ላይ በሚስሩ ስራዎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የሁለቱ ከተማ ነዋሪዎች ያሏቸው ባህላዊ እሴቶችን መለዋወጥና እንዲያድጉ መደጋገፍም በስምምነቱ የተካተተ ነው፡፡

በሁለቱ ከተማዎች ላይ የሚሰሩ የአረንጓዴ ፕሮጀክቶች ላይ ልምድ መለዋወጥ፣ በትራንፖርቴሽንና በኮንሽትራክሽን ዘርፉ ላይ የመፍትሄ ሀሳቦችን መለዋወጥና ድጋፍ ማድረግ በአዲስ አበባና በዋሽንግተን ዲሲ መካከል የእህትማማች ከተማነት ስምምነቱን እንደ አዲስ ለማደስ በተፈረመው ስምምነት ላይ የተካተተ ነው፡፡

በቀጣይም ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማትና ነዋሪዎች የተካተቱበት የስምምነቱን አፈጻጸም የሚከታተል ኮሚቴ በሁለቱም በኩል እንደሚቋቋም ከከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

(ኢ.ፕ.ድ)

2 Comments

 1. The private Telecom company called Hidassie Telecom Company is expected to provide cheap telephone services b/n Addis and DC, 40 Ethiopian Cents per minute telephone services between Addis Ababa and Washington DC , USA is expected to bring more investments for both cities.

 2. ለኦሮሞ ተወላጅ ለሆኑ ሥራ ፈላጊዎች የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ ሊታደል ነው::

  November 12, 2019 –

  ለኦሮሞ ተወላጅ ለሆኑ ሥራ ፈላጊዎች የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ ሊታደል ነው!!
  ብሔርተኛ ሲባል “ራስ ወዳድ ጥቅመኛ ነው” የምላችሁ ለዚህ እኮ ነው። በአርከበ ዕቁባይ ዘመን የትግሬ ብሔርተኛ ከትግራይ ትምህርት ቢሮ ነቅሎ መጥቶ አዲስ አበባ መስተዳድር ውስጥ ከተሰገሰገ በኋላ የከተማውን ነዋሪ ግጦት ሄደ። በታከለ ኡማ ዘመን ደግሞ የኦሮሞ ብሔርተኛ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች መልሶ ለመጋጥ እንዲህ አሰፍስፏል። የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ባወጣው ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ላይ “የታደሰ የአ/አ መታወቂያ መያዝ” እንደ መስፈርት ተቀምጧል።

  ከታች በምስሉ ላይ ያለው በኦሮምኛ የተፃፈ መልዕክት በተጠቀሰው ክፍት የሥራ ቦታ ለሚያመለክቱ የኦሮሞ ተወላጆች የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ ለማደል በስልክ ቁጥር 0921879712 ላይ እንዲደውሉ ጥቆማ ይሰጣል። የዚህን ስልክ ባለቤት ጨምሮ በዚህ ህገወጥ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ተጠያቂ ካልሆኑ ከከንቲባ ፅ/ቤት እስከ ቀበሌ ድረስ እየተሰራ ያለው ወያኔን ለመተካት መሆኑን በተጨባጭ ያረጋግጣል። ለኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብቻ በሚስጥር ሲተላለፍ የነበረው መልዕክት የአማርኛ ትርጉም እንደሚከተለው ቀርቧል።
  ************************************************
  No photo description available.የአ/አ (የፊንፊኔ ) ከተማ አስተዳደር በሁሉም የትምህርት መስክ አምስት ሺህ ሰዎችን አወዳድሮ ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የሥራ ማስታወቂያ በማውጣት ገልጿል፣

  የምዝገባ ቀን 2/3/2012
  መመዝገቢያ ቦታ አዲስ አበባ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ
  አስፈላጊ መመዘኛዎች
  — በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ
  — በ2010 እና 2011የተመረቃችሁ ብቻ
  — የሥራ ልምድ 0 ዓሠት
  አንድ ተወዳዳሪ ይዞ መገኘት ያለበት
  የ10ኛና 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
  የ8: 10 12ኛ ክፍሎች ካርድ ኦርጅናልና ኮፒ

  የተመረቁበት ወረቀት ዋናውንና ኮፒውን
  የታደሰ የአ/አ መታወቂያ መያዝ

  ይህን መሥፈርት አሟልታችሁ የአዲስ አበባ ከተማ መታወቂያ የሌላችሁ የኛ ልጆች 0921879712 ላይ ደውሉ

  -በውስጥ መስመር ብቻ ሼር ተደራረጉ።(በሚስጥር ሲተላለፍ የነበረው መልዕክት)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.