ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ – አለምአቀፍ ኢትዮጵያዊያን ትብብር ለፍትህ

1 min read

ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር
ዶ/ር አብይ አህመድ
አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች የአማራ ነገድ ተወላጆችና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ ቄሮ የተባለው አክራሪዉ አሸባሪ ቡድን ያደረሰውን ዘግናኝ፣ አሰቃቂ አረመኔያዊና ኢሰበአዊ ጭፍጨፋ በጽኑ እናወግዛለን ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ አጥብቀን እንጠይቃለን  

ከሰሞኑ በሐገራችን ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተለያዩ ከተሞችና የገጠር መንደሮች ይኖሩ በነበሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች፡ ወንጌላውያን፡ እስላሞች፡ በብሄር አማሮች ላይ ያነጣጠረ እንዲሁም የጋሞ ፣ የስልጤ ፣ የዶርዜ ብሄር አባላት የሆኑ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ በአቶ ጃዋር መሐመድ አነሳሽነት በእርሱ የሚመራዉ አክራሪዉ ቄሮ በተባለው አረመኔያዊና አሸባሪ ቡድን እጅግ ዘግናኝ አሰቃቂና ፍጹም ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ መንግስት ባመነዉ ፹፮ የሚደርሱ ነገር ግን ቁጥሩ ከዚያም በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ተጨፍጭፈዋል ። ከአራት መቶ በላይ መቁሰልና የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ። በንብረት ላይም ግምቱ ያልታወቀ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል ።

ይህ ኢሰብአዊና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ህጻናትን ፣ ነፍሰ ጡር ሴቶችን ፣ የአልጋ ቁራኛ አረጋውያንን ፣ ህሙማን ሆስፒታል በተኙበት፡ በሕግ ጥላ ስር የነበሩ  እስረኞችን ፡ የሃይማኖት አባቶችን ፣ የወንጌል አስተማሪዎችን ሁሉ በጭካኔ የጨፈጨፈ ነበር ። ይህ አረመኔ አሸባሪ ቡድን የ፹ ዓመት የአልጋ ቁራኛ የነበሩ አረጋዊ አባት እንኳን ርህራሄ በሌለው ሁኔታ ሰውነታቸውን ቆራርጦ ገድሏል ። አክራሪዉ አሸባሪ ቄሮ ይህን የሽብር ተግባር የፈጸመው በሜንጫ አንገታቸውን እየቀላ በስለት እየወጋ በዱላና በድንጋይ እንደ አውሬ እየቀጠቀጠ እጅና እግራቸውን እየቆረጠ ፣ የሴቶች ጡት እየቆረጠ፣ የወንዶችን ብልት እየሰለበ እንዲሁም መላ ሰውነታቸውን እየከታተፈ ለመናገርና ለማመን ፈጽሞ በሚዘገንን አረመኔያዊና ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ነው ። ይህ አይነት አረመኔያዊ ጭፍጨፋ እንኳን ሐገረ እግዚአብሔር በሆነችው ሐገራችን ኢትዮጵያ ይቅርና በየትኛውም የሽብር ጥቃት በተፈጸመባቸው ሐገሮች ተሰምቶም ተዘግቦም አያውቅም ።

በ፳፩ኛው ክፍለ ዘመን የሰው ልጅ ከራሱ አልፎ ለእንሰሳ ሕይወትና አያያዝ ከፍተኛ ሰብአዊ ርህራሄ እያሳየ ባለበት ጊዜ በአንጻሩ በሐገራችን ኢትዮጵያ የእግሂአብሔር ፍጡር የሆነ ሰው በእንደዚህ አይነት ዘግናኝና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ መገደሉ እጅግ አሳዝኖናል ፣ አስቆጥቶናልም ። ለዚህ ሁሉ አሰቃቂ ኢሰብአዊ ጭፍጨፋና ከ፹፮ በላይ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በዘግናኝ ሁኔታ መገደል ከሶስት መቶ በላይ ለሚሆኑ የተለያየ አካል ጉዳት መድረስ እንዲሁም ግምቱ ገና ላልታወቀ የሐብትና ንብረት ውድመት ብሎም ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ድንጋጤና ጭንቀት መንስዔ የሆነው አቶ ጃዋር መሐመድ ተከብቤያለሁ ድረሱልኝ የሚል ሰይጣናዊ ጥሪ በማስተላለፉ ምክንያት ነው ። ከዚህም የተነሳ ጃዋርና ግብረ አበሮቹ  ለዚህ ሁሉ ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት ወንጀል ዋና ተጠያቂዎች ናቸው።

በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ ይህ ሁሉ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸም ኢትዮጵያን እመራለሁ የሚለው የፌዴራል መንግሥት፣ የኦሮሚያ ክልል አመራር፣ የከተሞች ከንቲባዎችና ፡ በጠቅላላ የጸጥታ መዋቅሩ ጭፍጨፋውን ለመከላከል ምንም አይነት እርምጃ አለመውሰዳቸዉ ነው ። አንዳንድ በአሸባሪዎች ጥቃት ቆስለው በህይወት የተረፉ ወገኖቻችን እንደገለጹት ከሆነ የኦሮሚያ ፖሊስ ፣ አድማ በታኝ ፣ ልዩ ኃይል ቆሞ እያየ ከተጠቂዎች እርዳታ ቢጠየቅም ምንም አይነት ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆኑ ነው ።

መንግሥት ቁጥር አንድ ተግባሩ የሐገርና የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ሆኖ እያለ ለምንድነው ዝም ብሎ የተመለከተው?  የሐገር ደህንነትና የጸጥታ መዋቅሩ ዋና ስራው እንደዚህ አይነት ከፍተኛ ወንጀሎች ገና ሲጠነሰሱና አንዳንድ ምልክቶች ሲታዩ ማምከን አይደለም ወይ ? ጭፍጨፋው እንደተጀመረስ ለምን ፖሊስ ልዩ ኃይል በአስቸኳይ እንዲያስቆመው አልሆነም ? ፖሊስ ለአሸባሪዎች ወግኖ ሃላፊነቱን መወጣት ካልፈለገ የሐገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ለምን ሁለት ቀን ዘግይቶ እንዲገባ ተደረገ ? ወይንስ ሆን ተብሎ የሃይማኖትና የዘር ማጽዳት ጭፍጨፋ ነው የተካሄደው ? ይህ ሁኔታ ሁሉንም የሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ከተጠያቂነት አያድናቸዉም ።

ሌላው ዋነኛ ጉዳይ ደግሞ መንግሥት የተከሰተው ግጭት ነበር እያለ በተደጋጋሚ በመግለጽ ላይ ቢሆንም እውነታው ግን ጭፍጨፋ እንጂ ፈጽሞ ግጭት አይደለም ። ግጭት የሚባለዉ ሁለት ኃይሎች ጎራ ይዘው ሲፋለሙ ነው ። የሆነው ግን በአቶ ጃዋር መሐመድና ግብረ አበሮቹ የተነሳሳው ወይንም ትእዛዝ የተቀበለው ፅንፈኛዉ ቄሮ የተባለው አሸባሪ ቡድን ወገኖቻችንን በሃይማኖታቸውና ብሄራቸው ለይቶ ነው ጭካኔያዊ ጭፍጨፋ ያደረሰባቸው ።

ይህ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በአቶ ጃዋር መሐመድ ብቻ ሳይሆን በሕውሃትና በኦነግ ትብብር እንዲሁም የኢትዮጵያ ጥንተ ጠላት በሆኑ የውጪ ኃይሎች የተቀነባበረ ለመሆኑ ብዙ አመላካች ሁኔታዎች አሉ ። ይህ ጭፍጨፋ ተራ የሽብር ወንጀል ሳይሆን የሰው ዘርን ከማጥፋት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ስለሆነ በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የሚያስከስስም ይሆናል ። ቢዘገይም እንኳን ሁሉም በየደረጃው የሚጠየቁበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም ። ለማስታወስ ያህል በደርግ ስልጣን ዘመን የደርግ አባል የነበረው መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ በቀድሞዉ የጎጃም ክፍለ ሐገር በደብረ ማርቆስ ፣ በሞጣ ፣ በአገው ምድር ፣ ቆላ ደጋ ዳሞት ወዘተ ከተሞች የነበሩ የኢሕአፓ አባላትን በእብሪተኝነት ያለምንም ፍርድ ሂደት በራሱ ስልጣን ከየእስር ቤቱ እያስወጣ ብዙ ወጣቶችንና ምሁራንን በመረሸኑ ከብዙ ክትትል በኋላ ወንጀሉ ተረጋግጦ ከደርግ ውድቀት በኋላ በስደት በሚኖርበት ሆላንድ ውስጥ ወንጀሉን ከፈጸመ ከ፵ ዓመት በኋላ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ወህኒ ቤት ውስጥ ይገኛል ። ይህ ሁኔታ አሁን ባለጊዜ ነን ብለው ወንጀል ለሚፈጽሙ የመንግስት ሃላፊዎች፣ የወንጀል ተባባሪ ለሚሆኑ ወይንም ከለላ ለሚሰጡ ሁሉ ከወንጀለኛው ጋር እንደመተባበር ስለሚቆጠር ከተጠያቂነት እንደማይድኑ በመገንዘብ ከዚህ በኋላ ከዚህ መሰል  አስነዋሪና ህገወጥ ተግባራቸዉ በመማር ህግን በስርአት ማስከበር እንደሚገባችው ማወቅ ይኖርባቸዋል ።

እንደዚህ አይነት ዘግናኝና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ያቀነባበሩና የፈጸሙ በወንጀላቸው እንዲጠየቁ እንዲሁም በሐገራችን ኢትዮጵያም ሆነ በየትኛውም የዓለም ክፍል ዳግም እንዳይከሰት ለማድረግ ለኢትዮጵያ መንግሥትና ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እናቀርባለን ።

ለኢትዮጵያ መንግሥት

፩ኛ ይህንን ጭፍጨፋ በማነሳሳትም ሆነ ወይንም ድብቅ ትዕዛዝ በመስጠት የሽብር ድርጊቱ እንዲፈጸምና ከ፹፮ በላይ ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉና በመቶዎች የሚቆጠሩ የተለያየ የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸውና ሃብት ንብረታቸው እንዲወድም ምክንያት የሆነው አቶ ጃዋር መሐመድና ግብረ አበሮቹን ለፍርድ እንዲያቀርብ አጥብቀን እንጠይቃለን ።

፪ኛ ፅንፈኛዉ ቄሮ የተባለው አሸባሪ ቡድን ይህንን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በማካሄዱ ወንጀሉን የፈጸሙት ተለይተው ለፍርድ እንዲቀርቡ ፣ እንዲሁም የፅንፈኛዉ ቄሮ አደረጃጀት በሕግ እንዲታገድ እንጠይቃለን ።

፫ኛ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በፅንፈኛ አሸባሪ ቄሮ ቡድኖች ሲፈጸም እያዩ መከላከል ያላደረጉ የኦሮሚያ የፖሊስ ፣ የአድማ ብተናና የደሕንነት አባላት ተለይተው ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን ።

፬ኛ ይህ ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ለዓመታት ሰፊ ቅስቀሳ ሲያካሂድ የቆየውና እያካሄደም ያለው ከሩዋንዳው ሚሌኮሊንስ የሬዲዮ ጣቢያ ጋር በጣም የሚመሳሰለው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ እንዲዘጋ አጥብቀን እንጠይቃለን ። በጣቢያው እየቀረቡ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ የነበሩ ሁሉ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንጠይቃለን ።

፭ኛ የኦሮሚያ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሺመልስ አብዲሳ ይህንን ጭፍጨፋ ያስነሳው አቶ ጃዋር መሐመድ መሆኑን እያወቁ ወንጀለኛ ስለሆነ ለሕግ መቅረብ አለበት ሳይሆን ወንድማችን ነው እንዲያውም የተጠናከረ ጥበቃ ይደረግለታል ማለታቸው ጭፍጨፋውን ለሚያካሂዱ አረመኔዎች አይዟችሁ የጀመራችሁትን ቀጥሉበት የሚመስል መልዕክት ያዘለ በመሆኑና ጭፍጨፋው ቢቀጥልም ለማውገዝም ሆነ ለማስቆም ምንም ጥረት ባለማድረጋቸው በሕግ እንዲጠየቁ እንጠይቃለን ።

፮ኛ የኦሮሚያ የሕዝብ ደህንነት ሃላፊዎች ፣ የፖሊስ አዛዦች ፣ የዞን ፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች ጭፍጨፋውን ከመድረሱ በፊት ባለመከላከላቸውና ከተጀመረ በኋም በፍጥነት ባለማስቆማቸው በሕግ እንዲጠየቁ እንጠይቃለን ።

፯ኛ በባሌ ሮቤ ከተማ አንዳንድ የአባገዳ መሪዎች ቀጣይ የዘር ማጽዳት በኦርቶዶክስ አማኞች ፣ አማሮችና ኦሮሞ ባልሆኑት የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ በማወጃቸው በሕግ እንዲጠየቁ እንጠይቃለን ። አካባቢውም በመከላከያ ሰራዊት ጥበቃ ውስጥ እንዲሆን እንጠይቃለን ።

፰ኛ የኢፌድሪ የሕዝብ ደህንነት ሃላፊ ይህ ጭፍጨፋ እንዳይካሄድ የሚያስችል መረጃ በመሰብሰብ ሕዝቡን ከዕልቂት ለመታደግ ባለመቻሉና ከተጀመረም በኋላ ለማስቆም ይህ ነው የሚባል ጥረት ሲያደርግ ባለመታየቱ በሕግ እንዲጠየቅ እንጠይቃለን

፱ኛ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አሕመድ ይህ ጭፍጨፋ መካሄዱን እንዳወቁ ለማስቆም የፌዴራል ፖሊስ ፣ የደህንነት አባላትና የመከላከያ ሰራዊት በአስቸኳይ እንዲገባ ትዕዛዝ ባለመስጠታቸው በሕግ እንዲጠየቁ እንጠይቃለን ።

፲ኛ ለሞቱት ቤተሰቦች ተገቢው ካሳ መንግሥት እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን ።

፲፩ኛ በእዚህ አሰቃቂ ወንጀል አካላቸው የጎደለ ሕክምና እንዲያገኙ መቋቋሚያም እንዲሰጣቸው እንዲሁም ቤት ንብረታቸው የንግድ ቤቶቻቸው ለወደሙባቸው ሁሉ ተገቢው ምትክ እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን ።

፲፪ኛ ከጨፍጫፊውና አሸባሪው ፅንፈኛዉ የቄሮ ገዳይ ቡድን እራሳቸውን በመከላከል ላይ የነበሩ ወጣቶችን ፖሊስ እንደ ወንጀለኛ በጅምላ አስሯቸው ስለሚገኝ ከወንጀለኞች ጋር ተደምረው መታሰራቸው አግባብ ስላልሆነ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን ።

፩፫ኛ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለዚህ ሁሉ የማያባራ እልቂት ዋነኛ ምክንያቱ አሁን ያለው ዜጎችን በእኩልነት የማያይ ሕገ መንግሥትና ጎሳና ቋንቋን መሰረት አድርጎ የተቋቋመው የፌዴራል የክልል አወቃቀሩ ስለሆነ ባስቸኳይ ይህ ሕገ መንግሥት ታግዶ ሌላ ሕገ መንግሥት ተረቆ በማጽደቅ በእውነተኛና ተቀባይነት ባላቸው የፌዴራሊዝም መርሆዎች ላይ የተመሰረተ ፌዴራላዊ የክፍለ ግዛት አወቃቀር እንዲመሰርት እንዲያደርግ እንጠይቃለን ።

ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ

፩ኛ አቶ ጃዋር መሐመድና ተባባሪዎቹ የዓለም አቀፍ ሽብርተኞች ከሚፈጽሙት እጅግ የከፋ ኢሰብአዊ የሆነ የዘር ማጽዳትና በሃይማኖት ላይ ያነጣጠረ ከፍተኛ ወንጀል ስለፈጸሙ የኢትዮጵያ መንግሥት ሄግ ለሚገኘው የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አሳልፎ እንዲሰጥ ጫና እንዲያደርግበት እንጠይቃለን ።

፪ኛ አቶ ጃዋር መሐመድ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ስለሆነ አሜሪካ ይህ ከባድ ወንጀል የፈጸመ ዜጋዋ በኢትዮጵያ መንግሥት ተይዞ ለአሜሪካ ተላልፎ እንዲሰጥና በአሜሪካን ሕግ እንዲጠየቅ በጥብቅ እንጠይቃለን ። ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ የተባለው ሚዲያውም ከአሜሪካም ሆነ ከየትም እንዳይተላለፍ እንዲታገድ እንጠይቃለን ።

፫ኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ጭፍጨፋው ከመጀመሩ በፊት ባለመከላከሉ ከተጀመረ በኋላም በቶሎ ባለማስቆሙ ብሎም የሽብር ድርጊቱ ዋና ተዋናይ የሆነውን አቶ ጃዋር መሐመድን ወደ ፍርድ ቤት እንደማቅረብ ወደ ሽምግልናና እርስበርስ የመታረቅ ሂደት ላይ በመሆኑ ይህ ድርጊቱ ከወንጀሉ ጋር ተባባሪ ስለሚያስመስለው ዓለም አቀፍ ማሕበረሰቡ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ተገቢውን ጫና በማድረግ አቶ ጃዋርንና ተባባሪዎቹን በቁጥጥር ስር እንዲያውል አጥብቀን እንጠይቃለን ።

፬ኛ ይህ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮችንና የአማራን ነገድ የማጥፋት ብሎም በእስልምና እምነት ተከታዮችና ሌሎች ወገኖች ላይ የደረሰዉ የሽብር ወንጀል በገለልተኛ ወገን መጣራት ስላለበት የተባበሩት መንግሥታት መርማሪ ቡድን ገብቶ እንዲያጣራ አጥብቀን እንጠይቃለን ።

፭ኛ የዶክተር አብይ መንግሥት ስልጣን ከያዘ በኋላ ዘርና ሃይማኖትን ላይ ያተኮሩ ጭፍጨፋዎች ሁሉ ለምሳሌ የቡራዩ ፣ የኬሚሴና አጣዬ ፣ በሲዳማ የተካሄዱ ጭፍጨፋዎች ሁሉ ፣ በሰኔ ፲፭ በአማራ ክልል አመራሮች ላይና በሁለት የመከላከያ ጄኔራሎች ላይ የደረሰው ግድያ እንዲሁም የኢንጂነር ስመኘው ሚስጥራዊ ሞትና ከሃምሳ በላይ አብያተ ክርስቲያናትና መስጊዶች መቃጠል በዓለም አቀፍ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን እንዲጣራ እንጠይቃለን ።

፮ኛ አሁን ከደረሰዉ እጅግ የባሰ ሃይማኖትንና ብሄርን መሰረት ያደረገ ጭፍጨፋ ሊካሄድ ስለሚችል የተባበሩት መንግሥታት በኦሮሚያ ክልል የሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲያሰማራ እንጠይቃለን ።

ኢትዮዽያ የደረሰባት ቀዉስ እጅግ አደገኛ ስለሆነ ከሩዋንዳ የከፋ ዕልቂት እንዳይፈፀም፣ ብሎም ለቀጠናዉ አገሮች ብቻም ሳይሆን ለአለም ሰላምና ጸጥታ መደፍረስም ሆነ የንግድ ዝዉዉር መታወክ ምክንያት ስለሚሆንና እንዲሁም ለሚሊዮኖች ስደት ስለሚዳርግ አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚሻ የኢትዮጵያ መንግስትንና የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ልናስጠነቅቅ  እንወዳለን።

የኢትዮዽያ ህዝብ በገጠር በከተማ የሚኖረዉ በየሰፈሩ ተደራጅቶ ራሱን ፣ ቤተሰቡን ፣ የሃይማኖት ተቋማትን ፣ የራሱንና የአገር ሀብት እንዲጠብቅ ወገናዊ ጥሪ እናቀርባለን ።

ግልባጭ :-

ለኢፌዲሪ ፕሬዜዳንት

ወ/ሮ ሣህለወርቅ ዘዉዴ

ለኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር

አቶ ደመቀ መኮንን

ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ

አቶ ታገሰ ጫፎ

ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት

ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ

ለኢትዮዽያ ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ሚንስቴር

አቶ ብርሃኑ ፀጋየ

ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

ለአማራ ክልላዊ መንግሥት  ርዕሰ መስተዳደር

አቶ ተመስገን ጥሩነህ

ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር

አቶ ሺመልስ አብዲሳ

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባስደር

አቶ ፍጹም አረጋ

ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ

አቶ ቢኒያም አባተ

አዲስ አበባ

ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ማኅበር ዋና ዳይሬክተር

አቶ ያሬድ ኃይለማርያም

ብረሰልስና ጄኔቫ

 

2 Comments

  1. ጊዜ አታባክኑ። ጠ/ሚሩ ምንም ማድረግ አይችሉም። በዶዶላ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች በኦሮሞዎች የደረሰባቸውን ሲተርኩ መስማት መንግስትና ህግ አለ ማለት አይችልም። የመንግሥት አካሉ ራሱ አብሮ ነዳጅ እያቀበለ የሰው ቤት ሲያቃጥልና አንገትህ ላይ ያለውን ማተብ ብታወልቅ ይሻላል የሚባልበት ምድር ላይ ተቀምጠን መንግሥት ይድረስልን ማለት መፍትሄ የለውም። በተደራጀ መልኩ ራስን መመከት ተገቢ ነው። ደካማው ሽማግሌ እጅና እግሩ ተቆርጦ ሆድ ተዘንጥሎ ማየት ደስ ከሚለው የኦሮሞ ጥርቅም ጋር መደራደር የለም። ተፋልሞ የሞተው ይሙት። ሃገር የሚባል ነገር የለም። ጭራሽ። ውሸት ነው። ግፍ ከበፊቱ የበለጠ እየፈሰሰ ነው። ጠ/ሚሩ ድብቅ አጀንዳ ያላቸውም ይመስላል። እንዴት የኦሮሞ ብሄርተኞች የሰውን አንገት ሲቀሉ፤ ቤት ሲያቃጥሉ ሲዘርፉ፤ ከክልላችን ውጡልኝ ሲሉ ዝም ተብሎ ይታያል?
    በዶዶላ በቀረበው የዓይን ምሥክር መረጃ መሰረት የጥቃቱ ተባባሪ የነበሩ የጸጥታ ሃይሎችን ለይቶ ማወቅ ይቻላል። ሰዎች እንደ ጠቦት ተጎትተው የሚገደሉበት ምድር ምን ዓይነት ፍትህ ነው ሊኖር የሚችለው። የኦሮሞ የጅምላ ጭፍራ አረመኔአዊ እንደሆነ ተግባራቸው እያሳየን ነው። በድህረ ገጾች ላይ ሰዎች እያለቀሱ የደረሰባቸውን ሲገልጽ ከሥር በኦሮሞዎች የሚጻፈውን ማንበብ ደም ያፈላል። የቢለዋ ስዕል አስቀምጠው ገና እናርዳችሁሃለን ከምድራችን ውጡ። ማን ከማን ያንሳል። ይለይለት እና እንፋለም። ሰለቸኝ ዝም ብሎ ሙታንን መቅበርና ማልቀስ። እዚያም ቤት እሳት አለ መባል አለበት።
    የሚገርመው ይህ የገዳይ ጭፍራ የተደራጀና በሶስት ዘርፍ የተከፈለ ነው። ነዳጅ ይዞ ቤቶችን የሚያቃጥል፤ ሰዎችን በድንጋይ የሚደበድብ፤ በድብደባው ያልሞቱትን ቆንጭራ ይዘው አንገት የሚቀሉ። ይህች ናት የኦሮሞ የነጻነት መግለጫ። ይህ ነው የኢሬቻው የሰላም ጥሪ። የሰው ደም የሚጠጣ አድባር።
    ስለሆነም የሰው ልጅ መብት ተቆርቋሪ የሆናቹሁ ሁሉ ዝም ብላችሁ “ይድረስ ለጠ/ሚ አብይ፡ ግልጽ ደብዳቤ ለጠ/ሚር አብይ” ወዘተ. እያላቹሁ አታሰልቹን። ሰውየው የሚሰማ ጀሮ የለውም። እኔ በጠ/ሚሩ ላይ እምነት ያጣሁት የሙታንን ቁጥር በዘርና በቋንቋ በሃይማኖት አስልተው መግለጫ ከሰጡ ወዲህ ነው። ተልካሻ ፓለቲካ። ሰው በሰውነቱ ሳይሆን በፈጠራ በተበጀ የዘር ክልል መፋለምና አውራ ጣት ከአመልካች እጣት ይበልጣል ብሎ ማመን። የሙታን ፓለቲካ! እናንተ በየጊዜው በተለያየ መንገድ ለጠ/ሚሩ ጥሪ የምታቀርቡ ወገኖች አንድ ነገር ልጠይቃችሁ። ለምን ይሆን ጠ/ሚሩ በሚዲያ ቀርበው ሰውን የሚያፈናቅሉ፤ ሰው የሚገሉ፤ የዘር ፓለቲካ በሚያራምድ ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን። የጸጥታ ሃይል ሆነው በዘር የተሰለፉትን ሁሉ ለፍትህ እናቀርባለን ብለው ግልጽ አቋም ያልወሰድት? ዝምታም እኮ መተባበርም ነው።
    ስለሆነም ፍትህ በምድሪቱ ከሞተ ቆየ። የኦሮሞው ፍትህ ደግሞ ድርቡሻዊ ሆነ። ይገርማል። እንዴት ሰው የሰው አንገት ቆርጦ እንቅልፍ ይወስደዋል? የአውሬዎች ስብስብ!በህዝባችን ላይ በኦሮሞዎች የሚፈጸመውን ሁሉ በድምጽ፤ በምስክር፤ በቪዲዮ፤ በጽሁፍ ለዓለም ህዝብ ሁሉ ማሳየት መቻል አለብን። አውሮጳና ስሜን አሜሪካ የእነዚህን እንስሶች ተግባር ማወቅ አለባቸው። ይህ መረጃ ለፓለቲካ ፍጆታ ተብሎ ተጣሞ፤ ታክሎብት፤ ወይም ተቀንሶ መቅረብ የለበትም። እውነትን ተመርኩዞ እንጂ! አስከሬን ፎቶ ማንሳት፤ አንገቱ የተቆረጠም ቢሆን ገደል የገባ፤ በድንጋይና በድላ ተቀጥቅጦ የሞተም ቢሆን የግድ ነው። የሞተ ፎቶ አይነሳም የሚባል ነገር የለም። መረጃ ነው። የተቃጠሉ ቤቶች፤ የወደሙ ንብረቶች፤ የተቃጠሉ ቤ/ክርስቲያኖች የሞቱ ሰዎች ስም ዝርዝርና ቦታ ከጾታና ከእድሜ ጋር፤ ጥቃት አድራሺዎቹ ስምና አድራሻ፤ ቀኑ፤ የተጀመረበት ሰአትና ያቆመበት ጊዜ፤ የጸጥታ አካል ሆነው በዝምታ ያዪ ወይም በተግባሩ የተካፈሉ፤ የአመራር አካል ሆነው ነገሩን በዝምታ ያዪ ሁሉ በዝርዝር ሊያዝና በዳታቬዝ ሊጠራቀም ይገባል። እርቅ የሚባል ጉዳይ አይሰራም። ህግ የለም። የእነዚህን የ 21ኛው ዘመን አረመኔዎች ለዓለም ህዝብ ማሳወቅና በፋይናስ አይዞአቹሁ የሚሉትን ሁሉ ጉዳይን በማስረዳት ምንጫቸውን ማድረቅ ተገቢ ነው። ቀን እያለ ራስን ለማይቀረው ፍልሚያ ማዘጋጀት እንጂ በጫካና በቤ/ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ተጠልሎ ሁልጊዜም መኖር አይቻልም። ሞት በሞት ብቻ ነው መሻር የሚቻለው! የመንግሥት ጥሩንባ ምርመራ፤ ተይዘዋል፤ እንዲህ እንዲያ የሚባለው ሁሉ የውሸት ነው። የኦሮሞ ፈዜኛ ለመሆኑ አንድ ልጥቀስ እና ይብቃኝ። የአዲስ አበባ ፓሊስ እስረኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ 24 ቀን ተጨማሪ ይፈቀድልኝ ሲል ዳኛው 48 ቀናት ፈቅጃለሁ የሚባልበት ጦረኛና ዘረኛ ችሎት ነው። በቃኝ!

  2. I am really surprised why people want to blame shift from and exaggerate what was done and try to hide the reality. As usual, Abyssinians continued disseminating their fake news. If you remember, during the last 28 years, TPLF used to blame OLF and other national liberation fronts for any crime they themselves committed. They wanted to create confusion among the international community by blaming freedom fighters as terrorist when in actual sense, the TPLF leaders were terrorists themselves promoting state terrorism. These days, the other group from northern Ethiopia, the Amhara power thirsty elites were working day and night to condemn human rights activities/Jawar and Oromo youths/Qeerroo who were the driving engine for crumbling of the tyrannical dictatorial regime of TPLF. They are doing this out of fear that either Jawar or the Qeerroo are highly accepted in the Oromo community and deny them acceptance in their futile domination of Ethiopia as has bee done since the invasion of Minilik. These political elites don’t want anything about other people except their own voices using their Amharic. That is why the incriminate, Oromo activities and youth revolutionaries/Qeerroos without any reason. Qeerroos emphasized on demanding the rights of their people to be respected in their own region peacefully. to change the images of Qeerroos and activist Jawar Mohammed and OMN, the only private media that contributed to the downfall of the TPLF regime as terrorists. The allegations are generally baseless and the only thing considered as crime are that Jawar/Qeerroo/OMN are not willing to be going in the old ways only admiring/appreciating Abyssinian elites’ feelings. OMN is a voice for many ethnic groups who are voiceless. The Amhara political elites and their private media, ESAT and others always making campaigns on the Oromo media and political elites to fulfill their ego by silencing the voices of the conscious Oromo political elites and other elites from other nations and nationalities like Sidama, Kimant, Agaw, etc. Therefore, the international community and other Ethiopian who have logical thinking can critically look at the false allegations of the Abyssinian elites of the Neo-Neftegas aspring to return Ethiopia to the time of Amhara domination. To these group, I strongly advice them to stop such cheap popularity when they are filled with evil spirits of returning back to the dark ages of the old Abyssinian rule of Neftega.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.