የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ተባለ

1 min read

በሲዳማ ዞን የሚደረገው ህዝበ ውሳኔ ሰላማዊ፣ ፍትሀዊ፣ ታዓማኒ እና የህዝቡን ፍላጎት ያረጋገጠ እንዲሆን የፀጥታ አካላት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

ይህ የተገለፀው የፌዴራል ፖሊስና የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን “ጀስትስ ፎር ኢትዮጵያ” ከተሰኘ ተቋም ጋር በአዳማ ከተማ በጋራ ባዘጋጁት ስልጠና ላይ ነው፡፡

ስልጠናው ለፀጥታ አካላት የተዘጋጀ ሲሆን ህዝበ ውሳኔው ሲካሄድ ያለምንም ግርግርና ግጭት በሰላም እንዲጠናቀቅ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡

በዚህ ወቅት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ሲደረግ የዜጎችና የምርጫ አስፈፃሚዎችን ደህንነት ማስጠበቅ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር ህዝበ ውሳኔው በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

በሲዳማ ህዝብ ውሳኔ ድምጽ ሲሰጥ ህዝቡ ያለማንም አስገዳጅነት የራሱን ውሳኔ እንዲወስን ሊደረግ ይገባል ተብሏል፡፡

በሲዳማ የሚደረገው ህዝበ ውሳኔ በቀጣይ ለሚደረገው አገራዊ ምርጫ ትልቅ ትምህርት ሊሆን እንደሚገባም ነው የተገለፀው፡፡

ሪፖርተር፦ ዳዊት በጋሻው

2 Comments

  1. The Managing Director of The Viital Events of Ethiopia Ato Mujib Jamal who also. happens to be the main person overseeing, Immigration Nationality of Ethiopia said ” This voter registration is being done in a perfectly legal way.”
    Ato Mujib Jamal , also said ” This referendum’s voter registration is the first perfect , legal and fair voting registrion of it’s kind in Ethiopia . “

  2. The Managing Director of The Viital Events of Ethiopia Ato Mujib Jamal who also happens to be the main person overseeing, Immigration and Nationality of Ethiopia said ” This (Sidama’s referendum) voter registration is being done in a perfectly legal way.”

    Ato Mujib Jamal , also said ” This Sidama’s referendum voter registration is the first perfect , legal and fair voting registrion of it’s kind to be held in Ethiopia . “

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.