ኦሮሚያ ለሚባል ምናባዊ አገር ምስረታና …

3 mins read

(ይህንን ከዚህ በታች የሚገኝ የአበበ ቦጋለን ጽሑፍ ከሳተናው ድረገፅ ወስጄ እንዳለ ላክሁት – አጭር ነው – ለማንበብ አትፍሩ፡፡ አስተያየቶቹ አስተማሪ ናቸው ብዬ ስላሰብኩ በአንድ ድረገፅ ብቻ ተወስነው መቅረት እንደሌለባቸውና ፈቃደኛ የሆኑ ድረገፆች ቢያስናግዱልኝ ብዬ በልመና መልክ ሰደድኩት፡፡ የነአባዊርቱ ልፋትና ድካም፣ የነአባጫላ ድንቁርናና ልበሥውርነት በስፋት መታወቅ ይገባዋል፡፡ ከምሥጋና ጋር፡፡ ግን እኔ ማን ነኝ? ማንስ ብሆን ምን ቸገረን፡፡ ዋናው ቁም-ነገሩ ነው፡፡)

ነጻነት

ኦሮሚያ ለሚባል ምናባዊ አገር ምስረታና ኦሮሞ ለሚባል ማንነት ፈጠራ እረፍት የሚያጡ ኦሮሞ ወገኖቼ ጉዳይ

November 9, 2019

421

SHARES

ኦሮሚያ ለሚባል ምናባዊ አገር ምስረታና ኦሮሞ ለሚባል ማንነት ፈጠራ እረፍት የሚያጡ ኦሮሞ ወገኖቼ ጉዳይ በየቀኑ እንደ ኣዲስ ይገርመኛል። የሰው ልጅ አእምሮ ምጥቀት በባህርና በየብስ በብዙ ማይልስ ተራርቆ የሚኖሩ የአለም አገሮችን አቀራርቦ አንድ ድንበር አልባ መንደር ባደረገበትና ሰው እንደልቡ ተዘዋውሮ በመረጠው አገር ሰርቶ የመኖር መብቱ ከምንጊዜውም በላይ እያደገ በመጣበት 21ኛው ክፍለዘመን ላይ እንዲህ አይነት አስተሳሰ ከእርግማን ወይስ ከአእምሮ መላሸቅ እንደሚመጣ አልገባ ብሎኛል።

ከሁሉም የሚደንቀኝ ደግሞ የዚህ ሃሳብ ዋና ኣቀንቃኞች የሥልጣኔ፣ የሰላምና ብልጽግና ማእከል በሆኑት ምእራብ አገሮች የኖሩ፣ የሚኖሩ ወይም ተምረው የተመለሱ መሆናቸው ነው።
ታሪክ እንደሚመሰክረው አንድ ወቅት ከቦረና ወደ አራቱም የአገሪቱ ማእዘን የተንቀሳቀሰው ኦሮሞ በየደረሰበት
እየተጋባ፣ እየተዋለደና በአምቻ ጋብቻ እየተዛመደ የመጣ ሌላው ቀርቶ በጦርነት ወቅትም የማርከውን
በሞጋፋቻና በጉዲፈቻ ባህሉ ጭምር
የራሱ ወገን እያደረገ አሁን ለምናውቃት ኢትዮጵያ የመሰረት ድንጋይ የሆነ ህዝብ ነው።
እና የኦሮሚያና የኦሮሞ ጉዳይ እረፍት
የሚነሳችሁ ወገኖቼ የናንተ ኦሮሚያና ኦሮሞ የምትሉት ያልተከለሰ ያልተበረዘ ማህበረሰብ ከወዴት ይምጣላችሁ? ወይስ political Oromoን ብቻ ኦሮሞ እያላችሁ ከሁሉም ጋር ስትላተሙ ለትኖሩ?

ተወደደም ተጠላ የአገራችን እውነታ አብላጫው ህዝብ እንደ ብራዚል ህዝብ mixed (በደምና በሥጋ የተቀላቀለ ) ህዝብ መሆኑ ነው ።
ህዝባችንን በቋንቋና በሃይማኖት ከፋፍሎ ቅኝ ለመግዛት ሞክረው ያልተሳካላቸው አውሮጳዊያን ጥለውት የሄዱትን የአማራና የኦርቶዶክስ ጥላቻ Internalize አድርጋችሁ ኢትዮጵያዊነት ላይ ክህደት መፈጸም ኦሮሚያ የተባለ ነጻ አገርና ኦሮሞ የተባለ አንድ ወጥ ህዝብ አይፈጥርምና እባካችሁን አትጃጃሉ ።
ሁሌም የተበዳይነት ፣ የተጨቋኝነትና የእንናቃለን ባይነት ስሜት ሰለባ አንሁን !
እራሳችንን የታሪክ ተበዳይ አድርገን ከመቁጠር ነጻ እንወጣ ዘንድም ምናልባት በፕሮፈሰር ጌታቸው ሃይሌ የተተረጎመውን የኣባ ባህሪን ዘናሁ ዘጋላንና ፕሮፌሰር መሃመድ ሃሰን The Oromo and the Christian kingdom of Ethiopia 1300 – 1700 ብለው ያሳተሙትን መጻህፍት ማንበብ ሳይጠቅም አይቀርምና እይት አድርጉት ።
በጎ በጎውን ያሳያችሁ ዘንድ የዘወትር ጸሎቴ ነው።

አበበ ቦጋለ

10 COMMENTS

 1. እውነቱNovember 9, 2019 at 4:39 pm

ግሩም ጥሪ ነው አበበ ቦጋለ:: ፅንፈኛ ኦሮሞዎች የያዙት ቅዠት ነው:: በምንም መመዘኛ ቋንቋ ብቻውን የማንነት መገለጫ ሊሆን አይችልም:: እኔ የማውቀው የሰላሌ ኦሮሞ ከመርሀ ቤቴ ጋር እጅግ የሚያዛምደው መቀራረብ ማንነቱን ይገልፃል ከጃዋር ባለቆንጮራው አርሲ ኦሮሞ:: ፅንፈኞቹ በምናባዊ የቀረፁት አዲስ ሀገር በምንም መመዘኛ እውነት ስለማይሆን እንደተንቀዠቀዡ ይቀራሉ::ሌላው እነዚህ ፅንፈኞች ያላወቁት እጅግ ብዙ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ድብልቅ ነው:: ብሄር ኢትዮጵያዊ በአንድነት ከተነሳ: ይነሳልም ይገዳደራቸዋል::

 1. አባዊርቱNovember 9, 2019 at 5:13 pm

አቶ አበበ አንተን የደነቀህ የነዚህ ህልመኞች”ሀገረ ዖሮምያ” ቅዠት ነው። እኔን ደግሞ በይበልጥ የሰበረኝ የብዙሃን ወገኖቻችን ዝምታ ነው። እንዴት ከቁጥራችን አንጻር አደባባይ ወጥቶ ይህን እብደት እበደት ነው የሚል አይን የሚገባ ቁጥር ይጥፋ?አሳሳቢ ነገር ነው። የመጨረሻውስ ጄኔሬሺን እድሜ ለወያኔ ሎሌነትን፣አድርባይነትን፣ ቅጥፈትንና ቅጥአጥነትን ብሎም ኢትዮጵያን ክህደትን በደንብ ተምረዋል። የመሃለኛው ጄኔሬሺንና የጥንቶቹ ምን ወጣት ቢበዛ ቁጥራችን ቀላል አይደለም። እንዴት እነዚህ ከሀድያንን አትወክሉኝም አይባልም? በዝምታ አገር የሚያስረክብ ህዝብ። አንድ የዖነግ አንጋች የሆነ ቦታ ላይ RIP ETHIOPIA ያላትን ምንጊዜም አልረሳውም። ኢትዮጵያን ስሙዋን እኮ ነው መስማቱን የጠሉት እንኩዋንስ ህልውናዋን። በጣም ያሳዝናል። እነሱ አመድ ይሆናሉ እንጅ ኢትዮጵያስ አትሞትም። ምናልባት በዝምታ የሞተውን ኢትዮጵያዊ መነካካታቸው ይሆናል ለነገሩ።

 1. KebedeNovember 9, 2019 at 6:58 pm

በሳል አስታያየት ነዉ። አሳዛኙ ነገር ግን ፅንፈኛ ኦሮሞዎች ይሄ አይገባቸዉም።

 1. TesfaNovember 9, 2019 at 11:23 pm

የሃበሻው ፓለቲካ የቱልቱላ ፓለቲካ ነው። ሰውን እሩቅ ሆኖ እሳት መማገድ፤ የሌለ ነገር ፈጥሮ ሰውን ማጋጨት፤ ሰው እንደ አውሬ ነፍሴ አውጪኝ በማለት ጫካ ገብቶ የሚደበቅበት፤ የዘርና የጎሳ ፓለቲካ የተሰራፋበት የእብዶች ስብስብ ነው። አንድ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ተቀምጦ “Eritrea for Eritreans only” የሚል ነገር ታኪሰው ላይ ለጥፎ ሳይ አይ ሃገር መቸመ ልብ አይሞት ነው። እንዲያ ከሆነ አንተን ከዚህ ምን አመጣህ በማለት በልቤ ነገሩን አለፍኩትና በታክሲው ተሳፍሬ ያሰብኩት ቦታ ወረድኩ። የስማ በለው ፓለቲካ። ይህ እንደዚህ ሆኖ ጠ/ሚሩ ምንም ነገር ለሃገርም ሆነ ለራሳቸው ያልተገበሩ በተለያየ ብሄርና ስም በውጭና በሃገር ውስጥ የነበሩ የፓለቲካ ተቃዋሚዎችን (አንዳንዶች የታጠቁ) ኑ ግቡ ሃገራችንን እናልማ እንመከካከር ሲባሉ የውስጥና የውጭ የሻገተ የፓለቲካ ቅራቅቦዎቻቸውን ይዘው ሃገር በመግባት አንድ የጠ/ሚሩን መንግስት በ 24 መገልበጥ ይቻላል ሲል ሌላኛው ደግሞ በፈጠራ ኡኡታ የሰው አንገት ያስቀላና ቤ/ክርስቲያንና መስጊዶችን ያቃጠለ የእብዶች መንጋ መሪ የሚናጥጥባት ሃገር ሆናለች። በምትኩ ራሳቸው ፈጭተው በጋገሩት የፈጠራ መፈንቅለ መንግሥት ሰበብ አማራው እየታፈነ የሚደርስበትንና የደረሰበትን ታግተው በቅርብ ከተለቀቁ መስማት የአብይ መንግሥት ከወያኔ አለመሻሉን ያሳያል። የእንጂኒየር ስመኝውን ሞት የራስ በራስ ግድያ ነው የሚለው የኦሮሞ ተኩላ በምትኩ ማንን ለህዳሴ ግድብ እንደተካ የሴራውን ሚስጢር ያሳያል። አልፎ ተርፎም በአማራ ስም ታፍሰው እስር ቤት የገቡ የተጠየቁትን ጥያቄዎችና የደረሰባቸውን በደል ላመዛዘነ የባህርዳሩ ግድያ በማን ተለኩሶ በማን እንደተፈጸመ በግልጽ ያሳያል። አንዲት ኢትዮጵያዊት እህታችን ስለ ሃገር አንድነት ስትናገር አንድ ከመካከል በመነሳት እንዲህ የወፈርሽው እኮ ኦሮሚያ ላይ የተመረተውን እህል ተመግበሽ ነው በማለት እንደዘለፋት አይቻለሁ። ምናባዊም ሆነ እውናዊ ኦሮሚያ የሚባል ሃገር አይኖርም። ቢኖርም እርስ በርሳቸው የሚተራረዱበት ሜዳ ነው የሚሆነው። የወለጋ ኦሮሞ ከሃረር ኦሮሞና ከሽዋ ኦሮሞ ጋር በምንም መንገድ አይስማማም። ዝም ብሎ የፓለቲካ እብደት ነው እንጂ በመገነጣጠል ሰላም ያመጣ ሃገር የለም። ደ/ሱዳን፤ ኤርትራና ሌሎችም ሁሌ ህልማቸውና በመሬት ላይ ያለው እውነታ ተጣጥሞ አያውቅም። ግን የኦሮሞ መንጋ ሃገር ከማፍረስ፤ ሰውን ከመግደል፤ ከመሬቴ ውጡልኝ ከማለት ያርፋሉ ብሎ መገመት ሞኝነት ነው። አቶ በቀለ ኦሮምኛ ከማይናገር ጋር አትጋቡ፤ አትነግዱ ሲሉ፤ ሌላው ምሁር ነኝ ባይ ደግሞ ስሜና ሃይማኖቴ የተቀየረው በአማራ ነው። ተገድጄ ተጠምቄ ነው ክርስቲያን የሆንኩት ይለናል። በሜቺጋን ውስጥ የራሱን ኑሮ እየመራ ወደ ሃገር በቅ በማለት የጫቱ ፕሮፌሰር ደግሞ አብይና ለማ ኦሮሞዎችን አይደሉም። የኦሮሞን ህዝብ አይወክሉም ይሉናል። እነዚህ ተምረው የደነቆሩ የወስላቶች ድምር ናቸው። ጀግንነት የሰላማዊ ሰው አንገት በቢላዋ መቅላት ከሆነ አይናችን አይቷል። ጨለማነትና ኋላ ቀርነት እንጂ ሌላ ትርፍ ግን የለውም። አዲስ አበባ የእኛ ነው የሚሉ እነዚህ ጎዶች መኖር የሚሹት አፍንጫቸው ዙሪያ በተለጠፈች ሥፍራ ብቻ ነው። ከዚህ የብሄር መንጋ ጋር ድርድር አያሻም። ራስን አደራጅቶ ራስን መመከት ግን አስፈላጊ ነው። የጋሞ ብሄረሰቦችን እንደ እንስሳ ቀጥቅጦና አርዶ የገደለው የጃዋርን የድረሱልኝ ጥሪ ሰምቶ የተሰባሰበ የቄሮ መንጋ ነው። ዛሬ በትምህርት ተቋማት፤ በሥራ ቦታ፤ በንግድ ቀናችን ነው በማለት ሌላውን እያባረሩ ስፍራውን በኦሮሞ ብቻ እንዲያዝ ያደረጉት የዚሁ የፓለቲካ የውስጥ ጥምረት የፈጠረው አንድነት ነው።
ጠ/ሚሩን የተቀቡ ቃላቶችን እየደረደሩ ሰውን በማፍዘዝ ለኦሮሞዎች ብቻ ነገርን በአድሎ እንደያዙ የሚያሳየው ጃዋርን አለማሰራቸው ነው። ግን የጃዋር ተከታዮች እኮ ጠ/ሚሩን ኦሮሞ አይደለም አማራ ሚስቱን አቅፎ እያደረ ኦሮሞ ነኝ ይላል እያሉ ሲያፌዙበት ተሰምቷል። በመሰረቱ አንድ መንግሥት ሃገርና ወገንን በሚያርድና በሚያፈናቅል ላይ እርምጃ ካልወሰደ ለራሱም ቆይቶ እንደሚያሰጋ የታወቀ ነው። የኦሮሞ ፓለቲካም ለእኛ ብቻ የሚል በመሆኑ ከወያኔ ፓለቲካ ቢከፋ እንጂ የሚሻልበት አንድም ነገር የለም። እየወሰለቱና እየተወሳለቱ አንድ ላይ እሳት ሲጭሩና ለራሳቸው ነገርን ሲያመቻቹ ሳያስቡት ይፍረከረካሉ። ፓለቲከኞች የተኩላና የጅቦች ጥርቅም ናቸው። ለህዝብ አስቦ በህዝብ ታምኖ የኖረ በምድሪቱ ላይ ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም። የዛሬውም የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ እንጂ ሥራቸው ሁሉ የሞሶሎኒ አይነት ነው። ሰው ዘቅዝቆ የሚሰቅል የቄሮ ጭፍራ ለኦሮሞ ህዝብ ሰላም ያመጣል ማለት ህልም ነው። ለማንም ለምንም አይበጁም። ካላመንክ ጠብቅና እይ!

 1. Abba CaalaNovember 9, 2019 at 11:38 pm

“የሰው ልጅ አእምሮ ምጥቀት” ከምድራችን አልፎ፣ በሌሎች ክዋክብት ዙሪያ ያሉ ፕላኔቶችን እያሰሰ ባለበት ዘመን፣ ያንተ አዕምሮ ግን ፊት ለፊት የሚታዩትን ኦሮሚያና የኦሮሞን ህዝብ ማየት ያቃተህ፣ ማንን ለመምከር እንደምትንጠራራ በጣም ግራ የሚያጋባ ነው! ሃገርና ህዝብ ምን እንደሆኑ ሊገባህ ካልቻለ አዋቂዎችን መጠየቅ ካልሆነም አዕምሮህን ማስመርመር ይገባሃል።
እኛ ኦሮሞ እና ኦሮሚያ ስንል፣ ንጹህ ኦሮሞ፣ ከኦሮሞ ሌላ ማንም የማይኖርባት ኦሮሚያ ማለት እንዳልሆነ ዛሬ ከህጻን እስከአዋቂ ሁሉም ይረዳዋል (ምናልባት እንዳንተ አዉቀው የደነቆሩ ካልሆኑ በስተቀር)። አንድን ማህበረሰብ ‘ህዝብ’ ወይም ብሄር የሚያሰኙት መስፈርቶች መሃል ደግሞ ‘የደም ጥራት’ የሚል የለበትም። ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ፣ ስነልቦና እና ጂኦግራፊ የመሳሰሉት ናቸው አንድን ህዝብ ከሌላው የሚለዩት። ኦሮሞ የሚባል ህዝብ የለም ማለትህ፣ ሶማሌ፣ ኩኩዩ፣ አረብ፣ እንግሊዝ፣ ቻይና፣ ወዘተ የሚባሉ ህዝቦች የሉም ማለት ነው። ያንተ አረዳድ ለኦሮሞ ብቻ ትርጉም አይሰጥምና! You can not selectively apply your definition only to the Oromo! ማለት የፈግከው፣ ኢትዮጵያዊ የሚባል እንጂ ሌላ ብሄር ብሄረሰብ የለም ለማለት ነው። ይህ የናንተ ኢትዮጵያዊ ግን አማርኛ ተናጋሪ፣ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን፣ ደገኛ፣ ፊቱ ሰልካካ የሆነ ቀይ ወይም ጠይም ሰው የሚል ነው። ባጭሩ፣ ለመቶ አመታት ተሞክሮ የከሸፈው የአንድ ቋንቋ፣ አንድ ባህል፣ አንድ ህዝብ መፈክር ማስተጋባት ነው!
የኦሮሞ ህዝብ ላለፉት 100 አመታት ለነጻነቱ ሲታገል የቆየው፣ በሃበሻ ነገስታት ቅኝ አገዛዝ ስር ከመማቀቅ አልፎ፣ እንደአንድ ህዝብ ተለይቶ ቋንቋ፣ ታሪክና ማንነቱ እንዲጠፉ መንግስታዊ ፖሊሲ ተቀይሶ ባህላዊ ጀኖሳይድ የተጋረጠበት ስለሆነ፣ ይህን የጥፋት ተልዕኮ በጋራ ለመቋቋም ነው። ይህ ደግሞ ባንተ ምጢጢ አዕምሮ እንደታሰበው፣ “የአማራና የኦርቶዶክስ ጥላቻ Internalize ማድረግ” ሳይሆን ጭቆናና ባርነትን ለማስወገድ እየተደረገ ያለ ያለም ህግ የሚደግፈው ሃቀኛ ትግል ነው። “ጭቆናና ባርነትን ያመጡበት አማራና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ናቸው” የምትለን ከሆነ ደግሞ፣ እናንተን ላለማስቀየም ብለን ባርነትን ለዘለአለም አንሸከምም፣ ማንኛውንም የጭቆና ስርዐት መዋጋት ተፈጥሮአዊ መብት መሆኑን ለማሰብ ሞክሩ እንላለን! ባርነትን መዋጋት የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ እንቅስቃሴም ነው እንጂ ሌላ የውጪ ሃይል የሚገፋው ተልዕኮ አይደለም!
እስከዛሬ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን ለመረዳት ሳትችሉ፣ በሌላ መንገድ ለመተርጎም መሄዳችሁ፣ የአዕምሮ ድክመታችሁ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ማሳያ ነው! ማፈር ይገባችሁ ነበር!

 1. አባዊርቱNovember 10, 2019 at 5:05 am

አባጫላ እንደው ፈቃድህ ሆኖ ብጠይቅህ? ከልቤ ነው የማሾፍ እንዳይመስልህ። እንደውም ጥያቄ ሳይሆን ግምቴም ነው። መቼስ ዘመናዊውን ትምህርት ተቃምሰሃልና ነው። ይህ ቁቤ ከመጣ በሁዋላ ነው እንዴ ስለ ዖሮሞ ማወቅ የጀመራችሁት ወይስ ከቁቤው ጋር ተበጥብጦ አቅልን አስቶ የራስን ታሪክ እስከመሳት ድረስ እንደው ምን አገኛችሁ ወገኖቼ? ደሞስ ስለ አለም መራቀቅ ለማውራት ብቃቱስ አለህ የእውቅ ዩኒቨርስቲው ምጡቅ የጎሳ ወንድምህ በአምላክ አምሳል የተፈጠረን ሰው ሲያስበልትና በዛ ደም ሰክሮ ሲፈነጥዝ እያየን? አይንህን በጨው ያጠብክ ደፋር ነህ ።
ኸረ ለመሆኑ ማን ስልጣን ሰጣችሁ ማን እውነተኛና ውሸተኛ የሆነ ዖሮሞ ብሎ ለመወሰን? ጉልበቱስ አላችሁ?: ነፍሰ ገዳዮችንና አራጆችን አሰማርታችሁ ኢትዮጵያዊነትን እናሸንፋለን ብላችሁ ታልማላችሁ:: ኢትዮጵያን አታውቁም:: ልታውቁም አይገባም። ዲዘርቭም አታረጉዋትም። በጣም ደስ የሚለው ቁጥራችሁ እጅግ አናሳ ነው። እናንተን ብዙ ያስመሰላችሁ በደም ጉቦ የገነባችሁት የማስ ሚዲያ ፊሽካ ነው። ዖኤምኤን! ሌላው ደሞ ብዙ ያስመሰላችሁ የስራአጡ ቁጥር ነው። ይህ ስራአጥ የቦዘኔ መንጋ ዛሬ ለጃዋር ነፍስ የሚያጠፋ ተወርዋሪ የጽልመት ወታደር ነገ ደግሞ ስራ አግኝቶ ወደአይምሮው ሲመለስ መልሶ ጃዋርን አራሱ ይሰለቅጠዋል። ይቺን ታጣለህ እንደው?
በነገራችን ላይ “ኢትዮጵያዊ የሚባል ….ሰልካካ….” ያልካት እኮ የናንተ አክራሪ የዖነጎች ሚጢጢዬ አስተያይ ነው። ቀሺም አረዳድም ነው። አነጋገርህ ውስጠ ወይራ ሌሎችን እናንተ “መከራ የምትበሉላቸው ” እነ ነገደ ቅማንትን ፣ ወይጦን፣ በአማሮቹ ወንድሞቻችን ላይ ለማሰር የምትመዙዋት የመከፋፈያ ሀረግ ናት። እያደር ምስጢሩ ሁሉ እየወጣ እየተደመምን እኮ ነው። አልተረዳህም እንዴ አባጫላ? የኛ ኢትዮጵያውያን የ “ኢትዮጵያዊነት” አረዳድ ያለውን ህዝብ ብቻ ሳይሆን እንስሳቱንና እጽዋቱንም ጨምሮ ነው እኮ። ለዚህም ነው እነ ብርቅዬ ዋልያና ማኛ ጤፍ ሁሉ ብርቅዬ ኢትዮጵያውያን ናቸው የምንለው። ነው እናንተ የአፍንጫ ስንደዶነት ላይ ቀራችሁሳ። ያቺ ደግሞ መከረኛ “ኩሽና ሴም” ተብሎ ከነ አቦይ የተቀበላችሁት አዲሱዋ የመከፋፈያ ስንኝ መሆኑዋ ነው። ቀሺሞች። ለማንኛውም እመነኝ ሀገረዖሮምያ ብሎ ነገር የለም። አይኖርምም። ዖሮሞን ከመሰረታት ሀገሩ ኢትዮጵያ እንኩዋንስ የዘመኑ የላፕቶፕ ፊሽካዎች ቀርታችሁ ሀያላኖቹም ለዘመናት ሞክረው አልተሳካላቸውም። ለመሆኑ የወጣለት አናሊስት ነው። ምሁር ነው የምትለው ጁዋር አብሮ “ደቦ የሚወጣውን ፣ ወይም ” “ደረባ ” የሚያድረውን ጎረቤቱን፣ የገዛ ወገኑን በፈጠራ ድርሰት አገዳድሎ ሲያበቃ ፍሪዳ አርዶ ያበላው አይደል? ይህ ነው የናንተ ዖሮሙማ ሰበካ። ዳሩ ምን ይጠበቃል በጫት ከነፈዙ “ምሁራን” ። ደሞ በስለሰው ልጅ ጠፈር ምጥቀት ባትጀምረውስ ክርክርህን? እጅግ አሳዘንከኝ። ሰላም ሁን ባለህበት እኛም ሰላም እንድናገኝ።

 1. Abba CaalaNovember 10, 2019 at 10:37 pm

አባዊርቱ፣ አንድ በጣም የሚያናድድ ነገር ቢኖር፣ ከሃበሾች የደቦ ፕሮፓጋንዳ የቀራረምካትን ዕውነት ነው ብለህ እንደቅዱስ መጽሃፍ የምታምናትን ጥራዝ ነጠቅ እውቀት፣ ሌሎች እንዴት ሊያዩት አልቻሉም ብለህ መመጻደቅህ ነው! “beekaan wanna dubbatu beeka; gowwan wannuma beeku dubbata” jedha Oromon. አንተ በሃበሻ ድስኩር እንደታወርከው ሳይሆን ስለኦሮሞ ማንነቴ፣ ገባርነት ኦሮሞ ላይ መቼና እንዴት እንደተጣለ፣ ገና ትምህርት ቤት ሳልገባ ያወቅሁ፣ የኃይለ ሥላሴን ሰው በላ የገባር ስርዐት ባይኔ ያየሁ፣ የደርግ እና የወያኔ መንግስታት ኦሮሞን በኦሮሞነቱ ብቻ ለይተው በጅምላ ሲያፈናቅሉት፣ ሲያስሩና በግፍ ሲገድሉት በግዛ ዘመዶቼ እና ጓደኞቼ ላይ የደረሰ፣ ባጠቃላይ እስካሁን ያሉ የነፍጠኛ (በጠብመንጃ ሃይል የሚገዙ) መንግስታት እኔንና ህዝቤን ለድህነትና ለሰብዐዊ ሰቆቃ የዳረጉ ስለሆነ፣ ያንተ ተራ የአማራ ኒኦ ፋሽስቶችን ድንፋታ እንደገደል ማሚቶ ማስተጋባትን ከቁብ የሚቆጥር ሰው አይደለሁም!!
እናም “ኦሮሞ የሚባል ብሄር የለም” ወይም “ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድ ነው፣ ተዋልደናል፣ ተጋብተናል” የሚለው ዲስኩር ኦሮሞን ነጥሎ ከመጨቆንና ከመበዝበዝ፣ ብሎም ይህ ለምን ይሆናል የሚል ጥያቄ ያነሱትን የኦሮሞ ልጆች ያለርህራሄ ከመገደልና ከመሰቃየት አላዳነም! ቢያንስ ካለፉት 40 አመታት ጀምሮ እስከዛሬ የተደረገ ያለውን፣ በጨቋኞች ልፈፋ ካልታወርክ በቀር ሁሉም በገሃድ የሚያየው ነው! ባንተ ቤት ላለፉት 4ና 5 አመታት የኦሮሞ ወጣቶች እስካፍንጫው የታጠቀውን የአጋዚ ጦር ባዶ እጃቸውን ተጋፍጠው ውድ ህይወታቸውን የሰውት ጭቆና አንገሽግሾአቸው ነው እንጂ ሞት አምሮአቸው ወይም ለአድቨንቸር አልነበረም! አንተ ግን “የራስን ታሪክ መሳት” ትለዋለህ!
ይባስ ብለህ፣ ተደራጅተውና ታጥቀው የሚጠብቁ የአብን ተቀጣሪ ነፍሰገዳዮችና የነፍጠኛ ርዝራዦች፣ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ወጣቶች ላይ በመዝመት የፈጸሙትን ጭፍጨፋ፣ የቀጣሪዎቹ ሃብት የሆኑ አብዛኞቹ የሃብሻ ማስ ሚዲያዎች አዙረው ኦሮሞን በጅምላ ለመኮነንና ለማስኮነን የሚያደርጉትን አንድ ወጥ ፕሮፓጋንዳ “ነፍሰ ገዳዮችንና አራጆችን ኢትዮጵያዊነት ላይ አሠማራችሁ” እያልክ ታስተጋባለህ! ከዚህ የባሰ ቱልቱላነት አለ?? ለነገሩማ አንተም በኦሮሞ ላይ ለመዝመት ዝግጁ መሆንህን ገልጸህ በቶሎ እንዲያዘምቱህ የበላዮችህን ስትማጸን ነበር!
በዚህ ከጠመንጃ አፈሙዝ አልፎ ማሰብ የማይችል አዕምሮህ፣ አማራን በኢትዮጵያዊነት ባንድ በኩል፣ ኦሮሞ፣ ቅማንት፣ ወይጦ፣ ወዘተ በሌላ አስቀምጠህ በጨፍጫፊነቱ ከሚፎክረው የአማራ ልዩ ሃይል (ፋኖ) ጋር ተሰልፈህ የጭፍጨፋው ሰለባዎች ላይ አብረህ ማቅራራት አማረህ!
እዚህ ላይ “እውነተኛና ውሸተኛ የሆነ ዖሮሞ ብሎ ለመወሰን”፣ “ኢትዮጵያን አታውቁም፣ ዲዘርቭም አታረጉዋትም።” ብለህ መቀባጠርህ የምን የሚሉት ነው? እነዚያ የምትጮህላቸው ወገኖች ምን እያጠጡህ ነው?? ኦሮሞነትንም ሆነ ኢትዮጵያዊነትን የሚወስነው ማነው?? እናንተ? ቅዠታችሁ ከልክ አላለፈም?? እንኳን ስለኦሮሞና ኦሮሞነት ቀርቶ እሞትለታለሁ የምትለውን ኢትዮጵያዊነትን ከመፈክርና ቀረርቶ አልፈህ በቅጡ አታውቀውም! “አንዲት ኢትዮጵያ ወይም ሞት!” ለማለት ግን የሚቀድምህ የለም። Little knowledge is dangerous የተባለው ለአንተ አይነቶቹ ነው!
Sorry, I know, trying to bring prejudiced and opinionated people to their senses is a waste of time!
Nagaatti!

 1. አባዊርቱNovember 11, 2019 at 7:07 am

አስቀድሜ ሳተናዎችን ይህ አርስት ከዚች ቦታ ፈቅ እንዳይልብኝ በትህትና እለምናለሁ። ፒን አርጉልኝማ።
ይህን የተወናበደ አንጋች እስቲ ልንገረው።

አባጫላ በመጀመርያ የጃንሆይን መንግስት ማየትህ ትንሽ ተስፋ ሰጥቶኛል። ለምን እንደምል ግን ላትረዳ ትችላለህና ልለፈው። ብዙ ነገሮችን ነካክተሀልና ከዬት እንደምጀምር ያስቸግራል ኖት መውሰድ ሊኖርብኝ ነው። እስቲ በጥቂቱም ቢሆን እንዲህ ልበል አንብቤህ ካስታወስኩት። ትረዳለህን እንኩዋ አላልመውም። ይውጣልኝ ለማለት እንጂ።

፩) ዖሮሞ በዖሮሞነት ስለመጨፍጨፉ
በወያኔው ስራት ይህ መሆኑ፣ ሌላው ቢቀር እስር ቤት በሙሉ መግባቢያው ዖሮሚፋ ስለመሆኑ ድፍን ወገን ያውቀዋል። ታድያ እኮ ይህንን ያረጉት ዛሬ መቀሌ እየተመላለሳችሁ የምታሸረግዱላቸው ነፍስአባቶችህ እነ አቦይ እንጂ እናንተ አክራርያን የምትከሱዋቸው ደሀው የአማራ ልጆች አይደሉም። ለነገሩ ኦህዴድ ይሁን ባእዴን ያው የወያኔዌቹ አገልጋዮች ስለነበሩ ተጠያቂዎቹ ህውሀቶች ናቸው። ኸረ በፈጣሪ ትዝብትን ፍራ ፈጣሪን እንኩዋ ባትፈራ። እነ በቀለ ገርባ ያንን አስከፊ የነ አቦይን ገፈት ቀምሰው ተመልሰው ሄደውም አይደል እንዴ የወያኔን ጫማ በአደባባይ የሚልሱት? ተው እንጅ አታናግረኝ። ላስታውስህ እስቲ በተመሳሳይ ጉዳይ እዚሁ ቤት ያወጋነውን። ምን ብለኽኝ ነበር እነ ኦቦ ዳውድ በመቀሌ አምባሻ ተቁዋድሰው ሰራዊታቸውን አስባርከው ያለፉ ጊዜ? ካልጠፋ ኬላ? “ይህ መንግስት ለፖለቲካ ፍጆታ ሸውዶን ነው። ፎቶሾፕ ነውና አትመን አላልከኝም? ” መረጃው አለኝ እኮ እዚሁ ሳተናዎቹ ቤት። ከወራት በሁዋላ ጉዋዶችህ እነ ሊቁ ህዝቅኤል ሳትቀሩ መቀሌስ ተመልሳችሁ ስታሽቃብጡ የነበረውን በቲቪ ያየነውን እሱም ፎቶሾፕ ይሆን? ህዝቅኤልስ በምርቃና ነው እንበል፣ የበቀለ ገርባው ፣ ያንን መከራ ያየ ሰው እንደምን ወስፋቱ አብሮ ውስኪ ለመቃመስ እሺ አለው? እኔ የማውቀው ዖሮሞ ያሳደጉኝ ወላጆቼ ይሁን ዘመዶቼ አናረገውም። በወያኔ ስርአት አፈር የሆኑት ህጻናት ደም ይፋረዳችሁዋል። አይቀርም ደሞ።
፪) ስለ ዖሮሞ ብሄርነት ትግል

ነገሩን አጣመምከው እንጂ ዖሮሞ የለም አልነበረም አቶ አበበም ያለው። ዖሮሞነት ያለኢትዮጵያዊነት ምንም አይደለም ለማለት እንጂ ። አንተ እኮ RIP Ethiopia ያልክ ደፋር ነህ። አንተ ስላልክ የሚሆን እንኩዋ ባይሆን በብዙ ሚሊዮኖች የሚያፈቅሩዋትን አገረ ኢትዮጵያ እንዲህ ማወራረድ የበጎ አይደለም። ደሞስ ከጠሉዋት ወጥቶ መኖርም ይቻላል እኮ ሞቱዋን ከመመኘት። የኔን ጥራዝነጠቅነት አቆየውና በመጀመርያ በሀገርና ብሄር መካከል ያለውን ልዩነትና አንድነት ደግመህ አጢነው። ዖነግን የምኮንነው ስለ ዖሮሞ ህዝባችን እኩልነት ፣ የስራ ይሁን የቁዋንቁዋ፣ የእኩል እይታን ሆነ ተከባብሮ ብልጽግናን ከልቡ ቢታገልማ ስንት ተከታይ ይኖራችሁ ነበር። ዳሩ አካሄዳችሁ ለዖሮሙማ ምንም የማይፈይድ፣ የወጣችሁበትን ህዝብ ነፍስና ንብረት የምታጋዩ፣ መንግስትን በዴሞክራሲ ሳይሆን በሽብር ለመቆጣጠር የምታድክሩ ዘመናዊ ሽፍታዎች በመሆናችሁ ነው። ማስረጃ ትፈልጋለህ? ስለምታውቀው ይቅርብኝ

፫) በአጋዚ ስለተጨፈጨፉት ልጆቻችን
ይህ ግርም የሚል ነው። አጋዚ ዛሬ እጉያቸው ገብታችሁ የምትርመሰመሱት ሰዎች ናቸው ወይስ አማራዎቹ ሊሆኑ ነው? አጋዚማ አዋርዶን ከፊሉን አገርቤት ያሉትን ምርኮኛ አርጎ በሎሌነት 27 አመታት ከተገለገለባቸውም በሁዋላ ዛሬ ደሞ የትግል ጓዶችህን የምስራቅ አፍሪካ ቱሪስት ጄኔራሎችን ከስደትም መጥተው እየተገለገለባቸው አይደል እንዴ? አታናግረኝ እንጅ! እንደውም ምን ሰይጣን ቢሆኑ ስራቸው ድንቅ ነው። ያን ሁሉ የዶ/ር መአት ከመቀሌ የሚዘውሩ። ዖሮሞ የተባልንን ሁላ አንገታችንን እንድናቀረቅር አረጋችሁን እኮ። እንደ አንድ ዖሮሞ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ሁሌ እንደተቃጠልኩ እስከወዲያኛው አሸልብ ይሆናል። ለመሆኑ ዛሬ አጋዚ የለም፣ አቢይ አጋዚ መስለው ካልታዩዋችሁ በቀር። ምን ጎደለና ነው ልጆቻችን መንበሩን ይዘው ስራ አላሰራ እያላችሁ እንዲህ አገር የምታምሱት? ስንት ስለወገናችን የሚወራና የሚሰራ ጠፍቶ ነው? አቶ በቀለ ሆነ ዶር ተብዬው ገመቹ እንዲህ የወረደ አነጋገርና አስተሳሰብስ ምን የሚሉት ነው?። ተሳቀብን እኮ አባጫላ። አያቃጥልህም? ዳሩ አቶ በቀለንም ልትሆን ትችላለህና በከንቱ መድከሜ። ደሞ ኢዜማ ከመቼው ጉልበት አበጀና ነው የሚጨርሰን? በሀቅ ምርጫ ተብዬዋን ማሸነፉ ሊቸግር ነውና ሁሉን ጥላሸት እንቀባ ያውም በሽብር ካልሆነ በቀር።

፬) አብን ዖሮሞን ስለመጨረስ

አንብቤአለሁም፣ ስምቻለሁም ፣ ይህ ደሞ ለኔ አዲስ ነው። የአብን ልጆች ወህኒ መማቀቃቸውን ግን ሰምቻለሁ እንጂ የዖሮሞን ልጅ ሲገድሉ አልሰማሁም። ካደረጉት ድፍን ኢትዮጵያዊ ሊፋለማቸው ይገባል። ያውም ቆፍጣናው ለማ መከላከያ ሆኖ ነው ይህ የሚሆነው ወይስ ለማ የፋኖና አብን ተጠሪ ነው ልትለኝ ነው? ይቺ ያው የፈረደበትን ሁለቱን በሀዘንና ደስታው አብሮ የኖረውን ህዝብ ለመለያየት አዙሮ የማያይ ስራፈት የፌስቡክ ትውልድን መሰብሰቢያ ዖነግ ጥላ ስር ካልሆነች እውነትነቱዋን እጠራጠራለሁ። ማስረጃ አምጣና አሳምነኛ። ሀሜት አልወድም።

፭) ስለዖሮሞነትና ኢትዮጵያዊነት

በመጀመርያ የማውቀው ዖሮሞነት እንኩዋንስ የሰው ህይወት የእንሰሳ፣ አእዋፍና እጽዋትን “ነፍስ” የሚታደግ ፍጹም ርሁርህ ማንነት ሆኖ ሳለ ይህ የጽልመት ሎሌ ጁዋር ባስነሳው ግርግር ይህ ሁሉ ነፍስ ሲጠፋ ከ ታዬ ደንደአና መረራ ጉዲና በቀር ማን ተነፈሰ? አንተስ ብትሆን እዚችው ቤት ስለጁዋር ሊቅነትና አናሊቲክ ማይንድ የምትነግረን እውነት ዖሮሞ ነህ? አዎ በትውልድ ልትሆን ትችላለህ ፣ በባህሪ ግን ሲያልፍህም አይገኝ። አሳዛኙ ክስተት ግን ነኝ ብለህ ማመንህ ነው።

በመጨረሻ አባጫላ እስቲ ልጠይቅህ፣ ለመሆኑ እናንት አክራሪ ዖነጎ ልጆች እስቲ አገር እንዲህ እየተተራመሰች፣ እንዲህ በግልጽ በሽብር ተነክራችሁ፣ ምን ልትፈይዱለት ነው ለደሀው ህዝባችን? ደሞስ ከጎረቤቱ እያዋጋችሁ እርስ በርስ እንድንጨካከን በማድረግ ዬትኛውን የዖሮሙማን ማንነት ልታጎለብቱ ነው? ህዝቡ የሆነ ህዋ ላይ እንዲኖርላችሁ ነው ወይስ እውነት አብሮት ከኖረው ህዝብ አለያይታችሁ ፣ አቃቅራችሁ የጎሪጥ እየተያዩ ልጆቻችን እንዲያድጉልን ነው? ምነው ሰፉ ጠፋ? ሀይ ባይ የሚል አባገዳም ጠፋኮ አብሯችሁ የሚያዳንቁ ብቻ። በልጅነቴ የአዛውንትን ምክር እንሰማ ነበር። አሁን አሁን ምክሩም የለ፣ አዛውንቱም አለቁ መሰለኝ። የተቀረነውን ለመከራ ማን ሊሰማን? እኛ አቶ ቡልቻን እንዴት እንደማስባቸው። ምነው ከ25 አመታት በፊት በሆነና ልካችሁን ይነግሩልኝ ነበር። ግራቀኙን ባየው አንድ አዛውንት አጣሁ። አሳዛኝ ዘመን። አቢይንም ይመክሩልኝ ነበር ጉልበቱ ባይከዳቸው። ለማንኛውም ክፉ አይንካህ፣ በህይወት አቆይቶህ ግን ኢትዮጵያ እንደማትሞት ፈጣሪ ያሳይህ። ስለ ቅማንትና ሌሎች ወገኖቻችን እስቲ ለነሱ ተውላቸው። ማ ይሙት የቅማንቶች ጉዳይ ጨንቆህ ነው? አቶ ጌታቸው ረዳ እንደጨነቀው? እውነትም ጥራዝ ነጠቅ ነኝ ይህ እንኩዋ የማይገባኝ ገልቱ። አቲስ ናጋን ናተኢካ ዬ ኦቦጫላቶ። ጋሩ ያድኒኬ ካንቢራ ታኤቱ ማሌ ዋዬ ዋራ ቂማንቲ ታናፍ ፎጋልታኒ ሂንቤኩ ጄቴቱ ? ዋልሻኪና አቤ? ሜ ዱቢ ሲቲንዴ’ራቹ……..

 1. TesfaNovember 11, 2019 at 12:38 pm

Abba Caala – The comments you post on several sites are so demented and divisive and one sided. Yet, you proclaim to know it all in the name of the Oromo People. What is clear is you are shortsighted and shallow. You keep lamenting on something that may have happened many years back. yet, you fail to denounce the killings of our brothers and sisters by lumpens roaming the streets of Ethiopia. Standing up for the rights of the Oromo people also respects the rights of others. You can’t have peace and tranquility while your next neighbor is suffering by the hands of the hooligans of the Oromo youth.
You tell us “Sorry, I know, trying to bring prejudiced and opinionated people to their senses is a waste of time!” yet, you completely missed to see yourself. Always pointing to others to be the source of conflict and headache. Examine yourself, get checked your head, find out if there is any medication that will cure you from your narrow and twisted mind of divisive politics. Stop being drunk with ethnic politics. You have pointed out in one of your lengthy and rubbish comments about being pure Oromo. I assure you there is no “pure Oromo” for that matter no one on the globe is pure race. It is a sick mind that tells you such pointless facts. Ethiopia is a woven society from all different tribes, ethnics, and languages. If any ethnic group in the country claims to be “pure” I suggest prove it to us via a DNA test. The fact is you and your kinds are trying to destroy the very fabric of our society along ethnic lines. You will fail. The country’s unity will emerge much stronger than before. As one of the morons wrote “RIP ETHIOPIA” will never happen. Your hatred and divisive idea will die with you and Ethiopia and its people will rise up sooner than later. Think Globally. Stop pitting our people to kill each other while you are enjoying a peaceful life outside Ethiopia. If anything, go there and be part of the solution!

 1. አባዊርቱNovember 11, 2019 at 7:44 pm

የመጨረሻ የምልህ ነገር ቢኖር ሁለተኛ “አበሾች” እንዳትለኝ። ኢትዮጵያዊ ነኝ። ስሙን ላለመጥራት አበሻ የምትለዋ ለአንተ አይነቱ አገርጠል “ራቶፍቱ” ይመች ይሆናል። ለኔ ግን በግሌ ስድብ ነው። ወዳጆችህ ጀርመኖቹ (ሁሌ ታጣቅሳቸዋለህና) ማን ብለው ይጠሩህ ይሆን? መቼስ አባጫላ አይሆንም። ከታደልከው ኢትዮጵያዊው ይሉሀል፣ ከተረገምክ ደግሞ ጥቁሩ ሰው ወይም የማልጠቅሰውን ስም መሆኑን አትዘንጋ። ለይተህ ጀርመኖቹ እንኩዋ ደፍረው የማይሉንን “አበሾች” አንተ ስትጠቀምበት ማየቱ እራሱ እጅግ ያሳዝናል። እኔስ ፖለቲካውን እንዳንተ ጥርስ ባልነቅልበት “ጥራዝነጠቅ” ልሁን፣ ያንተው ደግሞ የለየለት ገልቱነት መሆኑም አይደል? ይህን ነው ነውኮ የዖሮሞነትን ጸጋ አልተላበስክም የሚያስብለኝ።
ይቅርታ አቶ አበበ። መስመር ስቼ ወደሌላ ወሰደኝ ይህ ግለሰብ። አሁን ጨርሻለሁ። በሌላ ጉዳይ ያገናኘን አባጫላ። ናጋቲ።

ኦሮሚያ ለሚባል ምናባዊ አገር ምስረታና ኦሮሞ ለሚባል ማንነት ፈጠራ እረፍት የሚያጡ ኦሮሞ ወገኖቼ ጉዳይ

10 Comments

 1. I read the comments listed above. I would like to tell one fact to our Abyssinian brothers. The Habasha elites always wanted to deny facts. These arrogance emanates from the aspiration to keep Oromo as it has no own identity, country and culture and language. I read that Oromos migrated to its present day country from around Borana. But, this what the Abyssinian clergy and dabtera historian used to tell for long. However the true history of Oromo origin is generally North eastern Africa extending from Egypt to Meroe, Napata and finally reached today’s northern Ethiopia where they lives with other Cushitic people like, Kunama, Beja, Saho, Tige, Irob, Affar, and the like. They gradually expanded their territory to the current day of Borana and then up to Tanzania and the lakes region. This being the fact, Habesha political elites wanted to tell the public that the Oromos came to current day Ethiopia from southern part. This is totally false. Historical evidence of place names and archaeology confirms that the Oromos lived in Gondar, Tigray and other northern parts long ago. Some of the place names have Oromo meaning like Wal Duubaa (Waldibba), Ona, Warra Lakee, Aadde Guddoo, and many others (in Tigray)as well as many place names in Gojam, Gondar have so many Oromo names. Do you think that these place name came by miracle? Not all. I am saying this to ell to the Habesha elites who intentionally deny Oromo being as one of the indigenous people of the North east Africa. You can refer historical facts for example between the Abbaa Gadaa’s Kallacha and the top of the Axum stelae. Secondly, as L. Tsegaye G/Madhin put is the name Axum came from Aak Sumaa, meaning “it is you”. I am not telling this that oromo claims all places with the name having Oromo meaning but to tell that had this people [Oromo] didn’t live on these areas, these names didn’t have come. So, instead of basing our analysis on hearsays, let us focus on the historical facts that took place thousands of years ago. One of the writer wanted to say that there is no Oromo and Oromia as such. This pure arrogance. Oromo existed long, long, ago and the name Oromia is coiled by Oromo freedom fighters as the name Ethiopia is coiled from the word of Greek by Abyssinian rulers hindered years ago after they left saying Abyssinia being advice by their European adviser, (French adviser)who told Minilk to use the name Ethiopia to the newly conquered territories than sticking to Abyssinia. The French advisor told Minilik that if you call the current coutry as Abyssinia, you will face challenge as most of the people incorporated to your former Abyssinia were not Habeshas. So, Minilk took the advice and named the territory he colonized and added to Abyssinia as Ethiopia. I thin this being the fact that we know, why do we always deny facts and want to tell the false narratives. False narratives will take us nowhere. confessing the real history is the only way that positively contributes to current day Ethiopia’s people to live together peacefully. Otherwise, the likelihood of disintegration is very high as today is not yesterday.

 2. Now every body should be clear that there are Oromo brothers and sisters who are really genuine and want to live with other people keeping their identity and respecting the identity of others; yet others claim that they are Oromo and struggle for the betterment of the Oromo but want to clear all other people and want to live alone!! Both are our people if they struggle around the table, the problem is that the latter uses force showing that their mind is empty; they relay on the muscle and gun! So, let us organize and fight accordingly.

  I don’t see other solutions! only fight accordingly; and will see the winner.

 3. The following was my last reply on Satenaw:
  Abba Caala November 13, 2019 at 1:58 am

  ያልሰማሁትን ምን ትነግረኛለህ አባ? እንተ እና መሰሎችህ እየተነዳችሁ ያላችሁት በአክራሪ የአማራ ኒኦ ፋሺስቶችና የቀድሞ ሥርዐት ናፋቂዎች መደዴ ፕሮፓጋንዳ ነው! ከጅምሩ ፕሮፓጋንዳ ደግሞ የማደናገሪያ ፖለቲካ እንጂ የታሪክ ማስረጃ አይደለም። አንድ እና አንድ ሶስት ነው ሲሉህ ትክክል!፣ ሌላ ግዜ ደግሞ አንድ እና አንድ አምስት ነው ሲሉህ እሺ! ካልክ ጥፋቱ የፕሮፓጋንዲስቱ ሳይሆን የአንተው የአዕምሮ ብስለት ማጣት ነው! እኔ ሁሉንም የፕሮፓጋንዳ ምንጭ ተከታትዬ በማስረጃ ላስተባብልልህ አልችልም! ሆኖም ባነሳሃቸው አንዳንድ ነጥቦች ላይ ታች የምለው ይኖረኛል። ከዚያ በፊት ግን አንዳንድ ጭብጦችን ማስገንዘብ እወዳለሁ።

  በአሁኑ ሰዐት 90% የኢትዮጵያ ሜዲያን (መንግስታዊ ተቋማት እንኳ ሳይቀሩ) ተቆጣጥረውት ያሉት አክራሪ የአማራ/ኢትዮጵያዊ ብሄረተኞች፣ አሃዳዊነትን ቢቻል በፕሮፓጋንዳ ዉዥንብር አሊያም በሃይል ለመመለስ ግዜው አሁን ነው ብለው ታጥቀው እንደተነሱ በሰፊው እያየንና እየሰማን ነው። የነዚህ በአንድ ላይ የተሰለፉ የፕሮፓጋንዳ ቧንቧዎች፣ ስለሃገሪቱ ፖለቲካ ውዥንብር ከመንዛት አልፈው፣ ከደማቸው ከተዋሃደው የኦሮሞ ጥላቻ በመነሳት ኦሮሞ ተረኛ ሆነ በማለት የኦሮሞን ወጣት ትውልድና የኦሮሞን ህዝብ በጅምላ ለማዋረድንና ስሙን ጥቁር ለመቀባት በዐለም ዙሪያ ያቅማቸውን እየደከሙ ነው። በዚህ የፕሮፓጋንዳ ጦርነት፣ የፖሊቲካ ጨዋነትን እንኳ እርግፍ አድርገው ትተው፣ ድሮ የተረሱትን ቃላትና ዘረኛ ስድቦች በገሃድ ማዥጎድጎዱን ተያይዘውታል። ዘረኛ አባባሎች በመደበኛ ሚዲያ መጠቀም ከተጀመረ ደግሞ፣ ፋሺዝም ሩቅ አይደለም! እነዚህ አካላት በውሸት ፕሮፓጋንዳ መንግስትን በማዳከም፣ አሊያም ህዝቡን በማጫረስ፣ ባቋራጭ የሃገሪቱን በትረ ሥልጣን ለመቆጣጠር አሰፍስፈዋልና ነገሮችን በጥሞና ማስተዋል ያስፈልጋል፣ ባይ ነኝ።

  ባላምንበትም፣ አንተን የሚያስቆጣህ ነገሮችን ጠልቆ ካለማየት ነው ብዬ ልውሰድ! ከሆነ ደግሞ፣ የነቀፋችሁ መነሻ ባብዛኛው ነገሮችን ባግባቡ ካለመረዳት፣ ከፈጠራ ወሬና የሃሰት ፕሮፓጋንዳ የመነጩ ትርክቶችን ዕውነተኛነት ሳታረጋግጡ እንዳሉ ወስዳችሁ የፖለቲካችሁ ተቀናቃኝ የሚትሉትን ስለምትወነጅሉበት፣ “አልፎም ከኛ አስተሳሰብ ውጪ እውነት ሊኖር አይችልም” በሚል እብሪት ወይም አላዋቂነት ሌላውን ስለምትከሱ ነው። ይባስ ብሎ ደግሞ የኢትዮጵያዊነት መለኪያው ምን እንደሆነ ሳትገልጹ (በውስጠ ታዋቂነት አማርኛ ተናጋሪ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ) ራሳችሁን የኢትዮጵያዊነት ሰጪና ከልካይ አድርጋችሁ የኛን አስተሳሰብ የማይደግፍ ሁሉ ኢትዮጵያዊ አይደለም የምትሉ ወይም እናንተ ብቻ (እነማን እንደሆናችሁ የማይታወቅ) ለሃገር ለወገን ተቆርቋሪ ሌላው ግን ሃገር አፍራሽ፣ ገንጣይ፣ የአረብ ቅጥረኛ፣ ወዘተ እያላችሁ የደርግን ያረጁ መፈክሮች ስትደግሙ ትውላላችሁ። ሥራችሁ ዝም ብሎ ብቻ እኛ ኢትዮጵያዊ ‘ጥሩ’ እናንተ ‘መጥፎ’ የሚል አይነት የበጎች ምልልስ ይመስላል።

  ከዚያ ይልቅ፣ ደረጃውን የጠበቀ፣ በማስረጃ የተደገፈ፣ ለዘመኑና ላለንበት የፖሊቲካ ዉስብስብ የሚመጥን አረዳድና ትንታኔ ማቅረብ ያስፈልጋል። በመንደር ወሬና በካድሬዎችን ፕሮፓጋንዳ ተሞልቶ የሚደረጉት እንካ ስላንትያ ከራስ ህመም ውጪ ፋይዳ የላቸውም።

  1.
  “ዛሬ መቀሌ እየተመላለሳችሁ የምታሸረግዱ” ብሎ የሚደጋግማት የካድሬ ድስኩር አባዊርቱ ከዬት እንዳገኘው አላውቅም። “እናንተ” ብለህ የምትከሠው እነማንን ነው? አንድ ሰው መቀሌ ቢሄድ መብቱ ነው፣ ከመቼ ወዲህ ነው መቀሌ ለመሄድ ፓስፖርትና የእናንተን በጎ ፈቃድ የሚያስፈልገው? መቀሌ የማይኬድበት የወንጀለኞች ዋሻ ከሆነ፣ እዚያ ያሉትን ዋነኞቹን ወንጀለኞች ለምን አታሳድዱም? ወይስ ወንጀለኛ መሆን የሚችለው ኦሮሞው ብቻ ነው?? “በወያኔ ስርአት አፈር የሆኑት ህጻናት ደም ይፋረዳችሁዋል” እና ትግሬን አታናግሩ የምትል ከሆነ ደግሞ፣ ከሣህለ ሥላሴ ዘመን ጀምሮ ኦሮሞን ሲጨፈጭፉ ከነበሩት አማራ የተወለዱትን ሁሉ ላናናግራቸው ነው ማለት ነው? ኦሮሞን ያልጨፈጨፈ የኢትዮጵያ ገዢ መደብ አለ??
  2.
  “ዖሮሞነት ያለኢትዮጵያዊነት ምንም አይደለም” የሚለው የተገላብጦሽ ነው! ይህ ነው ቅጣምባውን ያጠፋባችሁ! ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ባይኖሩም ኦሮሞና ኦሮሞነት ይኖራሉ! አማራነት፣ ትግሬነት፣ ዎላይታነት፣ ሲዳማነት፣ ወዘተ ይኖራሉ! ኦሮሞነት ከኦሮሞ ቤተሰብ ወይም በደም፣ በቋንቋና ባህል ከተሳሰረው ከዚህ ማህበረሰብ ውስጥ በመወለድ የሚገኝ አባልነት ሲሆን፣ ኢትዮጵያዊነት ግን ዜግነት ነው። ዜግነት ደግሞ በአንድ ልዑላዊ ሃገር ህገ መንግስት ላይ በተደነገጉ መስፈርቶች መሰረት የሚገኝ አባልነት ነው። (Understand the difference between nationality and citizenship! One can be an Oromo national but a Kenyan, a US or a British citizen. You can change your citizenship, but not your nationality.)

  3.
  አንድ ህዝብ ለነጻነት የሚታገለው ያለበትን ሃገር ስለጠላ ሳይሆን፣ በሃገሩ የሚደርስበትን ጭቆናና ብዝበዛ በመቃወም ነው። ነጻ አውጪ ድርጅት ማቋቋም፣ እንደእግር ኳስ ክለብ ለመደሰቻና ግዜ ማሳለፍያ ተብሎ አይደለም። ከመጀመሪያው ለትግል እንዳይነሳሳ ለማድረግ ደግሞ ጭቆናና ብዝበዛውን ማስወገድ እንጂ የመብት ጥያቄ እንዴት ታነሳላችሁ፣ ተናቅን ተደፈርን ብሎ መፎከር አይደለም መፍትሄው! ይህ ጭፍን የአምባገነኖች መንገድ ኢትዮጵያን ዛሬ ከምን እንዳደረሳት እየታየ ነው። አሁንም ቢሆን የኦሮሞ ህዝብ ተበደልኩ ብሎ ሲነሳ፣ ምንድን ነው የተበደልከው አይደለም የናንተ ጥያቄ። ምን ተደርጎ፣ “የመልዐክ ወንድም የሆኑ እምዬ ምንሊክ” እንዴት ስማቸው በክፉ ይነሳል?! አካኪ ዘራፍ ነው የምትሉት! “ታሪካችሁን የማታውቁ፣ የናት ጡት ነካሾች” እያልክ አይደል አንተው ሁሌ የምትረግመን? ለምን ዝም ብሎ ባርነት አይሸከሙም ነው ክርክራችሁ! ለምን ለህዝብህ መብት ተከራከርክ ብሎ በሃጥአተኛነት መፈረጅ የጨቋኞች ቋንቋ ነው!
  4.
  ማንም ተራ ወንጀለኛ ሲያጠፋም ሆነ፣ የደህንነት አካላት በሚሸርቡት ሴራ የሰው ህይወትና ንብረት ሲጠፋ፣ እዚያ አካባቢ ኖረም አልኖረ፣ ወንጀሉን የምታላክኩት ‘ኦነግ’ ላይ ነው! ከመንግስት ተብዬው የዘራፊዎች ክበብ የበለጠ፣ ከኛ ሌላ ኢትዮጵያዊ ላሳር የምትሉ ትምህክተኞች፣ ህዝባቸውን ከጭቆና ለማላቀቅ የሚታገሉትን ሁሉ የአምላክን ህግ እንደጣሱ ሰይጣኖች ትቆጥራላችሁ፣ ትጠላላችሁ! ለዚህ ነው ሁሌ አፋችሁን በከፈታችሁ ቁጥር ‘ኦነግ’ እና የመሳሰሉትን በጭራቅነት የምትስሉት!
  OLF ግን የኦሮሞ ህዝብ፣ አልፎም የተጨቆኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች ከጥቁሮች ቅኝ አገዛዝ ወጥተው፣ የራሳቸውን የወደፊት ዕጣ በራሳቸው የሚወስኑበት ነጻነት እንዲገኝ ረጅምና የተቀደስ አላማ አንግቦ ከጨቋኞችና አምባገነኖች ጋር በመፋለም ብዙ መስዋዕትነት የከፈለ፣ እየከፈለም የሚገኝ የህዝብ ድርጅት እንጂ እናንት የጨቋኞች አፈቀላጤዎች የጌቶቻችሁን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እንደበቀቀን የምትደግሙበት የራሱን ህዝብ የሚያሸብር የወንበዴ ቡድን አይደለም!! ኦነግ በናንተ የጦርና የፕሮፓጋንዳ ጋጋታ ወይም ዕርግማን፣ ሴራም ሆነ ስም ማጥፋት የማይወገድ የኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ፈለግ ነው! ኦሮሞ ከጭቆና ሳይላቀቅ ኦነግ አይጠፋምና አትልፉ!

  በይበልጥ ግን የኦሮሞንና የመሪ ድርጅቱን ስም ጥላሸት እንቀባለን በሚል ሰበብ የምታራግቡት መጠነ ሰፊ የማያባራ የውሸት ፕሮፓጋንዳና ዘረኛ ስድቦች በህዝቦች መካከል ሊኖር የሚገባውን ጤነኛ ግንኙነት ከፉኛ በመመረዝ፣ አልፎም ዱሪየዎችንና ነፍሰገዳዮችን በማደራጀትና በማስታጠቅ አጠቃላይ ውንብድና ለማካሄድ የምትጓዙበት መንገድ እናንተንና የአዞ እንብ የምታነቡላትን “ኢትዮጵያችሁን” ጭምር ገደል የሚከት ስለሆነ፣ ለሚመጣው ሰብዐዊ ሰቆቅና የሃገር ውድመት ብቸኛ ተጠያቂ መሆናችሁን ከወዲሁ ተገንዘቡ!

  ጽሁፌን ከማጠናቀቄ በፊት ለትምህርትም እንዲሆን አንዳንድ ዕውነታዎችን ላስቀምጥ፣
  ከምንሊክ 2ኛ በፊት ኢትዮጵያ በአሁኑዋ መልክ ኖራ አታውቅም! ከየጁዎች በስተቀር ሌላው ኦሮሞ እና የደቡብ ህዝቦች ከዚያ በፊት የሃበሻ ሃገረ መንግስት አካል ሆነው አያውቁም። ኢትዮጵያ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማገባደጃ ገደማ የሃበሻ ገዢ መደብ ባጎራባች ህዝቦች ላይ ባደረገው ወረራ የተመሰረተች እምፓየር ነች! ለዚህም ነው፣ አጼ ኃይለ ሥላሴ በእንግሊዝኛው አጠራሩ HIH Haile Selassie I, Emperor of Ethiopia ተብሎ የታወቀው እና በክብር His Imperial Highness (Majesty) ተብሎ ሲጠራ የነበረው። እምፓየር ሳይኖረው ኤምፐረር ተብሎ የሚጠራ የለም።

  ኢትዮጵያ መፍረሱዋ አይቀርም የሚባለው፣ እንድትፈርስ በመፈለግ ሳይሆን የእምፓየር መፍረስ የማይቀር ታሪካዊ ሂደት ስለሆነ ነው! የሮማን እምፓየር ፈረሰ፣ የጅንግስ ካን (ሞንጎሊያን)፣ የኦቶማን፣ የኦስትሮ ሀንጋሪ፣ የእንግሊዝ እና የሌሎችም እምፓየሮች ፈርሰዋል። የኢትዮጵያም እምፓየርም እየፈረሰ ነው። ባይሆን በቦታው ምን እንተካ እሚለው ላይ ብንነጋገር ዋጋ አለው። የሮማን እምፓየር መፍረስ አከባቢውን ለብዙ መቶ አመታት የጦር ቀጠና አድርጎት ቢቆይም፣ አሁን የአውሮፓን ህብረት ወልዶአል። እኛም በተመሳሳይ ሂደት ውስጥ ከማለፍ ይልቅ ከታሪክ ተምረን ሃገሪቱን በሰላም ወደ ዲሞክራሲያዊ ፈደራሊዝም እንቀይራት (transform እናድርጋት) ሲባል ግን፣ የበላይነትን የለመደ እኩልነት ጭቆና ይመስለዋል እንደተባለው፣ የሃበሻ/አማራ አክራሪዎች አሻፈረን፣ ወደ እምፓየር ካልመለስናችሁ እያሉን ነው።

  የእምፓየሩ ወራሽ ነኝ የሚለው አብን የተባለው የቀኝ አክራሪዎች ቡድን የተቋቋመው ዕውነት የአማራን ብሄር ከፖሊቲካ ጭቆና ለማላቀቅ ሳይሆን፣ የአማራን የበላይነት ለመመለስ ነው! ለማደናገር ካልሆነ በስተቀር አማራ እንደህዝብ ተጨቁኖ አያውቅም! ቋንቋው አልተጨቆነም፣ ከድሮም ጀምሮ የሃገሪቱ ‘ብሄራዊ’ ቋንቋ ነው። ባህሉ አልተጨቆነም፣ ባለም ዙሪያ የኢትዮጵያ ባህል ነው ተብሎ የሚቀርበው፣ ባገሪቱ ያሉትን መንግስታዊና የግል የሚዲያና የባህል ማዕከሎችን በሞኖፖል የያዘው የአማራ ባህልና እሴት ነው። አማራ በፖለቲካው መስክ አልተጨቆነም፣ እስካሁን 60% ያህል የፌደራል መንግስቱን የሲቪል ቢሮክራሲና፣ የመከላከያና ደህንነት ተቋማት ስራ የያዙት አማሮችና አማራ ነን ባዮች ናቸው። ሃይማኖታቸው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መንግስታዊ ሃይማኖት ነበር፣ ዛሬም ወደ ቤተመንግስት ሊመለስ እየሰራ ነው። አማራ በኢኮኖሚ አልተጨቆነም፣ አብዛኛው የሃገሪቱ ሃብት በእጃቸው ነው! አብዛኛው የአማራ ህዝብ ድሃ ነው? አዎ ድሃ ነው። ድህነቱ ግን እንደሌሎቹ ከጭቆና የመነጨ ሳይሆን፣ በርሱ ስም ሌሎች ህዝቦችን የሚጨቁነው የገዢው መደብ፣ የደሃውን ልጅ ለጦርነት እየማገደ የዘረፈውን ሃብት በሰፈረበት ሃገር ለተንደላቀቀ ኑሮ ከማዋልና ወደ ውጪ ሃገር ከማሸሽ በቀር የፈየደው እምብዛም ስለሌለ ነው!

  አብን፣ “ኢትዮጵያን የፈጠረው አማራ ነው፣ ማንኛውም ፍጡር ፈጣሪውን እንደሚያመልከው ሁሉ፣ ኢትዮጵያውያንም አማራን ማምለክ አለባቸው” እያለን ነው በግልጽ ቋንቋ! በንግግርም አልቆሙም፣ በአማራ ክልል ፋኖን በማነሳሳትና የአማራ ልዩ ሃይል በማለት በ’ህግ’ ባቋቋሙት ግብል ሃይሎች፣ በክልሉ ባሉ ሌሎች ብሄረሰቦች ላይ በማዘመት ዘር ማጥፋትና ማጽዳት (genocide and ethnic cleansing) እያከናወኑ ነው! ውሸት ነው ካላችሁ፣ የጉሙዝ፣ የቅማንት፣ የወሎ ኦሮሞ እናቶችን ጠይቁ! በዚህም ሳያበቃ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ክልል እንዲሁም በበኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ያሉትን አማሮች በማደራጀትና በስውር በማስታጠቅ ለሽብር በተጠንቀቅ እንዲቆሙ አድርገዋል። ሽብርንም አስፈጽመዋል! ለምሳሌ ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ የተከሰተው ጥቃትና በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተፈጸመው የተማሪዎች ግድያ በነዚህ የሽብር ግብረ ሃይሎች የተካሄደ ነው!
  ባጭሩ ለመግለጽ፣ የሰርቢያ አክራሪ ብሄረተኞች በዩጎዝላቪያ ለደረሰው ዕልቂትና የሃገሪቱ መበታተን ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑት ሁሉ፣ በአብን የድንቁርና አይዲኦሎጂ የሚመራው የአማራ አክራሪ ብሄረተኝነት በኢትዮጵያ ላይ ላንዣበበው የእልቂት ጦርነትና የኢትዮጵያ መበታተን ብቸኛ መንስዔ ይሆናል!! ይህን ለማየት ነቢይ መሆን አያስፈልግም!

  • ሀ) ስለ ተራ ስድብህና ፕሮፖጋንዳ አስመልክቶ

   እስቲ ዝባዝንኬዎችህን በነጥብ ልሞግትህ። በቀና ልብና ትህትና እንደሆነ በቅድምያ አስታውቅሀለሁ። እንዳንተ ታች ወርጄ ብስለት ማጣቴን አላስተባብልም ወይም ደስ ይበልህና አልክድም። ባይሆን እዚችው ቤት በምክር ቢጤ ታበስለኝ ይሆናልና ተስፋ አትቁረጥ። እኔም ደግሞ ምናልባት አንድ የጠፋ በግ በለስ ከቀናኝ እመልስ ይሆናል ከሚል ነውና ይመችህ። ሳስበው ግን እንኩዋንስ በሳይበር ውይይት በጠረጴዛውም ላትመለስ እስከወዲያኛው በክነህ የጠፋህ ትመስለኛለህ። ለምን? በመሰረታዊ ኢትዮጵያዊነት ጥያቄ ላይ ከባድ ችግር አለና። እስቲ ለማንኛውም ልሞክር።

   ለ) ስለ 90% ሚዲያዎች ዖሮሞ ጠል ዘመቻና ግለሰቦች ሚዲያዎች ሚና

   ይቺን 90℅ ስታትስቲክስ ከኪስህ ካላወለካት በቀር እንዲህ የተጋነነ ባይሆንም ፣ ያለውን የአገሪቱን ብሶትና ችግሮች አስታከው በዖሮሞ ህዝብ ላይ የጥላቻ አራራቸውን የሚወጡ በሽተኞች ለመኖራቸው ግልጽና ግልጽ ነው። ወያኔዎች እንደ ደህና ነገር ከተውሉን ሌገሲ እርስ በርስ እንዳንተማመንና ኢትዮጵያዊነትን ሆን ብሎ ከጅምሩም ለማዳከም ስለሆነና ነበረም ይህ ሊገርመን አይገባም። you just have to stay above the fray under such circumstances.ለመሆኑ እነዚህ አገር አፍራሽና እርስ በርስ አናካሽ የጽልመት ውላጆች ባብዛኛው የጽልመት ዲጂታል ካድሬዎች እነ ትግራይ ኦንላይን፣ ሁላችሁም ጫፍ ረገጥ አክራርያን ፣ እነ ዖነግ ሸኔና ቶርቤ፣ አብን፣ አክራሪ ዔጄቶዎች በተለያየ የአማራና ዖሮሞ ስም የደመቁ ስለመሆናቸው ምራቁን የዋጠ መቼስ አይጠፋውም። ያንተው እንዲህ አጋነህ ማቅረብህ የሆነ ኮንስፒረሲ ያለ ያስመስላል። አይደለም አባጫላ። የ28 አመታት ሰብል አዝመራው ደርሶ በገፍ እያጨድነው ስለሆነ ነው።ሁሌ እኔም አሳዝኖኛል። እያሳዘነኝም ነው። የሚደንቀው ደግሞ እነ አቢይና ለማ የዛ ኮንስፒረሲ አቀንቃኞች መሆናቸውም አይደል?

   ሐ) ስለ” እኛና እናንተ ዖነጎች” እናም አለኛ በቀር ኢትዮጵያዊነት ላሳር ክስህ፣

   ቀድሞውኑስ እኛና እናንተን ማን አመጣውና ነው ወንድም? እናንተ እኮ አሁን በምናውቃት ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖራችሁ በገዛ ፍቃዳችሁ እራሳችሁን ባእድ አድርጋችሁ ፣ እናንተ “አበሾች” እኛ ደግሞ ዖሮሞዎች ብቻ ነን ብላችሁ ለያችሁ እኮ። እናንተ ስል ዖነግ ሸኔንና አባቶርቤን ነው። የመጫና ቱለማ ማህበርን ዋና መነሻ አላማ ስታችሁ ስለ ዖሮሞ በኢትዮጵያ ጥላ ስር መብቱንና ማንነቱን የእኩልነትና የእኩል አብሮ መኖርን አጀንዳ አክራችሁ ጫፍ አስረግጣችሁ ከአበሻ ኢምፓየር ስር ነጻነትን ብላችሁም አይደል እንዴ በየቆንጥሩ ለብዙ አስርተአመታት ጎራ ለይታችሁ የወጣችሁ?:አንወዋሽ እንጂ ። ሌላው እናንተ የምለው የሁሉም ጎሳ ጫፍ ረገጥ አክራርያንን ነው በኔ በኩል። ታች እመጣልሀለሁ በዝርዝር።

   መ) ስለ ትግራይ ጉዞና ትግሬን አታናግሩ የውሸት ቅዠትህ (የእምዬን ለአብዬ)

   ኸረ በኢትዮጵያ አምላክ? ትግሬን አታናግሩ? አቶ በቀለን መሰልኩህ እንዴ? እንኩዋንስ ትግሬን ባለማተቦቹንና የኢትዮጵያችን ዋና መስራች ህዝብ ቀርቶ በግፍ የወጉንንም ፋሺስቶች አታናግሩ አልልም። ይቺ ጠፍታህ አይደለም መቼስ ወደሁዋላ ሄዶ የጻፍኳቸውን ለሚያይ ሰው ይገርመዋል። ክፋቱ ያየውን ይዞ የሚጋልብ እንጂ አጥልቆ የሚያይስ ብዙ የለምን ማደናገርያ መሆኑ ነው? ትግሬ ለማናገርስ ምን መቀሌ ይወስድሃል ባገራቸው ኢትዮጵያ በገፍ አሉልን አይደል እንዴ? ኦቦ ዳውድ አፍ ገጥመው ከነአቦይና ጌታቸው ረዳ ጋር፣ ሰራዊቶቻቸው ሳይቀሩ በመቀሌ ያለፉት ማ ይሙት የኢትዮጵያዊ ናፍቆታቸውን ሊወጡ ነበር በለኝና አስፈግገኝ እባክህ። እውነትም ያልበሰልኩ እንጭጭ ነኝ። እሺ መንግስትስ በራሳቸው በማናውቀው ምክንያት ወንጀለኞችን ባለማቅረባቸው ይጠየቁበት፣ እናንተ (ዖነጎች) ለዖሮሞ ልጆች እልቂት ተጠያቂ የሆኑትን ግለሰቦች ሄዶ አብሮ ሸንጎ መቀመጥና መወያየት የወገን የሰላምታ ጥየቃ ከሆነማ ደስታውን አልችለውም። በነካ እግራችሁ ጎንደርንም፣ ባህርዳርንም፣ ጠያይቁና አገር ወዳድነታችሁን እንየዋ። ወይስ እውነት ዖነግና ህወሃት ምን የሚያመሳስል ነገር አገኙ? ፍርዱን ለህሊናህ። ቢያንስ ወገኖቼን የገደሉብኝ ሰዎች እዛ ሸፍተው ስላሉ እንደው የሙት መንፈሳቸው እንኩዋ እንዳይታዘበኝ ከማለት እንጂ እንደትግሬስ እንግዳ ተቀባይ አለ እንዴ? ምኒልክስ ጡት ቆረጡ ብላችሁ ነው ስማቸው ሲነሳ የሚያስጓራችሁ። መቀሌ ያሉት ሽፍቶች ከጡት አልፈው ልጠቅሰው የማልፈልገውን ሰቆቃ አድርሰው ልባችሁ ይቅር ካለ ለምን ፌር ሆናችሁ የምንሊክን ትውልድ ያውም የበህይወት የሌሉትን ንጉስ ትውልድ ይቅር ለእግዜር አላላችሁም ታድያ? የማይመስል ነገር ነው አባጫላ።

   ሰ) ስለ ዖሮሞነትና ኢትዮጵያዊነት ዳግም ትችትህ

   “ቅጥአምባውስ” የጠፋባችሁ እናንተ ዖነጎች ናችሁ። ዖሮሞነት ያለ ኢትዮጵያዊነት ሴንስ የሚሰጠው ሲጀመር በአገረ ኢትዮጵያ ማንነትና ህልውና ስምምነት ሲኖር ነው። አንተ አገሪቱን ያየሀት ልክ እንደ ጣልያን ፣ ጀርመን ወይም አሜሪካ አይነት የሲትዝነሪና ናሽናሊቲ አመለካከት ነው። ዝርዝሩን በኢምፓየር ትችትህ ስር እመጣልሀለሁ። ታገሰኝ። በዚህ ጉዳይ ላንስማማ ብንተወው ይሻላል። በጥብጬ ብግትህም ላትቀበለው አልደክምም።

   ረ) ስለ ዖሮሞነት በደልና መብት ጥያቄና ትግልና ምንሊክ

   ዖነግ እውነት ስለ ዖሮሞ ህዝባችን እኩልነት ፣ ፍትሀዊነትና የማንነት ጥያቄማ ቢሆን በትክክል የሚታገለው በ ብዙ አመታት ህልውናው ብዙ ለውጥን ባመጣ ነበር። ያልሆነውን የዲሞክራትነትን ማእረግ ባትሰጠውስ? ስለ ዖሮሞ እኩልነት የሚታገል ስለሁሉም ህዝብ እኩልነትን ይፋለማል። እንኩዋንስ የሰው ነፍስ ቀርቶ ላሙዋን እንኩዋ የምታልብ የዖሮሞ እናት “ጋዲ” ስታስር የላሚቱ እግሮች ስር ተሳቃና ላለማስከፋት ተቆጥባ ነው የምታልበው። የልጅነቴ ዖሮሞ እናት አሁንም ያው ናት። ገጠር ያደገ ያውቀዋል። እናንተ ዖነጎች አጠገባችሁ የራሳችን ወገን በገጀራ እየተቆረጠ እያያችሁ፣ ይህን እኩይ ስራ ያነሳሳው አደባባይ የሚያውቀው በጁዋር ሰበብ መሆኑ እየታወቀ፣ ጭራሽ ለሱ አሌጂየንስ በመቆም ታሳፍሩን? ይህ ነው ያንተ ከጭቆና መላቀቂያ ትግል? እሺ አታውግዙ። አትቃወሙ ይሁን። ከግድያው በሁዋላ ከሱጋር ፍቶ መነሳት አስፈላጊ ነው? ከ አቶ ታዬና ፕሮ መረራ በቀር የኮነነ የዖነግ መሪ ይሁን አንጋች አንድስ ነበር? እባክህ ስለ ዖሮሞ በደልና እኩልነት ነው የቆምነው ብለህ የባሰ አታሳቀኝ። ያሳቅቃል ይህን መስማት ውሸት ስለሆነ። ሌላው ይህ የምንሊክ ምች እውነት ስውዬው ጡት እንዳልቆረጡ አጥታችሁት ሳይሆን ያቺ ከታች የማወሳትን የኢምፓየር ፈጣት በመሆናቸውና በዚሁ ቂም ስለያዛችሁ ነው። እንጂማ እንኩዋንስ በህይወት የሌሉትን ምኒልክ የዛሬውን አቢይ ስታብጠለጥሉ ማ ዝም በሉ አላችሁ? ስም አታንሳማ አፍ መሎገም ነው። በደልም ነው። ባይሆን ባልሆነና ባልተደረገ ታሪክ በኔ እምነት ከሞቱትም ካሉትም እጅግ ብልህና የአገር ባለውለታ የሆኑትን ሰውዬ በውሸት አትክሰሱ ነው። አንተም ስለመቁረጣቸው ማስረጃው የለህም። ካለህ ወዲህ በለኝና አጽማቸው እስኪገላበጥ ልርገማቸው። ሌላ ምንስ ማድረግ ይቻላል አባጫላ? ከልቤ ነው።

   ሠ) ስለ ዖነግ ትግል ረብሻና ሁሉን ዖነግ ላይ ማላከክና የወደፊት እልቂት ትንበያህ

   ይህ እውነትነት ሊኖረው ይችላል ብዬ እገምታለሁ ምክንያቱም በቀደም አቢይን በ 48 ሰአታት “ብፈልግ ልክ አስገባለሁ” አሉ የተባሉት ጄኔራል ከማል አንድ ጠረጴዛ ላይ ከ ዶር አቢይና ሌሎች ጽንፈኞች እነ አብን ጋር ጠቀምጠው አይቼ ደስታና ሀዘን ተሰምቶኛል። ደስታው አብሮ ለውይይት መቀመጣቸው ሲሆን ሀዘኑ ደግሞ ድንገት ያን የተጻፈውን ብለውት ካልሆነስ ብዬ ነው። እውነት ብለውት ካልሆነ ክፉ በመናገሬ ይቅር ይበሉኝ እላለሁ። ምን እናድርግ አባ ጫላ የናንተም ጎራ እኮ እብሪት አይሉት ንቀት “ኸረ እኛ እጃችን የለበትም” ስትሉ አንድ ቀንም ሰምቼ አላውቅም ። ለምሳሌ የወለጋን ባንኮች ማ ዘረፈ? ለምንስ መንበሩን የኛው ልጆች ይዘውት ሳለ ለምን በዖነግ ላይ በግፍ ይለጠፋል? ደሞስ ውሸት ከሆነ ለምንስ ነው ኦቦ ዳውድ ባደባባይ የማያስተባብሉት? እባክህ መናገርያ ሚዲያ አጥተን ነው አትበለኝ። ሌላው ቢቀር ያቺ ነገረኛ ቤቲ የተባለች ልጅ እነ ዶ/ር ገመቹን የወረደ አስተሳሰብ ከምታናዝዝ ብሶታችሁንና የውንጀላውን ሀሰትነት ከነ ማስረጃው ማቅረቡን ምነው ተሳናችሁ? አስገራሚ ነው በእውነቱ። እኔ የሰማሁት ገና ከመግባታቸው ስለመሳርያ አልፈታም አላስፈታም የትእቢት ከመንግስት ጋር እሰጥ አገባ እንጂ አንዴም ስለ ዖነግ ብሶት ሲያወሩ አልሰማሁም። ለመሆኑ እነ ሌንጮ ባቲ ከናንተው ለቀው ከወጣት ልጆቻችን ጋር ያውም አማካሪ ሆነው ሲሰሩ እነ ኦቦ ዳውድና ያንተ ቢጤው አንጋቾቻቸው ግን ጭራሽ ስለ ዘመነ መሳፍንት ቅዠት ውስጥ ቀራችሁ። እኔ የአክራሪ ዖነግ አንጋች ብሆን ፣ በተለይ ወጣቶቹ እኝህን ሰውዬ በክብር አሰናብታለሁ። የጥንት ውለታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ።

   ፩) ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ኢትዮጵያ በፊት (ዘመነ መሳፍንትና) ድህረ ምኒልክ “ኢምፓየር” ትረካህና ወደዘመነ መሳፍንት አይነት የምኞት ጉዞ – ይገርማል

   ይህ በጣም የሚገርም ብቻ ሳይሆን ለመጀመርያ ጊዜ የአክራሪ ዖነግን የልብ ትርታ ያዳመጥኩበት ነጥብ ነው። አሁን ተረዳሁት። እንዳንተ አገላለጽ ምኞትህ ወደ ቅድመ ምኒልክ ዘመነ መሳፍንት፣ ሁሉ በየራሱ ኦቶኖመስ ሆኖ እራሱን እንዲያስተዳር፣ ኢትዮጵያ የተባለችን ኢምፓየር የግድ አፍርሰን የቅድመ ዳግማዊ ምንሊክን ማለትም ሁሉ በየራሱ” ቆሮ ” እንዲተዳደር ነው። ለዚህም አረዳድህ ማጣፈጫ አርገህ ያቀረብከው ዖሮሞና ሌሎች በቁጥር እንደ ዖሮሞና አማራው ያልታደሉት ወገኖቻችን መከራ የበዛው ከድህረ ምኒልክ ኢምፓየር ምስረታ በሁዋላ መሆኑ ነው። አንተ እንደዘረዘርከው ሌሎች ጎሳዎች ይሁኑ ዖሮሞው በግዳጅ ኢትዮጵያዊነትን ስለለበሰ ያንን የኢትዮጵያዊነት ሸማ አውልቀንበት ሁሉ በየጎሳው የየራሱ አስተዳዳሪ ሾሞ በበየራሱ ክልል ይኑርን ነው። እርግጥ የአጼዋቹ ስርአት ገባር እያደረጉ፣ እየቀሙና እየገደሉም እንዳልከውም ኢምፓየር መስርተዋል። ከአለም ኢምፓየር ምስረታ የኛው ምንም የተለየ አይደለም። ለነገሩ ደርግ ኢምፓየር ተብዬውን ካፈረሰ 50 አመታት ሆኖታልና ችግሩ እሱ አይደለም። የዖነግ ትግል መሆን የነበረበት ወቅቱን ወዳልጠበቀው ወደ ቅድመ ምንሊክ የጨለመ የዘመነ መሳፍንት ጉዞ ሳይሆን በዛሬዋ ኢትዮጵያችን ውስጥ እንዴት አርጎ ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ጋር በመተባበር እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት በብቃትና ኩሩነት የዖሮሞ ወገኑን መብት ማስከበር ነበረበት። የምንሊክ አንጋቾች እኮ በህይወት የሉም አባጫላ እንደው በትውልድ አማራ ናቸው (ያውም አንዳንዶች ጥያቄ ጥለውበታል በዚህ ጉዳይ) ስለተባለ የኢምፓየርነት አበሳውን ትውልዳቸው ይክፈል ካላልክ በቀር። የቅድመ ምኒልክን መሳፍንታዊ አገዛዝን ኢትዮጵያን አፍርሶ ከመመኘትና ለዚያም ምኞት ማሳክያ ተብሎ ደም ከሚፈስ ለምን የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ላይ ተሁኖ ትክክለኛው ፌዴራላዊ አስተዳደርን ለመመስረት አትታገሉም? ለምን ኢትዮጵያ የተባለች ስም አለርጂ ትሆንባችሁዋለች ትልማችሁ በፌዴራሉ ውስጥ እኩልነትን ያማከለ ኦቶኖሚ ዛሬ መፍጠር ከተቻለ? ዛሬ እኮ ጉድ የፈላብን ወያኔ በቁንቋ መስፈርት ብቻ ስለሸነሸነን ግራ ተጋብተን እንጂ ትክክለኛው ፌዴራላዊ ስርአት ቢገነባ አንተ የምትለውን አብሮ መኖር በእኩልነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያን መገንባት ይቻላል እኮ አባጫላ። ለምን ይቺ አገር የዛሬ 50 አመት በፈረሰ ኢምፓየር ዛሬ ትፍረስ ምንም እንኩዋ ባንተ አተያይ ገና ፈርሳ አላበቃችም ብትልም። የሚደንቅ አተያይ ነው።
   አንተ ረግጠህ የቆምከው የዛሬ 50 አመት ላይ ይመስላል። በዛሬ ዘመን የጃንሆይ ይሁን የምኒልክን ኢምፓየር አስተዳደር የሚመኝ ወይም ዳግም ለማምጣት የሚታገል እውነት እንዳልከው አማራዎቹ ከሆኑ የጤና አይሆንም ። እንደዛ ከሆነ አብኖችም እንደናንተው አቅላቸውን ስተዋል ወይም የአይምሮ ምርመራ ይፈልጋሉ። የአማራ ጨቋኝ እንጂ ተጨቋኝ የለም ያልካት ግን ሀሰት ነው። ባንተ አረዳድ የዖሮሞ ጨቋኝም የለም፣ የሲዳማም፣ የወላይታም፣ የአገውም፣ ልትለኝ ነው። ለዚህም ማጣፈጫህ አማርኛ እንዲህ ገኖ፣ የአማራው ባህል እንዲህ ደርቶና ተንሰራፍቶ እንደምን ተጨቆነ አይደል? ያውም አማርኛ ፌዴራል ቋንቋ ሆኖ እያልከኝ ነው። ይህ አረዳድና ግምት ከወያኔ በሁውላ የተወለዱትን የፌስቡክ ያልታደሉ ልጆችን ልብ ማሸፈቻ ይሆናል እንጂ የኔቢጤውን እድሜ ብርቅ ላልሆነበት ልብ የሚሰብር አስተያይ ነው። በኔ አተያይ ሁሉም የግፍ አገዛዝ ሰለባ ነበር። ግፍ ጎሳን አይመርጥም። የኔው ዖሮሞ ባላባት ዘመዶቼ የገዛ ወገናቸውን ዘመዶቻችንን ሳይቀሩ ከበረት ምሶሶ እያሰሩ ይገርፉ ነበር፣ በቃላት የማይገለጽ ግፍ ሰርተው አልፈዋል።ጭራሽ ጢሰኛ አማሮችም ነበሩዋቸው። ምናልባት በሌላው ዖሮሞ ክፍሎቻችን አልተለመደ ይሆናል እንጂ ለሸዋ አዲስ አይደለም። የትግሬዎቹም። ወላይታዎቹም፣ ሲዳማዎቹም ሁሉም በየፊናውና ጎሳው ከራሱ በወጡ ልጆች መከራውን በልቷል። ለአማራው ብቻ የተሰጠ “ጸጋ” አልነበረም ለማለት ነው። የአማርኛው በመላው አገር መንሰራፋት የብዙ መቶ አመቶች የየመንግስታቱ ስራ ውጤት ነው። የፊደል አፈጣጠርና መበልጸግ ትልቅ ሚና አለው። ብንታደለው ኖሮና አማርኛ የአማራው ንብረት ብቻ ነው ብላችሁ ባታዩ ኖሮ የሁላችን “ንብረት” የኢትዮጵያ በሆነና እኩል በተገለገልንበት ነበር። ለኔ ዖሮሚፋን ለማቀላጠፍ በፊደል እጅግ ይቀላል። መቅለልም ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ንብረት በመሆኑ ብቻ በደስታ እገለገልበታለሁ። በዚህ ብዙ ከዚህ ቀደም ስለተባባልን አልደግመውም።ሌላው በፖለቲካው ይሁን በኢኮኖሚው አማራው ነው አብላጫው ያልከውን መረጃው ስለሌለኝ እቸገራለሁ። አቢይ እያስተዳደሩን ይህ ከሆነ ስህተት ነው። ብቃት እንጂ የዘር ሀረግ ሙያ ውስጥ ከገባ የማንወጣበት ማቅ ሰጥመን እንቀራለን እንደ ዘመነ ወያኔ። ምናልባት ዶር ገመቹ እንዳሉት አማርኛ ተናጋሪ ሁላ፣ ወይም የኔ ቢጤው ባለማተቡ ዖሮሞ (መስቀል) ወይም የ ወ/ አበበች በዳ’ኔ አይነቷ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ዖሮማራን አማራ ብለህ ካላልከ በቀር። የተቀያየጠውን አማራና ዖሮሞ እንደወጥ አማራ ብቻ ካየኸው በርግጥም አስፈሪ አሀዝ ነው። አሳዛኝም አመለካከት ነው። እንደው ልጠይቅህ፣ የአማርኛን መስፋፋት ከማውራት ዖሮሚፋን በጥልቀት ዛሬ በጋራ አጎልብቶ ፌዴራላዊ ቁዋንቋ ለማድረግ እድሉና ሁኔታው እያለ የአቶ በቀለ አይነቱ ጭራሽ ዖሮሚፋ በቀር አማርኛን ንክች አታርጉ ማለት ዖሮሚፋን እንደ አማርኛ እንዳይስፋፋ “ምቀኝነት” ካልሆነ በቀር የዖሮሙማ ኩራት ሊሆን ነው? ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዖሮሚፋ አኩርፎ ጭራሽ እንኩዋንስ ሊያጠናው ለመስማቱስ አይቀፈውም ብለህ ነውይህን ሲሰማ? ምን አይነት አይምሮ ነው ይህን የሚያፈልቅ? ባንድ በኩል ዖሮሚፋ ተቀበረብን ይባልልኛል ደግሞ። እነ አቢይና ለማ ወደመንበሩ ሲመጡ የዖሮሚፋ እድገት ተስፋው ታይቶኝ ነበር። ዛሬማ እድሜ ለዚህ ሰይጣን ጁዋር ልጅ እንኩዋንስ ቀሪው ዖሮሚፋን ሊማር መስማቱንም ይፈራል። አሃ! ለካ አንተ የምትመኘው ዘመነ መሳፍንት ዖሮሚፋ ለ ዖሮሞ ብቻ ሆኖ ምናልባት የየመሳፍንቱ ዱኮች የጋራ መግባቢያቸው ወይ እንግሊዘኛ ወይ ሱዋሄልኛ ሊሆን ነው። አለበለዚያማ እያንዳንዱ መስፍን በምንኛ ሊግባባ ነው በቅድመ ምንሊክ ዘመነ መሳፍንት አስተዳደራዊ ምኞትህ? የኢምፓየሩን ልሳን ላለመናገር ተብሎ ላንግባባ ነው ወይስ እያንዳንዱ ዱክ የራሱ አገር ሊፈጥር ነው? ። እጅግ ለማሰብ አድካሚና አሳዛኝ አካሄድ። ኦርቶዶክስን እንኳ ተወው። ሀይማኖት ውስጥ አንግባ። ለፍርድ አይመችምና። የሃይማኖትን ነገር ለፈጣሪ እንተወው። ባያስድ ሆኜ ሀሳብ በሀይማኖት አልሰጥም። እነ ሙፍቲ እድሪስን የመሰለ ቀና አባት ያለን ህዝብ አንዱ ሌላውን በሀይማኖት ባይጎሽም ይመረጣል። ኦርቶዶክሴን ለቀቅ የራስህን እዚያው አጥብቅልኝ።

   ፪) ስለአብን፣ አማራ አለመጨቆኑ፣ ስለአብን ውሀ ልክ ማለት፣ የአማራው ባህል ቋንቋ መዳበርና ድህነት በተመለከተ፣

   አብን በእርግጥም ብሏል ምንም ሁዋላ ላይ ለማስተካከል ቢሞክሩም። በበኩሌ አንድ ጽንፈኛ ተነስቶ እንዲህ ሲል ወግድ የማመልከው ፈጣሪን እንጂ ከቶ አማራን አይሆንም ነው የምለው። አንድ ቡድን እንደዛ ስላለ አይመለከም። ከዛ አልፎ በሀይል አጠፋሀለሁ ካለ አለ ነገር። የምሱን ያገኛልና። በሀቅ እንነጋገር ከተባለ አንተ የጠቀስካቸው የጉሙዝ፣ ቅማንት ፣ ደቡብ እናቶች የልጆቻቸውን ገዳይ አማራ ስለመሆኑ ምንስ ማስረጃ ሊኖራቸው ነው አባጫላ? አንተ ትግሬ ወገኖቻችን የምትላቸው ወያኔዎችና ቅጥር አንጋቾቻቸው አማርኛን እያቀላጠፉ የአብን ቲሸርት ለጥፈው ለሰይጣናዊ ስራቸው ተሰልፈው እንደሆነስ ብለህ አስበሀል? ለነገሩ ለእኩይ ስራቸው ዖሮሞንም እየሆኑ የዖነግን ኮፍያ የለበሱ ቢያገዳድሉን ምን ይገርማል? እናም የአብን ወጣቶችን የኢትዮጵያዊ ከኛ በላይ ላሳር ወዲያ በሉ ብለህ በጽናት ለአላማህ መታገል ነው። ችግሩ ያንተ ወይም የዖነግ አላማ ኢትዮጵያን አፍርሶ በህልፈቱዋ ዘመነ መሳፍንትን መመለስ መሆኑ ነው። እዚህ ፌርማታ ላይ ነው ምን የተቀደሰ አላማ እንኩዋ ብታነግብ ስፍር ቀጥር የሌለው ኢትዮጵያዊው ዖሮሞ ወራጅ አለ የሚልህ። አብንን በተመለከተ በርግጥም ብዙ መረጃ የለኝም። እስቲ ካሁን በሁዋላ በደንብ ለመረዳት እሞክራለሁ።

   ማጠቃለያ
   ወንድም አባጫላ፣ ይቺ የመጨረሻ መልስህን ካየሁ በሁውላ እንኩዋንስ በሳይበር መስኮት ልንግባባ በጠረጴዛ ዙርያም ብንቀመጥ እንደማንስማማ ስለማውቀው ፈጣሪ ቀናውን አሳይቶ ወደህሊናችሁ እንድትመለሱ እጸልያለሁ። በነገራችን ላይ በቀደም አበሻ አሁን ደሞ ካድሬው ብለኸኛል። የግርጌ ማስታወሻ ይሁንህና የማንም ካድሬ አይደለሁም። ቃሉንም በጽሁፍ ነው የማውቀው። የማወጋህም የህሊናዬን ነው። እውነት እንደምትለው የዖሮሞ ጉዳይ የሚያብሰለስልህ ከሆነ ልክ እንደ ሌንጮ ባቲ የቀራችሁም ከነ ኦቦ ለማ ጋር አብራችሁ ስሩ። ይህ የኢምፓየር ቅኝታችሁ እንኩዋንስ ሴንስ ሊሰጥ ሲሰሙትም ለጆሮ ይከብዳል። ብዙዎቻችሁ የምእራቡን አኑዋዋር አይታችህዋል ምንም እንኩዋን አብላጫው ተከታይ በየቆንጥሩ ቢከርሙም። እነ ኦቦ ዳውድ ከባድ ሀላፊነት አለባቸው። ዛሬ ወጣቱ ለ 28 አመታት ክፉኛ ተወናብዶ አይደንቲቲውን ሁሉ አጥቷል። ኦቦ ዳውድ እራሳቸውን ዝቅ አርገው ተከታዮቻቸውን በቅንነት መምራት ይገባል። አንድ ትውልድ ባሩድ እንደጮኸበት ነው ያደገው። እስቲ አስበው፣ ኢምፓየሩን ለማፍረስ (አለ ብንለውም) ብሎም የምትመኙትን ቅድመ ምንሊክ አስተዳደር ለማጎልበት የሚወጣውን ሪሶርስ፣ የሚጠፋውን ነፍስ አስልተሀል? ቀላል አይደለም እኮ ትክክል ነው እንኳ ብንል። ከዚህ ሁሉ ጠቅላላው የዖሮሞ ልጅ ከነ ኦቦ ለማ ጎን ተሰልፎ እየተረዳዳችሁ ስለሚመጣው ዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም ብትሰሩ አይሻልም? ካልሆነ ደግሞ ነጻአውጪነቱን ትታችሁ ፣ ፖሊሲያችሁን ሳትቀይሩ በሰላም በጠረጴዛ ዙርያ እንደሰለጠነ ተፎካካሪ መሆን አይበጅም ለወገናችን? አሁን ማን ይሙት በዚህ ዘመን ስለ ቅድመ ምኒልክ የሚያስብ ቀርቶ የሚያልም ዖሮሞ ኢትዮጵያዊ አለ ብላችሁ ታስባላችሁ? ምናልባት በየሻይ ቤቶቹ ወይም የዖነግ ውይይት ክበቦች፣ ከከፋ ደግሞ በየቆንጥሩ ልትኖሩ ትችላላችሁ። ይህ ቁጥር ደግሞ የብዙሀንን ዖሮሞ ፍላጎት በጭራሽ አይወክልም። በምን አወክ እንዳትለኝ ብቻ። ከእድሜ ተሞክሮና ካለኝ አረዳድ እንጂ ምንም ሳይንሳዊ ጥናት ላይ የተመረኮዘ ስታትስቲካል ሳምፕሊንግ አላደረኩም። ግን አንድ ማስረጃ አለኝ። እነ ዶ/ር አቢይና ለማ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ ባደረጉበት ወቅት በ አራቱም ማእዘን እየተመመ የተቀበላቸው ህዝብ ከበቂ በላይ ነው። ዛሬም ሪፈረንደም ቢጠየቅ እራሱ ዖሮሞው ህዝባችን በጭራሽ እናንተ ወደተመኛችሁት ቅድመ ምንሊክ መሄድን እንዳልሆነ ከልቤ አምናለሁ። ይህው ነው. ይቅርታ አስረዘምኩብህ። ካሁን በሁዋላ ካንተ ጋር ስዳረቅ አልገኝም። በቡሄ የደነቆረ ወያሆዬ እንዳለ ይቀራል ይባል የለ። አንተም ላታምንበት በከንቱ መድከሜ። ለነገሩ አይምሮዬን ከሚያስጨንቅ ከኔው እንዲወጣልኝ ነው። ናጋቲ። ሲአቺ ኤሳቲስ ዋላጋራ ሞቲ።

 4. ውድ አባዊርቱ – እባክህን በዚች አድራሻየ እንገናኝና በግላችን እንጨዋወት፡፡ አባጫላን ተወው፡፡ ድንጋይ ላይ ውኃ ማፍሰስ ነው፡፡ በዓላማና በጥቅም የታወረን ሰው ለመመለስ መሞከር ራስን ማድከም ነው፡፡ እውነቱን አጥቶት ሳይሆን እንደወንድሙ ጃዋር ጥቅሙና ለዘመናት በመላ ሰውነቱ የተወደወደበት የጥላቻ ፖለቲካ አስረውት ነውና አንፍረድበት፡፡ ጊዜ ባለውሉ ሁሉንም ቁልጭ አድርጎ ምናልባትም በቅርቡ ስለሚያሳየን እኛ የኢትዮጵያ ወገኖች ማድረግ ያለብን በግልም በቡድንም መመካከርና ትውልድን ለማዳን በየአቅማችን መሞከር ነው፡፡
  ይህን “ንትርክ” ከሣተናው ወደዘበሃበሻ ያመጣሁት ሰው ነኝ – ነፃነት፡፡

 5. አባዊርቱ፣
  ያረዳድ ችግር ብቻ ሳይሆን፣ ነገሮችን አጣሞ፣ ያልተባለን ተብሎአል ብሎ የማቅረብ የሃበሻ አባዜ ተጠናውቶሃል ልበል?

  1. ሰዎች የሃሳብ ክርክር የሚያደርጉት፣ የአንዱ አሸንፎ ሌላኛው ደግሞ መቶ በመቶ እጅ የሚሰጥበት የአምባገነኖች አካሄድ ለመከተል አይደለም። አንዱ ሌላኛውን ለማሳመን በሚደረግ ልውውጥ መማማር፣ ከዚህም ከዚያም ሃሳብ የተወሰኑትን ተቀብሎ፣ የማይገጣጠሙትን ጥሎ ወይም ለሌላ አቆይቶ እውቀትን በማዳበር ወደ መስማማት የሚኬድበት መንገድ ነው። ያንተ ክርክር ግን ሲጠቃለል ጭንቀትህ በጭራሽ ስለኦሮሞ ህዝብ ሳይሆን ነፍጠኛው የሃበሻ ገዢ መደብ እንዴት ስሙ በክፉ ይነሳል የሚል ሆኖ እናገኘዋለን! ከእንዳንተ ዐይነቶቹ የጨቋኞች ጠበቃ ጋር መሟገት አስፈላጊም አልነበረም። የምትሟገተው ለመማማር ሳይሆን በሃሳብ ለመርታት፣ ካልሆነም ያው ነፍጥህን ለማንሳት ነው!

  2. ሚዲያ ሲባል፣ ራዲዮ፣ ቴለቪዢን፣ ጋዜጦችና ተመሳሳይ በተቋምነት የተደራጁ የዜና አዉታሮችና የህዝብ መገናኛ መሳሪያዎች ማለት ነው። ግለሰቦች በዩትዩብ እና በፌስቡክ የሚለፍፉትን አይጨምርም። እናም፣ ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በውጪ ሃገራት በስመ ኢትዮጵያውያን ከተቋቋሙት የዜና አውታሮች ከጥቂቶች በቀር የተያዙትና የሚዘወሩት ሃበሾች በሚባሉ ሰሜነኞች ነው! ከነዚህ ውስጥ ስለኦሮሞ፣ በተለይም ስለዕውነተኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀና አስተሳሰብ ያላቸው የሉም ማለት ይቻላል።

  3. “ኦነግ ሸኔ” ወይም “አባቶርቤ” የሚባሉ ድርጅቶችን አላውቅም! ያለው አንድ ABO/OLF ነው። በወሬ ሆነ በሌላ የሚመግቡህ ወገኖች የሚነዙትን ትረካ ይዘህ ቁም ነገር አወራለሁ አትበል! ‘እናንተ’ እያልክ ሁሉን ባንድነት ስትጨፈልቅ የምትውለው እኮ “ሸኔንና አባቶርቤን” ሳይሆን ኦሮሞ የተባለ፣ የኦሮሞ መጨቆን፣ መገርረፍና መገደልን የሚቃወመውን ሁሉ ነው! ጃዋር፣ በቀለ፣ ፕሮ. ህዝቅዬል፣ ዶ/ር ጸጋዬ የመሳሰሉት በማን ስሌት ነው የ”ዖነግ ሸኔ” አባል የሆኑት?? የኔንስ አባልነት ከዬት አገኘሄው?? እሺ እኛስ “እዖነግ ሸኔና አባቶርቤ” እንሁን። ራስህን ጨምረህ “እኛ” የምትላቸውስ እነማን ናችሁ?? እግረ መንገድህን፣ “ሃበሻ” የሚለውን ከየመን ለፈለሱ ነገደ ሃበሻት/ሰሜነኞችን (አማራ፣ ትግራይ፣ ትግሬ) ብቻ የሚመለከት እንጂ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችን አይጨምርም።
  ነጻ አውጪ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ብቻ አልተቋቋሙም! ከሌሎች ሃገሮች ታሪክ በመነሳት እነ ANC (South Africa), PLO (Palestine) እና ሌሎችም ሃገራቸውን ከኮሎኒያሊዝም በትጥቅ ትግል ነጻ ያወጡ ድርጅቶች ለምንና እንዴት እንደተቋቋሙ የምታውቀው አለ? ባንተ አረዳድ እነዚህ ሁሉ ራሳቸውን ከሚታገሉለት ህዝብ ራሳቸውን “ባዕድ” አድርገው ነው?? በለመደው የነፍጠኛ ገዢ መደብ አፈቀላጤነትህ ባጭሩ ለማለት የፈግከው፣ “ኦሮሞ አልተጨቆነም”፣ “ኦነግ የሚታገለው በሰላም፣ በእኩልነት አብረው የሚኖረውን አንድ ቋንቋ አንድ ባህል ያለውን አንድ ህዝብ ለመከፋፈል ነው”፣ “ኦነግ አሸባሪ ነው” ወዘተርፈ…። አንተም ቲቪ ጣቢያ ክፈትብን እንድግዲህ!

  4. “ስለ ትግራይ ጉዞ” ለምን እንድሚያቃዥህ አይገባኝም! ወይስ አንድ ትልቅ ወንጀል ያገኘህበት መስሎህ ነው?? አትቀባዥር! ዳውድ እብሳ በመቀሌ አላለፈም፣ በህልም ወይም ጌቶችህ የሚነግሩህን በጥሞና ስላላዳመጥክ ይሆናል! በስልጠና ላይ የነበሩ የABO ታጋዮች በአውቶቡስ አልፈውበታል። እና ምን ይሁን?? በቀለ ገርባ እና ፕሮፈሰር ህዝቅየል የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ስለሆኑ ወደ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሄደዋል። ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የወታደር ቤት ወይም ካምፕ አይደለም! ስለ አካደሚክ ነጻነት ሰምተህ ታውቃለህ? የከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ ሃሳቦች በፍጹም ነጻነት የሚንሸራሸሩበት፣ አዲስ ሃሳቦች እና ፈጠራዎች የሚፈልቁበት የምርምር ማዕከል ነው። አሁን አድገውና በልጽገው የሚናያቸው ሃገሮች፣ እዚህ የደረሱት የህዝባቸውን የሃሳብ ነጻነት እውን በማድረግ ምሁሮቻቸው የሃሳብና የፈጠራቸውን አድማስ ያለገደብ እንዲያስፋፉ ከማገዝ አልፈው ከ3ኛ አለም ምሁራንና ሊቃውንትን በማስኮብለል ነው። ኢትዮጵያ ግን በንብረት ብቻ ሳይሆን በዕዉቀትም የደሃ ደሃ የሆነችው፣ እስከዛሬ ያሉ አምባገነን ወታደራዊ መሪዎችዋ፣ የዕውቀትና የነጻ ሃሳብ ጸሮች ስለሆኑ ነው! በደርግም ይሁን በኢህአደግ፣ እንኳን መናገር፣ ማሰብም ያስከስስ ነበር እኮ! በየዐመቱ ስንት ምሁራን ከኢትዮጵያ እንደሚኮበልሉ ታውቃለህ?? አንተ ግን ማሰብም በመለዮ ልክ እንዲሆን ትሻለህ!

  5. “ዖነግ እውነት ስለ ዖሮሞ “ህዝባችን”! እኩልነት ፣ ፍትሀዊነትና የማንነት ጥያቄማ ቢሆን በትክክል የሚታገለው በብዙ አመታት ህልውናው ብዙ ለውጥን ባመጣ ነበር” ስትል፣ የአንድ ድርጅት አላማ ትክክለኛነት የሚለካው በአገኘው ድል ልክ ነው ማለት ነው። እንዲያ ከሆነማ፣ ደርግን አሽቀንጥሮ የራሱን አምባገነናዊ ስርዐት የዘረጋው ሕወሃት፣ ውስጣዊ ቅኝ አገዛዝ መፍጠሩ ትክክል ነበር ማለት ነው! ደግሞስ፣ አሁን ለውጥ የመጣው የABO እና በአጠቃላይ ኦሮሞ ህዝብና ቄሮ ከፍተኛ መስዋዕት መሆኑን አልተገነዘብክም? እንዴትስ ትገንዘባለህ፣ የነጻነት ጸር ለሆኑ ነፍጠኞች ዘብ እየቆምክ!? ለዚህም ነው ዛሬም ABO በሰላማዊ መንገድ የኦሮሞን መብት ማስከበር እችላለሁ ብሎ ወደ ሃገር ቤት ከገባም በሁዋላ የደርግ ዘመን “እምቢኝ ሃገር ገንጣይ ወንበዴ!” ፕሮፓጋንዳና ከንቱ መፈክር የምታስተጋባው። መንግስትና የሽብር ሸሪኮቹ የሚፈጽሙትን ውድመት፣ @“ኸረ እኛ እጃችን የለበትም” ስትሉ አንድ ቀንም ሰምቼ አላውቅም@ እያልክ እቶ ፈንቶ ትደረድራለህ። አውቀህ ተኝተህ ወይም በነፍጠኞቹ የሽፋን ጩሄት ደንቁረህ እንዴት ልትሰማቸው?!

  6. “ዖሮሞነት ያለ ኢትዮጵያዊነት ሴንስ የሚሰጠው ሲጀመር በአገረ ኢትዮጵያ ማንነትና ህልውና ስምምነት ሲኖር ነው” የሚለው ዐረፍተ ነገርህ ምንኛ ነው?? ዖሮሞነት/አፋርነት/ሶማሌነት ያለ ኢትዮጵያዊነት ሊኖር አይችሉም ከሆነ ሙግትህ ሂድና የኬንያ ቦረናዎችን፣ የጂቡቲ አፋሮችን ወይም የሃርጌሳ ሶማሌዎችን ጠይቅ! ሲጀመር ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም፣ ሰው ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሊኖረው ይችላል። ዜግነት ደግሞ በሃገሩ ህገመንግስት የሚደነገግ ህጋዊ ማንነት እንጂ በደም የሚገኝ ህልውና አይደለም! መዘባረቁ ይቁም!

  7. “ወደዘመነ መሳፍንት አይነት የምኞት ጉዞ” ብለህ ከምትገረም፣ በአስተሳሰብ በዘመነ ምንሊክ ላይ ቆመህ ቀርተሃልና ዲሞክራሲና ፌደራሊዝም ምን እንደሆኑ በቅጡ ተረዳ! ስለነዚህና ታሪክ፣ ፖሊቲክል ሳይንስ እንዲሁም ሎጂክ የመሰሉ ተያያዥ ጉዳዮች ምናልባት የአንድ አመት ኮርስ እንጂ የኔ ኮሜንቶች ከችግሮችህ ሊያወጡህ አይችሉም!

  8. “የሃበሻ ገዢ መደብ የገነቧት እምፓየር” ስል አማሮች ብቻ ገነቧት ማለት አይደለም። “ሃበሻ” የሚለውን ትርጉም ከላይ ተመልከት! ደግሞም ለሆዳቸው ያደሩ ወዶ ገቦች ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች አልነበሩበትም ማለትም አይደለም። አቅኚው ገዢ መደብ ግን የሃበሻው “ሰለሞናዊ” ስርወ መንግስት ነበር።

  9. አርሲ ሂድና አንዱን የአርሲ ሽማግሌ “ምንሊክ ጡት አልቆረጡም” በላቸው! መልሱን እዚያው ታገኛለህ! “ምንሊክ ኦሮሞንና የደቡቡን ህዝብ አላስጨፈጨፉም፣ ባሪያ አልፈነገሉም፣ ደቡቡን ገባር አላደረጉም” ብሎ መለፈፍ፣ በህዝቡ ስነ ልቦና ውስጥ ተቀርጾ የቀረን አሰቃቂ በደል በመካድ ህሊናችሁን መልሳችሁ አደንቁራችሁ በደሉ የደረሰበትን ህዝብ መልሶ ለመስደብ የምታደርጉት ብልግና ነው!

  በመጨረሻም የምለው፣ በኦሮሚያ የሚትደረግዋን ጥቃቅን ነገር ሳይቀር በመፈልፈል ኦሮሞን እና ድርጅቶቹን ለመወንጀል የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም። ባአንጻሩ ደግሞ በተለይ በአምሃራ ክልል የሚፈጸሙትን ኦሮሚያ ውስጥ ከታዩት በጅጉ የባሱትን እንዳላየህ ሆነህ፣ አሊያም እያደባበስክ ለማለፍ ትሞክራለህ። ለእውነትና ለሃቅ የቆምክ ቢሆን ኖሮ፣ በጉሙዞች፣ በቅማንቶች እና በኦሮሞዎች ላይ (በከሚሴ፣ በደራ እና በካራዩ በኩል) በፋኖዎች እና አሳምነው አሰልጥኖ ባሰማራቸው የአማራ ክልል ልዩ ፖሊስ የተፈጸሙ እና እየተፈጸሙ ያሉትን ጭፍጨፋዎችንና የዘር ማጽዳት ወንጀሎችን በሚመጥን ቋንቋ ትኮንን ነበር። ዳሩ ግን በነፍጥ ከሚያስብና ለዕብሪተኞች ወገን ሽንጡን ገትሮ ከቆመ ‘neo-Nazi’ ይህ አይጠበቅም!
  አበቃሁ!

 6. “አበቃሁ!” ያልካትን ቃል ወደድኩልህ። like አደረግኋት ማለቴ ነው በኢንተርኔት ቆንቃ። በናትህ እንዳበቃህ ቆይልን! አፍህን በከፈትክ ቁጥር ከቁናሣሙ ጭቅላትህ የሚወጣው ጃዋራዊ ንግግር ሁሉ በተለይ በአማራና ኦሮሞ ነገዶች ዕልቂትን የሚያውጅ ነው።እግዜር ጠብቆን እንጅ እንደ አባጫላና ገመቹና በቀለና ሕዝቅኤል … ቢሆን ኖሮማ አንድም አማራ በአሁኑ ወቅት በሕይወት ባልተገኘ። ስለዚህ እንዳበቃህ ቆይ የኔ ሌንጫ ማለትም አንበሣየ። “ንግግርህ እንትን እንትን ይላል”እንደተባለው ጅል አማች ነህ።

 7. Netsanet፣ አባዊርቱ የተላከበት ተልዕኮ ስለከሸፈበት አፈግፍግ ማለትህ ነው? እውነት ካላችሁ በጓዳ ከማሴር ለምን እዚሁ በህዝብ ፊት አታቀርቡትም? ወይስ በድብቅ ሌላ የፕሮፓጋንዳ ሴራ ለመሸረብ ነው??

 8. “እንደ አባጫላና ገመቹና በቀለና ሕዝቅኤል … ቢሆን ኖሮማ አንድም አማራ በአሁኑ ወቅት በሕይወት ባልተገኘ።” ዋቅቶላ፣ እቅጩዋን ዕውነት ስለተናገርን/ ስለጻፍን አማራ የሚያልቅ ከሆነ፣ አማራነት ውሸት ነው ማለት ነው!! Good to know!
  በተለይም ዕውነት እንዴት እንደሚመርህ/እንደሚገማህ አስረግጠህ ነገርከን! አሜን!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.