የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኮርቻ ግድቡ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኮርቻ ቅርፅ ግድብ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ በላቸው ካሳ እንደገለፁት ቀደም ሲል ከ14 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የድንጋይ ጥቅጥቅ ሙሊት ስራ ተከናውኗል፡፡

ከኮርቻ ግድቡ ቀሪ ስራዎች መካከል 30 ሳ.ሜ. ሙሊት ይፈልግ የነበረው የላይኛው አርማታ ሙሊት (ፌስ ስላብ) ስራ ዛሬ ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡ ይህም ከህዳሴ ግድብ ስራዎች መካከል አንዱ ወሳኝ ስራ መጠናቀቁን ያሳያል ብለዋል፡፡ የኮርቻ ግድቡ 97 በመቶ አፈፃፀም ላይ ደረሰ ሲሆን ከዚህ በኋላ ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራዎች ብቻ የሚከናወኑለት ይሆናል፡፡

በኮርቻ ግድብና በዋናው ግድብ ላይ አተኩሮ ሲሰራ የነበረው የሲቪል ስራ የኮርቻ ግድቡ በመጠናቀቁ ዋናውን ግድብ በፍጥነት ለማጠናቀቅ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን አቶ በላቸው ተናግረዋል፡፡

ኮርቻ ግድቡ 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 50 ሜትር ቁመት አለው፡፡

One Response to የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኮርቻ ግድቡ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ

 1. That is great!!!!!!!!!

  You also better unleash to realize the project for interest of millions of poor Ethiopian people.

  Every Ethiopians, scholars, expertise on the project field and diasporas around the world shall support to achieve the project on time.

  Long live to Ethiopia!

  Avatar for Yetesfa Chilanchele

  Yetesfa Chilanchele
  November 13, 2019 at 12:06 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.