በፕሮፊሰር መስፍን ወቅታዊ አስተውሎ ላይ የግርጌ ማስታወሻ ለመጨመር – ነዓምን ዘለቀ

1 min read

“ከአለንበት ማጥ በጊዜ ለመውጣት የምንሻ ከሆነ ያለን አማራጭ አንድ ብቻ ነው። አብይን እስከ ችግሩ ደግፈን ሃሳብ ማንገስ ይበጃል። አብይን ማዳከም አዳዲሶቹን ጉልበተኞች ማጠናከር ነው።”
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

1. ያደራጁት ሃይል በእጃቸው በሌለበት፣ አማራጭ ራዕይና ፕሮግራም ባላዘጋጁበት፣ አገርን ሊያረጋጋ ፣ ሕዝብን ከጥቃት ሊከላከል የሚችል ወታደራዊና የጸጥታ ሃይሎችን ባላሰለጠኑበት፣ በማይመሩበት፣ ለዚህ ደግሞ መንግስታዊ አቅሙም፣ ችሎታም፣ ስትራቴጂካዊ ጥናቶች ሆነ ቅደመ ዝግጅቶች ማንም ምንም በወጉ ባላሰቡበት፣ ባልተዘጋጁበት ሁኔታ በስልጣን ላይ የሚገኘውን ብዙ ተግዳሮቶች የገጠመው ነገር ግን ለውጥን ለማምጣት ደፋ ቀና ሲል የቆየውን የለውጡን አመራር በከፍተኛ ርብርብ ለማዋከብና ለመሸርሸር የተሄደበት ርቀት ትልቅ ታሪካዊ ስሕተት ይመስለኛል።አገራችንን ኢትዮጵያን አጣብቆ የያዘውን መንግስታዊ ሃይል ቢዳከም ፣ እነዚህ የታሪክም የፓለቲካ መሰረት ያላቸው ልዩ ልዩ ቅራኔዎች በየቦታው ቢፈነዱ፣ በህዝብ መካከል የእርስ በእርስ ግጭቶች ቢበራከቱ በብዙ አቅጣጫና ውስብስብ የብሄር ቅራኔዎች፣ ሌሎች ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፣ ማህበራዊ ችግሮች የተጠመደች አገራችንና የኢትዮጵያ ሕዝብ ወዴት ሊወስዱ እንደሚችሉ ከግምት ማስገባት አስፈላጊና ወሳኝ ይሆናል።

2. ዛሬ ትላንት አይደለም። ትላንት የሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ፣ የአብዛኛው የዲያስፓራ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ትኩረትና የትግሉ ግብ ፣ የትግሉም ኢላማ በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሲዘወር በነበረ ግፈኛና ጨካኝ አገዛዝ ላይ ያነጣጠረ እንደነበር የሚካድ አይደለም። ከጎንደር እስከ ሐረር፣ ከባሌ ዶሎ እስከ ወሎ፣ ከሐረር እስከ ባሕር ዳር የኢትዮጵያ ህዝብ ከኦሮሞ እሰክ አማራው፣ ከጋምቤላ እሰከ ሶማሌ፣ ከአዲስ አባባ እስከ አምቦ ትግሉ ከመንግስት ሃይሎች ፣ ከጨቋኝና ግፈኛ ገዥዎችና የመጨቆኛ መስራሪያዎቻቸው ፣ ተቋማቶቻቸው ጋር ሲያፋፍም የነበረ፣ አለፍ ካለም የእነሱ ጥቂት ደጋፊዎች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር የማይረሳ ነው።ዛሬ ግን ቅራኔዎች፣ ግጭቶች፣ ጥላቻው የጎንዮሽ በሕዝብ መካከል ሆኖአል፣ በማህበረሰቦች መካከል ሆኗል። ዛሬ ቅራኔው ለዘመናት አብረው በኖሩ ማህበረሰቦችና በሕዝብ መካከል መሆኑ ነው። ይህ እውነታ በስፋትና በጥልቀት በበርካታ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚታይ እጅግ አደገኛ ሂደት መሆኑ ግልጽ አየሆነ ነው።
3. ይህን ልዩና እጅግ አስጊ ሁኔታ ለመለወጥ ከፍተኛ ጥንቃቄ፣ ዘዴዎች፣ ብልሃቶች ይጠይቃል። መንግስታዊ የማድረግ አቅም የመኖር አለመኖር ብቻ ሳይሆን የመንግስት እርምጃዎች፣ የመንግስት ድርጊቶች ሊፈጥሩ የሚችሉትን አሉታዊ የሆነ የአንድ ወይንም የሌላ ወገን የአጸፋ ምላሽ ለመቋቋም የሚያስችል፣ ያልተጠበቁ ትላልቅ አደጋዎች በህዝብ ላይ እንዳይደርሱም እስቀድሞ ችግሮቹ በቀጥታ የሚመለከታቸውና ከችግሩ ጋር ተፋጠው የሚገኙ የመንግስት መሪዎችና ልዩ ልዩ የመንግስታዊ ተቋማት ሃላፊዎች ሊደረግ ብቻ የሚችል የቢሆንስ ትንታኔም የሚያስፈልገው ነው። የመንግስት መሪዎች ወደ ስልጣን ያመጣቸው ፓርቲና ሕዝብ ውስጥ ያላቸው ቅቡልነት፣ ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብ ዝግጁነት፣ በየጊዜው የሚፈተሽ ዕቅድና ይህንኑ የማስፈጸሚያ/የማድረግ አቅም የሚሰጡ ልዩ ልዩ የመሳሪያዎች ሳጥን በአግባቡና በብቃት ማዘጋጀትን የሚጠይቁ ናቸው።

4. በኢትዮጵያ ሃገራዊ ህልውና ላይ የተደነቀረ ከባድ አደጋ ለመሻገር ከተፈለገ ይህን አደጋ ከሚያባብሱ፣ ከሚቀጣጥሉ ቃላት፣ ቅስቀሳዎች፣ ቁንጽልና በቅጡ ያልታሰቡባቸው፣ ያልተጠኑም በርካታ የሀሰትም ወሬዎች ከማሰራጨት መቆጠብ የግድ ይሆናል። በምትኩ የሚዲያዎችና የማህበራዊ ሚዲያዎች ሚና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ መስጠት፣ ማሕበረሰቦች እንዲቀራረቡ የበኩላቸውን ሚና መጫወት ያለባቸው ይመስለኛል፡፡

5. የሚቀጥለው እሳት ወደ ሰደድ እሳት እንዳያመራ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ ለትላልቆቹ የፓለቲካ ልዩነቶች መፍትሄ ማፈላለግ ያስፈልጋል ። የተጀመረው አዝጋሚና ብዙ ተግዳሮቶች የገጠመው የለውጥ ሂደት ከእናካቴው እንዳይቀለበስ ሁሉም የድርሻውን ማበርከት አለበት ብዬ አምናለሁ። ይህን አጋጣሚ ለመጠቀም ያቆበቆቡ ፣ ይህን ሁኔታ ለመጠቀም ሰሞኑን በሀዘን የተመለከትነውን ጥቃት በማጦዝ፣ በማራገብ ጮቤ የረገጡ ፣ ልዩ ልዩ ዘዴዎችንም በመጠቀም ከተለያዩ የፓለቲካም የሚዲያም ተዋናዮች ጀርባም በመሆን ቅራኔዎችና ችግሮች እንዲሰፉ፣ እንዲባባሱ የእነማን ዘርፈ ብዙ ጥረት እንደሆነ የሚጠቁሙ በርካታ መረጃዎች በየጊዜው እንደሚያሳዩ ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ግልጽ ይመስለኛል። ወደ ሁለንተናዊ ትርምስ ጎዳና ሊያስገባ የሚችል እድል እንዳንሰጣቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ነቅቶ መጠበቅ እንዳለበት በጽኑ አምናለሁ።

6 Comments

 1. I really appreciate Prof. Mesfin’s suggestion to support the current transitional government. Otherwise, we will be facing an unprecedented challenge the country has never faced so far. The best way, as indicated by the known politician, Prof. Mesfin, is to come to our minds/conscience and start to act proactively than opposing and aggravating the existing conflict. As most of us knows, Ethiopia is not a country of uniformity but diversity with opposing groups, history, culture and the like. It needs caution to bring sustainable solution to our contradictions. We will not bring solution by aggravating the existing contradictions, but professional and mature analysis of problems.

 2. Prof. Mesfin you always deserve my respect and appreciation. you have been fighting all the evil leaders, Cadres, bureaucrats, narrow minded hypocrites all your life to bring bright future and change of progress to our country. The PM Dr.Abiy has shortcomings and although he could have formed people like yourself and those who have extensive knowledge as advisors, to help him relieve from some of the complex issues the country is facing. As he nominated more female ministers in his cabinet he could have also created older wiser advisors committee to get experience and courage.We can not afford another innocent civilian death like the one we had recently if the PM Dr. Abiy prioritize the unity of the country than the unity of his party. Party comes after the country.I heard him say we do not need all these hundred something parties for Ethiopia. The Author the late BEALU Girma in his book “DERASSIW” let me call it “THE ROOKY AUTHOR” said while the dad was walking with his daughter past the “Emmanuel Hospital “She asked him what and why and who lives there her dad responded it is a mental hospital for mentally sick. she did not get it when she saw from far the people there, their hairs are disheveled they cry and some are very big. There were two skinny guards for the whole building and the daughter said what if the mentally sick get united and broke free those skinny guard can not stop them she asked. Her dad said mentally sick people do not know to unite and get free that is what the hundred something parties are for me if they prioritize the country before anything else we will not need all those parties and it would have easier for the PM as well to unite the country.
  God bless Ethiopia and its people and may those who passed rest in peace.

  Mesfin Abbai Kassa
  Ottawa, Canada.

 3. Abiy has become (or was he from the beginning?) the Trojan horse of anti-democratic and anti-federal unitarist Habesha extremist groupings like EZEMA and NaMA. Moreover, blinded by an infantile dream of becoming Ethiopia’s 7th Caesar, he sidestepped parliamentarism and the constitution of the country! Instead of quickly putting in place the state structure necessary for a political transition, he spent and still spends his time in personal image building.

  He is acting like a brutal dictator, putting part of the country under martial law (Oromia and the South), while being too soft on the Amhara Region where a rogue paramilitary, trained and organized by the late rebel General Asaminew, is conducting widespread mass killings and ethnic cleaning against minorities in Amhara region. The Tigrai region has remained from the outset outside his control. At the same time, most of those who have committed barbarous human rights violations, or denied the administration justice, or plundered the wealth of the country through state capture remain at large or have even been promoted within the state heirarchy.

  The whole scenarion is such that the state itself is acting outside the law and thus can not fight lawlessness! Ethiopia is heading towards being a failed state, if not already so.

 4. This is crucial issue that we have failed state and the current leaders can’t bring democracy among the destitute of the community in Ethiopia. Some of the leaders are seeking to address ethnic al issues and can’t bring unification among the marginal community of the country.

  Moreover, people are dying and Orthodox churches are destructed and Orthodox church leaders are dying every day and the country is lawless this time. It is possible to say that the country has no genuine leader and more of these leaders are with political conspiracy leading the country to the worst phase.
  Hence, the best choice of the country is to establish transitional government which costitute all polical parties

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.