በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ላይ ሰኔ 15 ከተፈፀመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከሰጠው መግለጫ

1 min read

ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 70 ተጠርጣሪዎች መያዣ ወጥቶባቸው 31ዱ በቁጥጥር ስር ውለዋል

የ147 ሰዎችን ቃል መቀበል ተችሏል

የ22 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሂሳብ ታግዷል

ወንጀሉን ከሚያዚያ ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለመፈፀም ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል

ጥቃቱ በብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ መሪነት የተፈጸመ ነው

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ማጣራት ተደርጎ ከተጠርጣሪዎቹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች፣

በርካታ ተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ የውጭና የሃገር ውስጥ ገንዘብ፣ 5 ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ በርካታ ቁሳቁሶች በኤግዚቢትነት ተይዘዋል

በወቅቱ በስራ ላይ የነበሩ 4 ጠባቂዎችን ጨምሮ 8 አጃቢዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል

የፌዴራል ፖሊስ፣ መከላከያና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች የተቃጣውን ጥቃት ቀልብሰውታል

ድርጊቱ መንግሥትን በኃይል ለመቆጣጠር የታቀደ የመፈንቅለ መንግሥት ነበር

15 የሰው ሕይወት ሲያልፍ 20ዎቹ ቆስለዋል

ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ በተንቀሳቀሱት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ለመመስረት ዝግጅት ተደርጓል።

 (ጌጡ ተመስገን) 

15 Comments

 1. Pleaseeeee

  Next the prosecutor might say, it was also Asaminew who led the attack on civilians in Debre Berhan , Kemise , Ataye and other nearby regions.

   • Fitaw

    If only General Asaminew was still alive till this day, the Getachew Assefas right hand man previously whomturned into Abiys rightnhandman now , the ODP member the now Prosecutor in Charge Ato Berhanu Tsegaye would have accused General Asaminew for all the massacares that are being committed in Ethiopia until now.

  • Yes, he had trained over 35,000 strong Amhara Liyu Hayl with the budget of the Amhara Kilil! He used this paramilitary to conduct his Coup d’Etat. Part of his coup followers are still at large.

   • ABA Caala

    Meles Zenawi raised / trained Abiy Ahmed team Lemma.
    Mengistu Hailemariam trained many, including the highly trained ranking air Force pilots which Meles Zenawi depended upon during the fight against Ethio-Eritrean Badme war.

    Hailesselasie trained Mengistu Hailemariam and Isayas Afeworki…

    PEOPLE GOT THEIR OWN MIND REGARDLESS WHO TRAINED THEM THEY CAN CHOOSE WHICH TRAININGS THEY RECEIVED ARE GOOD AND WHICH ARE NOT SO THEY HOT THE FREEWILL TO.CHOOSE WHICH TRAININGS TO APPLY AND WHICH TRAININGS TO ABANDON..

    Liyu Hayl that were trained by Asaminew doesn’t mean a thing as long as they did their jobs of protecting Amara, which they proven to do so .

    Abiy Ahmed sent troops to Ataye , Debre Berhan and Kemise areas to fight Liyu Hayl so the Civilians getting massacqred don’t get help ,if Liyu Hayl tried to save the innocent civilians that were being massacred Abiys troops we’re ready to attack them while the massacre in the civilians were being carried out. The proof of Abiy ordering not to save the civilians was in the hands of Saere which then reached Asaminew and Ambachew so Abiy shut them up all..then this prosecutor using the old habits is accusing the victim Asaminew as the criminal making itore obvious that he is not reformed he is sticking to his old evil ways of prosecution he learnt from Getachew Assefa ..

    This ODP backed Prosecutor who previously was trained by Getachew Assefa how to lie now Abiy right hand man is definitely trying to cover up the messy crimes of Abiy with more scandal defaming Asaminew. .

 2. SHAME ON YOU LIAR OLF CADRE BREHANU TESGAYE: YOU LIED FOR 27 YEARS, AND AS OLD HABITS DO NOT DIE, YOU CONTINUED WITH YOUR WHITE LIE.

  IN FACT, I AM NOT SURPRISED BY WHAT THE OLF CADRE LIAR BREHANU TESGAYE SAID AS THAT IS WHAT ONE EXPECTS FROM A DUMB OLF GUY.

  HOWEVER, I AM VERY, VERY DISAPPOINTED BY WHAT THE SELL OUT AND TRAITOR ABERE ADAMU IS DOING. WE WILL SEE TOMORROW WHERE YOU ARE GOING TO LIVE. EITHER YOU WILL GO BACK AGAIN TO SWEDEN OR ASK ASYLUM AT “FREE OROMIA”. BELIEVE ME, THEY WILL LAUGH AT YOU. YOU KNOW THAT YOU WILL NOT LIVE WITH THE GREAT AMHARA PEOPLE AS WE HAVE ALREADY DISOWNED YOU

   • Low IQ chala Cheka: did not your liar low life uncle share you the secrets.
    Our Dr. Amachew and co as well as heroes General Asaminew were assassinated by a conspiracy organized by OLF and TPLF insects.

   • Berhanu Tesgaye is lying again.

    The OLF cadre, so called attorney general, is lying again with the intenion of dividing the Amhara people at this difficult time, and assassinating the characters of our HERO GENERAL ASAMINEW TISGIE.
    This dirty low-IQ OLF cadre has been one of the authors of the fake film against Muslim Ethiopians, Adnaragachew Tisge etc and he is at it again.

    THE EGALITARIAN AMHARA PEOPLE: Be wise, do not get trapped by this sabotage, rather stand together and crush your enemies as you have done it time and again.

    We know who killed our Amhara heroes and it will be revealed when the right time comes.

 3. They blaming the victim because he can not defend himself. Does the victim General Tsigie has a defender? They are blaming him because he is dead. All is done by Abiy, Demeke, Gedu, … all the rest is fake or fabrication.

 4. በወንጀል ድርጊት የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው በህግ አግባብ መጠየቅ አለበት በሚለው ሁሉም ህሊና ያለው ሰው ይቀበለዋል፡፡ ጠ/አቃቤ ህግ ያወጣውንም መግለጫ ከነችግሮቹ እቀበለዋለው፡፡
  ነገር ግን
  1. ለምን በዚህ ሰዓት ይህን መግለጫ ማውጠት ተፈለገ የሚለውን ግን ህሊናዬ መልስ ሊያገኝለት አልቻለም
  2. በህዝብ ደም ሲሳለቁ የነገሩ ወንጀለኞች መቀሌ መሽገው ሳለ ለምን በውስን ሰዎች ላይ ብቻ ህጋዊነትን ለማትረፍ ፈለጋችሁ፡፡ ይመስለኛል ወያኔን ሰሞኑን ገዳዮቹ ይገለጹልን ስላለ እነሱን ለማስደሰት ሊሆን ይችላል ብዬ ባስብ ተገቢ ጥርጣሬ አይደለም እንደማትሉኝ ነው
  3. በኦሮሚያ ክልል ሰሞኑን የ86 ሰዎች ህይወት የቀጠፈ ድርጊት መፈጸሙ አይዘነጋም፡፡ ህዝቡ፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች ጭምር ለዚህ ድርጊት አነሳሽ የሆኑትንና የተሳተፉትን ለፍርድ አቅርቡልን ብለዋል፡፡ 400 የሚጠጉ ሰዎች ተጠርጥረው መያዛቸውን ተገልጻል፡፡ ግን አዝማቹን ትቶ ዘማቾቹን ብቻ መያዝ ፍትህ መዛባቱን አያሳይምን
  4. በመጨረሻም ማንም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው እየተባለ በናንተ መልካም ፍቃድ ብቻ ስትፈልጉ ልትከሱ/ልትይዙ፣ ሲያሻችሁ ደግሞ ወደ ህግ ፊት የማታቀርቡ ከሆነ እንዴት አድርገን በመንግስት ላይ እምነት ሊኖረን ይችላል፡፡
  5. የህግ የበላይነትን የማስከበር ሃላፊነት ለፌዴራሉና ለክልል መንገስታት የተሰጡ ናቸው፡፡ በየአጋጣሚው መንግስት የህግ የበላይነትን ማስከበር አቅቶታል ሲባል እንሰማለን፡፡ ይህን አቤቱታ ከመቀሌ ጭምር ነው እየሰማን ያለነው፡፡ ለመሆኑ ክልል መንግስታት በምን ያህል ደረጃ ህግን እያከበሩና እያስከበሩ ይገኛሉ፡፡ ችግሮች (ግድያ፤ ዝርፊያ፣ ማፈናቀል፣ የመሳሰሉት) ያሉት ክልሎች በሚመሩት መስተዳድሮች ሆኖ ሳለ የሁሉም ሰው አቤቱታው ፌዴራል መንግስቱ ላይ መሆኑ የህግ የበላይነት አፈጻጸም ክፍተት እንዲኖረው አስችሏል፡፡ ይሄ ሸፋፋ አስተሳሰባችን መቼ ነው ተቃንቶ ክልሎች የህግ የበላይነትን ማስከበር ባለመቻላቸው ሰላማዊው ህዝብ መከራውን እየበላ እንደሆነና ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ክልል መንግስቱ ሹም ድረስ መታረም የሚገባቸውን ነቅሰን ለራሳቸው መንገር የምንችለው፡፡ እባካችሁ ስራ በዋናነት ያልተሰራው ከቀበሌ ጀምሮ በክልሎች በመሆኑ እዚያ ላይ ብናተኩር፡፡ በክልሎች ለሚደርሰው የህግ ጥሰት ሁሉ ፌዴራሉን መንግስት ተጠያቂ ባናደርግ መልካም ነው፡፡

 5. አሁን ማን ይሙት አዕምሮ ያለው ሰው የዚህን ምርመራ ውጤት አምኖ ይቀበላል? ግን ሴራው ሥር የሰደደ እና የተቀነባበረ በመሆኑ ገዳዮቹ እነርሱ፤ መርማሪዎቹ እነርሱ፤ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጡት እነርሱ በመሆናቸው ምንም ዓይነት የገለልተኛ ወገን ጉዳዪን እንዲያጣራ ቦታ አይሰጥም። የፈጠራውን መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አቀናበሩት የሚባሉት የአማራ ተወላጆች ጭራሽ የሌሉበት ግድያውና ትርምሱ በፌዴራል ደረጃ የተከናወነ ወንጀል ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። የምርመራ ውጤቱ ግን አንድ ነገር ላይ ያተኮረ ነው። የችግሩ ሁሉ ምንጭ “አማራ” ነው ይለናል። በዚህ ላይ ሰው ማስተዋል ያለበት ቀሪው የሃገራችን ህዝብ በአማራ አመራርና ህዝብ ላይ አሜኔታ እንዲያጣ ሆን ተብሎ በተጠነሰሰው ሴራ የሃገሪቱን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የገደለው የአማራ ተወላጅ ነው። የሞቱት የትግራይ ተወላጅ ናቸው በማለት በሁለቱ ህዝቦች መካከል ብልጭ ብልጭ የምትለውን የሰላም ብርሃን ያዳፈነ የውሸት ፓለቲካ ነው። ቀጥሎም ሲያትት የአማራ ባለሃብቶች ለመፈንቅለ መንግሥቱ ገንዘብ በማዋጣት እንደተባበሩ ይጠቅስና የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ የሆኑ ድርጅቶችን እንደ አብን የመሳሰሉትን ይኮንናል። ይህ የውስልትና ፓለቲካ ነው። ሰው በክፍለ ሃገር ( በወያኔ ቋንቋ በክልል ደረጃ) መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አያደርግም። አሁን አፈር የመለሱበት ጄ/ል አሳምነው ጽጌ ግርግሩ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በህዋላ አንዲት ጋዜጠኛ በመደወል እዚህ መፈንቅለ መንግሥት እየተደረገ ነው ይባላል እርስዎ እንዴት ያዪታል ስትለው ጄ/ሉ ” በመንደር ውስጥ መፈንቅለ መንግሥት ይደረጋል እንዴ?” በማለት ጥያቄዋን በጥያቄ እንደመለሰው ህዝባችን ያስታውሳል።
  የፈጠራው መፈንቅለ መንግሥት ምርመራ ውጤ ሌላም የሚነግረን አለ። አንድ የኦሮሞ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንንም በሴራ ውስጥ ሊገደል ነገር ይለናል። አይ ውሸት። የሰውን አንገት በሰላ ነገር የሚቀነጥሰውና አሁን በተለያዪ የትምህርት ተቋማት ዘርና ቋንቋን ተገን አርጎ ሰውን የሚያሸብረውን የኦሮሞ መንጋ በዝምታ እየተመለከተ ራሱ አቡክቶ የጋገረውን የፈጠራ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ምርመራ ውጤት ስሙኝ ቢለን ከማያልቀው የውሸት ስልቻ የቆነጠረው የገመና ወሬ እንጂ ፍትህ ለማንም አይሰጥም። የሚሰማም የለም። ኢንጂኒየር ስመኘው ራሱን ገደለ በማለት አፉን ሞልቶ ሰውን ያታለለ መንግሥት ማን ያምነዋል? የዚህ የፈጠራ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሴራ ግን አላማና ግቡ የአማራን ህዝብ አዳክሞ፤ በሌሎች ወገኖቹ እንዲጠላ የሚያደርግ፤ ለአማራ ህዝብ የሚያስቡና የሚቆረቆሩትን በፈጠራው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ለእሥራትና ስቃይ የሚዳርግ ቀደም ብሎ ታልሞ የተዘጋጀ ሰነድ ነው።
  የዶ/ር አብይ መንግስት አድሏዊ ለመሆኑ በጃዋር ጥሪ ያለቁትን ሰዎች የስም ዝርዝር በዘርና በሃይማኖት ከፍሎ ብዙ የሞተብን እኛ “ኦሮሞዎች” ነን ካለን ወዲህ ነው። ወንጀል ለሚሰራው ጥበቃና ከለላ። ለሃገር አንድነትና ህብረት ለሚታገሉት እንግልትና ድብደባና እስራት። አይ ለውጥ። ድንቄም ለውጥ! ሰው በዘሩ የተሰለፈባት ይህች ምድር መቼ ይሆን የመጠላለፍ ፓለቲካ ቆሞ ህዝባችን በፈለገው ሥፍራና ጊዜ አንገቱን ቀና አርጎ የሚራመደው? የዶ/ር አቢይ መንግሥት በሰዎች ላይ የሚፈጸመውን ግፍ መግታትና የቀን ተቀን አሸባሪዎችን በቁጥጥር ስር እስካላዋለ ድረስ በፈጠራ የፓለቲካ ትርክ ሃገርንም ሆነ ህዝብን መጥቀም ጭራሽ አይቻልም። ጎበዝ በምድሪቱ እውነት የለም። ሰው በዘርና በእምነቱ እየሞተ ነው። ልብ እንበል። ኢንጂኒየር ስመኘው ሲሞት በቦታው ማን እንደተተካ። ጄ/ል ጻዕረ መኮነን ሲገደሉ ማን እንደተካቸው ማስተዋል አለብን። የወያኔስ ፓለቲካ ከዚህ በምን ከፋ? ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ እንዲሉ ነው። የምርመራ ውጤት የተባለውም አንድን ህዝብ ለማዳከም ሆን ተብሎ የተሸረበ ሴራ ነው። በምድሪቱ ህግና ስርዓት የለም። የኦሮሞ ፓለቲከኞች በሁለት ነገር ሰክረዋል። በዘር ፓለቲካና በሥልጣን ጥም። ወቸው ጉድ እንዲህም ብሎ አፍቃሪነት የለም። የጅሎች ፓለቲካ!

  • Yes, except the conspiracy theorists like you! For conspiracy theorists, every thing is fraudulent except what they themselves imagine or fabricate.

 6. When bomb was thrown at Prime Mischiefer Abiy Ahmed in Addis Ababa with the people who threw the bomb getting caught red handed, Abiy said my team of federal investigators are not to be trusted and went to ask the United States Federal Bureau of Investigation (FBI) to carry out the investigation.

  Despite the repeated call from many human rights advocates and political parties demanding independent investigators to conduct the “Coup generals and Ambachews murder” investigation ,Abiy decided to go with Berhanu Tsegaye for this investigation , all of a sudden Abiy developing trust for the same individuals he didn’t trust to investigate the murder attempt of his own. It DOESNOT make sense. Berhanu Tsegaye is the same Berhanu Tsegaye .

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.