“200 ሚሊዮን ብር በሚገመት ወጪ በአርባ ምንጭ ቤ/ክርስቲያን እያስገነባች የምትገኘው ብርቷዋ ሴት

1 min read


ወ/ሮ ቤዛወርቅ መኮንን ይባላሉ። በአርባ ምንጭ ግንባታው በቅርብ ጊዜ ተጀምሮ ወደመጠናቀቁ የተቃረበውን የዝጊቲ አቡነ-ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳምን ህንጻ ቤተክርስቲያን፣ ግዙፍ አዳራሽ፣ ብዛት ያላቸው የዕንግዳ ማረፊያ ክፍሎችን በማስገንባት ላይ ይገኛሉ።

ወ/ሮ ቤዛወርቅ ከአርባ ምንጩ ዝጊቲ አቡነ-ገብረመንፈስ ቅዱስ አጥቢያ ጋር የተዋወቁት እርሳቸው በጡት ካንሰር ልጃቸው ደግሞ በጣፍያ ካንሰር በሚሰቃዩበት ወቅት ፈውስን ፍለጋ ወደገዳሙ በመጡበት ወቅት ነበር።

እርሳቸውም ሆኑ ልጃቸው ህመማቸው በመጨረሻው የካንሰር ደረጃ ላይ የደረሰ ነው ተብሎ በህክምና ተቋም ቢነገራቸውም የዕምነቱ ተከታዮች “ታዓምረኛው የፀበል ሥፍራ” ብለው ወደሚጠሩት ዝጊቲ አቡነ-ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም መጥተው እንደዳኑ ምስክረነታቸውን ሰጥተዋል።

ከዚህ በኋላ ነው ወ/ሮ ቤዛወርቅ እኔና ልጄን ላዳነኛ ፈጣሪ ክብር ይሆን ዘንድ ከአርባ ምንጭ ጥቂት ኪሎ ሜትሮችን ወጣ ብላ በምትገኘው ገጠራማ ሥፍራ የምገኘውን ገዳማ ህንጻን ላማስገንባት ቃል የገቡት።

ወይዘሮዋ ካላቸው ጥሪት እና በሚታስተባብሩት ገቢ ብቻ 200 ሚሊዮን ብር የተገመተውን የአርባምንጭ ዝጊቲ አቡነ-ገብረመንፈስ ቅዱስ ህንፃ ቤተክርስቲያንን፣የፀበልተኛ አዳራሽ፣የእንግዳ ማረፍያ እና የይዞታ ማስፋፍያ ስራዎችን እየሰሩ የሚገኙት።

አሁን ላይ የዚህ ቤ/ክርስቲያን ግንባታ ሥራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል። ቅዱስ ፓትሪያሪኩን ጨምሮ ሌሎች ብጹዓን አባቶች ተገኝተው ምርቃቱን ያበስራሉ ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል።

ጋሞ ከጥንታዊቷ የብርብር ማርያም ገዳም አንስቶ እስካሁን ዘመኖቹ የዚጊቲ አቡነ-ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም ድረስ በዕምነቱ ተከታዮች በብዛት የሚጎበኙ በርካታ ጥንታዊ ሀይማኖታዊ ሥፍራዎች አሏት። በተለይም ወደ አርባምንጩ ዝጊቲ አቡነ-ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም ከተለያዩ ክፍሎች የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል። ይሄም አካባቢው በመንፈሳዊ ቱሪዝም መዳረሻነት ተመራጭ እንዲሆን እያደረገው ይገኛል።

[መረጃው የቤተክርስቲያኒቱ መረጃ ገጽ ነው]

4 Comments

 1. W/O Bezawork what a devout spiritual lady and MOM and a perfect example of strong faith and perseverance.
  If you decide to do and contribute to a good cause heavenly intervention will take over to complete the blessed cause.
  May the blessing of your strong faith and prayer protect Ethiopia and its people from some evil intentions that is going at present, hatred, jealousy and disunity. As a devoted woman you passed all the hardship and difficulty is a sign The Almighty Lord had a plan to use you for this holly and blessed historic action.
  Thank you and when time permits we will come visit and receive a blessing from ABUNE GEBREMENFESKIDUS.
  GOD bless you and your family and all who participated with you.
  MESFIN & TSEGE
  OTTAWA, CANADA.

 2. በመጀመሪየያ ወ/ሮ ብዙወርቅ እንኳን አንቺንም ልጅሽን እግዚአብሄር ማራችሁ፡፡ ለእርሱ ምን ይሳነዋል ፡፡ በመቀጠል ለፈጣሪ ምስጋናሽን ለማቅረብ የጀመርሽው ሥራ ደግሞ እጅግ ስሜትን ይነካል፡፡ ክርስትና ማለት ይሄ ነው፡፡ በጣም እድኛ ስለሆንሽ ልትደሰች ይገባሻል ፡፡ ኦርቶዶክሳችን እውነተኛ እምነት እንደሆች ለተጠራጣሪዎች ምስክር ሆነሻል ፡፡ በርቺ ፡፡

 3. ድንቅ እምነት፣ ከሥራ ጋር የታየበት
  ብርቱ ሴት በ200 ሚሊዮን ብር ቤ/ክ አስገንብቼ እጨርሳለሁ ብለው የተነሳሱ፡፡ አሁን በሁሉም የአገራችን ክፍል የምንገኝ ኢትዮጵያውያንና አማኞች፣ በአርባ ምንጭ የምንገኝ ነዋሪዎች እኚህን እህታችን ለምን አናግዛቸውም፡፡ ማድነቅ ብቻ ሳይሆን ባለን አቅም እንተባበርና ህልማቸውን እናሳካ
  ወ/ሮ ብዙወርቅም የባንክ አካውንትዎን ያሳውቁን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.