አማራ ሆይ! ሰው እንሰሳ ነው! – በላይነህ አባተ

1 min read

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

“እግዚአብሔርም ..ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር” አለና እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ ፈጠረው፡፡ ዘፍ ፩፡ ፳፮-፳፯. ይህ መለኮታዊ ቃል አማራ ክስድስት ሺ ዘመናት በላይ ኑሮህን የመራህበት ቃል ነው፡፡ በዚህ ቃል መሰረትም ሁለት እጅ፣ ሁለት እግር፣ ሰላሳ ሁለት ጥርስና እሚናገር ምላስ ያለውን ሁሉ እንደ ሰው በመቁጠርና በሰው አካልም “እግዚአብሔር አለ” እያልክ ለብዙ ሺ ዓመታት ለአደጋ ስትጋለጥ ኖረሃል፡፡ በዚህ ዓለምን ሰይጣን በሚያስተዳድርበት ዘመን ሳይቀር “ሰውን እግዚአብሔር ባምሳሉ ፈጠረው!” እያልክ እንደ እብራውያን የመሰደድና እንደ አረማውያን የመጥፋት አደጋ ተደቅኖብሃል፡፡

ተንኮልና ደባ ሸርቦ የመጣውን ሰው መሳይ ፍጡር ሁሉ የእግዚአብሔር እንግዳ እየመሰለህ ለለበጣ “ቤተ-ለእቦሳ!” ሲልህ “እምቦሳ እሰር” እያልክ ተቀብለህ ምርጥ ምርጡን እያበላህና ከአልጋህ እያስተኛህ ያሳደርከው እንግዳህ ሲያሰቃይህና ጦርነት ሲከፍትብህ ኖረሃል፡፡ ጦርነት ከፍቶብህ ያስጨነከው ጣልያን “በማርያም ይዤሃለሁ!” እያለ ማተብህን እንደ ድክመት ቆጥሮ ሊያታልልህ ሞክሯል፡፡ እንደ ጣልያን ሁሉ የጣሊያን ትርጁማንና እንቁላል ቀቃይ ልጆች ይኸንን መለኮታዊ ባህልህን እንደ ድክመት ቆጥረው ከቤትህ እየበሉና እያደሩ አንዳንድ የተረገሙ ልጆችህን በሆዳቸው ገዝተው አንተን የሚጠልፍ ወጥመድ ዘርግተው ዛሬ ካለህበት መቀመቅ ዶለውሃል፡፡ በእንግድነት ተቀብለህ ከምግብህ፣ ከመጠጥህና ከጥበብህ ያካፈልካቸው እርጉሞች በአያቶችህ ደም በከበረችዋ አገርህ “ሰፋሪን አባር” እያሉ የጎዳና ተዳዳሪ አድርገውሃል፡፡

አማራ ሆይ! በምድር ያለው ሕዝብ እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠረው ቢሆን ኖሮ እንኳን ክልል የአገርና የአሀጉርስ ድንበር ይኖር ነበር ወይ? ዛሬም “ሰው”ን ሁሉ እግዚአብሔር በአምሳሉ ፈጠረው በሚል ፍች የሌለው ህልም እየዳከርክ ነወይ? እግዚአብሔር አይምሮ የሰጠን ሰው የሆነውን ሰው ታልሆነው፣ ክፉውን ከደጉ እንድንለይ አይደለም ወይ? እና ይኸ የሰላሳ ዓመታት መከራህም እግዚአብሔር በአምሳሉ ያልፈጠራቸው ሰዎች እንዳሉ አላስተማረህም ወይ?

መከራና ደስታን አብሮ ያሳለፈን ህዝብ በድንጋይ ቀጥቅጦ ገድሎ እንደ በግ ዘቅዝቆ የሚሰቅል ጭራቅ እግዚአብሄር በአምሳሉ ይፈጥራል ወይ? ሴት ልጅ እንደተኛች ወግሮ ገድሎ ጨቅላ አለእናት የሚያስቀር አረመኔ አምላክ በአምሳሉ ይፈጥራል ወይ?

በበደኖ ባለቤቷን ገለውና አስራ ሶስት ልጆቿ እያሉ የአርባ ዘጠኝ ዓመት እናትን ተሰልፈው በየተራ የሚደፍሩ ከሃምሳ በላይ ታጣቂዎች እግዚአብሔር ይፈጥራል ወይ? ልጆችህን ከነነፍሳቸው ከፈላ ወደ ቀዝቃዛ ውሃ እየከተተ እንደ ዶሮ የሚገሸልጥ፣ በብልታቸው የሞላ ኮዳ እያንጠለጠለ እግዚአብሔር የፈቀደውን ዘር እንደ ኩራዝ እሚያጠፋ፣ ዓይናቸው እያየ ህብለ- ሰረሰራቸውን እየቆረጠ ሽባ የሚያደርግና እግርን እሚቆርጥ፣ በቁማቸው ዓይናቸውን መንቅሮ እንደ ድንች እሚያወጣ ጭራቅ ዲያብሎስ እንጅ እግዚአብሔር ይፈጥራል ወይ? ቤታቸውን በግኒደር እንደ ቋጥኝ ፈንቅለው ሴት ልጆችህን እንደ ፈረስ ከመስክ እንዲወልዱ የሚያደርጉ አውሬዎች ሰይጣን እንጅ እግዚአብሔር ይፈጥራል ወይ?
ቅዱሱ መጽሐፍ እንደሚለው እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በአምሳሉ ነው፡፡ “እግዚአብሔር ሰውን ባምሳሉ ፈጠረው!” ውስጠ ወይራው ሲገለጥ በእግዚአብሔር አምሳል ያልተፈጠረ ፍጡር ሰው አይደለም ማለት ነው፡፡ አማራ ችግርህ በእግዚአብሔር አምሳል ያልተፈጠረን ፍጡር እንደ ሰው መቁጠርህ ነው፡፡ የመከራህ ሁሉ መንስኤው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን ሰው በዲያብሎስ አምሳል ከተፈጠረው ሰው መለየት አለመቻልህ ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰው ዲያብሎስ ከፈጠረው ሰው መለየት ከቻልክ እዳው ላንተ ገብስ እንደሆነ ቱርክም፣ ግብጥም፣ ጣልያንም የሚያውቀው ነው፡፡

ዲያብሎስ በአምሳሉ የሰራው ሰው ጉልበት ሲያገኝ በመንጋጋው ሰው እሚግጥ አውሬ ጉልበት ሲያጣ ደሞ በፊት ጥርሱ ሳር እሚግጥ እንሰሳ ነው፡፡ ሳይንስም ሰውን እሚያውቀው በእንሰሳነቱ ነው፡፡ የሳይንሱ ሰው እንደ ጅብ ካሉ እንሰሳት እሚለየው ለህሊናና ለይሉኝታ የሚታዘዝ እውቀትና ጥበብ ስላለው ነው፡፡ ህሊናና ይሉኝታ የሌለው ሰው ሲጎለብት አውሬ ሲደክም ከብት እሚሆን እንሰሳ ነው፡፡

አማራ ሆይ! እየኖርክ ያለኸው ይህ ሲጠግብ አውሬ ሲደክም ደሞ ከበት የሚሆን እንሰሳ በሚገዛት ዓለም ነው፡፡ በዚች ዲያብሎስ በአምሳሉ በሰራው አውሬ በሚቆጣጠራት ዓለም እግዚአብሔር በአምሳሉ የሰራው ሰው ሆኖ መገኘት እሚጠቅምህ ምናልባትም በሰማይ ቤት ብቻ ነው፡፡ ይህ አጉል ብጽዕና በምድር የሚያስከትለው መጥፋትን ነው፡፡ በዚህ አጉል ብጽዕና ተሸፍነህ ዲያብሎስ በአምሳሉ የሰራውን ሁሉ እንደሰው መቁጠር ከቀጠልክ እንደ ጀመርከው መንምነህና ሳስተህ እንደ በራ ማለቅህ ነው፡፡

አማራ ሆይ! ተማለቅ የምትተርፈው ዓለም በዲያብሎስ “አምላክነት”ና በአውሬዎች አዳኝነት የምትገዛ መሆኗን ተገንዝበህ ዲያብሎስን በፀበል አውሬንም በነፍጥ ተመከትክ ብቻ ነው፡፡ አውሬ አፉን እንደ ሰማይ ቦርግዶ፣ አቀንጣጤውን እንደ ጦር አስልቶ፣ ጥፍሩን እንደ ወስፌ አሹሎ ከጭራቅ ከፍቶ ሲመጣብህ በውይይት፣ በምክክር፣ በእርቅና በፍቅር ለመመለስ መጃጃል ፈጣሪንም መፈታተን ነው፡፡ ፈጣሪ ለእባብ እንዳዘዘው ከአውሬ መግባባት እምትችለው አውሬ በሚገባው ቋንቋ ብቻ ነው፡፡

አማራ ሆይ! ጅብ ሊበላህ ሲመጣ በክርስቶስ፣ በማርያም፣ በቅዱሳን መላእክት እለምንሃለው ብትለው አይሰማህም፡፡ በሽምግልናም አይለመንህም፡፡ ዳኛ የለም እንጅ ለዳኝነትም አይገዛም፡፡ ጅብ ለፈሪም ሆነ ለማኝ አይሸሽም፡፡ ተጅብ የምትገላገለው “እግዚአብሄር ሆይ ይኸንን አውሬ እንድቋቋመው ጉልበትኑና ብርታቱን ስጠኝ” ብለህ ስትተናነቀው ነው፡፡

አማራ ሆይ! ድክመትህን ደጋግመህ አጢነው! ትልቁ ድክመትህ “እግዚአብሔር ሰውን ባምሳሉ ፈጠረው” እያልክ እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰው ዲያብሎስ ከፈጠረው ሰው አለመለየትህ ነው፡፡ ይህ ድክመትህ የሚጠገነው እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰው ዲያብሎስ ከፈጠረው ሰው ለመለየት ዓይንህን እንደ ባውዛ ያበራህ እለት ነው፡፡ ድክመትህን ጠግነህ እንደ እብራውያን ከመሰደድ፣ እንደ አረማያንም ከመጥፋት የምትድነው ዲያብሎስን “ቿ!” አርገህ በፀበል ስታጠነፍገው አውሬንም “ዘራፍ!” ብለህ በሚገባው ቋንቋ ሰምና ወርቅ ስታናግረው ነው፡፡

አማራ ሆይ! አትዘንጋ! የዛሬ ሰው ሲጎለብት በመንጋጋው ሰው እሚግጥ አውሬ ሲደክም ደሞ በፊት ጥርሱ ሳር እሚግጥ እንሰሳ ነው! የዛሬ ሰው በእግዚአብሔር አምሳል ያልተፈጠረ እንሰሳ ነው! ህልውናህና ክብርህ እሚከበረውም ይኸንን ተገንዝበህ አውሬን በአውሬነቱ ስታስተናግደው ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

ህዳር ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

6 Comments

 1. Yes there are many crimes committed by amhara extremistswhile still claiming they are christians; They killed many innocent people with machetes and some were stoned to death. etc

 2. “ሰው እንስሳ ነው”! እሺ አማራስ ምን ሊሆን? የተለየ ፍጡር?? ምን ያህል ተምታቶብሃል ጃል!??

 3. ዛሬም ወደፊትም እኔን በሃበሻው ጉዳይ የሚገርመኝ አንድ ነገር አለ። ያም በዘር ተሰላፊነትና እውነት ፈጦ እያዪ ነገር መዘባረቅ ነው። አሁን ከዚህ በላይ “አክሎግ” በሚል ስም የጻፈው ሰው ከአእምሮ ድውያን አንድ ነው። የሚታይና የሚዳሰስ ነገር ለማየት አይኑን ጨፍኖ በጨለማ የሚሄድ የዘር ሰካራም። አስቴር ስዪም (ወይም የወያኔ አረመኔዎች በሚጠሯት ጥቁር ድንጋይ) በመባል የምትታወቀው የወያኔ መከራ ገፈታ ቀማሽ እህታችን በእንባ የደረሰባትን በከፊል “ኑሮ በዘዴ” በተባለ ፕሮግራም ላይ ስታካፍል አንድ ጠማማ የወያኔ ፓለቲከኛ የሄይስ ተክሉ በማለት የሚከተለውን ጽፎ ለጥፏል። “ነፍጠኛ ጥሩ ድራማ ሰሪዎች ናቸው” ይለናል። ወያኔ አረመኔ እንደሆነ አእላፍ መረጃዎች ይመሰክራሉ። እስኪ ልጅቷ ከተናገረቸውና ሌሎች በወያኔ ጨለማ ቤቶች በደል የደረሰባቸውን ሲዘረዝሩ ከሰማነው እንጥቀስ።
  1. ልብስ አስወልቀው ብልትን በእንጨት እየነካኩ መሳቅ
  2. በበረዶ በተዘጋጀ በርሚል ውሃ ውስጥ ሰውን ለተወሰነ ጊዜ ከቶ ( hypothermia) በታሳሪው ላይ ከተከሰተ በህዋላ ዝሙት ማረግ።
  3. ውስጥ እግርን በኤሌክትሪክ መጥበስ
  4. ጀርባን በጫማ መምታት
  5. አፍን፤ አይንን አስሮ በሆድ በማስተኛ ልዪ ልዪ ነገሮችን በታሳሪ ላይ መፈጸም
  6. ሴት መርማሪ አምጥተው ሽንቷን በሌላው እስረኛ ላይ እንድትሸና ማድረግ
  6. በጀሮ እርሳስና እስክርቢቶ መክተት – ጆሮ ሲደማ መሳቅ እና ሌሎችም። ልጅቷ ስትናገር ሁሉን መጥቀስ አልፈልግም፡ ኢትዮጵያዊ የማያደርገውን የሚያደርጉ፤ ለትውልድ ሊነገር የማይገባ ድርጊት በማለት ያለፈቻቸው ነገሮች ሶዶማዊ ተግባሮች እንደሆኑ መገመት ይቻላል።
  የተማረች አማራ በመሆኗ ብቻ በግንቦት 7 ስም ለመከራ የተዳረገቸው ይህች ልጅ እናቷን ያጣቸው በወያኔ ነው። የባሏ ወንድም የት እንደገባ አይታወቅም። አፈር ከመለሱበት ቆይታል ብየ አምናለሁ። ሰክረው፤ ቅመውና በዘር ፓለቲካ ተክነው በሰዎች ላይ ያን ሁሉ ግፍና መከራ ያደረሱት ወያኔዎች ዛሬ መቀሌ ላይ ተቀምጠው “ህገ መንግሥቱ ይከበር” ይሉናል። ግን ትላንትም ዛሬም እሳት እየጫሩ ህዝባችንን የሚያጫርሱት እነርሱ ለመሆናቸው ጥብቅ መረጃ አለ። ወያኔ በሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሰራውና የሚሰራው ግፍ ለትግራይ ህዝብ እንዳይታይና እንዳይሰማ ነጋ ጠባ የሚለፈፍለት “ድርግን ጥለን” ጀጋኑ እየተባለ የማያቋርጥ ከበሮና ክራር እየከረከሩ ማቅራራት ነው። የሰው ልጅ መብት መከበር ለአቦይ ስብሃት ጉዳያቸው አይደለም። በበረሃ ከጀርባ ወገናቸውን የረሸኑ፤ በጉድጓድ ውስጥ ሰው ከተው በጪስ አፍነው የፈጅ አረመኔዎች ናቸው። ቆመው በመራመዳቸው ሰው ቢመስሉን ልባቸውና ተግባራቸው የእንስሳ ነው። ጨካኞች። በኦነግ አባልነትና በአማራ ስም ስንቶች መከራ ተቀበሉ? ስንቶችስ በሜዳ ወደቁ? ወያኔን የተካው የኦሮሞ ጠባቦች ስብስብ ደግሞ ባለተራ ነኝ በሚል የሞኝ ፈሊጥ ጠላቴ አማራ ነው ብሎ ቤ/ክ ያቃጥላል፤ አንገት ይቀላል፤ መማርና ማስተማሩ እንዳይኖር ያስተጓጉላል፤ ተማሪዎችን ይገላል። መንገድ ይዘጋል። የዚህች ሃገር ገመና ማለቂያው መቼ ነው? የአማራ ህዝብ መከራ የሚቆመው መቼ ነው? የልመና ፓለቲካና አስተዳደር ለህዝቦች እፎይታን አያመጣም። ትላንት በህዝባችን ላይ ሰቆቃ ያደረሱ፤ ዛሬም በቄሮ ስምና በሌሎችም ድርጅቶች እየተገፉ የሰው አንገት የሚቀሉ ሁሉ የሥራቸውን ካላገኙ ጭራሽ ሃገሪቱ ልትወጣ ወደማትችልበት ማጥ ውስጥ እየገባችን እንደሆነ ለማየት ቀላል ነው። ዛሬም ስብሰባ፤ ነገም ስብሰባ፤ ዛሬም ዲስኩር፤ ትላንትም ዲስኩር። ይሰለቻል። በወሬና በምክክር ብቻ ሃገር ሰላም ቢሆን ኑሮ ስንት ጊዜ ተመክሮ ነበር። አይሰራም። ዛሬም ሞት፤ መፈናቀል፤ መታሰር፤ ኡኡታና ለቅሶ። ልጅ እያጠባች በቤቷ የተቀመጠች ሴትን ዘር ተኮር በሆነ ጥላቻ ብቻ የሚገል ትውልድ ተጋፎ እሳት ውስጥ መጣል አለበት። የዚህ አይነቱ ትውልድ ለሃገርም ለራሱም አይበጅም። የሰው ተባዮች ናቸው። ዶ/ር አብይ ግን በቃላት ድርደራ ብቻ ተራራ ሊወጣ የሚከጅል ፍጡር ነው። መራመድና መንፏቀቅን፤ በዚህም ምክንናት መጋጋጥና ወድቆ መነሳትና መቅረትንም አውቆ የመደመር ሂሳቡን የመቀነስ ምልክት ካላከለበት ሳያስብ ራሱን የሚጨፈልቅ ሌላ ሃይል ሊመጣ እንደሚችል መገመት አለበት። ያ መጪ ሃይል ደግሞ መደመርን ሳይሆን መከፋፈልንና ሃገርን መረበሽን የተላበሰ ዳግማዊ ወያኔ ነው። ጠ/ሚሩ ቢነቁ ይሻላል። ባንቀልባ እንደታዘለ ልጅ “ሁሉን እሹሩሩ” በማለት የህዝብና የሃገርን ሰላም ማስፈን አይሻልም። የአማራም ህዝብ ሁሉን አቃፊ በሆነው ፍቅርህ የሚያቅፉህን አቅፈህ መከራ ያደረሱበህናን እያደረሱ ያሉትን ለመጋፈጥ ራስህን ማደራጀት ተገቢ ነው። ያልሞት ባይ ተጋዳይነት ወንጀለኛ አያደርግም። ግፍ አበቃ ስንል እንደገና ሞልቶ እየፈሰሰ ነው። እናስብ ጎበዝ!

 4. Aba Caaaalaaaaaaaa,

  Do you understand reading Amharic? The writer has described what a person created in the image of God looks like.

  Although your are their uncle, you know the Qeros who killed the young lady in the picture are not created in the image of GOD! The are beasts created by devil.

  Mention a single Amara, who could do this kind of crime?

 5. ABA Caala

  You are the one who is intentionally trying to Confuse people by asking this dumb question .
  The writer wrote it clearly any layman can comprehend what he wrote, the questions you raised were uncalled for to say the least.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.