በአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ስም ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ሰባት ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደረሱ

1 min read

በአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ስም ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ሰባት ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ፡፡

ፓርቲዎቹም የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( አዴፓ) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ኦዲፒ) የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ( ኦነግ)፣ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ( ኦፌኮ) ፣ የኦሮሚያ ብሄራዊ ፓርቲ (ኦብፓ) እና የአማራ ማህበራዊ ራዕይ ግንባር ናቸው፡፡

በሁለቱ ክልሎች እና ዩኒቨርሲቲዎች እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች እንዲቆሙ የድርሻቸውን በመወጣት በአማራና በኦሮሞ ህዝቦች አንድነት ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ፓርቲዎቹ የሁለቱን ህዝቦች ትስስር ከሚያላሉና ወደ ብጥብጥ ከሚያመሩ ማናቸውም ተንኳሽ ጉዳዮች ለመቆጠብ እና በህዝቦች ላይ የተደቀኑ አደጋዎችን ለመቀልበስ በመተባበር ለመስራት ወስነዋል፡፡

ልዩነቶች ቢኖሩነም ልዩነቶቻችን ከሀገራችን እና ህዝባችን የማይበልጡ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል ፓርቲዎቹ፡፡

ፓርቲዎቹ ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት ቅድሚያ ሰጥተው በጋራ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡

በአላዛር ታደለ / ኤፍ.ቢ.ሲ

2 Comments

 1. ለሀገራችን ምስቅልቅል መሰረት የሆነውን ፣ ሉኣላዊነትን ለዜጎች ሳይሆን ለጎሳዎች የሚሰጠውን ፣ የግለሰብ ነጻነትን የሚደፈጥጠው፣ ኣድሎኣዊ የሆነውን ህገ መንግስት ኣፍርሶ ዜጎችን በእኩልነት የሚያይ፣ የግለሰብ ነጻነትን፣ human valuesን በሚያከብር እንዲተካ የመጀመሪያ ስራችሁ ኣርጉት።
  ከዛ ብሁዋላ የሚደረግ ውይይት የእኩል ወንድማማቾች እና እህቶች ስለሚሆን ውጤቱም የሰመረ ይሆናል።
  ኣሁን ባላች ሁበት ሁኔታ፣ የሚደረገው ምክክርም ሆነ ውይይት በእኩያዎች ማህል ሳይሆን እኩል ባልሆኑ መሃል ነው ።
  ምክንያቱም ህገ መንግስቱ የኣንዱን ህዝብ ጥቅም በሌላው ኪሳራ እንዲሆን ሆን ተብሎ የተዘጋጀ በመሆኑ ለመለያየት እንጂ ተቀራርቦ ለመነጋገር inherently ኣመቺ ነት ስሌለለው።

  Anyway it is a good step forward.
  I call upon you, Bothers and Sisters to raise the level of Ethiopian political dialogues from backward,selfish and corrosive ethnic politics to that of ideals and values, principles,ideologies and the like .
  God bless Ethiopia !

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.