ለጤናወ ግድ ይለወታልን? እንግዲያስ ይቺን ያንብቡ!

1 min read

ጤና ይስጥልኝ!

ለጤናወ ግድ ይልወታልን? እንግዲያስ  mahderetena.com   ይጎብኙ

በኢትዮጵያዉያን ዘንድ የተለየ፣ በሌሎች አገሮች ብዙ የማይታይ  ሰላምታ አሰጣጥ አለ። ሰዎች ሲገናኙ ብቻ ሳይሆን ሲለያዩም ይጠቀሙበታል።  «ጤና ይስጥልኝ»  የሚለው ሰላምታ። ጤና ክቡር ነው። ጤና ተፈላጊ ነው። ጤነኛ መሆን የሁሉም ሰው ምኞት ነው። ጤነኛ መሆን መታደል ነው።

አንድ ሃብታም ሴት ነበሩ። ድረደዋ። የስኳር በሽታ በጣም አጠቃቸው። ከዚህ አለም በሞት ሊለዩ ጥቂት ቀናት በቀራቸው ጊዜ ሊጠይቋቸው ለመጡ ጎሮቤቶቻቸው «ምነው ጤና ኖሮኝ ቁልቢ የኔቢጤ (ለማኝ) በሆንኩ !» አሉ ይባላል። አዋ ቆመን ስንሄድ፣ ላይታየን እና ላይታወቀን ይችላል። ነገር ግን ፣ ከጤና የሚበልጥ ነገር የለም።

ዘመኑ የቴክኖሊጂ ዘመን ነው። የጤና በለሞያዎች ሕክምና ነክ ዝርዝሮችን ለማግኘት አይ ፓዳቸውን እና ኮንፒተራቸውን ጠቅጥቅ ማድረግ ልማዳቸው ከሆነ አመታት አልፈዋል። በርካታ በሽታዎችን እንዴት መከላከል እንደሚቻል፣ ለሚያጋጥሙን የጤና መታወኮች ምን ማድረግ እንዳለብን፣ የባለሞያ እርዳታ ካስፈለገ በአካባቢያችን ያሉ ስፔሻሊስቶችን አድራሻ፣ ከሕመማቸው የዳኑ ወገኖችን ምስክርነት የመሳሰሉ መጠነ ሰፊ መረጃዎች በኢንተርኔት በሽ በሽ ናቸው።

የኢትዮጵያ ማህበረሰብ እንደሌሎች ጋር ዜጎች  እነዚህ ጤና ነክ መረጃዎች እምብዛም ሲጠቅም አይስተዋልም። ሕዝባችን ጠቃሚ፣  ጤና ነክ መረጃዎች በቀላሉ እንዲደርሱት ለመርዳት ማህደረ ጤና  ድህረ ገጽ ተቋቁማለች። ድህረ ገጿ ወቅታዊ በጤና ዙሪያ በማጠንጠን በኢትዮጵያዉን ዘንድ ፈረንጆች እንደሚሉት አዌርነስ ለመፍጠር ትሞክራለች።

በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዉያን የጤና ባለሞያዎች፣ ምክራችሁን ለሕዝባችን ታቀርቡ ዘንድ፣  ማህደረ ጤና ድህረ ገጽን እንደ መድረክ መጠቅም እንደምትችሉ በአክብሮት ለማሳወቅ እንሞክራለን። ጽሁፎችን፣ አስተያየቶች ላኩልን። እናስተናግዳለን።

ከአገር በፊት ማህበረሰብ፣ ከማህበረሰብ በፊት ቤተሰብ፣  ከቤተሰብ በፊት የእያንዳንዳችን ሕልውናና ጤንነት ይቀድማል። ከጤና የሚበል ነገር የለም። እኛ ጤናማ ስንሆን ነው ሌላ፣  ሌላ ማድረግ የምንችለው።

እግዚአብሄር ባለንበት ለሁላችንም ጤንነትን  ያብዛልን !

  በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዉያን የጤና ባለሞያዎች፣ ምክራችሁን ለሕዝባችን ታቀርቡ ዘንድ፣  ማህደረ ጤና ድህረ ገጽን እንደ መድረክ መጠቅም እንደምትችሉ በአክብሮት ለማሳወቅ እንሞክራለን። ጽሁፎችን፣ አስተያየቶች ላኩልን። እናስተናግዳለን።

admin@mahderetena.com

aatebeje@gmail.com

1 Comment

 1. Welcome MaherdreTena.com health is before everything number one and sharing what is good for you to others is important. I am not a doctor do not think all who are abroad are doctors or experts but I read and apply what makes good sense to my health and to my family.
  I recently learned about oat milk. “YEAJA WETET”.
  The steal cut OATS “KINCHEW” is much better.
  Soak it in water for 30 minutes rinse it and blend in a blender.
  Ingredients
  :- 1cup of steal cut oats
  :_ 4 cups of water
  VOILA mix and blend and use a sieve or clean fabric to separate the milk from the soaked oats.
  you can add a flavoured spice for the taste I tried it and Boy! it tastes better than hormone injected cow milk that I have been drinking it is vegan and very health.
  When I happened to learn some thing good I will share.
  Thank you and keep our people with good healthy materials and topics.

  Mesfin Abbai Kassa.
  Ottawa, Canada.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.