ፖለቲከኞች የራሳቸውን ስራ ይስሩ፤ ከዚያ ውጪ ያለን ሰዎችም የየራሳችንን ሥራ እንስራ፤ ይህ ሲሆን ሁሉም ይስተካከላል – ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት

1 min read

• የትም አገር ለውጥ ቀላል ሆኖ አያውቅም፡፡ የተለያየ የቡድን ፍላጎት ይኖራል፡፡ ወደፊት ወደኋላ የሚያስኬዱ ሁኔታዎችም አሉ፡፡

• አሁን ላይ አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ። ምንም አይነት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት የለም፡፡ ዳኞች እንዲያውም አሁን “ነፃ ሆነን ህጉን ተከትለን እየሰራን ነው” በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡

• ማንኛውም ህዝብ በሰላም ወጥቶ ለመግባት ሥርዓት ኖሮ በህግ መተዳደር ይፈልጋል። ነገር ግን፤ አንዳንዴ ችግር ይኖራል፡፡ በሽግግር ላይ ደግሞ ችግር ያጋጥማል፡፡
• ችሎት ማስቻያ ቦታ የለም፡፡ ጊዜያችንን የሚወስደው “ዳኛ የት ይቀመጥ” የሚለው ነው፡፡

• በየትኛውም አገር ላይ የፍርድ ቤት ሥራ ሲታይ ዳኞች አይመሰገኑም፡፡ ዳኛ ሁለት ተከራካሪ አካላትን ይዳኛል፡፡ ህዝቡ በሰለጠነበትና ሥርዓቱ በደረጀበት አገር ላይ አንድ ሰው ቢሸነፍ ባይቀበሉትም “ዳኛው ተሳስቶ ነው” ብለው ያልፉታል፡፡

• በግልፅ ሰው ገድሎ የተፈረደበት ሰው አጥፍተሃል ሲባል አላደረግኩም ብሎ በዳኛ ላይ ያፈጥጣል፡፡ አንዳንዴ የተፈረደለትም የተፈረደበትም ይግባኝ ይጠይቃል፡፡ይህ ከሥራው ባህሪይ የመጣ ነው፡፡

• ፍርድ ቤት ጦርም ሆነ ገንዘብ የለውም፡፡ ፍርድ ቤት ያለው የሞራል የበላይነት ብቻ ነው። ገንዘቡም ጦሩም ያለው በአስፈፃሚው እጅ ነው፡፡

• እኔ ስለመጣሁ ተአምር ልሰራ አልችልም፡፡ ይዤ የምሰራው የነበሩትን የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች፤ የነበረውን ግብአት ነው።ትዕግስት ያስፈልጋል፡፡ የሚሰሩት ሥራዎች ዘላቂ እንዲሆኑ ተቋማችንን እየገነባን ነው፡፡

• የደሞወዝና ሌላ ጥቅማ ጥቅም ነገሮች ከመንግሥት አቅም በላይ የሆነ ጥያቄ በማቅረብ ችግር ላለመፍጠርም ማስተዋል ይገባል፡፡ ምክንያቱም ይኸው ጥያቄ ወደክልልም ስለሚወርድ በደንብ ማየት ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን፤ መጠነኛ ማስተካከያ መኖሩ አይቀርም፡፡

• ዳኞች በሙስና ከተጠረጠሩና በማስረጃ ማረጋገጥ ከተቻለ ርምጃ መውሰድ ይቻላል፡፡

• ጥናቶች የሚያሳዩት ደመወዝ አደገም አላደገ ሞራል የሌለው ሰው ወይም መዝረፍ የሚፈልግ ወደኋላ አይልም፡፡ ፍርድ ቤት ከሙስና ጋር ተያይዞ ለሚፈጠሩ ብልሹ ተግባራት ምንም አይነት ርህራሄ የለውም፡፡

• ከበፊት ጀምሮ ብቃት ሳይሆን የፖለቲካ ወገንተኝነት መስፈርት ሆኖ ሹመት ይካሄዳል፡፡

• የዳኛ ሹመት እንደሌላው አይደለም። ሹመቱ የሚፀድቀው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው፡፡ እንደማንኛውም የመንግሥት ኃላፊ በቀላሉ ማስነሳት አይቻልም፡፡

• ፍትህ የፍርድ ቤት ጉዳይ ብቻ አይደለም። በተለይ በወንጀል ጉዳይ ላይ ሌሎችም አካላት አሉ፡፡ ዳኛው ውሳኔ ቢሰጥም ሌሎች አካላትም ይካተታሉ፡፡ አቃቤ ህግ፤ ፖሊስ እና መረጃ የሚሰጡ ተቋማት አሉ፡፡

• የዳኛው ሥራ ከእነዚህ አካላት ጋር ሁሉ የተገናኘ ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ በሰነድ ክምችትም ቢሆን ከሌላው አገር አንፃር ሲታይ ዳኞቻችን መወቀስ ያለባቸው አይደሉም፡፡

• ነገር ግን፤ ነፃነት ውጫዊ እና ውስጣዊ ነው።፡ አንዳንድ ጊዜ አብሮ የቆየን ነገር ከውስጥ ለማውጣት የመቸገር ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ ነፃነቱን ወደ ሌላ ፅንፍ የሚወስዱና ከመንገድ የሚወጡ ይኖራሉ፡፡

• በኢትዮጵያ ግን “ዳኛ ተሳስቶ ይሆናል” ተብሎ አይታሰብም፡፡ ዳኛው በትክክል ቢፈርድ እንኳን በተቋሙ ላይ እምነት ስለሌለ ተከራካሪዎች ዳኛውን ከመኮነን ወደኋላ አይሉም፡፡

• በለውጡ ዙሪያ የህግ የበላይነትን አስመልክቶ ህዝቡ በተደጋጋሚ ሃሳብ ያቀርባል። ሆኖም፤ የህግ የበላይነት ፍርድ ቤትን ብቻ ሳይሆን ህዝቡን ጨምሮ የተለያዩ አካላትን የሚያካትት ነው፡፡

• በህግ ለመተዳደር ፍላጎት ያለውን ህዝብ ከዚያም ውጪ ጠንካራ ተናብቦ የሚሰራ መርማሪ ፖሊስና ዓቃቤ ህግ ያስፈልጋል፡፡

• የፈለገ ጥረት ቢደረግ ሁሉንም ማስደሰት አይቻልም፡፡ ዋናው ነገር ሚዛናዊነትን ጠብቄ ኃላፊነቴን ለመወጣት እየታገልኩ ነው፡፡

• ዞሮ ዞሮ ለውጥ ላይ በመሆናችን ችግር አለ። “ችግሩ እየተባባሰ እንዳይሄድ ምን ማድረግ አለብን?” የሚለውን አስመልክቶ እያንዳንዱ ሰው መስራት አለበት፡፡

• የፍርድ ቤት ሚና ክርክር ይዘው የቀረቡትን አካላት ማስተናገድ ነው፡፡ ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ነገር ስሰማ ዝም አልልም፡፡ በቀጥታ በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እነጋገራለሁ፡፡

• አንድ ሰው በቂ ጥርጣሬ ሳይኖር መያዝ የለበትም፡፡ በእርግጥ ይሄ በቀጥታ ከኔ ሥራ ጋር የተገናኘ አይደለም፡፡ በበቂ ጥርጣሬ ከተያዘ ደግሞ ክስ ቀርቦበት ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት፡፡

• ምርመራ ቶሎ አይጣራም። ፍርድ ቤት ተደጋጋሚ ቀጠሮ ይሰጣል። ከዚያ “ጥፋተኛ አይደላችሁም” በሚል ሰዎች እየተለቀቁ ነው የሚል ተደጋጋሚ አቤቱታዎች ይሰማሉ፡፡ ይህ ትክክለኛ ቅሬታ ነው፡፡ በኛ በኩል መስተካከል ያለበትን ጉዳይ እናያለን፡፡

• አስተዳዳሪዎች በእያንዳንዱ ፋይል ላይ ጣልቃ መግባት አንችልም። በዚህ ሂደት ጥሩ ሥራ ሊሠራም ሆነ ስህተት ሊፈጠር ይችላል። በየዓመቱ ከ200 ሺህ በላይ ጉዳዮች ይታያሉ። ማወቅ አይቻልም፡፡ ያለአግባብ የተፈፀመ ነገር ካለ ለቁጥጥር ክፍል መጠቆምና እርማት መውሰድ ይቻላል፡፡

• ዑጋንዳ ለስብሰባ ሄደን ሪፖርት ሲደረግ “ሩዋንዳ ሊቢያዎችን እየረዳች ነው፡፡ ዑጋንዳዎች 40 ሚሊዮን ነን፡፡ አንድ ሚሊዮን ስደተኛ ቢመጣ ምን ችግር አለው” ይላሉ፡፡ ኢትዮጵያ በታሪክም እንግዳ ተቀባይ መሆኗ ይነገራል፡፡ ታዲያ አንዱ ሌላውን ለምን ያገልላል?

• የዳኝነት ዘርፉ ሆነ ተብሎም ሆነ በሌላ ምክንያት ተረስቶ የቆየ ነው፡፡ ነገር ግን፤ እነዚህ ሁሉ ጫናዎች እያሉ ደግሞ አዲስ ችግር መጥቷል።

• አንዳንድ ጊዜ በቡድን ሆነው በዳኛ ላይ ጫና ሲፈጠሩ ህዝቡ ዝም ማለት የለበትም። ህዝቡ ራሱ በዳኞች ላይ ጫና የሚፈጥሩትን መቃወም አለበት፡፡

• በሴትነቴ ያጋጠመኝ ችግር አለ ብዬ አላስብም። ባለቤቴ ከጎኔ ሆኖ ይደግፈኛል። አብሬ የምሰራቸው ወንዶችም ይቀርቡኛል፡፡ ግልፅ ነኝ። “ሥራ ለምን አልተሰራም” ብዬ ግፊት አደርጋለሁ፤ አይቃወሙኝም፡፡

• ለህዝቡ ማስተላለፍ የምፈልገው፤ በአንድ በኩል ህግ ይከበር ይባላል። በሌላ በኩል ደግሞ ያለአግባብ ሰዎች መያዛቸው ይገለፃል፡፡ ፍርድ ቤቶች የሚታገሉት በዚህ መካከል ነው፡፡
ምንጭ አዲስ ዘመን ህዳር 05 ቀን 2012 ዓ.ም ፖለቲካ አምድ

 

4 Comments

 1. Meles Zenawi raised / trained Abiy Ahmed team Lemma.
  Mengistu Hailemariam trained many, including the highly trained ranking air Force pilots which Meles Zenawi depended upon during the fight against Ethio-Eritrean Badme war.

  Hailesselasie trained Mengistu Hailemariam and Isayas Afeworki…

  PEOPLE GOT THEIR OWN MIND REGARDLESS WHO TRAINED THEM THEY CAN CHOOSE WHICH TRAININGS THEY RECEIVED ARE GOOD AND WHICH ARE NOT SO THEY HOT THE FREEWILL TO.CHOOSE WHICH TRAININGS TO APPLY AND WHICH TRAININGS TO ABANDON.BERHANU TSEGAYE DIDNOT ABANDON HIS CONNIVING WAYS.

  Liyu Hayl that were trained by Asaminew doesn’t mean a thing as long as they did their jobs of protecting Amara, which they proven to do so .

  Abiy Ahmed sent troops to Ataye , Debre Berhan and Kemise areas to fight Liyu Hayl so the Civilians getting massacqred don’t get help ,if Liyu Hayl tried to save the innocent civilians that were being massacred Abiys troops we’re ready to attack them while the massacre in the civilians were being carried out. The proof of Abiy ordering not to save the civilians was in the hands of Saere which then reached Asaminew and Ambachew so Abiy shut them up all..then this prosecutor using the old habits is accusing the victim Asaminew as the criminal making itore obvious that he is not reformed he is sticking to his old cunning evil ways of prosecution he learnt from Getachew Assefa ..

  This Berhanu Tsegaye the ODP backed Prosecutor who previously was trained by Getachew Assefa how to lie now Abiy right hand man is definitely trying to cover up the messy crimes of Abiy with more scandal defaming Asaminew. .

 2. እኛስ ማለት ህዝቡ
  ህዝቡ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ በአጽንዖት እንዲረጋገጥ ይፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ በክልልና በፌዴራል መንግስት መዋቅሮች በሙሉ፡፡
  ሰዎች ሁሉ በህግ ፊት እኩል ናቸው—ጃዋርም፤ ጌታቸው አሰፋም፣ ክርስቲያኖም ሰው ናቸው፡፡ ስለዚህ ህዝብ በተለያዩ መድረኮች፣ በተቃዋሚዎችና በሃይማኖት አባቶች በቀረበው ጥያቄ መሰረት ጃዋርም፤ ጌታቸው አሰፋም እና ግብረ በላዎቻቸው ለፍትህ መቅረብ አለባቸው፡፡
  ሺህ ቢወራ እነዚህ ግለሰቦች የት እንዳሉና ምን እንደሰሩ ጭምር በግልጽ ይታወቃልና ለህግ እስካልቀረቡ ድረስ ጥቂት ባይተዋሮችን በመያዝና በመክሰስ ብቻ ፍትህ ተረጋግጧል ብንባል የሚሆነው ትዝብት ላይ መውደቅ ነው፡፡
  አሁንም ማንም በዚህች አገር የሚኖር ከህግ በላይ ሳይሆን ከህግ በታች መሆኑን በተግባር እናረጋግጥ
  አሁን ተያዙ የተባሉትም በህግ አግባብ ተፈትሸው ብቻ ውሳኔ ማግኘት አለባቸው፡፡

 3. ህግና ህጋዊነትን ለማስከበር በመጀመሪያ መንግስት ራሱ ህጋዊና ለህግ ተገዢ መሆን አለበት። በኢትዮጵያ እስካሁን የሚስተዋለው ግን መንግስት ከህግ በላይ ሆኖ ነው። በንጉሣውያን ዘመን “ንጉሥ አይከሰስ፣ ሰማይ አይታረስ” ይባል ስለነበረ ንጉሡ ራሱ/የርሱ ቃል ህግ ሆኖ ይተገበር ነበር። ከሱ በታች እስከምስለኔ የነበረው በሙሉ በየዕርከኑ ከህግ በላይ ነበሩ። የፈለጉትን ማሰር፣ መግደል፣ የፈለጉትን ግብርና መዋጮ ማስከፈል፣ ሲያስፈልጋቸውም የድሃውን የግል ሃብትና ሚስት ጭምር መውሰድ ይችሉ ነበር።
  በተከተሉትም የደርግ እና የሕውሃት አምባገነን መንግስታት፣ ርዕሰ ብሄሩ ብቻ ሳይሆን በየእርከኑ የነበሩ ባለሥልጣናት ከህግ በላይ ነበሩ። ያን ተከትሎም ፖሊስ፣ ደህንነቱና ብሎም መከላከያ ሰራዊቱ ሲቪሉን በተመለከተ ከህግ በላይ ነበሩ። ከሙሰኝነት የተነሳ፣ ሃብት እና ሥልጣን ያለው በሙሉ ከህግ በላይ ሆነ። ህግ እንዲያከብር ይገደድ የነበረው ሃብት ወይም ሥልጣን የሌለው ደሃው ህብረተሰብ ብቻ ነው። እንዲህም ስለሆነ ህግ የህብረተሰቡ የጋራ ውል መሆኑ ቀርቶ፣ የመጨቆኛ መሣሪያ ተደርጎ ስለተወሰደ፣ ደሃውም ህጉን ለማክበር የሞራል ግዴታ አልታየው አለ። የሥርዐት አልበኝነቱ መንስዔና ምንጩ ከህግ በላይ የሆነው መንግስት ተብዬው ነው!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.