ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን በመጠቀም ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ሲያትሙ የነበሩ የውጪ ሀገር ዜጎችን በቁጥጥር ስር ዋሉ

1 min read

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቅንጅት ባደረጉት ክትትል ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን በመጠቀም ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ሲያትሙ የነበሩ የውጪ ሀገር ዜጎችን በቁጥጥር ስር አዋሉ፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ያደረገውን ክትትል ተከትሎ ስምንት የውጪ ሀገር ዜጎች በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ሜታ ፋብሪካ አካባቢ ሁለት መኖሪያ ቤቶችን በመከራዬት በሕገ-ወጥ መንገድ ሀሰተኛ ገንዘብን አስመስለው ሲሠሩ መያዛቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ዘርፍ የጉዳዩ መርማሪ ዋና ሳጅን በሪሁን ስለሺ ገልፅዋል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ በሕገ-ወጥ መንገድ አመሳስለው ያዘጋጁት 512 ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር፣ ትክከለኛ የሆኑ 455 ሺ 200 መቶ የኢትዮጵያ ብር እና 1 ሺህ 900 የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም በብር እና በዶላር መጠን የተዘጋጁ ብዛት ያላቸው ወረቀቶች፣ ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ለማዘጋጀት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ልዩ ልዩ ኬሚካሎችና ቁሳቁሶች እንደተያዙ ከዋና ተገልጿል፡፡ ተጠርጣዎቹ በዚህ ወቅት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው በማረፊያ ቤት ሆነው ጉዳዩ እየተጠራ መሆኑን መርማሪው አስታውሰው መኖሪያ ቤት፣ የንግድ ቤትና መጋዘን ተከራይተው መሰል ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን አከራዮች ተገንዝበው አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ዋና ሳጅን በሪሁን ስለሺ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ኢብኮ እንደዘገበው ኅብረተሰቡ ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሥራ ውጤታማነት እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ተቋማቱ ምሥጋና አቅርበዋል፤ ድጋፍና ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፦ #አብመድ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.