‘‘አገር የግል እና የተወሰኑ ቡድኖች መጠቀሚያ አይደለችም’’ – የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም

1 min read

አዲስ አበባ፡- “አገር የግል እና የተወሰኑ ቡድኖች መጠቀሚያ አይደለችም። ስለዚህ ሁሉም በጋራ የኢትዮጵያን አንድነት ሊጠብቅ ይገባል” ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ጥሪ አቀረቡ፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ትናንት በፍሬንድ ሺፕ ሆቴል ባዘጋጀው የህዝብ ለህዝብ መድረክ ላይ አፈጉባኤዋ ወይዘሮ ኬሪያ እንደተናገሩት፤ በግለሰቦች እና በተወሰኑ ቡድኖች ምክንያት በተለይ ባለፉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በየክልላቸው በሰላም ወጥተው መመለስ እየተቸገሩ ነው፡፡በብሄራቸው እና በሃይማኖታቸው ምክንያት በህይወታቸው እና በንብረታቸው ላይ ግፍና በደል እየደረሰባቸው ነው። የመንግሥት፣ የህዝብ እና የሃይማኖት ተቋማት ንብረት ሃይ ባይ በሌለበት እየወደመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

‹‹ለአስከፊው አደጋ የተጋለጥንበትን ውጫዊና  ውስጣዊ ምክንያት መጥቀስ ቢቻልም ከምንም በላይ የሁላችንም ድርሻ አለበት›› ያሉት አፈ ጉባኤዋ፤ በስምምነትና በዘላቂነት ችግሮችን ለመፍታት ከተሰራ የማይፈታ ችግር አይኖርም ብለዋል፡፡ ለዚህም በችግሮቹና በመፍትሄዎቹ ላይ ውይይት ያስፈልጋል በማለት ገልፀዋል፡፡ የህዝብ ለህዝብ መድረኩ ለመዘጋጀቱ ዋነኛው ምክንያት ይሄ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ አፈጉባኤዋ ገለፃ፤ ህዝቦች ከተጋረጠባቸው አደጋ እንዲወጡ እንዲሁም ሰላምና ደህንነታቸውን ለመጠበቅ የህግ የበላይነትን በማስከበር የዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብት እንዲከበር ሁሉም በአንድነት ሊቆም ይገባል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክብረ በዓልን በማስመልከት የተዘጋጀው የምዕራብ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የህዝብ ለህዝብ የጋራ የምክክር መድረክ እንዲሳካ ሁሉም የድርሻቸውን በመወጣታቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡

‹‹ህገ መንግሥታዊ ቃልኪዳናችን ለዘላቂ ሰላም›› በሚል በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አዘጋጅነት ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የህዝብ ለህዝብ መድረክ ላይ የኦሮሚያ፣ አማራ፣ ጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።በወቅታዊ ጉዳዮች እና በጋራ እሴቶች ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው የየክልሎቹ ተወካዮች ምክክር አድርገውበታል፡፡

አዲስ ዘመን ህዳር 7/2012

1 Comment

  1. እምይ ጓል ተምቤያዋይ፣ you are becoming the very classical “ያብዬን ለምዬ”!
    ለወደፊቱ ከመናገርሽ በፊት መቐለዋይ ውስጥ አዲሱ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተሰርቶ እስኪከናወንላቸው ጊዜ ድረስ፣ ለጊዜው ኣኽሱም ሆቴል ውስጥ ተሰግስገው ከሚገኙት ቅድመ አያቶችሽ ጋራ እየተደዋወልሽ መሆኑን ያዋጣል::
    የምትናገሪውንና የምታስቢውን ለማጣጣም ደግሞ ኦክሲጂንም በጆሮሽና በፀጉርሽም በኩል ሁሏ አካባቢም ሳያስፈልግሽ የቀረ አይመስለኝም፣ በነገራችን ላይ፣ ግን የኣኽሱም ሆቴል ተሰግሳጊዎች ወደዚያ መሽቀንጠራቸው ለመቐለ አንድን ጥቅም ብቻ ሳያስከትል አልቀረም፣ የአዲስ አበባው ፍልውሃ ከራቀባቸው ጊዜ ጀምሮ፣ የውሃ እጦት ማለት ምን እንደሆነ ስለገባቸው፣ ይሄው ለመቐለ በሚል አስመሳይነት ግድብ እያስቆፈሩ ነው፣ እንዲሁም ቁጥር የለሾቹ የአዲስ ሆቴሎች በክፉኛ ከራቋቸው ጀምሮም፣ መቐለ ኢንተርናሽናል ስታንዳርድ ያለው ሆቴል “እንደሚያስፈልጋት” ተገንዝበው ሲያበቁ፣ ከፍ ያለ መዝናኛዎች ያለውን ሆቴል እያስነደቁ ነው፣ እንዲህ ነው ሁሌ ራስን ማሰብና ግን በሌላ አምሃኝቶ በገዛ ራስ ተጠቃሚ መሆን ይሉሻል፣ ስለሆነም ወደ መነሾ ነጥቤ ልመለስና፣ ለማስመሰል ስታስቢ መጀመርያ የማስመሰል “ሊቀ ሊቃውንት” ቅድመ አያቶችሽን እያማከርሽ ቢሆን ያዋጣሻል!ወይንስ አዲስ መቐለ ደግሞ ስልክ ልውውጥ ተቋረጠ እንዴ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.