‹‹የአማራና የትግራይ ሕዝቦች በጋራ እሴቶቻቸው የተጋመዱ፤ የተንሻፈፈ ፖለቲካ የማያቆራርጣቸው ናቸው፡፡›› በጎንደር የትግራይ ተወላጆች

1 min read

‹‹ጎንደር ከትግራውያን ጋር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማድረግ ዝግጁ ናት፡፡›› የጎንደር ከተማ አስተዳድር አዴፓ ጽሕፈት ቤት

በ1957 ዓ.ም ነበር ፍቅር ጎንደር ላይ እንዲከትሙ ያደረጋቸው። ያኔ ውኃ አጣጫቸውን አግኝተው አስር ልጆችን አፍርተዋል። ባለታሪካችን ትውልዳቸው ትግራይ ክልል ኑሯቸው ጎንደር ነው፤ አቶ ወልደገብርኤል ትኩ ይባላሉ፡፡

ዋልታና ማገሯ ጎንደር ያለ ልዩነት አኑራቸዋለች። “ጎንደር ውስጥ ከሰውነት ቀጥሎ ብሔር ብርቅየየ አንድነትን መፍጠሪያ አጋጣሚ ነበር” ይላሉ በለታሪካችን ሲናገሩ። ባለፉት ሁለት ዓመታት ግን የፖለቲከኞች ሽኩቻ የንፁኃንን መሰደድ እና የሥነ ልቦና ስብራት አድርሷል። “ለሀገር ሠላም እና አንድነት የክርስትናና እስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ያደረጉት ጸሎት ጎንደር አሁንም የኢትዮጵያን አንድነት ለማምጣት ጥረት እያደረገች እንደሆነች ምሳሌ እንደሆነ አምናለሁ” ብለዋል አቶ ወልደገብርኤል ትኩ።

አቶ ወልደ ገብርኤል “የአማራና የትግራይ ሕዝቦች በጋራ እሴቶቻቸው የተጋመዱ፤ የተንሻፈፈ ፖለቲካ የማያቆራርጣቸው ናቸው” ብለዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፖለቲከኞች አማካኝነት የሚፈጠር ጣት መቀሳሰር ሕዝባዊ እየመሠለ ይምጣ እንጂ አርቆ አስተዋይ አባቶች በእንጭጩ ቀጭተው የትውልድ አደራቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። በጎንደር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች፣ የጎንደር ከተማ ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች የሁለቱን ሕዝቦች እውነተኛ የአንድነት ለመመለስ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዛሬ በጎንደር ከተማ የትግራይ ተወላጆች ከከተማዋ ከተወጣጡ ወጣቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ምክክር አድርገዋል። “ሴረኛ ፖለቲካ ለዘመናት የተጋመዱ፣ የተለዬ እሴት የሌላቸው የአማራና የትግራይ ሕዝቦችን ግንኙነት አይቆርጠውም” ያሉት የጎንደር ከተማ ነዋሪው አቶ ደጉ ቢተው ናቸው።
አቶ ደጉ የሁለቱን ክልል ሕዝቦች ለማስተሳሰርና የሴረኛ ፖለቲከኞችን ዓላማ ለማክሸፍ ሕዝቦቹ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና የሃይማኖት አባቶችን ያቀፈ የአብሮነት ምክክር ማዘጋጀት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

መንግሥት የሁለቱ ሕዝቦች ግንኙነት እንዲጠናከር ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን ቀዳሚ ሥራ ማድረግ እንደሚገባም አመላክተዋል። መድረኩን በጋራ ያዘጋጀው የትግራይ ትብብር ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር ኢንጂነር ግደይ ዘርዓጽዮን ሌሎችን በመጥላት ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ ለየትኛውም ሕዝብ እንደማይጠቅም ተናግረዋል። ‹‹ህወኃት ወደ አማራው ጣት እየቀሰረ ሕዝቡ አንድ እንዳይሆን እየሠራ ቢሆንም ለትግራይ ሕዝብ ወንድም ከሆነው አማራ በላይ የሚቀርበው የለም›› ነው ያሉት ኢንጂነር ግደይ።

የአማራ ሕዝብም የትግራይ ወንድም ሕዝብን እንደቀድሞ ፍትሕ እንዲያገኝ፣ የተፈናቀለ እንዲመለስ፣ ከተለየው ሕዝብ እንዲተቃቀፍ በማድረግ አስሮ ከያዛቸው የፖለቲካ ሴራ መነጠል እንዲቻል መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳድር የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞላ መልካሙ “ጎንደር እኩል የሁሉም ዜጎች ናት” ብለዋል። ይህንን የዋልታና ማገርነቷን እሴት ጥቂቶች ከፋፋዮች ሊቀሟት እንደማይችሉም ለተሳታፊዎች ተናግረዋል። የጎንደር እሴቶች ከትግራይም ሆነ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር የሚጣጣም መሆኑን ያመለከቱት ኃላፊው ሕግ የማስከበርና ሠላምን የማረጋገጥ ተግባር ቀዳሚ ሥራ መሆኑን አብራርተዋል። “ጎንደር ከትግራይ ሕዝብ ጋር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማድረግ ዝግጁ ናት” ያሉት አቶ ሞላ በቀጣይ ይህንን ለማረጋገጥ ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ምክክር እንደሚያደረግ ተናግረዋል።

ምክክሩም ስድስት የሠላም እና የአንድነት የአቋም ዕቅዶች በማውጣት ተጠናቅቋል።

ዘጋቢ፦ ግርማ ተጫነ ከጎንደር

አብመድ

5 Comments

 1. ትኩ ሳይሆን፣ የሰውየው ስም ትኩእ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፣ በፅዮኑ ልጅ ፋሲል ይሁንብኝና!

  ፎገራ ሆቴል ጎን ለሚገኘው የምስራቅ ፐንስዮን የምግብ ቤት (ወጥ ቤት) እና የዘበኝነት ሰራተኞች የአክብሮት ሰላምታዬን አቀርባለሁኝ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ሽረ ኣኽሱም አቅጣጫ በተጓዝኩበት ጊዚያቶች ላይ የማሌሊት ጴንጤ ካድሬዎች በሌሊት ከፐንስዮኑ አውጥተው ለጅብ ሊሰጡኝ ተንጋግተው ሲመጡ፣ እነዚያ የፔንስዮኑ ሰራተኞ በግብግብ ጴንጤ ካድሬዎቹን በማባረር ሂይወቴን ያዳኑ ጀግኖች ናቸው ስል ቃለ ምስክሬን እሰጣለሁ!!!

 2. እናንተ ሰዎች ምን ታማታላችሁ? የትግራይ ተወላጆች በሙሉ ከአማራ ክልል ተባረዋል ትሉ አልነበረም? ታዲያ የትግራይ ልጆች በጎንደር ከየት ተገኙ? አይ ፓለቲካ። እንጀራ የማይወጣው ሊጥ የሚያቦካ እኩይ ህልፈተ ቢስና መንቻካ ትውልድ። ሰው በሃገሩ ክልል እየተባለ አንገቱ እየተቆረጠ የማምለኪያ ሥፍራው እየተቃጠለ መንግሥት ዝም የሚልባት ሃገር። ትላንትም ስብሰባ፤ ዛሬም ፍቅርና አንድነት ግን እኮ ፍሬ አልባ ገለባ ነው። በአዲስ አበባ አንድ ባለሃብት ቤት እየሰራ ባለበት ወቅት ቆንጨራ የያዙ ሰዎች ከበቡትና አቁም ቤት በለገጣፎ ከኦሮሞ ተወላጅ በስተቀር መስራት አይችልም ይሉታል። እርሱም ሃገሬ ነው በህግ የተመራሁት ቦታ ነው ቢል ሰሚ አልተገኘም። እቃውን መሰባበር ይጀምራሉ። ለፓሊስ ይደውላል። ፓሊሱ ከስፍራው ደርሶ ሌሎች አባሪ ሃይሎችን ከጠራ በህዋላ በዝምታ ቆሞ በማየት የቆመው ቤት መስታውትና ሌላም ነገር ሰባበሩበት። ካላቆምክ ይቃጠላል በማለት ዝተው ወደ መጡበት ተመለሱ። ፓሊሱም እነርሱን አጅቦ አብሮአቸው ተሰወረ። ይህ ገመና የደረሰበት ሰው የትግራይ ተወላጅ ነው። ትላንት ቢሆን አፉን ከፍቶ የሚናገር ማንም አይኖርም ነበር። ግን እኮ እድሜ ለወያኔና ለሻቢያ የኦሮሞ አጥፊ ሃይሎችን ክህነትና ቅድስና የሰጧቸው እነርሱ ናቸው። ይህ ቀን እንደሚደርስ ግን ማየት ከቶ አይችሉም ነበር ለማለት አይቻልም። አውቀው ያደረሱት የፓለቲካ መከራ ነው። የዘር ፓለቲካ!
  እናማ አሁን የአማራ ህዝብ የትግራይ ህዝብ ገለ መሌ እያሉ በጠባ በነጋ መሰብሰቡ ምንም መፍትሄ አያመጣም። የሃገሪቱ መሰረት ተንዷል። እንዲናድ ያድረጉትም ወያኔና ሻቢያ ናቸው። እኔ ነብይ ወይም የነብይ ልጅ አይደለሁም። በሃገሪቱ ያለው የፓለቲካ አዙሪት ልክ እንደ ቀድሞዋ ዮጎዝላቪያ እንደሚያደርገን አመላካች ነገሮች አሉ። ይህ ከአንገቷ በታች ተቆርጣ በቀረቸው ኢትዮጵያ የሚነደው እሳት ኤርትራንም እንደሚልሳት ምንም ጥርጥር የለውም። አቶ ኢሳያስ የዘር ፓለቲካን እንደሚጠሉ አውቃለሁ። ግን የታፈነ እውነት ነው። ዘር አይደለ ህዝቡን አብልቶ የማያድርን መንግሥት ቅኝ ገዛን በማለት ኤርትራዊያን መገንጠልን የመረጡት። ነጻነት እማ ቢሆን አሁን ሲከፋን እዛያው ብቅ ብለን የኦሮሞ መንጋ ከሚያደርስብን የመከራ ዶፍ በተጠለልን። ግን አይቻልም። ሰው ከደቡብ ኮሪያ እንዴት ወደ ሰሜን ኮሪያ ሂዶ ጥገኝነት ይጠይቃል? የማይሆን ነገር!
  ሰው በሃይማኖት በዘር፤ በቋንቋ በክልል ፓለቲካ ተቃምሶአል። ሃገራዊ ወይም ዓለም አቀፋዊ እይታ የለውም። ዶ/ር ደብረጽዪን በመቀሌ አካኪ ዘራፍ ሲሉ ከሞት የተረፉት የአማራ መሪዎች ደግሞ ምላሹን ይፎክራሉ። ሰው ወንድምና እህቱን ገድሎ የሚፎክርባት፤ ጀግና ነን እያለ ለዘመናት ከበሮ የሚመታባት ሃገር የሃበሻው ምድር ብቻ ናት። የውስልትና ጀግንነት። የውጭ ሃይሎች መጠቀሚያና የሥራ ማስፈጸሚያ ጀግንነት። ጀግኖች እማ ድሮ ቀሩ። ማይጨውና አድዋ ላይ ጠላትን የተጋፈጡ፤ የጣሊያንን ጦርን ፊት ለፊት የገጠሙ። አሁን ማን ይሙት የደርግን መንግሥት ማፍረስ ጀግንነት ነው? አይደለም። ደርግን የጣለው ጊዜ እንጂ እሳት የሚያቀብለው ቢያገኝ ኑሮ ለዝንተ ዓለም መገዳደላችን አይቆምም ነበር። የፓለቲካ ጉራ ግን የሰካራም ፍጨት ነው። ስሚ የለውም። ዛሬም በኦሮሞ ባለጊዜዎች አንገቱን የሚቆረጠው ክርስቲያን፤ ቤትና ንብረቱ እየተዘረፈ ከመኖሪያው የሚፈናቀለው ወገናችን ሁሉ እንባና ደም በእጃቸው ላይ ያለ የኦሮሞ ጠማማ ፓለቲከኞች ከፍርድ አያመልጡም። ነበረ ሸሁ ከመስጊዱ፤ ካህኑ ከመቅደሱ፤ ገበሬው ከግብርናውና ከኑሮው ተጠራርተው በአንድነት ደማቸውን ለሃገሪቱ ያፈሰሱት። ተምረናል፤ አውቀናል የምንል የደንቆሮ ክምችቶች ደግሞ በቋንቋዬ ካላወራ የእቃ ሽያጭ አትፈጽሙ፤ ስሜ የተለወጠው በአማራና አጥምቀው ክርስቲያን አርገውኝ ይሉናል የኦሮሞ ቱልቱላዎች። እስቲ በሞቴ ተገንጠሉ እና ኦሮሚያ ውስጥ ኑሩ። እንያቹሁ። አንድ ቀን በሰላም አታድሩም። እርስ በርሳችሁ ትባላላቹሁ። ወያኔ ትግራይን መገንጠል ፈለገ። ሂድ የምን ልምምጥ ነው። እንካፈልና ሁሉም እንደ እንስሳ ተገን አበጅቶ ይኑር። የጠባብ ብሄርተኞች በሽታ የጎጥ ፓለቲካ ናፍቆት ነው። ጠ/ሚሩን ማን እንደ ደገመባቸው አላውቅም። ያፍዝ ያደንግዝ ይዞአቸዋል። ተማሪ ሞተ፤ ትምህርት ተረበሸ፤ ፓሊሱ በዘሩ ተሰልፎ ህግ ማስከበሩ ቀረ፤ ጃዋር ሃገር አቃጠለ እየተባሉ ዛሬም መደመርን ሲሰብኩ መስማት ያማል። ግፍ ሳይቆም ተደመሮ ማለት ፌዝ ነው። የጎንደሩ የትግራይና የአማራ ተወላጆች ስብሰባም በሰው ላይ ማላገጥ ነው። ማን ማንን ያምነዋልና! መተማመን ድሮ ቀረ! ጊዜ አታባክኑ። ለካሜራ ከሆነ መዝፈኑ ይሻላል። ዘፈኑ። ሃገሪቱ እንደሆነ የዘፈንና የቀረርቶ ሃገር ሆናለች። ሰላም በምድሪቱ የለም። አብሮ ቀን የመከረውን ነው ማታ ከአፍራሽ ሃይሎች ጋር ሆኖ የሚንደው። ፉርሽ ፓለቲካ!

 3. አማራ ትግሬን ከጎንደር አባረረ ብላችሁ የአማራን ስም በሃሰት አጥፍታችኅል ለወንጀላችሁ ይቅርታ መጠየቅ ሲገባችሁ አሁንም የትግሬ ተፈናቃይ እያላችሁ ትዋሻላችሁ። የወያኔ ሰላይና ካድሬ ትግሬዎች የሰሩትን ወንጀል ስለሚያውቁ ለውጡ ሲመጣ ማንም ሳያባራቸው እቃቸውን ሳይቀር በአውሮፕላን ጭነው ሄደዋል። የሚገርመው አሁንም ድረስ ጎንደር ውስጥ እየኖሩ ያሉ በሽዎች የሚቆጠሩ ትግሬዎች አንድ ቀን እንደዚህ በሃሰት ስሙ እየጠፋ ላለው ምስኪን አማራ ትግሬን እንዳላባረረ መስክረው አያውቁም።

  ትግሬ አማራን በተለይ የጎንደር አማራን ይቅርታ መጠየቅ አለበት።

 4. ከእባብ ጋር መዛመድ 100ሺ ጊዜ ይመረጣል !! ይገነጠላሉ ብየ ስጠብቅ ጭራሽ ተመልሰው ጎንደር ሊመጡ እነዚህ ዘረ ቅማላሞች ?
  የኛወቹ ከብቶች መቸም የማይማሩ ደደቦች ስለሆኑ ምንም ማድረግ አይቻልም ድጋሚ ሞታቸውን ይጋታቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.