የሰሞኑ ጥቃት! – አለማየሁ አበበ

1 min read
አቶ አለማየሁ አበበ

የጥላቻ ንግግር በህግ የሚያስጠይቅ ከሆነ በቅድሚያ ብዙ የኦሮሚያ ቁንጮ የመንግስት ባለስልጣናትና ካድሬዎች ላይ ጉድ ሊፈላ ይሆን ?
ይህን የምለው በግምትና በጥርጣሬ ሳይሆን ቢያንስ ባለፈው አንድ አመት በተለያዩ ኢቨንቶች ; ስብሰባዎችና የመሣሠሉት ጊዜያት በአፋን ኦሮሞ ለታዳሚዎቻቸው በሚያደርጉት ንግግር ; በማህበራዊ ሚዲያ በሚፅፉት ፅሁፍ : ምናልባትም ለመወደድና ለኦሮሞ ፍፁም ወገንተኞች ናቸው እንዲባሉ የሚጠቀሙበት ቃላቶችና አባባሎች በግልፅ ጥላቻን የሚያንፀባርቁ ናቸው ። ሕጉ ወደኋላ ላለፈው የሚሠራ ቢሆን ኖሮ መረጃውና ማስረጃው ሺህ ነበር ።

በጣም የሚገርመው ደግሞ እነኚህ ተናጋሪዎች ወይም ፀሀፊዎች እንዲያ ሲናገሩና ሲፅፉ ከኦሮሞ ውጪ ሌላ ማንም አፋን ኦሮሞ መናገር : መስማት : መፃፍና ማንበብ የሚችል ጨርሶ የማይችል ይመስላቸዋል እንዴ ? ለአብነት ያህል እንደምሣሌ የሚጠቀሙባቸው ቃላቶች ብንጠቅስ የኦሮሞ ሕዝብ ኦሮሞ ያልሆነን ሌላ ኢትዮጵያዊ በኦሮሞ ዘንድ እንደ ጠላት : እንደ ክፉ ባላንጣ እንዲታይ : እንዲጠረጠርና ጭራሽ ለኦሮሞ ጭቆና ;ምዝበራና ሰቆቃ ምክንያት እንደሆነ ተደርጎ በኦሮሞዎች ጭንቅላት እንዲቀረፅ ሆን ብለው የሚናገሩና የሚፅፉ ይመስላል ።

ምሣሌ ብንጠቅስ ዘወትር በተደጋጋሚ ከንግግራቸውና ከፅሁፋቸው የማይጠፋው “ዲኒ ” “ዲኒ ኬኛ” የሚለው ኦሮምኛ የአማርኛ ትርጉሙ “ጠላት ” ጠላቶቻችን ” የሚለው መቼም ጣሊያንን ወይም እንግሊዞችን ነው የሚሉት አትሉኝም ። ሌላው ዘወትር ከአፋቸው የማይጠፋው “ጀሪ ” የሚለው ኦሮምኛ ሲሆን የአማርኛ ትርጉሙም ” ሰዎቹ (non-oromos” ወይም እንደ አረፍተ ነገሩ አገባብ “የኛ ያልሆኑት ሠዎች” ማለት ሲሆን ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያኖች ለኦሮሞ ወገንተኛ አንደማይሆኑ የሚፈረጁበትና ለኦሮሞ ጥሩ አመለካከት ያሌላቸው ናቸው የሚል እንድምታ ያለው ነው ። ሌላው በጣም የተለመደውና የሚያሣዝነው ቃል “አለጋ” የሚለው ሲሆን ትርጉሙ “ባዕድ” ማለት ነው ። በንግግራቸውና ፅሁፋቸው አገባብ ደግሞ ኦሮሞ ያልሆነ ሠው ወይም ስብስብ ወይም ቡድን ሁሉ ለኦሮሞ እንደ ባዕድ የሚቆጠርና የሚፈረጅ የጥላቻ ስሜት ያዘለ ነው ። በጣም ያሣዝናል ። ኦሮሞ በባህሉ አቃፊና ሰው ከኦሮሞ ባይወለድም በጉዲፈቻም ሆነ በሌሎች የባህሉ ትሩፋቶች ኦሮማይዝ የሚያደርግ ነው እየተባለ ጊዜ አገኘን የሚሉ ባለስልጣናትና ካድሬዎች ይህን የጥላቻ መርዝ ሲረጩ ምን ይባላል ? ከፊሉ በኦሮምኛ የተናገሩት ነገር ተተርጉሞ ሲወጣባቸው ይቅርታ እንደመጠየቅ ስም ለማጥፋት ነው ገለመሌ እያሉ ይከራከራሉ ። እስቲ ይህን የኔን ትዝብት ኦሮምኛ የምትችሉ ሰዎች ሌሎችን የለየላቸውን ሚዲያና አክቲቪስቶችን ብቻ ሳይሆን ባለስልጣናትና ካድሬዎችን በኦሮምኛ ሲናገሩ ተከታተሉና አዳምጧቸው ወይም በማህበራዊ ድረገፅ ላይ የኦሮምኛ ፅሁፋቸውን አንብቡና ፍረዱ ።

የጥላቻ ንግግርና ፅሁፍ ህጉ ያለምንም አድሎ የሚፈፀም ከሆነ የመጀመሪያ ሰለባዎቹ ማን እንደሚሆኑ ለማየት ያብቃን ።ሰሞኑን እየደረሰ ያለው ጥቃት እኔ ላይ እንደደረሰ ነው የምቆጥረው ለሞቱት ነብስ ይማር ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ።

አመሰግናለሁ
አለማየሁ አበበ

12 Comments

 1. To Alemayehu Abebe,

  I think you don’t know the meaning of hateful speech. If you convert every word to the meaning you want it to reveal, according to your theory, every Oromo term is going to be loaded with “hateful” speech.
  1) Diinni means enemy when referring to the historical enemies of Oromo – the neftegan system and those currently promoting that system. Do you deny that Neftegan system didn’t exist in this country and the neo-neftegnas who aspire to bring back that system didn’t exist. We Oromos refer to ‘Diina’they area referring to the system and not particularly targeting a specific people of the country. Now a days, there are many ruminants of the old system and their followers. So long as there are followers of the old system, the subject people has the legitimate right to fear that the old system may come back and threaten them.
  2) Jarri means those referring to what the Oromos don’t consider as their own, mainly those with negative feelings against the Oromo. This negatively filled groups may be ruminants of the old regime. So, Jarri by no means refer to all non-Oromos or people who were victims of the neftegna system. So, what is wrong when this term is used in speeches. Do you deny that Oromos and other southern nations and nationalists including farmers of the Amhara and Tigray being victims of the Neftegan system. If you deny that, it means that you are also one who doesn’t want to learn from past history and one who promotes the old inhuman system to come again.
  3) Halagaa means in Afaan Oromoo one that was not related to you. This is a simple term and doen’t mean anything except this one I mentioned.
  In you opinion, you want to make every word of Oromo to be filled with hate speech, which is absurd. So, simply knowing the meaning of terminologies in Afaan Oromo doesn’t make you to clear tell why the word is used. Saying what has happened may not be considered as a crime. Oromos will continue mentioning wat has been done in the past as past history and none has the right to tell say this and don’t say that. The time now a more civilized time and you cannot get any information as you needed. You cannot forbid others to do what you don’t like to hear. It is not like the time of Minilik, when everything was done behind the screen.

 2. Badho,do you claim that you clearly know what hate speech is ? crazy enough. You have no even the slightest shame when you say that using the word enemy aganist fellow Ethiopians is not a hate speech at this moment in time in any political discourse by leaders ? What a wild thought and ignorance ? For you Jarri is a word to be used to express those cornered as enemy,and not all non oromos.Sad to see you muddling still a notion of enemy and friend between the citizens of one country ? What a dark ,uncivilized outlook ! You are mentioning neftegna system ,neftegnas to justify your case.For you Neftegna system is still well and alive in Ethiopia.Facts or fictions? Anyone who have different opinion than you is an enemy according to your discription.And you need to put in place ethinic apartheid system by intimidating ,harassing and discriminating in such rude and hate mongering techniques. That will never happen,believe me !

 3. አስፈሪና አሳሳቢ እየሆነ የመጣዉ የዘረኝት የኃይማኖትና የጥላቻ ፖለቲካ ለየት ባለ ምልከታ ሲዳሰስ የወጣቶች እጣ ፈንታስ? ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል

 4. The internally displaced refugees who are estimated to be 4 million + Ethiopians are not allowed to move back to their homes. They are living in the worst living conditions imaginable , the 4 million + people will remember and talk about their sufferings for the rest of their lives, imprisoning them now might give them the much needed medical care so many might prefer being imprisoned right now than this current situation of a slow and painful death.

 5. Badhoo, You have to upgrade your software. You are using a very old software designed by Shabia/foreign powers and implemented by Woyane. What you call Neftegan system is a fiction created to weaken and dismantle Ethiopia. Wake up and see the big picture. Read world History with an open mind.I know it is very difficult to remove some harmful software.It takes time but it can be done. Mine was corrupted like yours but I have liberated myself from hate. Now I have good will not only for all human beings but also for animals. With Best Wishes!

 6. Mr. አለማየሁ አበበ፣
  Can single words be considered as “hate speech”?? Why didn’t you post whole speeches or at least full sentences to corroborate your allegation?? Are such words to be found only in Oromiffa?? Hadn’t you been hypocritical, you could have added some hate-loaded, deogatory Amharic terms such as ‘menga’/ መንጋ/ (meaning herd) to refer to specific groups even in front of the PM!
  On what measures is the word ‘jara/jarri’ meaning ‘they’ more hateful than designating certain groups as ‘menga’??

  Your hypocracy has no limits!

 7. አቶ አለማየው ‘’የጥላቻ ንግግር በህግ የሚያስጠይቅ ከሆነ በቅድሚያ ብዙ የኦሮሚያ ቁንጮ የመንግስት ባለስልጣናትና ካድሬዎች ላይ ጉድ ሊፈላ ይሆን ?’’ ብለው ለጠየቁት ምንም ጉድ አይፈላም ነው መልሱ፤ እንደምናስታውሰው በአለፉት 27 ዓመታት ለህዝባቸው እንዳይሰሩ ይደረግ የነበረው የማሸማቀቂያ ታፔላ በእነሱ ላይ በመለጠፍ ነበር፤ አሁን ግን ይህ ሴራ ሊሰራ የሚችል አይመስለኝም ፡፡ እንደው በከንቱ አይሞክሩት፤ ሰዎቹ ሰላም፤ ይቅርታና ፍቅር ብቻ ነው በሄዱበት ቦታ ሁሉ የሚሰብኩት፡፡

 8. ጤና ይሥጥልኝ ስልህ አሞሃል ወይም በሽተኛ ነህ ማለት አይደለም ። እንዲሁም ባዳ ነህ ስልህ ጠላቴ ነህ ማለት አይደለም ።

  ለያንዳንዱ ቃል የጥላቻ ፍቺ እና ትርጓሜ ከሠጠነው ፓራኖያን (Paranoia) አባዛነው ማለት ነው ። ለምን የሚያሠባሥበንን እና የሚያበረታንን አንፈልግም ?
  ጥላቻን የዘራ ጥላቻን ያመርታል ። መጪው ትውልድ የሚፈልገው ሠላምን ፍትሕን እና ብልፅግናን እንጂ ጦርነት ወይም ደም ማፍሰስን አይደለም ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.