አስገራፊው ዐቃቤ ሕግ የአብይ አስተዳደር ተሿሚ ናቸው!? – ኢዩኤል ፍስሃ

1 min read

ለለውጡ አፍቃሪያን ዛሬ የተሰማው መርዶ አስገራፊው ዐቃቤ ሕግም ሹም መሆኑን የሚገልጽ ነው። ያው ማዕከላዊ በሌላ ማዕከላዊ ተተክቶ የለም።ለሁሉም ያንብቡት አስተያየትዎን ይስጡበት ሼር አድርጉት

“ አስገራፊው ሰውዬ በሕግ ማስፈፀም ዘርፍ ም/ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሆኖ“

በኢ.ፊ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለሚገኙ ዐቃብያነ ሕጎች ከወንጀል ምርመራና ከክስ አመሰራረት ጋር ተያይዞ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ልደታ አዳራሽ ስልጠና እየተሰጠ ነው ይልሃል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፡፡ አያይዞም በስልጠና መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሕግ ማስፈጸም ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተወካይ የሆኑት፤ አቶ ብርሃኑ ወንድምአገኝ ናቸው ይልሃል፡፡

ብርሃኑ ወንድማገኝን ለማታውቁት ከታች ባያያያዝኩት ፎቶ ላይ ቆሞ የሚታየው ሰውዬ ነው፡፡ እጅግ አረመኔና ለፍትሕ ግድ የሌለው በቀደመው የሕወሓት ስርአት ዜጎችን በሀሰት ሲወነጅል የነበረ ዐቃቤ ሕግ ነው፡፡ ከማዕከላዊ ገራፊዎች ጋርም በቅርበት ሲሰራ የነበረ፣ ለሙያውም ሆነ ለራሱ ክብር የሌለው ተልካሻ ሰው ነው፡፡ ስንቱን ያለኃጢአቱ በእስር እንዲማቅቅ፣ ጥፍሩ እንዲነቀል፣ ኮዳ ብልቱ ላይ እንዲንጠለጠል…. ያደረገው ሰውዬ ዛሬም በፍትሕ ስርአቱ ውስጥ እንዲገኝ መደረጉ በዜጎች ስቃይና እንግልት ላይ መሳለቅ ነው፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎችን ተሸክሞ ነው እንግዲህ የፍትሕ ስርአቱን ሪፎርም ማድረግ ተችሏል፡፡ በስራችንም ማንም ጣልቃ አይገባብንም እየተባለ የሚደሰኮረው፡፡

መንግሥት የፍትሕ ስርአቱን ለማሻሻል እየሞከረ ነው፤ ፍላጎቱም አለው፤ የዳኞችና የዐቃቤ ሕጎች አቅም ማነስ ነው ፈተና የሆነበት፤ የሚሉ ምኑም ያልገባቸው የዋሆች ይህንን ሲያዩስ ምን ይሉን ይሆን?! አስገራፊው ሰውዬ በሕግ ማስፈፀም ዘርፍ ም/ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሆኖ የተሾመው መንግሥት የኋላ ታሪኩንና ስራውን ስለማያውቅ ነው እንደማትሉን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ዛሬ በአጋጣሚ ስለብርሃኑ አነሳሁ እንጂ ትላንት ሕወሓትን ሲያገለግሉ የነበሩ ዳኞች ዛሬም በቦታቸው እንዳሉ ማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ በሌላ ቀን ስለእነሱ እመለስበታለሁ፡፡

 

3 Comments

  1. OPDO ODP youth league members are the makers and shakers ordering prosecutors and judges who to prosecute and who to deem guilty.

  2. በየክልሉ የሚገኙ የመንግስት መስርያቤቶች የኢህደግ አወቃቀር እና አደረጃጀት ሀላፊዎቹም አስፈፃሚዎም የድሮዎች ናቸው ኢህደግ ቢዋሀድም ቢቀላቀልም እንደ ተግዳሮት የሚሆነው በተመሳሳይ ሀላፊዎችም አስፈፃሚዎችም እነሱ ናቸው የሚሆኑ ብዙ ለውጥ አይኖርም ለውጥ የሚኖረው ሌላ አዲስ ፓርቲ በአገር አቀፍ ካሸነፈ/ከተመረጠ ነው፡፡

  3. @Efrem!!
    And, OPDOs are the urines of ugly nafxanyas. OPDO was created in the house of nazi tigrean ruling class for and by the enemy of Oromos-TPLFites. Oromo has no hope on this servant/ashkar organization. No matter how long the night is, the day shall follow for Oromo diginity, liberty, and prosperity with all Ethiopians. Urine of nafxanyas, TPLFites, and their servants will not hinder us from our journey.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.