በኢትዮጵያ እና በአለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ መካከል የ90 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈረመ

1 min read

 በኢትዮጵያ መንግስትና በአለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ መካከል የ90 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈረሟል።

ስምምነቱን በሮም የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ እና የአለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ፕሬዚዳንት ጊልበርት ሁንግቦ በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል።

የብድር ስምምነቱ ለቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መሆኑን በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በረጅም ጊዜ የሚመለሰው ይህ የብድር ስምምነት በሀገሪቱ በአየር ንብረት ብክለት ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን ለመደገፍ የቀረበውን ጥናት ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ መሆኑም ተመላክቷል።

ከዚህ ባለፈም ለቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ቀጣይነት ያለው ልማትን ለማረጋገጥና በዝናብ ላይ ብቻ ተመስርተው የሚሰሩ የግብርና ስራዎችን ለማገዝ የሚያስችል መሆኑ ነው የተገለጸው።ኤፍ ቢ ሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.