ደመቀ መኮንን እንዴት ህወሖትን ጉድ እንደሰራት አቦይ ስብሀት መቐለ ላይ ተናገሩ – አሸናፊ አብርሃ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

“ለትህነግ ታማኝና ታዛዥ ነበር። ፈፅም! የተባለውን ነገር ለመፈፀም ‘ ለምን? ‘ ብሎ እንኳን አያውቅም። አንድ ቀን ግን የሱዳን ግዛት የሆነውን አዋሳኝ መሬት ለመስጠት ፈርም ሲባል ና “አይሆንም አልፈርምም!” ብሎ አሻፈረኝ ሲል ያኔ ይህ ሰው አንድ ቀን እንደሚሸውደን እርግጠኛ ሁኜ ለጓዶቼ ነግሬያቸው ነበር። ሁሉም የእኔን እይታ ሳያቅማሙ ሲቀበሉኝ ጌታቸው ግን አታስብ እሱ መዳፋችን ውስጥ ነው። የትም አይደርስም!” ብሎ በንቀት ሲመልስልኝ ሲሰሙ ጓዶች በጌታቸው ላይ ከፍተኛ እምነት ስለነበራቸው እነሱም ወደጎን ተውት።

እኔ ግን “ጀግናን የሚገድለው ተራ ወይም የተናቀ ሰው ነው።” ብየ ጌታቸውን አስጠንቅቄው ነበር። የመጨረሻው የጠ/ሚ የውድድር እለት ዋዜማ ማታ ላይ በነበረን ስብሰባም ይህ ሰው አንድ ነገር እንዳያደርግ በሚል ጥሩ ስሜት እንደማይሰማኝ ስናገር በተለይ ጌታቸው አሰፋ፣ ጌታቸው ረዳ ና አቦይ ፀሀየ “አትጨነቅ ደመቀ በሚገባ አምኖበታል። የተባለውን ባያደርግ የሚደርስበትንም
ያውቃል ። በተጨማሪ ደግሞ ሁሉንም የብአዴን፣ የኦህዴድ ና የደህዴን አባላት ቀጣይ የከፍተኛ ሚኒስትርነት ስልጣን ና ዳጉስ ያለ ገንዘብ እንደሚሰጣቸው በራሳቸው ሰዎች ስለተነገራቸው በደስታ ተቀብለውታል። ” ብለው ሊያሳምኑኝ ሞከሩ። በእርግጥም በተለይ የደህዴንና የብአዴን አመራሮች ለስልጣንና ለጥቅም የማይከፍሉት ዋጋ እንደሌለ በማስረጃ ሲያስቀምጡልኝ ባላምንበትም ይሁን ብየ ተውኩት።

በትጥቅ ትግል ወቅትም ሆነ በስልጣን ላይ ከሆንን በኋላ ድርጅቴ ሊደርስበት ከተጋረጠ እስከ መፍረስ የሚያደርስ ከፍተኛ አደጋዎች በአለቀ ሰአት እንኳን እንደታደግሁ ስለሚያውቁኝ ይቀበሉኛል ብየ ተስፋ አድርጌ ነበር። አሁን ግን ከእኔ ውጪ የእኔን ሀሳብ የሚያስብ ና የሚደግፈኝ ሰው ሳጣ ዝም ብየ ቁጭ አልኩና የሚሆነውን ለማየት ወሰንኩ። በመጨረሻ ግን ለረጅም አመታት በነበረን የትጥቅ ትግል መሰሪው ሻዕቢያ እንኳን ሸውዶን የማያውቀውን ሽወዳ ደመቀ ሸወደን! አዋረደን! ለዚህ ውድቀታችን ተጠያቂዎች ሁለቱ ጌታቸው የተባሉትና ፀሀየ ናቸው። ”
አቦይ ስብሀት ዶ/ር አብይ በተመረጡ ማግስት ለትህነግ አመራሮች በመቀሌ ከሰጡት አስተያየት ከትግረኛ ወደ አማርኛ የተቀየረ።

ላወቀበት በ514 ቃላት ትልቅ መጽሐፍ መጻፍም ይቻላል! ይነጋል በላቸው (ከአዲስ አበባ)

3 Responses to ደመቀ መኮንን እንዴት ህወሖትን ጉድ እንደሰራት አቦይ ስብሀት መቐለ ላይ ተናገሩ – አሸናፊ አብርሃ

 1. Turinafa yehone sewye neww. 27+ ametat sirawun serto baleqe sieat Demeke min teamir lifetrielet asbo norwal? Lemayaqush
  tattegni!

  Avatar for Sef

  Sef
  November 27, 2019 at 11:12 am
  Reply

 2. I laughed so much my tears were coming out and it makes me laugh again that the old guard Sebehat Nega is not sleeping now a days. I remember reading or listening once that says “You do not see Demeke Mekonen wrestling you only realize you are on the ground “Demeke has out smarted the evil minded old guard Adwans from ADWA particularly SEBHAT NEGA the master evil Mafia.
  And now instead of confessing his sins and act as an elderly he is board and burning in revenge for what the smart Demeke has accomplished.
  I will laugh again when SeBFAT comes with another ABYI’s or GEDU’s prank they played to paralyze him.
  GOD PROTECT ETHIOPIA FROM ANOTHER EVIL ADMINISTRATION AND BLESS HER.
  MUCHFUN
  OTTAWA, CANADA.

  Avatar for Muchfun A Kassa

  Muchfun A Kassa
  November 27, 2019 at 11:48 am
  Reply

 3. ነገሩ እሾህን በሾህ ነው የሆነው እንጂ ጀግናን ደካማ ጣለው ብሎ ማውራት ግብዝነት ነው።ወያኔ በተፈጥሮዋ እ/ር በምድር ላይ ከፈጠረው ፍጥረት ሁሉ መሰሪና እጅግ ተንኮለኛ ፍጡር ናት።
  እውነታውም የእባብ መርዝ ለእባብ እንደማይሰራ ነው

  Avatar for አሻግሬ ጀማነህ

  አሻግሬ ጀማነህ
  November 29, 2019 at 12:08 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.