“የተፈፀመብን በደልና ህገ ወጥ ተግባር ይታወቅልን!” እነ ክርስቲያን ታደለ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

“ክርስቲያን ታደለ፣ በለጠ ካሳ እና ሌሎች አብረዋቸው በእስር የሚገኙት ህዳር 17 ለ18/2012 ከሌሊቱ 10:30 በአንድ ሻለቃ የፌደራል ፖሊስና አንድ ሻለቃ አድማ በታኝ በመጠቀም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መሬት ለመሬት በመጎተትና ድብደባ በመፈፀም ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት ያወረዷቸው ሲሆን፣ በየትኛውም ጊዜ እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚችልም ዛቻ ደርሶባቸዋል። በድባደባውም ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን እስካሁንም ምንም አይነት ህክምና አላገኙም። በተለይ በፈንታሁን ሞላ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

ይህን ህገወጥና ኢሰባዊ እርምጃ የተቃወመ የአንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባል (ሙሉቀን ወንድምነህ) የታሰረ ሲሆን፣ በሽብር ተጠርጥረሃል ተብሎ ሰሜን ማዘጋጃ ላዛሪስት ት/ት ቤት ፊትለፊት ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መሆኑ ተረጋግጧል።
እነ ክርስቲያን እና በለጠ ካሳ ቂልንጦ ዞን 4 ማግለያ ወይንም ሳጥን ቤት በመባል በሚታወቀውና ጣራውም ግድግዳውም ኮንክሪት በሆነ ክፍል ውስጥ የታሰሩ ሲሆን የሽንት ቤቱ ሽታና ፍሳሽ ወደ ማግለያ ክፍሉ የሚገባ በመሆኑም ለጤና ጉዳት ተጋልጠዋል።

የታሳሪዎቹ ንብረቶች በፖሊስ እጅ ናቸው። ለምሳሌ የክርስቲያን ታደለ መነፅር፣ እንዲሁም የሌሎችን ታሳሪዎችም የተለያዬ አልባሳትና እቃወች ተወስደውባቸዋል። ለታሳሪዎችም ምንም ዓይነት የህትመት ውጤቶች ሊገቡላቸው እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል። ወደ ቂሊንጦ ሲገቡም የተጠረጠሩበት የወንጀል አይነት “ሽብር” በሚል ካርድ ተሰጥቷቸዋል። መ/አ መሳፍንት ጥጋቡም አብሯቸው ታስሮ ይገኛል።”

(የመረጃው ምንጮች ቤተሰቦቻቸው ናቸው)
በላይ ማናየ

One Response to “የተፈፀመብን በደልና ህገ ወጥ ተግባር ይታወቅልን!” እነ ክርስቲያን ታደለ

 1. *The habesha’s irrelevant failed legal system by must be replaced completely with the time tested ABA Gaddaa legal system.

  *All governmental offices and non governmental businesses must close all day long on Fridays for Jumea prayer.

  *Employees and students must be allowed to pray at salat time if they choose to.

  *Arabic language needs to be thought in all public schools around the country with it having its own department with students majoring Arabic at higher learning institutions.

  Mohamed Habbas
  December 5, 2019 at 6:24 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.