አቶ ለማ መገርሳ ፣ከዚህ በኋላ፣ ሿሿ አልሠራኋችሁም ማለት አይችሉም። (ከትህዳኃ ሣኤማ)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |
       ሀገራችን   የፍትህ መቃብራ እየሆነች ነው። ፍትህ በየዕለቱ እየሞተ በየቀኑ ሲቀበርባትም እናሥተውላለን። ፍትህ ብቻም አይደለም ለህዝብ ምለው ተገዝተው የገቡትን ቃል እንደዋዛ ገድለው የሚቀብሩም እንዳሉ  ህዳር 2012 ሳይጠናቀቅ  በአቶ ለማ መገርሣ ተገንዝበናል።ጃዋርን ቀድመን አጥፊ ሃሳቡን ሥለምናውቅ እና የለየለት ያሸባሪ ነት ተግባሩን ሥላየን ዛሬ በይፋ እያደረገ ያለው የዘረኝነት ቅሥቀሣ (በግል ቴሌቪዥኑም ጭምር )አላሥገረመንም።እኛን ያሥገረመን፣ ከአንበጣው  ፣ ወቅቱን ካልጠበቀው ዝናብ  ጥፋት በኋላ እንሆ ዛሬ እውነተኛውን ሿ!ሿ! አቶ ለማ መገርሣ በአደባባይ  መፈፀማቸው ነው።”ፌክ” ሿሿ ሣይሆን ትሩ” ሿሿ!! “። ሥለሆነ ከእንግዲህ አያሥተባብሉም።
    “የተናገሩት  (የገቡት) ቃል  ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ።”  ማለት ፣ለሀቅ ሞቾች የዋዘ እንዳይደለ በመዘንጋትም ይሁን በማርክሥ ቲዎሪ እምነትን ክደው፣ እንሆ   አቶ ለማ ማንም አይጠይቀኝም በማለት ድፍን የኢትዮጵያ   ህዝብን ከምር “ሿሿ” ሰርተውታል። …
   አምና፣ “ኢትዮጵያዊነት  ሱስ ነው። ” ብለውን ሲያበቁ ፣ ተሸብልለዋል ። “የኢትዮጵያን ህዝብ ” ሿ!ሿ!” ሠርተውታል። “ተብለው ሲታሙ፣ ሀሜቱ ውሸት እንደሆነ እና እሳቸውም የኢትዮጵያን ህዝብ “ሿ !ሿ ! ” እንዳልሰሩ ማሃላ በቀረው ንግግር ፣ኮስተር ብለው ለኢትዮጵያዊነት ዘብ እንደሚቆሙ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ዛሬ ኢትዮጵየዊነት ሱስ ነው ያልኩት      “ከጫት፣ከሲጋራ፣ከመጠጥ ሱስ አንፃር ተመልክቼው ነው። ” የማለት ያህል የምፀት ንግግር የተናገሩ ይመሥል  ፣እሳቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒሥቴር ሆነው ሳለ     “እኔ የቆምኩት ለኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ብቻ ነው።” በማለት ከምር የኢትዮጵያን ህዝብ” ሿሿ !” ሠርተውታል።
      ከምር እንነጋገር ቢባል፣   ይህቺ  ሀገር የአንድ ፣የሁለት ፣የሦሥት ቋንቋ ተናጋሪ ሰዎች ሀገር ናት ወይሥ ከሠማንያ አምሥት በላይ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ህዝቦች ባለቤት?
         ኢትዮጵያ የእኔ፣  እና የአንተ፣ የእርሷ እና የእርሱ፣በአጠቃላይ የእኛ የሠማንያ አምሥታችንም ባለቋንቋዎች ንብረት አይደለችም እንዴ?!
   የኢትዮጵያ ምድርም ቢሆን የየትኛውንም ቋንቋ ተናጋሪ ሰው፣ ጠፍጥፎ አልፈጠረውም።ሁላችንም በፈጣሪ ተፈጥረን፣ ከሴት ማህፀን የወጣን ነን ። ኢትዮጵያም የሁላችን እናት ሀገር ናት።   የኦሮምኛ ቋንቋን እሥከ ሰባት ትውልድ የሚናገሩ ሰዎች ብቻም ለማንም ግልፅ ነው።
      ሁላችንም  ሰው ነን።ብዛ ቢል ከሃምሳ ትውልድ በፊት ወንድማማቾች እና እህትማማቾች ነበርን። የተለያየ  ቋንቋ ፣ኃይማኖት፣ባህል ፣ወግና ቱውፊት ያልነበረን።  የዘመን እርጅና እና የእኛው ያለመበልፀግ ነው  የተለያየ ባህል እንዲኖረን ያደረገን።
    በመበልፀግ የማይረቡና የማይጠቅሙ ባህላዊ ወግና  ሥርአቶቻችን ማስወገድ ይቻል ነበር። ለመበልፀግ ደግሞ ተግቶና ነቅቶ መሥራት ያሥፈልጋል።እንዳንነቃ እና ተኝተን እንድናቀላፋ እና ላለመንቃት አሻፈረን እንድንል የሚያሥገድዱን መንግሥታት በላያችን  ለዘመናት መጥፎ ጥላቸውን አሳርፈውብን እንዳንላወሥ አድርገዋል። ዘወትር የሚያሥተኛ የቆዳ ማዋደድ እና የቂጥ ገልቦ ክንብንብ ጥላ  አጥልተውብን ለዘመናት    ከቆዳ ማዋደድ እንዳንላቀቅ አድርገዋል ።
    እውነቱ ግን እኛ እንደማንኛውም የዓለም ህዝቦች የሰው ሥብሥብ ነን።ሥራችን አንድ ነው።በጊዜ ሂደት ከወንድም እህቶቻችን ተነጥለን ፣በዝተን እና ተባዝተን ዛሬ ኢትዮጵያ በምትሰኝ ሀገር ላይ ነገ አፈር እሥከምንሆን የምንኖር ነን።ቋንቋችን ቢለያይም አንዳችን አንበሣ አንዳችን ደግሞ ጦጣ ከቶም አይደለንም።
      የተለያየ ቋንቋ መናገር የሰው ልጅ ብቻ ችሎታ ነው።የትም ሀገር ሄዶ ለዓመታት ከሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች ጋር የሚኖር ከእርሱ ቋንቋ በተጨማሪ   የሀገሬውን ፣ ቋንቋ አቀላጥፎ መናገር ሰው ብቻ ነው።
    እውነት ነው፣   በግዜ ሂደት ውስጥ ወንድማማቾቹ እና እህትማማቾቹ እኛ ሰዎች ፣እየበዛን ኑሮን ለማሸነፍ ወይም በህይወት ለመቆየት በየአህጉሩ ተሰደናል። በዚህም የተነሳ የተለያየ ቋንቋ ሊኖረን ችሏል።
    በዚህ ዘመን፣ ሰው ሁሉ አንድ ቋንቋ ይናገር ።አንድ ባህል  እና የአኗኗር ዘይቤ  ይኑረው። አንድ ኃይማኖት ና የአምልኮ ሥርአት ይከተል። አይባልም።በትእዛዝ የሚሆን ነገር አይደለማ !!  ይሁን እንጂ ቋንቋን እንደ እንግሊዞች ፈረንሣዮች ፣ አረቦች ወዘተ ማሥፋፋት ግን ይቻላል።
     በኃብት እና በሥልጣኔያቸው ተጠቅመው አፍሪካን  በመውረር ቋንቋቸውን ለብዙ የአፍሪካ ሀገሮች እንግሊዞች አውርሰዋል።አረቦች እና ፈረንሳዮችም እንዲሁ።
       ካለንበት የኑሮ ደረጃ አኳያ እንጂ እንደ አሜሪካ ሁለንተናዊ ብልፅግና ኢትዮጵያዊያን ቢኖራቸው ቋንቋቸው አንድ ነው የሚሆነው። አንድ አይነት ቋንቋ መናገራቸውም ይጠቅማቸዋል እንጂ አይጎዳቸውም። ቋንቋውም ከወላጆቻቸው በመወለድ ስለማይገኝ ቋንቋን  የግሌ ነው ማለት አይችሉም።ሁሉም ቋንቋዎች የሰው ሁሉ ንብረቶች ናቸው ።(“ብሔር ” ማለት ሀገር ነው። “ሰብ” ደግሞ ሰው ማለት ሥለሆነ ብሔር ብሔረሰብ በማለት አልቀባጥርም።)
     የተከበሩ አቶ ለማ መገርሣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒሥቴር ሆነው ፣ ከ85 በላይ ቋንቋ የሚናገሩ ህዝቦች ተምሳሌት የሆነውን የሀገር ዋልታ እና መከታ የሆነውን የተከበረውን መከላከያ ሰራዊት እየመሩ ፣መጪው ምርጫ እንጂ  የያዙት ኃላፊነት ምንም ሳይመሥላቸው፣  በተጎናፀፉት  ምቾት ላይ ሌላ ምቾት ለመደመር ሲሉ “ሥለ አንድ ቋንቋ ተናጋሪ የሰው ሥብሥብ እንጂ ሥለሌላው አያገባኝም ።”በማለት በሾርኒ (በአግቦ) መናገራቸው   ያላሥገረመው ኢትዮጵያዊ  ያለ አይመሥለኝም።
እናም ከዚህ የሾርኒ ንግግራቸው ተነሥተን   አቶ ለማ አሁን  በእርግጠኝነት ” ሿ!ሿ!” እንደሰሩን ያለአንዳች ማመንታት መናገር እንችላለን።
      አንድ የኢትዮጵያ ትልቅ ባለሥልጣን ሆነው ፣ትልቁን የሀገር አውራ እንዲመሩ አደራ ተጥሎባቸው ሣለ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒሥቴር ተሰኝተው የክብር ወንበር ላይ እንዳሉ በመዘንጋት፣ በወረደ ዘረኝነት ውሥጥ ገብተው “ተልኮዬን አልፈፀምኩም። ኦሮሚያ ወይም ሞት! ነው መፈክሬ፣ ካልሆነም ደግሞ የጠቅላይ ሚኒሥቴር ወንበር ላይ የምቀመጠው በቋንቋ ፓለቲካ ብቻ ሥለሆነ ፣ በአንድ ፓርቲ ሥም በመካተት ዘረኝነት እንዲወድም አልፈልግም።” በማለት የነጃዋርን ሃሳብ ተቀላቅለዋል። ይህንን  ያልተጠበቀ  ከአብይ ፍፁም ተቃራኒ የሆነ የጃዋርያዊያንን ሃሳብ ማራመዳቸው፣እንደ አንድ ግለሰብ ባያሶነጅላቸውም ፣ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ ቢኖር ከዚህ ንግግራቸው በኋላ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒሥቴርነታቸው ያበቃ ነበር።ያም ሆነ ይህ በዚህ የአንድ የሀገር መከላከያ ሚኒሥቴርን የማይመጥን ንግግራቸው ጨዋ እና ኩሩ ኢትዮጵያዊ ሁሉ አፍሯል። (ምነው በዝምታ ሁሉንም ነገር ቢያሳልፉ?ምነው ህዝብ በሳቸው ላይ ተሥፋ ከሚቆርጥ ፣ ቢበደሉ እንኳ “ለሁሉም ጊዜ አለው።”በማለት ቢታገሱ? ብሏል።)
    በአሣፋሪ ቃለ ምልልሱ፣ ማፈር ብቻም አይደለም፣ ይህቺ ሀገር ፍትህ የተዛባባት። ግልፅነትም ሆነ ተጠያቂነት የሌለው ሥልጣን የሚታደልባት።  ሁሉም ለኪሱ እና ለጥቅም አጋሩ ኪሥ መደለብ ሢል በድሃው እና በእናት ሀገር ኢትዮጵያ እያሳበበ የሚነግድባት።መሆኖን በመገንዘብ መጭው ጊዜ የሤጣን እንዳይሆን እዝጊኦታውን ለፈጣሪው ሳያቋርጥ፣ በማሠማት ላይ ይገኛል።
   ይህ ህዝብ ቀና ብሎ ከሚያየው የእግዜር አገር ውጪ ምን መፅናኛ አለው???  የመከላከያ ሚኒሥቴሩ ለመከላከያውም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ታማኝ አለመሆናቸውን በግልፅ  ሲናገሩ ሠምቶ ካልደነገጠ እና እዚጊኦታውን ለአምላክ ካላቀረብ ነገ ማን ይታደገዋል???እናም  በሜንጫ አንገቱ እንዳይታረድ ሲል፣ በቋንቋ ታከው ለመንገሥ ሲሉ አገሪቱን ወደማያባራ ትርምስ ውስጥ መክተት የሚፈልጉትን እብዶች  ሁሉ ሁለመናቸውን እንዲያሥርለት ቀና ብሎ በእዝጊዮታ ፈጣሪውን ቢለምን አያሥገርምም።የሚያሥገርመው የአቶ ለማ አልደመርም ባይነት ነው።
    አፍ አውጥተው  አልደመርም በማለት ሲናገሩ፣ በቋንቋ ተገን ለመንገሥ የሚፈልጉ በሥልጣን ጥምም ያረሩ መሆናቸውን ይፋ አውጥተዋል። አልደመርም ማለት፣ ” ፍላጎቴ መገንጠልና እንደሂትለር  ዘር ማጥራት  እሥከ ሰባት ቤት ድረሥ ኦሮሞ ያልሆነውን እየጨፈጨፍኩ እግዜር ከፈጠራት ምድር ማሠናበት ነው ዓላማዬ ማለት ነው። ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ያልኩትም እንደ ጫት እና ካቲካላ ሱስ ቆጥሬ እንጂ ነው። ” እንደማለት ይቆጠራል።ያሳዝናል።
     ያሳዝናል።የኢትዮጵያ ዜጋ ሁሉ ሰው መሆኑን እና በምድር አጭር   ቆይታው፣ተደሥቶ ለመኖር ሌት ተቀን የሚፍጨረጨረው  ሆኖም  ግን ምንም ሳያልፍለት፣ ከትላንት እሥከዛሬ፣ በእሳቸው እና  በመሰሏቻቸው ብዝበዛ ራቁቱን ተወልዶ  ፣በድህነት ራቁታዊ ህይወት ኖሮ እንዲሞት የተፈረደበት ፣ካልተቋረጠ ሃዘንእና ችጋር  እንዳይገላገል መፍረድ ነው።
     መቼ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ” ሿ!ሿ!” ከሚሰራ የሌብነት ፖለቲካ የሚገላገለው???መቼ ነው ከ እሥከ ሳይባል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ፣በነፃነት፣በተሞላ ፍትህ መኖር የሚጀምረው? ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቱ ተጠብቆለትስ የሚኖረው መቼ ነው? መቼ ነው ሥጋውን እያበሉ ከእነ ግብራበሮቻቸው የደለቡ ባለሥልጣኖች በቪ 8 እየዘነጡ እና በባለአምሥት ኮኮብ ሆቴል እየተምነሸነሹ ፣ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እና በአንበጣ  ሰብሉ በማሳው ለሾቀበት  ገበሬ እና መኖር ከአቅሙ በላይ ለሆነበት ሠርቶ አደር የከተማ ነዋሪ ተቆርቋሪ እና ብልፅግናን ወላጅ ነን እያሉ የሚያሾፉ???መቼ ነው፣  የሰጠኸኝን አጀንዳ እያሥፈፀምኩ ነው። ለአንተ ነፃነት እና ሦሥት ጊዜ መብላት ነው ፣ሌት ተቀን እምታገለው(…..) እያሉ ማሾፋቸውን የሚያቆሙት??? ።
     የኢትዮጵያ የቋንቋ ፖለቲከኞች ፤ በመቀላመድ፤   የማይፈፀም   ቃል በመግባት ፤ ንቃተ ህሊናው ባልዳበረ ወጣት መሥዋትነት ፤ እንዲሁም በአፍ ብልጠት እና ሿሿ በመሥራት  ሥልጣናቸውን እሥከለተሞታቸው ለማራዘም በሤራ  ፓለቲካ እየተጠላለፉ የሚኖሩት እስከመቼ ነው???

2 Responses to አቶ ለማ መገርሳ ፣ከዚህ በኋላ፣ ሿሿ አልሠራኋችሁም ማለት አይችሉም። (ከትህዳኃ ሣኤማ)

 1. The 1996 firing oromo student from university, brought Jal Maro. The home back coming oromo students from amhara region will bring what? we will see it. To bring best result better to educate them in oromia region.

  Avatar for Abichu eyesake belachew

  Abichu eyesake belachew
  December 2, 2019 at 2:43 am
  Reply

 2. You better drop out the game being played by the OPDOs-Oromo no.1 enemies, the urine of nafxanyas. Sit down at round table and solve the empire’s problems. Oromo has been systematically excluded from the political, economic and social transactions of this empire. So, that has to be healed by hook or crook. Oromoo shall be ‘abbaa biyyaa’ on its territory and resource. This doesn’t mean we will exclude others from the region. We will live in a harmony with all peoples of this empire, but with respect and liberty. If you don’t want this go hell. No more abyssinian supperiority.

  Avatar for Gurbattii Namaa

  Gurbattii Namaa
  December 2, 2019 at 6:16 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.