“ዉሻዉ አብዮታዊ መስመር ይዟል! በግ መሆኑንም አምኗል” ታዬ ደንደአ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

መቸም ቀን ሄዶ ቀን ይመጣል። የህዳር 21/2012 እሁድም ታሪካዊ ቀን ሆኖ አልፏል።
የህወሀት ነገር ደግሞ ሁሌ ይገርማል። አንዳንዴ ፕሮፓጋንዳዉ ተፈጥሮን እስከ መቀየር ይደርሳል። ከሁሉ በላይ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሲደሰኩር የነበረዉን ጉዳይ መልሶ ይክዳል። ከአስር ዓመታት በፊት ጀምሮ በየጉባኤዉ ” የኢህአዴግ መዋሀድ እና የአጋሮች መደመር ከልክ በላይ ዘግይቷል” ብሎ ሲናዘዝ ከራርሟል። ዛሬ ደግሞ “ዉህደቱ ከብርሃን ጉዞ በላይ ፈጥኗል” ሲል ይሰማል። ይህ በምን ሎጂክ ሊሆን ይችላል? ለነገሩ ህወሀት ቤት ሎጂክ መች ይሰራል? ከፈለገ ዉሻን አሳምኖ “በግ ነኝ” እንዲል ያደርጋል። ሰዉ ገሎ ከቀበረ በኋላም ይፈልጋል!

በቃሊቲ እስረኞች አንድ ቀልድ ነበራቸዉ። ቀልዱ አብዮታዊ ታጋዮችን ይመለከታል። በ1980ዎቹ አጋማሽ አንድ ታጋይ በግ ለመግዛት ከካምፕ ወደ ገበያ ይሄዳል። መንገድ ላይ ወፈር ያለ ዉሻን ያገኛል። ወዲያዉ ተኩሶ ይገልና ተሸክሞ ወደ ካምፑ ይመለሳል። ጓዶቹ ሲያዩት ገረማቸዉና “ያመጣሄዉ በግ ዉሻ ይመስላል” ይሉታል። እሱም ዘና ብሎ ” አዎ መጀመሪያ በግ ነበር። አሁን ግን በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ተጠምቆ በግ መሆኑን አምኗል” ሲል ይመልሳል። እነሱም ታጋዩን አምነዉ ህደቱ ቀጠለ ይባላል። የዉህደቱ መዘግየትና መፍጠንም በዚያዉ ይለካል።
ከምንም በላይ ህወሀት መደመርን ይጠላል። ምክንያቱም መደመር የኢትዮጵያዊያንን እዉቀት፣ ገንዘብ እና ልምድ አሰባስቦ ወደ አቅም ይለዉጣል። ይህ ደግሞ ለህወሀት ህልዉና ከፍተኛ አደጋ ይፈጥራል። የህይወቱ ምሰሶ ክፍፍል መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። የመንኮታኮቱ ምክንያትም “እሳትና ጭድ” ሳይታሰብ በድንገት መደመራቸዉ እንደሆነ ጌች አንድ ወቅት ተናግሯል። የቀድሞ ጓዳችን ህኸሀት በብሔር፣ በሀይማኖት፣ በአከባቢ እና በተገኘዉ ቀዳዳ ሁሉ ኢትዮጵያውያንን ከፋፍሎ እያጋጬና እያጋዳደለ በህዝብና በሀገር ኪሳራ እያተረፈ ኖሯል። ዘና ብሎ ውስኪ ሲጠጣ ድንገት “መደመር” ሲመጣበት እንዴት ትላንት ያለዉን ሊያስታዉስ ይችልላ? ደግሞ በእርጅና ምክንያት መርሳትም ይኖራል።
በሌላ በኩል “ሆድ ሲያዉቅ ዶሮ ማታ” ይበላል። ህወሀት ሁሌም ብልጣብልጥ ሆኖ ለማታለል ይሞክራል። “አሁን ሀገር በአንገብጋቢ ችግሮች ስለተያዘች ውህደቱ ከምርጫዉ በኋላ ይሁን” ይላል። ራሱ በተማሪዎች፣ በብሔሮች እና በሀይማኖቶች መሀከል እሳት ለኩሶ “መጀመሪያ ስለሰላም እናዉራ” ሲል ይጠይቃል። ለመሆኑ ችግሩን በፈጠረዉ ከፋፋይ እሳቤና አወቃቀር ችግሩን መፍታት እንዴት ይቻላል? በህዝቡ ዘንድ የተጠላ ፕሮግራም፣ ስምና ምልክት ተይዞስ እንዴት ምርጫ ይታሰባል? ስሌቱ ይገባናል። ውህደቱ በዘገየ እና ቀዉሱ በቀጠለ ቁጥር ህዝቡ ከለውጥ ሀይሉ ተስፋ ይቆርጣል። በሰላም ወጥቶ መግባት ሲያቅተዉ ያለፈዉን ስርዓት ይናፍቃል። ያኔ ህወሀት አፈር ልሶ በመነሳት ወደ መንበሩ ይመለሳል። ይህም ዘመናዊ የፐለቲካ ዘዴ ይባላል።

ብልፅግና ፓርቲ እንዳይወለድ ህወሀት ብዙ ለፍቷል። “አሀዳዊ ስርዓት እየመጣ ነዉ” በማለት አሰልቺ ፕሮፓጋንዳ ነዝቷል። ጥቂቶችን ቀጥሮ ብዙዎችን አደናግሯል። ሰላም ለማደፍረስ ገንዘብ መድቦ ግጭት በመቀስቀስ ህይወት እና ንብረት እንዲጠፋ አድርጓል። ቅጥረኞች እና አላዋቂዎችም በወጥመዱ ተጠልፈዉ በሰፊዉ አግዘዉታል። ሆኗም የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ምናባዊ ጉልበት አሁን ላይ ክፉኛ ተዳክሟል። ዉሻን አሳምኖ ወደ በግ ሲቀይር የነበረዉ “ጠንካራ” ሎጂኩ ዛሬ ስለራሱም በትክክል መናገር ተስኖታል። እንግድህ ጊዜዉ ነዉ! በመጨረሻም እሳቤዉ ተሸንፎ ጥብቆዉ ተቀዷል! አሁን መደመርን መርሁ አድርጎ በእዉነት እና በእዉቀት ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና ማማ ለመዉሰድ እነሆ ብልፅግና ፓርቲ ተወልዷል። “እንኳን በሰላም መጣህ! መልካም ልደት! እደግ ተመንደግ! ለሀገር መከታ ሁን!” ብለናል። ያሉንን መልካም እሴቶች አጎልብተን፣ ስህተቶቻችንን አርመን፣ ህብረብሔራዊ አንድነታችንን አጠናክረን በነፃነት፣ በእኩልነት እና በወንድማማችነት መንፈስ የበለፀገች እና የተከበረች ኢትዮጵያን እንገነባለን! አሜን!
አሁን አብዮታዊ ጭምብል ወልቋል!
በግዴታ ማመን ቀርቷል!
የሀሳብ ነፃነት ሰፍኗል!
እዉነትም እዉነት ሆኗል!
taye dendea

5 Responses to “ዉሻዉ አብዮታዊ መስመር ይዟል! በግ መሆኑንም አምኗል” ታዬ ደንደአ

 1. አቶ ታዬ በመልካም ሁኔታ በማስረጃ አስደግፈህ ዘራፊና ማፊያውን ህውሀት እርቃኗን አስቀርተሀል:: በርታ:: እውነት መጨረሻ ላይ አሸናፊ ይሆናል:: የ27 አመታት የህውሀት ጥበብ ( ተንኮልና ሸር) አማራውንና ኦሮሞውን በመለያየትና በማጋጨት ኢትዮጵያን መዝረፍ ነበር:: ይህም ተሳክቶላቸው ነበር:: አሁንም ይህን ሳይጠብቁት ያጡትን ስልጣንና ዘረፋ ለመመለስ የሚቻለውን ሁሉ ከማድረግ አይመለሱም:: የብልፅግና ፓርቲ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በማሰባሰብ መታገል ይኖርበታል::
  ህውሀት በዚህ ወቅት ግራ የገባው ድርጅት ነው:: ቢገነጠሉ የ2018 ከትግራይ የተሰበሰበው ታክስ 5 ቢሊዮን ሲሆን ከአዲስ አበባ ብቻ 44 ቢሊዮን ነበር ከመላው ኢትዮጵያ ደግሞ 198 ቢሊዮን ነው:: መገንጠል መራብን ስለሚያስከትል አያደርጉትም:: ጫማ ስመው ብልፅግናን ቢቀላቀሉ ከሶማሌ ቀጥለው 6% ድምፅ ይይዛሉ:: ተደናግጠዋል:: ብዙ ቢያተራምሱ ሊገርመን አይገባም:: ሲሞቱ የመጨረሻ መፈራገጥ እንዳለ መጠበቅ ነው:: ህውሀት የሞተ የአንድ ክልል ድርጅት ሆኖ ይቀራል::

  Avatar for እውነቱ

  እውነቱ
  December 2, 2019 at 9:37 am
  Reply

 2. Abiy Ahmed’s vision is still unclear.
  Are we expected to sell our souls to the Abiy & Co. Prosperity propoganda ? What is it they try to attain in the next ten years anyways?

  -Are Ethiopians going to live in peace?
  -Are Ethiopian life expectancy expected to get in the 70s years of age?
  -Are Ethiopians expecting to travel to different areas for vacation?
  -Are Ethiopians expecting to pay off their foreign debts?
  -Are Ethiopians expecting to own expensive gadgets?
  -Are Ethiopians expecting to be self sufficient without begging for food from other countries?
  -Are displaced Ethiopians going to get resettled?
  -Is Ethiopia’s HDI rank expected to sky rocket to medium HDI ranking countries group?

  Avatar for Foziya

  Foziya
  December 2, 2019 at 11:50 am
  Reply

 3. “…… በህዝቡ ዘንድ የተጠላ ፕሮግራም፣ ስምና ምልክት ተይዞስ እንዴት ምርጫ ይታሰባል?…..”

  Melke xifuun be sim yidegifu alu. Ahun antem mefelasefih new. Jaawaar indalew Wayane yenanten medemer yemiqawemew silxan silaxa new. Medemer, bilxigin/bilgina……qibixirsooachiwun gin abzanyaw Oromo yixelal. Hizibus lemin xela atilenyim yene jilanfo????? Ye poletika seraa silehone bicha inji OPDO, EPRDF,…na masalochachew inxoroxos indiwardu new yetagelew. Ante lemin isir bet indegebahim yigermal. OPDO wusxi honeh wayanen metagel tichil neber firifariwunim iyeleqaqemki. Ayi miskiin.Lenegeru ahun waz iyamexah new. Lemehonu wayane bicha neber OROMON na lelawun hizib siyardina sizerfi yeneberew????????? Minasee, Taayyee T/haimanot,….na….jelewochachew min siseru neber??????? Ahun ante kenezi gar arbosh yaregeh mindinew. Logic indemiyawuq demo logic tilaleh????? Wusha. Oromon lelelaa zur gidiya na zirfiya asalifo mesxet lemin asfelege????????? Wusha neh be tikikil. Demo netsa hasab tilaleh????? Oromo ABO/WBOn siledegefe ayidelem inde iyasceresachiw yalachiwut????? Hattuu haadhakee. Namni nanbeeku jettee xibaarta. Saree hadhakee. Ati galtuudha. Ubaatiidha.

  Avatar for Gurbattii Namaa

  Gurbattii Namaa
  December 3, 2019 at 2:33 am
  Reply

 4. Biltsigina ke netsanet befit le Chainam yebejat almeselenyim letewenabedachiw. Mejemeriya ye hageritun sir yesedede chigir meqiref yibejal. Political problem is the basis for all other problems. National consensus must come first. Otherwise,……….wayolin.

  Avatar for Gurbattii Namaa

  Gurbattii Namaa
  December 3, 2019 at 2:43 am
  Reply

 5. አቶ ታየ አንተ ልትቀልድባቸዉ የመከረከወው ተጋዮች ቡዙዎቹ አሁንም በክብር ሀገራቸው በማገልገል ላይ ናቸው ሰለሆነም እነሱ ከየትኛውም ፖለቲካ ወጭ ሆነዉ ሲያገለግሉ አንተ የገዢ ፓርቲ አባል ሁነህ በነሱ መቀለድ ጥሬ ፖለቲከኛ ነህ.አና እኛ በፖለቲከኞች እንደ ማንገባው ሁሉ እናንተም በድሮ ታጋዮች የአሁን የኢ/ያ ወታደሮች ባትገቡ ይመከራል

  Avatar for Ambachew

  Ambachew
  December 4, 2019 at 6:28 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.