ለ “እዝጊኦ፣ትንሣኤ እና መሪር ሐዘን ” ግጥሞች እንደመግቢያ – ከመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊሥስ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

እዝጊኦ፣ትንሳኤና መሪር ሐዘን ፣ቀሥቃሽ፣አነቃቂ እና ቁጭትን ጫሪ ግጥሞቼ ናቸው።ይህን ዘመን እና ትውልድም ይመለከታሉ።
ይህ ትውልድ ፣ካለፉት አባቶቹ፣ “ሥድብን፣ብልግናን ፣ግፍን፣ሆዳምነትን፣መሥገብገብን፣ይሉንታ ቢሥነትን አብዝቶ ተምሯል ። “ብለው የሚሞገቱ ቢኖርም ቅሉ፣በሃሳባቸው አልሥማማም ።ይህ ትውልድ ፣ የወጣት ሥብሥብ እንደመሆኑ እና መረጃዎች በፍጥነት በሚደርሱበት ዓለም ውሥጥ ሥለሚኖር ለመሸበር እና የማያምንበትን ድርጊት ለመፈፀም ደመነፍሱ ሊመራው እንደሚችል መገንዘብ አለብን።
ደግሞም ተማሪ መሆኑን ማመን ይኖርብናል።ተማሪ እና ከኑሮ ትምህርት ቤት ፒኤችዲውን የያዘ አንድ አይደለም ።
ይህንን ተማሪ ዕውቀት ከመጋት ይልቅ፣ጥላቻ የሚግቱት ፒኤች ዲ ከኑሮ ዩኒቨርሥቲ እና ከባህር ማዶ የዕውቀት አካዳሚ ያገኙ ሁለት ፀጉር ያበቀሉ፣ እንደሆኑ ልብ ልንል ይገባል።
ጥላቻን ሲግቱትም፣በጫት ፣በሃሺሽ እና በአልኳል ሱሥ አጀዝበውት ነው።
እርግጥ ነው፣ አንደበታቸው ፣ከጫት፣ከሃሺሽ የከፋ”ገዳይ ኤቦላ ምላሥ ያላቸው ” ወላጆችም ለልጆቻቸው ጥላቻ እና በቀለኝነትን ያወርሳሉ።
ምን እነሱ ብቻ በየግል ሚዲያዎች እና በፊሥ ቡክም የምናሥተውላቸው፣ ይህንኑ የጥላቻ “ኤቦላ ” ዘወትር ይነዙ የለም እንዴ?!

እዝጊኦ!

እውቀት፣ከጠቢባን ጋር፣ቢወዳጅም፣
ሥንፍና ከሰነፎች ጋር፣ቢዘመድም፣
ህይወት በምትባል ጀልባ፣ሁለቱም ተጉዘው
ፍጻሜያቸው፣መቃብር ነው፡፡
ነገር ግን
ሰነፍም፣በሥንፍናው
ጠቢብም፣በጥበቡ
በታሪክ መፃፉ
በትውልድ መነበቡ
ገበናው ሁላ፣በአደባባይ መሰጣቱ፣
አይቀርም ታሪኩ፣በታሪክ መወሳቱ፡፡
ይሁን እንጂ፣
ታሪኩን የፃፈው ትውልድም ያልፋል
ታሪኩም በዘመን ብዛት፣ይደበዝዛል ።…
ይኽ በወደቀ የጫማ ቀለም ቆርቆሮ የሚጋደለው
በቆዳ ማዋደድ ፣በቋንቋ ፖለቲካ የሚወጋጋው
በሥድብ፣በአሉባልታ፣በጥሎ ማለፍ የተካነው
በምላሥ ጉልበት ፣ጭራ በመቁላት፣ የሚንቀባረረው…
“እንከን በእንከን ” የሆነው ይህ ትውልድም ያልፋል ። እንደዛኛው እንደ ኢህአፓው ትውልድ ይረሳል። የእንከናምነቱንም ሰበብ ለማወቅ ቀጣዩ ትውልድ ይጨነቃል።
ለታሪክ ደንታ ቢሥ ትውልድ ከተፈጠረ ደግሞ ታሪክ ራሱ ይጠፋል።

1989( ህዳር 22/2012 ታደተ) መኮንን ሻውል

ትንሣኤ

የብርሃን መንፈስህን፣አታውከው በጨለማ፣
የሱስ ባሪያ በመሆንም፣ህሊናህን ከቶ አታድማ።
በውርደት ሲኦል ውስጥ ተጥለህ እንዳትኖር
ከሰው በታች ሆነህ ፣በህይወትህ እንዳታፍር
አንተ ወጣት ዛሬ ወሰን፣ህሊናህን አጀግንና
‹‹ በስመአብ ! ……. ›› ብለህ
አዲስ ሰው ሁን
ሱስን አሸንፍ፣ በእምነት- ራስህን ቀድስና !!

1995

መሪር ሐዘን

የሀገር ወዳዱ ነፍስ ፣ ሌት ተቀን ሥትቃትት፣ሥትለፋ
በህዝብ ፍቅር ፣በሀገር ወዳድነት አባዜ ተለክፋ
አድካሚ ትግሉ ሳይሰለቻት በዝንጋታ ሳታንቀላፋ
ቆቅ ሆና ሥትጠብቅ ፣ድሉ ተነጥቆ እንዳይደፋ።
ትላንት የመቃብር ወግ እንኳን አልነበራትም
ዛሬም መሰዋትነቷ ከእነገድሏ አይዘከርላትም።
ነገር ግን ሁሌም በምፀት ፣ለዚህ ትውልድ ትናገራለች
ያለፈውን የተቀደሰ ተጋድሎዋን እንዳይዘነጋ ታሥታውሰዋለች።
በባለቅኔው በኩል እንዲህ ፣እንዲያ እያለች…
ለዚች ሀገር ታላቅነት በየበርሃው ብንቀርም
ተመሥገን ቀባሪ ግን አላጣንም።
ዕድሜ ይስጣቸውና እነዛ ጥንብ አንሳዎቻችን
›› ›› ›› ጆፌ አሞራዎቻችን
›› ›› ›› ጩልሌዎቻችን
›› ›› ›› ቀበሮዎቻችን
›› ›› ›› ጅቦቻችን
›› ›› ›› ተኩላዎቻችን …
መቃብራችንን ያሰናዱልናል በመደሰት
እነሱ ይሰበስቡናል ከወደቅንበት
ጆፌና ጩልሌዎቻችን ቀን በቀን
ጅብ ቀበሮና ተኩላዎቻችን በጨለማ በውድቅት…
እንዳልነበረ ያደርጉታል እኛነታችንን
ወደከርሳቸው ይከቱታል ታላቅ ሥብእናችንን፤

1982 ዓም(22/3/12 ዓ/ም ታደተ) ፣ መኮንን ሻውል
ይህ ግጥም ፣

3 Responses to ለ “እዝጊኦ፣ትንሣኤ እና መሪር ሐዘን ” ግጥሞች እንደመግቢያ – ከመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊሥስ

 1. ሕላዊ:
  አሁንማ ደስ ብሎሻል። የብሔር ፓርቲዎች ፈረሱልሽ አማርኛም ዳግም የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ሊጫንልሽ ነው። የምርጥ ዘሩ አማራ የበላይነትም አማራ ባልሆኑት ላይ ሊጫን አንድ ሳምንት ቀረው። ለዚህ ነዉ እንደ ዋሸራ ደብተራ ግጥም መደርደር ያማረሽ። ያልገባሽዉ ነገር ግን የምታቀጣጥይዉ እሳት ቂጥሽ ዉስጥ ሊነድ መሆኑን ነዉ።

  ሕወአት በወልቃይትና ጸገዴ አርጋ በደቂቃ ቂጥሽ ዉስጥ እንደ እባብ ስትገባ ታየኝና አዘንኩልሽ ። ያኔ እመቤቴ ማርያምን ግጥሙን የጻፍኩ እኔ አይደለሁም ብለሽ እንደለመድሽዉ ማሩኝ ብለሽ እግራቸው ስር ወድቀሽ ጫማቸዉን ትስማለሽ::

  Avatar for Ujulu

  Ujulu
  December 2, 2019 at 8:56 pm
  Reply

 2. ጸሐፊው እንዳሉት፧ “ይህ ትውልድ ፣ የወጣት ሥብሥብ እንደመሆኑ እና መረጃዎች በፍጥነት በሚደርሱበት ዓለም ውሥጥ ሥለሚኖር ለመሸበር እና የማያምንበትን ድርጊት ለመፈፀም ደመነፍሱ ሊመራው እንደሚችል መገንዘብ አለብን።” ለዚህ በህዝብ ፍቅር ፣በሀገር ወዳድነት፣ ማስተማር፣ መምከር፣ትክክለኛውን የህይወት መንገድ ሳይሰለቹ ማሳየት ያስፈልጋል። በዚህ እንትጋ፡ ሌላው ትርፍ የለውም።
  ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ፧

  Avatar for Mebertat

  Mebertat
  December 3, 2019 at 10:12 am
  Reply

 3. አቶ መበርታት
  ፀሓፊዉ ራሱን ሲገመግም በጣም ደስ ይላል።

  Avatar for gemeda

  gemeda
  December 3, 2019 at 11:33 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.