ኢትዮጵያ በተቃውሞ ምክንያት ለወደሙ የኢንቨስትመንት ተቋማት ካሳ ልትከፍል መሆኑን አስታወቀች

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

በአገሪቱ በየጊዜዉ በሚነሱ የፖለቲካ ተቃዉሞ ምክንያት የወደሙ የኢንቨስትመንት ተቋማትን ለመደገፍ ጥናቶች እየተካሄዱ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ የወደሙ የኢንቨስትመንት ድርጅቶች የፋይናንስ ማበረታቻ እንዲያገኙ እየሰራሁ ነዉ ብሏል፡፡ በኢንቨስትመንት ኮሚሽን የፕሮጀክቶች ድጋፍ እና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ሳሙዔል አሰፋ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ እንዳስታወቁት በቅርቡ በተረደጉ የፖለቲካ ተቃዉሞ ምክንያት የተቃጠሉ ድርጅቶችን ለማገዝ ግብረ ሃይል ተቋቋሞ ጥናት እያካሄደ ይገኛል ብለዋል፡፡

በዋና ኮሚሽነሩ የሚመራዉ ይህ ጥናት አድራጊ አካል የወደሙ ተቋማትን በጥናት አረጋግጦ ለእያንዳንዱ ድርጅት የፋይናንስ ማበረታቻ ይከፈላቸዋል ተብሏል፡፡ ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ አገሪቱ በኢንቨስትመንት ተቋማት ላይ በሚደርሱ ጥቃት ምክንያት በርካታ ገንዘብ እያወጣች እንደምትገኝም ተነግሯል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ ላልተወሰነ ወጪ መዳረጓን ያስታወቁት ዳይሬክተሩ ወጣቱ በኢንቨስትመንቱ ላይ የሚያደርሰዉን ጥቃት ሊያቆም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ለድርጅቶች ከሚደረገዉ የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የተለያዩ እቃዎችን ከቀረፅ ነፃ በሆነ መንገድ እንዲያስገቡ ስለሚደረግ ኢትዮጵያን የዉጭ ምንዛሬ እንድታጣ አድርጓታል ብለዋል አቶ ሳሙዔል፡፡

ከዚህ ባለፈ በኢንቨስትመንትቱ ላይ የሚያነጣጥረዉ ጥቃት ዘርፉን ከመጉዳቱ ባለፈ የሥራ አጥነቱን እያባበሰዉ እንደሚገኝም ዳይሬከተሩ አንስተዋል፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በነበረ ተቃውሞ ምክንያት ከ200 በላይ በሚሆኑ የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣የቡና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ላይ ከ348 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኢንቨስትመንት ውድመት ደርሶባቸው እንደነበር ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

በአጠቃላይ በሁለቱ ክልሎች ለደረሱ የኢንቨስትመንት ውድመቶችም መንግስት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የማገገሚያ ክፍያ ከፍሏል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍኤም

4 Responses to ኢትዮጵያ በተቃውሞ ምክንያት ለወደሙ የኢንቨስትመንት ተቋማት ካሳ ልትከፍል መሆኑን አስታወቀች

 1. ደብረሲኦል
  ጊዜ ወስጄ ብዙ ነግር ማለት ይቻላል፡፡ ግን ወያኔ እቃሰተ መተንፈስ እንጂ መስማት ተስኖታልና ማለት የምፈልገውን ላሳጥርለት ሳይሞት ቢያነበው እንኳን
  ደብረሲኦል ስላለፉት ዘመናት ሳይሆን በስልጣን መገፋት መነሻነት የቅርቡን ማጠልሸት ላይ ዘምቷል፡፡ ህዝቡና ወያኔ ተለያይተዋል፡፡ ወያኔ በሰበሰበው ገንዘብ ባሻው ጊዜ በሚሊዮን የሚገመት ብር በስብሰባና በኮንፈረንስ ስም ይበተርነዋል፡፡ ዋና ኦዲተር ሲመጣ ያልታቀደ ወጪህን ምን ብለህ እንደምታስተባብል ያኔ እንተያያለን፡፡
  1. ይቀርባሉ የተባሉ ምርምሮች—-ለመሆኑ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ምርምሩ እንዴት ሊደርስ ቻለ
  2. የምርምር ርዕሶች፡ ያለፈው የወያኔ አገዛዝ ትሩፋት—-ግድያ፣ እስር፣ ማሳደድ፣ ማሰቃየት፣
  3. ተሰብሳቢዎች፡ እስቲ ከደብረሲኦል ጀርባ ያሉትን ተመልከቱ—የባለፈው በፓርቲ ስም ድርጎ እሰቷቸው ጊዜያቸውን ያራዘሙላቸው የ20 አመታት ተቃዋሚ ተብዬዎች
  4. ብዛት፡ ስንት አስባችሁ ስንት መጡ፣ እስቲ በብህረሰብና በፓርቲ ለይታችሁ እነማን እንደሆኑ እነወቃቸው
  5. በኢትዮጵያ ስም የተደራጁ የተባሉት ተሰብሳቢዎች፡ የአየለ ጫሚሶው ቅንጅት፣ አንድነትን የናደውና ወያኔ በውርስ የሰጠው፣ ምእራብ ኢትዮጵያ፣ እና መሰል ድኩማን አባላት ማስፈረም ያቃታቸው፣ አባላት የሌሏቸው፣ ፕሮግራም ያልቀረጹ፣ ከህዝብ ጋር ተገናኝተው የማያውቁ፣ በአገራችን ይህ ሁሉ ሲደርስ አንድም ድምጽ ያማያሰሙ —ስብስቦች
  6. ደብርሽ ፓርቲዎዎቹ ኪሳቸውን ካሞላህላቸው ከመቀሌ ስለማይወጡ፣ ምናለፋህ በጆንያ ሞልተህ ያስቀመጥከውን የህዝብ ገንዘብ አድላቸው፡፡ አለያ አይወጡም ሁሉም ብር ሊይዙበት ከረጢት ይዘው ነው መቀሌ ከች ያሉት፡፡
  ለማንኛውም ይህ የዲፋክቶና ኮንፌደራሊስቶች ስብሰባ ከቻለ አገርን ከማፈራረስ፣ ክልሎችን፣ ብሄሮችን ከመበጣጠስ ያለፈ ሌላ አጀንዳ የለውም፡፡ ስብስቡ በሞራል የላሸቀ በመሆኑ ህዝብ ምን መከራ ቢደርስብ ደንታ የሌለው የወያኔ አሽከር ነውና ከወደቁ በኋላ መገላበጥ ለመላላጥ ብቻ መሆኑን ልንነግራችሁ እንወዳለን፡፡
  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

  Avatar for Nazrawi

  Nazrawi
  December 3, 2019 at 8:10 am
  Reply

 2. The government need to listen rather than listening after things are burning .
  Also The security apparatus need to take measures so similar incidents of Jawar
  Querro looting stop occuring .

  TPLF looted Sugar projects money then the ethnic MURSI ancestoral land is snatched to compensate the loss.

  Now Jawar Querro loots murders then tax payers pay for it while Jawar Querro contemplate where to loot next.

  You might as well give the taxpayers money
  directly to QuerroJawarr since it sounds like they loot then the government pays it off for them. NOT FAIR.

  THE WHOLE GOVERNMENT OFFICIALS NEED TO GO TO SCHOOL ON LAW101 JUSTICE FROM SCRATCH AGAIN.

  Avatar for Fochew Gud

  Fochew Gud
  December 3, 2019 at 8:15 am
  Reply

 3. Amara killed their own Amara leaders now NAMA is saying they will hold a civil disobedience to free the incarcerated. Only NAMA themselves will know the effect of their Civil Disobedience they intend to hold . The mainstream Ethiopians already know that NAMA is just an association of deviants , the mainstream Ethiopians won’t mind one bit if NAMA peacefully holds a civil disobedience.

  Many thought that NAMA already were in some sort of disobedience just from watching their whole hippie lifestyle . NAMA can hold civil disobedience all year long with the mainstream Ethiopians not being bothered by their civil disobedience as long as it is done in a peaceful manner.

  On the other hand those that got arrested kept in jail until now and their supporters had been belived to be excuting revolution through violence since June, that’s why their every move is being closely watched by the Ministry Of Peace so the coup perpetrators don’t engage in anymore anti peace actions , after that justice will be served, even if the Federal govt for some reason tries to pardon them it has been said that Amara region Ambachew , Asaminew , Saere … Supporters will not rest until justice is served.

  https://borkena.com/2019/12/04/amhara-national-movement-nama-demands-unconditional-release-of-senior-leaders/

  Avatar for Jeeynitti

  Jeeynitti
  December 5, 2019 at 2:15 am
  Reply

 4. The locality where the Gamo and other Ethiopians’ houses was set on fire should pay for the rebuilding and also for the fatherless children’s welfare and college education. If the locals can’t afford to pay they can sue Jawar Mohammed and his OMN for inciting his thugs to kill their family.

  In 1975 or 76 all properties in Addis were confiscated. Netsles sued the government after the communist era and got compensated with compound interest. The Ethiopians businesses or the Ethiopians who were robed of their entire life’s investments were never even considered, because they were Ethiopians. The Ethiopians that worked so hard to build businesses were beaten down so hard they didn’t even ask for nothing. Ethiopia is not the first country to go through stupid periods like communism that brought nothing but death and destruction. But she is the only one which allowed idiots to rule her since 1974.

  TPLF returned the houses to their original owners in Mekele.

  Avatar for Ibro

  Ibro
  December 6, 2019 at 11:03 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.