አገራችን ኢትዮጵያ እጅግ አስፈሪና አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ!

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

አገራችን ኢትዮጵያ፣ እጅግ አስፈሪና አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ለሁለተኛ ጊዜ ህገ መንግስትና ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝም ስርዓትን የማዳን አገር አቀፍ መድረክ ላይ ለመሳተፍ ለመጡ ተሳታፊዎች የመክፈቻ ንግግር ያቀረበ ጓድ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ገልፀዋል፡፡

ጓድ ዶ/ር ደብረፅዮን አገራችን ውስጥ ህገ መንግስቱ በግላጭ በሚጣስበት፣ የሰላም እጦትና የዜጎች ደህንነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመጣበት፣ መፈናቀልና የንብረት ውድመት የዘወትር ተግባር በሆነበትና የዜጎች ህይወት መጥፋት በተበራከተበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ካለ በሗላ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የጠቅላይነት አስተሳሰብ የተጫናችው ተግባራት በአግሪቱ እይተፈፀሙ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

ይህን መሰል አደገኛ ተግባራት በሚፈፀሙበት ጊዜ አገራችን ከጥፋት ለማዳን ውይይት ማድረግ ተገቢ ነው የሚሆነው፤ ያለው ጓድ ዶ/ር ደብረፅዮን ወይይቱ ለመሳተፍ በዙ ጫናዎች ችለው በመድረኩ ለተገኙ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሀሳብን የሚፈሩና የሚጠየፉ ፈሪዎች ከነሱ የተለየ ሀሳብ ያላቸው አካላት እዚሁ መድረክ እንዳይገኙ የተለያዩ ጫናዎች ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በዚሁ ምክንያትም ቁጥራቸው የማይናቅ አካላት ጫናው ከብደዋቸው ከመድረኩ ቀርተዋል፡፡ ይሁንና እነዚህ ሰዎች በሀሳብ እኛ ጋር በመሆናችው እዚሁ መድረክ ባይገኙም በያሉበት ሆነው ትግላቸውን አያቆሙም ያለው ጓድ ደብረፅዮን ሀሳብን ፈርተው የማፈን ስራ ሲሰሩ ለቆዩ ፈሪዎች ግን ወደ ፊት የሰሩትን ዝርዝር ተግባር ወደ ማጋለጥ ተግባር እንደሚገባ፣ የማፈን ተግባሩም እንደማያዋጠና አሸናፊም እንደማይሆን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በአሁኑ ሰአት አገራችን ከገጠማት እጅግ አስፈሪና አጣበቂኝ ችግር እንድትወጣ ከተፈለገ በመድረኩ የተገኙ የተለያዩ በህገ መንግስቱና ህብረ ብሄራዊ ፌደራል ስርዓቱ የሚያምኑ ብሄራዊና አገር አቀፍ ፖለቲካዊ ሀይሎች፣ ምሁራን፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና ምን ማድረግ ይሻለናል የሚል እውነተኛ ውይይት በማድረግ የመፍትሄ ሀሳቦች የሚቀመጥበት መድረክ እንደሚሆን ያለው ፅኑ እምነት ገልፀዋል፡፡ በየትኛውም ቦታ የሚገኝ አገሩ ወዳድ ኢትዮያዊም አገራችን ከገጠማት ችግር ለማዳን የበኩሉ እንዲያበረክት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ለሁለተኛ ጊዜ ህገ መንግስትና ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝም ስርዓትን እንታደግ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው አገር አቀፍ መድረክ ላይ ተገኝቶ ንግግር ያደረገ የውይይቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ሙሉጌታ በአካሉ በመድርኩ ከ 50 በላይ ብሄራዊና አገር አቀፍ ፖለቲካዊ ፓርቲዎች እንደተገኙ፣ ከ 700 የሚበልጡ ከተላያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ምሁራን፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና የሀይማኖት አባቶችና በመድረኩ እየተሳተፉ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡

መድረኩ እስከ ነገ የሚቆይ ሲሆን የህገ መንግስቱና ህብረ ብሄራዊ ፌደራል ስርዓቱ ትሩፋቶና በአሁኑ ሰአት የገጠሙት ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች፣ የህግ የበላይነትና የዜጎች ደህንነት፣ እንዲሁም መሰል ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ አምስት ጥናታዊ ፅሁፎች በመድረኩ ቀርበቅው ውይይት እንደሚደረግባቸው ገልፀዋል፡፡

ስዩም ተሾመ

7 Responses to አገራችን ኢትዮጵያ እጅግ አስፈሪና አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ!

 1. ኢዴፓን በሃይል ተነጥቀናል አሉ አቶ ልደቱ አያሌው::

  የምርጫ ቦርድና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ ባለመግባባት ተበተነ

  እነ አቶ ልደቱ ምርጫ ቦርድን እንከሳለን አሉ::

  Avatar for Einanu

  Einanu
  December 3, 2019 at 7:06 am
  Reply

 2. can you call this party after Bilgina, not prosperity.

  Avatar for Jawar viva

  Jawar viva
  December 3, 2019 at 7:07 am
  Reply

 3. Dr. Debretsion first and most what you are blaming and crying at now in Ethiopia you and your parte TPLF are the causes of this sick division. When you have a mountain size blockage in your eye you don’t blame the tiny one on your neighbour.
  Again practice what you are preaching in Tigray with the ARENA and SALSAWi & TAND then come with a proof of transparency and openness and democratic system otherwise it is a cry on a spilled milk.
  It seems you are sandwiched between the change hangry Tigrians and your masters the old guards.
  Dr. Abiy was in a same situation and now he is starting to liberate himself from anti-democratic forces and narrow minded Oromo elites who were in the way blocking the progress you better choose like he did before it is too late, you can not serve two masters you better choose the people of Tigray not the your masters the old dead guards.
  I hope you see the light sooner than later.
  God bless Ethiopia and Tigray within Ethiopia.
  Muchfun
  Ottawa, Canada.

  Avatar for Muchfun A kassa

  Muchfun A kassa
  December 3, 2019 at 8:17 am
  Reply

 4. ደብረሲኦል በምን እንመንህ
  ላለፉት 27 አመታት የሠራነው ሁሉ ግሩም ነው ካላችሁን በኋላ እንዴት ወደፊት በቀናነት መልካም እንደምትሰሩ እንመናችሁ፡፡ በሺዎቸእ የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረው፣ ተገላው ተሰደው እናንተ ከረስ ተኮር ልማትን ታወሩልናላችሁ፡ መንገድ ገለመሌ እያላችሁ፡፡
  ባለፉት 27 አመታት በናንተ መሪነት ወረቀት ላይ በተጻፈው ህገ መንግስት ሳይሆን በአሃዳዊነት ስትነዱን ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ የህገ-መንግስቱ እና የፌዴራል ስርዓቱ ተቆርቋሪ ነን ብላችሁ እየያችሁን አቀለጣችሁት፡፡ ውይይት ባልከፋ አላመው እናንተን ወደስልጣን ለማምጣትና አሁን የወጣውን ጸሃይ ለማዳፈን ጀሆ አረ እዛው በጠበልህ ብለናል፡፡
  50 ፓርቲና 700 ተሳታፊዎች ተገንተዋል ትሉናላችሁ፡፡ እነማን ናቸው፤ ስማቸውን ብትነግሩን እኛም ለማመስገን ይመቸናል፡፡
  ኢትዮጵያን ለማፍረስ ምን እየሰራችሁ እንደሆነ ስለምናውቅ ባንደሰትም አዲስ ወሬ አልሰማንም፡፡

  Avatar for Zeberga

  Zeberga
  December 4, 2019 at 11:20 am
  Reply

 5. ኢትዮጵያዊው የሃይል አሰላለፎች በግርጂፉ: (Drohende Gefahren der Schlammschlachten፣ ልንለውም እንችላለን)

  1. ከማሃከላዊው ስልጣን የተፈነገለው ወያነ መያዣ መጨበጫ ማጣትና፣ አሁንም ቢሆን የዘረፋው ባላባትነቴን አልለቅም፣ ከለቀቅሁኝ ግን ኢትዮጵያ ሰላም አታገኝም፣ እስከተቻለኝ ጊዜ ድረስም አራብሻታለሁኝ ባዩ መቐላዊው ቡድን፣

  2. ከዚያም ቀደም ብሎ ከስልጣን የተፈነገለውና ግን አሁንም ቢሆን ወደ ፊውዳሊዝም ኢትዮጵያን መልሼ ብቸኛው የጭሰኝነት ገዢ እሆናለሁኝ ብሎ የቅዠት ህልም ውስጥ የተንጠለጠለው የአማራው ቡድን፣

  3. ተደግፎ ወደ ስልጣን የተንተለጠለውና ግን የሃገር ማስተዳደር ልምድ የለሹ የኦሮሞ ቡድኖች፣ ለጂትም (ሃቀኝነት ያለው) የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄዎችንም ለማስተግበር የተቸገረና እርስ በራሱም ቅራኔዎች ውስጥ ተዘፍቆ እርስበራሱና ከሌሎች ጋራም Schlammschlachten ውስጥም ሊዘፈቅ የሚችል፣

  4.ወደ ከንያ አካባቢ ደግሞ መሰባሰብ የጀመረው “ዳግማዊው የ1960 ጀብሃ” በመሆን የኢትዮጵያ ጠላቶችን ለማገልገል የሚሽመነመነው ያለው የሱማሌዎች ቡድን፣

  5. ሌሎቹ ለእኩልነት የሚታገሉ ያሉት ብሄር ብሄረሰቦች ኢትዮጵያውያን፣

  6. የሃገሪቱ መረጋጋት ሳይሆን ቅድሚያን የሚሰጠው ወደ ስልጣኑ የሚቀናቀኑ ሃይሎችን ተቀላጥፎ ማጥፋት ተግባር ላይ ያተኮረው ደምሩኝ ልደምራችሁ በማለት ውሎ የሚያድረው መሃከላዊው መንግስት እስከነ አማካሪዎቹ፣

  7. የውጭ ሃይሎች: አረቦች በተለይም ግብፅና ሳውዲ፣ አሚአሪካ ሲደመርበት ኢሮፕ እና ቻይና፣ እንዲሁም የነዚህ የውጭ ሃይሎች ጉዳይ አስፈፃሚ ጎረቤት ሃገራት አፍሪቃውያን፣ ለምሳሌ ኤርትራ፣ ከንያ፣ ሱማሊያ እና ጅቡቲ እና ወዘተ ወወዘተ፣

  8. በዓደርባዕተው (ዓድዋ) የፕሽኩኑ አባት ይሁንብኝና፣ ምንም እንኳን እስካሁን ጊዜ ድረስ ራሽያ የኢትዮጵያ ጠላት ነች የሚያስብል ታሪክ ባይኖርባትና በንጥረ ሃብትም የታደለች ታላቅ ሃገር ብትሆንም፣ ግን ሃያል የዓለም መንግስታት ከሚባሉት ሃገራት አንዷ እንደመሆኗና ከዒራቕ ወረራ ልምድም የተማረችውና ስለሆነም በሶርያ የተጫውተችው ሚና ሲታይ፣ በሃያላን መንግስታት ጨዋታ ላይ ከእንግዲህ ወዲ እጅና እግሯን አጣጥፋ እንደምትቀመጥና ለኢትዮጵያም ከአወንታዊ ወይንም አሉታዊ ሚና የትኛውን ትመርጣለች ብሎ መጠየቅ ጠቃሚ ጥርጣሬ እንጂ የጠላትነት አስተያየት አይደለም፣

  9. ኢትዮጵያን የከበባት ህልው ሁናቴ በግርጅፉ ይሄን ይመስላል፣ ኢትዮጵያውያን ልብ ከገዙ፣ ኢትዮጵያ በህዝቦችዋ መሃከል ሰላምን አስፍና በሚቀጥሉት አምስት አመታት ውስጥ እንደ ወደነ ቻይና ዓይነት እድገት ለመከተል እድሉ አለ፣ ልብ ከሌለን ግን በሌሎች ሃገራት እንደታዩት፣ የርስበርስ እንደነ ሩዋንዳ ወይንም ደግሞ የውጭ ሃይሎች የሚራገጡባት እንደን ሶርያ ዓይነት እጣዎች ስር ለመውደቅ በሩ ክፍት ሆኖ ይገኛል፣

  10. መወጫው የኢትዮጵያውያን፥ ከአሁን በፊት የሆነ ቦታ እንዳልኩት ሁሉ፣
  “በአሁኑ ጊዜ መታየት የጀመሩት እንደ፣
  1.የሲዳማ ራስን በራስ ለማስተዳደር ሰላማዊ ምርጫ መከተልና፣ እንዲሁም
  2. አፋርኛ፣ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሶማሊኛ እና ትግርኛ እንደ ብሄራዊ ቋንቋዎች ሆነው መመደብ(ቀስ እያሉ ገና ሌሎቹም ይከተላሉ) ለወደፊቱ ትክክለኛ የነዋለልኝን መንገድ ተከትለን በUnity in diversity ጉዞ ተቃቅፈን እንድንበለፅግ እንደሚጠቅሙን እንተማመንና እንስራ!”

  Avatar for ዘረ-ያዕቖብ

  ዘረ-ያዕቖብ
  December 4, 2019 at 1:02 pm
  Reply

 6. ከወዲሁ ራሽያን አስመልክቶ በጣም ወሳኝ እርማት:
  እንደምትቀመጥና=እንደማትቀመጥና

  Avatar for ዘረ-ያዕቖብ

  ዘረ-ያዕቖብ
  December 4, 2019 at 1:11 pm
  Reply

 7. የነዋለልኝ??????????????
  He was evil predecessor of Zenawi-who said Ethiopia is not nation but nation-nationlities-word splitting! Look where we are. We are proud of eating each other! Not loving each other; not working together; not saving one another; not eyeing for civility, civilization or innovation. We are more than a century behind advanced economies but still we are not working to save ourselves; to simplify our daily life/living or feed ourselves. We keep on eating each other; fighting.
  His and Zenawi philosophy was Dumb philosophy that did not save the country!

  Which country in the world is composed of a single ethnic? Majority of world nations have a number of Ethnics but they don’t have the Nation/nationality Jargon. They function as single country.
  We are obsessed with selfishness and hate instead of creativity, diplomacy and civility. The Oromo and the Tigray extremists (amara nationalists coming?) with their Nation/nationality obsession are all the root cause of the trouble, killing/atrocity in the country. I am grown up adult; since my child hood, it is always them. In cryptic college wall notes, blown bridges, people dumped alive in pits, cut throat-it is either TPLF or OLF (oromo ignorant fanatics)-now Ja-war and his wuhabis. It is always their foul play and cry. They are always victims. When they get the opportunity to usurp the governance, the cook for themselves. They have no national or regional or international vision. They are the best breed (some say agazean-funny)in all world ethnics when in reality they can’t feed themselves-God save us! They mob kill, still, get drunk, excrete and when they loose they cry the country will be gone! That is what happens when a dumb cadre leads a big nation not a civilized being. Stop Ethnic strife, build a country and unity. Think as cerebral humans! Spread education, innovation, civility, heroism, humanism, love and kindness, respect…Don’t preach hate, killing, disintegration. Ethiopia is a nation. One country, one people proud in diversity. Don’t divide us in Ethnic basket instead of more plausible regional or geopolitical associations. We don’t need imported philosophy (Marxism..etc). A well nurtured, humble,ethical wise elected human leader is one that the country needs. All crazy philosophers/thinkers can teach or write books and who ever wants to listen/read them can listen and read them for leisure.

  Avatar for citizen

  citizen
  December 5, 2019 at 11:21 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.