የምንፈልጋት ኢትዮጵያ በ2032 በሚል ርእስ ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው‼

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

የምንፈልጋት ኢትዮጵያ በ2032 በሚል ርእስ ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ሀገር አቀፍ የውይይት መድረኩን በፎረም ኦፍ ፌዴሬሽን እና ዴስትኒ ኢትዮጵያ ኢኒሼቲቭ ናቸው በጋራ ያዘጋጁት።

በመድረኩ ላይም የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች እና ምክትል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የበርካታ ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ተወካዮችም በመድረኩ ላይ ተሳትፈዋል።

መድረኩ የሀገሪቱን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን በማቀራረብ የወደፊት የሀገሪቱ እጣ ፈንታ ላይ ለመወያየት በማለም የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችም፤ በመድረኩ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ፤ አሁንም ለኢትዮጵያ በርትተው እንዲሰሩ እድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ተወካዮቹ ከዚህ ቀደም በዚህ መድረክ ስር በጋራ በነበራቸው ቆይታ ስለ ሀገሪቱ ፖለቲካ በስፋት መምከራቸውን እና በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ችግሮች በውይይት ብቻ የሚፈቱ እንደሆኑ ከመግባባት መድረሳቸውን አስታውቅዋል።

የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፥ መድረኩ በሀገር ጉዳይ ሁሉም በንግግር የሚፈታ መሆኑን ልምድ የተገኘበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የአብን ሊቀ መንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ፥ መድረኩ የተራራቀ አቋም ያላቸው የፖለቲካ ሀይሎችን ያቀራረበ መሆኑን ተናግረዋል።

በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ምንም አይነት የተራራቀ የአቋም ልዩነት ቢኖርም፤ በመቀራረብ እና በመወያየት የማይፈታ ነገር እንደሌለ ያስተማረ መድረክ መሆኑን ተቅሰዋል።

የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳም፥ “መድረኩ መጀመሪያ ሲጀመር ውጤቱ ላይ ጥርጣሬ ነበረኝ፤ ወደ ስራ ስገባ ግን ቀስ በቀስ በመነጋገር፣ በመወያየትና በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ መፈለግ እንደሚቻል ልምድ ያገኘሁበት ነው” ብለዋል።
የአዴፓ ተወካይ ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል፥ “በመድረኩ በጋራ በመሆን ሀገርን፣ የዴሞክራሲ ስርዓትን፣ መንግስትን እና ኢኮኖሚን መገንባት እንደሚቻል አረጋግጫለሁ” ብለዋል።

የሀገር ሽማግሌ ተወካዮችም በመድረኩ ላይ መድረኩ ለኢትዮጵያ መፃኢ እድል በር የሚከፍት መሆኑን በመግለጽ፤ ለኢትዮጵያ ስንል ሁላችንም ዝቅ ብለን እንስራ ሲሉ መናገራቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በመድረኩ ላይም ከ50 በላይ የተቋማት መሪዎች በኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ዙሪያ ንግግር እንደሚያደርጉም ነው የተገለፀው።

#ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ

4 Responses to የምንፈልጋት ኢትዮጵያ በ2032 በሚል ርእስ ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው‼

 1. BALLS ANYONE?

  Any sane person who got balls would have said BY 2032 I want no nuclear missile to reach Abiy Ahmed , cost of living becomes affordable by most , the land grabs by foreigners to completely stop , the land grabs by Oromo “investors” to stop , the Jihadist movement to completely stop,selling out public properties to completely stop , selling out state properties to stop , borrowing from foreign sources to be kept at bay, all major EPRDFites criminals including Abiy Ahmed & Co. serving their sentences for the crimes they committed in the last three decades , have a much better foreign policy , one ethnic domination in the country completely stopped , Djibouti and Ethiopia becoming securing be country otherwise letting Djibouti secure her own port with her own navy while Ethiopian navy securing only its own waters-rivers and lakes , the talk with Eritrean people and Ethiopian people succeeding in uniting Eritrea and Ethiopia , the income gap between the looters and the looted not keeping on widening as it did for the last three decades and Ethiopians enjoying many many more blessings they got in stored for them by being free from the EPRDFites criminals looters grip on the economy politics and military power.

  Avatar for Beidilu

  Beidilu
  December 3, 2019 at 8:41 pm
  Reply

 2. እሰይ ማለፊያ ሃሳብ ነው ከሆነ። ቀኑ ረዘመና ተረስ እንጂ እውቁ ደራሲ በአሉ ግርማ ሀዲስ በተሰኘው መጽሃፉ ላይ እንዲህ ብሎ ነበር። “የምንተነፍሰው አየር ፓለቲካ፤ የምናልመው ህልም ፓለቲካ። ግን የሚገርመው ነገር ማንም ምንም አያደርግም። ቁና ሙሉ መፍትሄ – ቅንጣት ያህል ተግባራዊ ርምጃ የለም” አሁን ደግሞ የዘርና የቋንቋን አሰማመር ስናክልበት ሃገሪቱ በማይረባ ጎዳና ላይ እንዳለች ያመላክታል። በቅርቡ በአዲስ አበባ የሚኖር ኤርትራዊ ዘፋኝ በ 5 ሰዎች ድብደባ ደረሰበት የሚለውን ዜና ሳዳምጥ ያለምንም መረጃ ከረጅም ጊዜ ከሆነ ድብደባ ጋር አገናኘሁት። የድብደባው ፈጻሚዎች ወያኔዎች ናቸው። ሥፍራው ውጭ ሃገር ነው። ቁጥራቸው 5 ነው። አደባደባቸው ለመግደል ነበር። ያ ሰው አሁን ጥሩ ሆኔታ ላይ አይደለም። ይህ ኤርትራዊ የዓለም አጫዎች በወያኔ ጥቃት ደርሶበት ይሆን ብየ አስብኩ። ግን ምድሪቱ በእብዶች ከተያዘች ቆየችና ሻቢያም፤ አማራውም ኦሮሞውም የራሱ የብቀላ ድላ ስለሚኖረው በርግጥ ወያኔ ነው ለማለት አያስደፍርም። የጥቃቱ አሸራው ግን የእነርሱን ይመስላል።
  በ 2032 ይሆናል ተብሎ ስለታለመው የሰላምና የአንድነት ጉዳይ ሳስብ የሃገሬ ገበሬዎች የሚሉት አንድ ጉዳይ ትዝ አለኝ “የፊት የፊቱን” በደረስንበት አስበን እንኑር ማለታቸው ነው። በዘርና በጎሳ በቋንቋ በተሰመረች ሃገር ፍትህ ይመጣል ብሎ ማሰብ ጅልነት ነው። የክልል ፓሊስ፤ የክልል የጸጥታ ሃይል ወዘተ ሁሉም ለእኔ በራሴ የሚል የጅሎች ፓለቲካ ዛሬ በመቀሌ የአዞ እንባ ሲያነባ በሌሎች አካባቢ ደግሞ እኔም ክልል ልሁን ማለቱ ገና የሃገሪቱ ሃበሳ አለማለቁን ያሳያል። የሃበሻው ፓለቲካ የይስሙላ ጉዞ እንደሆነ የአቶ ለማ መገርሳ አፈንጋጭ ሃሳብ አጉልቶ ያሳያል። የሃገር መከላከያ ሆኖ ለዘሩ የሚያስብ የጠባብ ብሄርተኛ ተወካይ!ይመስለኛል ብዙዎቹ የሃሪቱን የወደፊት እጣ ፈንታ ለማሳመር ሳይሆን ለመታየት ብቻ የሚደሰኩሩ ይመስላል። አሁን ማን ይሙት የሃገራችን ህዝብ ከመንግሥቱ ሃይለማሪያም የበለጠ ዲስኩር አዋቂ አለ ብሎ ያምናል? እሳቸው ፈክረውና አፋክረው አንድ ጥይትና አንድ ሰው እስኪቀር እንዳላሉን ሁሉ የሃገሪቱን የቁርጥ ቀን ልጆች በ 17 ዓመት የስልጣን እድሜአቸው ጨፍጭፈውና አስጨፍጭፈው ሃገሪቷን ለወያኔና ለሻቢያ አስረክበው ነው የፈረጠጡት። እኔ የአሁን ጊዜ የሃገራችን ፓለቲከኞችና የዘርና የጎሳ መብት ተሟጋቾች እብዶች ይመስሉኛል። እብዶች ብቻቸውን የሚስቁት ነገሩ ቁልጭ ግጥጥ ብሎ ስለሚታያቸው ይሆን? አብደሃል፤ ምንም ተሰፋ የለህም። ኑሮህና ህይወትህ እንዲህ ነው የሚለው የሂሊና ደወል እያቃጨለባቸው ይሆን? ይመስለኛል። ፓለቲከኞችም እንደ እብዶች ወድቀው በተሰበሩበት በዚያው መሰላል ያለ ምንም ጥገና እንደገና ሊወጡ ሲከጅሉ ማየት ኦ ሰላም በስምሽ ስንት ግፍ ተሰራ ያስብላል። የሰላም ሚኒስቴር እንዳለሁ ሁሉ የተግባር ሚኒስተር ቢሾም ይረዳን ይሆን? አላውቅም። የሃገራችን ጉዳይ ማህረነ ክርስቶስ ያስብላል። እያደር ወደ ኋላ!

  Avatar for Tesfa

  Tesfa
  December 4, 2019 at 10:27 am
  Reply

 3. Way before 2032 *I do want to see the habesha’s irrelevant failed legal system be replaced completely with the time tested ABA Gaddaa legal system.

  *I also want to see all governmental offices and non governmental businesses to close all day long on Fridays for Jumea prayer.

  *I also want employees and students to be allowed to pray at salat time if they choose to.

  *I want Arabic language to be thought in all public schools around the country with it having its own department in higher learning institutions.

  Avatar for Mohamed Habbas

  Mohamed Habbas
  December 5, 2019 at 5:44 am
  Reply

 4. I want many more psychological evaluators to be trained each year, the evergrowinf demand for mental health help isnot going to get the supply ever.

  Poverty is not new to Ethiopia or Africa as a whole. Less than a dog type of ignorance among University level students
  now that is new unheard of before TPLFs generation grew up, even among the indigenous tribes of Ethiopia this type of ignorance was unheard off.Indegenous people cloth you and feed you in their own culture but rarely chase peaceful people away because they are not from their ethnicity.

  If EPRDF generation exhibit this much ignorance in schools how are these same people going to be towards each other for the rest of their life outside school is the biggest question. This is not simple goofing off bullying, it is real serious real life nightmare trauma which the retard Minister of Peace M K is keeping on minizing it to save her image , it is high time the Minister of Health step in with psychological evaluators to evaluate and treat the underlying mental condition cause for this savages ignorance .

  Sources say the khat addicted students and Professors want to chase all other ethnicity students out of their region to party all day with khat while watching OMN then by the end of semester students end up getting good grades without learning, finally graduating in whichever field they chose. . That’s why I recommend full time none cadre psychological counselors to be brought in to fight the insanity epidemic, their problem need to be recognized and treated before the country explodes. There is no use trying to teach mentally sick students, first cure there sickness.

  Avatar for Simasema

  Simasema
  December 5, 2019 at 7:31 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.