መቐለ በተካሄደው ሕገ መንግስትን እና ሕብረ ብሔራዊ የፌደራሊዝም ስርዓት የማዳን ሁለተኛ አገር አቀፍ መድረክ መጠናቀቁን ተከትሎ ከተሳታፊዎች የተላለፈ የአቋም መግለጫ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

አገራችን ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በመፈቃቀድ በጋራ የመሰረቷት ቤት እንደመሆንዋ በብዝሃነት ላይ የተመሰረተ አንድነትን ለመገንባት የሚያስችል ሕገ መንግስት እና ህብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝምን በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ይሁንታ ፀድቆ ወደ ሥራ ከገባ ወዲህ ከሃያ ዓመታት በላይ አስቆጥሯል።

በነዚህ ዓመታት ውስጥ ሕገመንግስታዊነትንና ህብረ ብሄራዊ የፌደራልዝም ስርዓትን ቀስ በቀስ እግር እየተከሉ በሰላም፣ በልማት እና በዴሞክራሲ ረገድ ብዙ ለውጦች የተመዘገቡ ቢሆንም ቅሉ በመንግስት ውስጥ እየገነገነ በመጣው ኪራይ ሰብሳቢነት፣ የፀረ ዴሞክራሲ አሰራር እና የመልካም አስተዳደር ችግር የተጀመረውን መልካም ሥራ በተለይም ሕገ መንግስቱንና ህብረ ብሔራዊ የፌደራሊዝም ስርዓቱን ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጠዋል። ኢህአዴግ በህብረ በሔራዊ የፌደራሊዝም ስርዓት እንዲመራት በአደራ የተቀበላት አገርና የተሰጠው የፖሊተካ ስልጣን መንገድ ስቶ አገሪቷን ወደ መበታተን አያመራች ነው።

አገራዊ ተጨባጭ ሁኔታችን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች ሕገ መንግስታዊ መብቶች እና ራስን በራስ የማስተዳደር መብታቸውን አደጋ ላይ የወደቀበት፤ የሕግ የበላይነት፣ ሰላምና የዜጎች ደህንነት የማይከበርበት፤ የዜጎች መሰረታዊ ጥያቄዎች በማዳፈን ስልጣን ላይ ያሉ ሀይሎች ያለ ገደብ ያሻቸውን ለማድረግ ሕግ የማይገዛቸው በሚመስል መልኩ የሚጓዙበት፤ የተጀመሩ መልከም ውጤቶች ወደ ኋላ የተመለሱበት በጣም አስጊ በሆነ መንገድ እየተጓዝን ባለንበት ሁኔታ ኢህአዴግ እነዚህ ተጨባጭ እና አንገብጋቢ አገራዊ ችግሮች ከመፍታት ይልቅ በለውጥና ሌሎች አማላይ ቃላት እየተንቆለጳጰሰ በውህደት ሥም ወደ ቀድሙት ስርዓቶች ለመመለስ ጫፍ ላይ ደርሷል። የመንግስትም የግልም ሚድያዎች አገርን የማዳን ሀላፊነታቸውን ከመወጣት ይልቅ ሀቆችን በማዳፈንና ችግሮችን በማባባስ ተጠምደዋል።

እኛ የመድረኩ ተሳታፊዎች ባካሄድነው ሰፊ ወይይት በሕገ መንግስታችንና በህብረ ብሔራዊ የፌደራሊዝም ስርዓታችን የተደቀነው አደጋ በብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች የጋራ ትግል ካልተገታ አገርን ወደ መበታተን ህዝቦችን ወደ የእርስ በርስ ዕልቂት ሊያስገባን እንደሚችል መደምደምያ ላይ ደርሰናል።

በአገራችንና ህዝቦቿ ላይ የተደቀነው ግልጽ አደጋ በመቀልበስ በኩል ከፍተኛ ሚና መጫወት ያለበት መንግስትና መሪ ድርጅቱ ቢሆኑም፤ ሕገ መንግስት፣ ህብረ ብሔራዊ የፌደራሊዝም ስርዓት እነዲሁም አገራችን የመንግስት እና የፖለቲከኞች ብቻ አይደሉም። አገራችን የብሄሮቿ፣ የብሔረሰቦቿና ህዝብቿ ናት። የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች ከባድ መስዋዕትነትን ከፍለው በሕገ መንግስቱ የተጎናጸፏቸው መብቶችና ነጻነቶች ወደ ቀድሞ ጨፍላቂና አሀዳዊ ስርዓት ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ከሁሉም በላይ ይጎዳቸዋል ብቻ ሳይሆን ገና ከወዲሁ ከፍተኛ መፈናቀል፣ ግድያ፣ ንብረታቸውን መዘርፍንና መቃጠል፣ በእምነታቸውን መሸማቀቅ ወዘተ በግልጽ እየታዩ ናቸው። ስለዚህም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች የተደቀነባቸውን የመበታተንና የመተላለቅ አደጋ ከወዲሁ በነቃ ተሳትፎና አደረጃጀት ፊትለፊት ወጥተው መታገል አለባቸው።
ስለዚህ ሕዳር 23-24/2012 ዓ.ም ሕገ መንግስትን እና ህብረ ብሔራዊ የፌደራሊዝም ስርዓት የማዳን ሁለተኛ አገር አቀፍ መድረክ በመቐለ ከተማ የተሳተፍን የብሔራዊ እና አገርአቀፍ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ ከብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች የመጣን የሀይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ እናቶች፣ ሙሁራን፣ ወጣቶች፣ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች፣ በአጠቃላይ የፌደራሊዝም ኃይሎች በተጨባጭ አገራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ የቀረቡት ጥናታዊ መነሻ ፅሑፎች አድምጠን ባደረግነው ሰፊ ውይይትና ተሳትፎ የጋራ መግባት ላይ ደርሰናል።

በዚሁም መሰረት ወደ ተግባር እንዲቀየሩ የሚኪተለውን የአቋም መግለጫ በጋራ አውጥተናል፦
1. ፀረ ህብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝም እና አሀዳዊ ሀይሎች ባለ በሌለ አቅማቸው በሕገ መንግስታችን እና ህብረ ብሔራዊ የፌደራሊዝም ስርዓታችን የከፈቱት ጥቃት ለመመከት የሚያስችለን ህብረ ብሔራዊ የፌደራሊዝም ሀይሎች ፎረም በመፍጠር፤ ፎረሙም ወደፊት በሚያስቀምጠው አቅጣጫ እና ውሳኔ መሰረት ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር መላ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች በማንቀሳቀስ ሕገ መንግስቱን እና ህብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝሙን ለመታደግ በጋራ ለመታገል ወስነናል።

2. በዚህ አገርን የማዳን መድረክ በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ወደ ተግባር ለመግባት ህብረ ብሔራዊ የፌደራሊዝም ሀይሎች በምናደርገው እንቅስቃሴ እና ትግል ሁሉም ባለድርሻ አካላትና የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች ያልተቆጠበ ድጋፍና ሰላማዊ ትግል እንዲያደርጉ ጥሪ እናስተላልፋለን።

3. እኛ ህብረ ብሔራዊ የፌደራሊዝም ሀይሎች የፖለቲካ ስልጣን ሉዓላዊ ባለቤቶች ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች ናቸው ብለን እናምናለን። በመሆኑም የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት በደነገገው መሰረት ስድትኛው የ2012 አገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ወቅቱን ጠብቆ እንዲካሄድ የሚገባው ሆኖ፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነታቸውን ተጥሶ የሚያዝ ፖለቲካዊ ስልጣን በምንም መስፈርት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።

4. የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች ነጻነታቸውንና ደህንነታቸውን ተጠብቆላቸው በአገራቸው ተንቀሳቅሰው የመኖር፣ የመስራት፣ ሀብት የማፍራት ሕገ መንግስታዊ መብት አላቸው። ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብቶቻቸው ተጥሶ በጅምላ እስከ መግደል የሚደርሱ ወንጀሎች እየተፈጸሙ መሆናቸውን እንገነዘባለን። ስለዚህም መንግስት በአፋጣኝ የዜጎችን መሰረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች እንዲከበሩ ሕገ መንግስታዊ ግዴታውን እንዲወጣ እናሳስባለን።

5. ህብረብሔራዊ ፌደራሊዝም ስርዓቱን ከአደጋ መታደግ ኢትዮጵያን እንደ አገር ማስቀጠል በመሆኑ ሁሉም መንግስታዊ እና የግል መገናኛ ብዙሀን፣ የፍትሕ እና የፀጥታ ተቋማት፣ ሲቪክ ማሕበራት፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ የወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀቶች፣ እንዲሁም መላ ኢትዮጰያውያን ሕገ መንግስታዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ እንጠይቃለን።

ድል ለህብረ ብሔራዊ ፌደራሊስት ሀይሎች!

ሕዳር 24/2012 ዓ.ም
መቐለ

11 Responses to መቐለ በተካሄደው ሕገ መንግስትን እና ሕብረ ብሔራዊ የፌደራሊዝም ስርዓት የማዳን ሁለተኛ አገር አቀፍ መድረክ መጠናቀቁን ተከትሎ ከተሳታፊዎች የተላለፈ የአቋም መግለጫ

 1. ሆዱ ዘመዱ። ሆዳም ጥርቅም ሁላ።
  ***Shameless People***
  OMG!

  Avatar for Fiseha

  Fiseha
  December 4, 2019 at 2:36 pm
  Reply

 2. thanks all

  Avatar for mesay

  mesay
  December 5, 2019 at 3:03 am
  Reply

 3. አይናችሁን ጨፍኑ እናሞኛችሁ አይነት ነገር፡፡ እሲኮ ትንሽ ፈጣሪን እንፍራ፤ ሞት እንደማይቀር 100% እርግጠኛ ናችሁ????? አንድ ቀን በፊቱ ቀርበን እንጠየቃለን ብሎ አለማሰብ፡፡ ሰው እኮ ምድራዊ ብቻ አስተሳሰብ ካለው በቃ እንስሳ ሆነ ማለት ነው፡፡

  Avatar for አሳሩ በዛብህ

  አሳሩ በዛብህ
  December 5, 2019 at 4:01 am
  Reply

 4. አሃዳዊነትና ፌዴራላዊነት አስተሳብና ትልም በብሄር ፓርቲዎች ምንና ምን ናቸው
  በብሄር የተደራጁ አብዛኞቹ ፓርቲዎች አገራዊ ስለሆነው ፌዴራሊዝም ቢሰብኩም እንወክለዋለን ስለሚሉት ብሄር እና ክልላቸው ያላቸው አስተሳሰብ ሙሉ ለሙሉ አሃዳዊነት ነው፡፡ ብዙዎቹ የብሄር ፓርቲዎች ለምሳሌ ኦነግ ያሉና መሰል ፓርቲዎች በክልል ስለሚኒኖረው የሌላ ብሄር ተወላጅ ምን ታስባላችሁ ቢባሉ መልሳቸው መኖር ይችላሉ ነገር ግን የክልሉ የስልጣን ባለቤት የኛ ብሄር ብቻ ነው ባዮች ናቸው፡፡
  በክልላቸው የሚኖውን ህዝብ ቋንቋውን፣ ባህሉን ሺ ጊዜ ቢያውቅና አብሮ ለዘመናትም ቢኖር የፖለቲካ ስልጣን የለውም ግን መኖር ይችላል፡፡ ና ስንለው ይመጣል( ለምሳሌ ምረጠን ስንለው) እኛ አታስፈልግም ስንለውም ከኛ ጋር ቁጭ ብሎ ስለሚኖርበት ክልል መምከር፣ ማቀድ መወያየት አይችልም ባዮች ናቸው፡፡
  ሳትሸፋፍኑ ኦነግን ጨምሮ በብሄር የተደራጃችሁ ፓርቲዎች ባላችሁት ክልል ብታሸንፉ ለዚህ ህዝብ ምን እንዳሰባችሁ በግልጽ ንገሩን፡፡ ለምሳሌ ስልጣን ሼር ታደርጉታላችሁ፣ ወይስ የለም መኖር ይችላሉ ግን የፖለቲካ ስልጣን ጉዳይ ላይ ወሳኙ አንድና አንድ ነው ትላላችሁ፡፡ ይህ ብዙ ጊዜ የማይነካ ግን አንገብጋቢ ነው፡፡
  በአገር ደረጃ ፌዴራሊዝምን፣ ህብረ ብሄራዊነትን፣ ብዝሃነትን እየሰበኩ በክልል ሲሆን ግን አሃዳዊነትን እና አንድ አይነትነትን ማራመድ ኢዲሞክራሲያዊ አካሄድ አይሆንምን;
  ይህን ሃሳብ በቅንነት፣ ስድብና እንካሰላንቲያ በሌለበት በንጹህ ልብ ብንወያይበት እላለሁ፡፡

  Avatar for Nazrawi

  Nazrawi
  December 5, 2019 at 6:45 am
  Reply

 5. It is really funny for an Ethiopian to see the useless old woman, Genet,with tyrant TPLF to save Ethiopia from destruction. She has continued her morron servant mentality to destroy this nation. TPLF is trying it’s best to come back to power and using the money it looted from poor Email to Ethiopians​.

  Avatar for Bekele Gebre

  Bekele Gebre
  December 5, 2019 at 7:48 am
  Reply

 6. በብሄር ከተደራጀህ ፌዴራሊስት በኢትዮጵያ ስም ስትደራጅ ደግሞ አሃዳዊ ብሎ መወሽከት
  እንዲሁም ህውሃት መዋሃዱን አልጠላውም ግን ፈጠነ፡፡ ሲፈጥን አሃዳ ሲዘገይ ደግሞ ፌዴራላዊ ብሎ በፈጣጣ ማውራት ሲበዛ ህዝቡን መናቅ ነው
  አሁን ደግሞ ሁሉም ሲከሽፋባቸው መንግስት መሰረተው ኢህአዴግ ነው፣ ብልጽግና ፈቃድ ከተሰጠው አገር የመመራት ሃላፊነቱን ያበቃለታል፡፡ ስልጣኑ ለማን መተላለፍ እንዳለበት ባይነግረንም ውህደቱን ስላልተስማማው ስልጣኑ እንደገና ወደ ህወሃት መምጣት አለበት የሚል ይመስላል፡፡ ስልጣኑ ቢሰጠው እርግጠኛ ነኝ ምርጫ ሁሉ ለ20 አመት ይራዘም ምክንያቱም ሰላም የለም እንደሚል ብንጠረጥር ምን ታስባላችሁ፡፡

  Avatar for Zeberga

  Zeberga
  December 5, 2019 at 10:48 am
  Reply

 7. TPLF is already dead! Now they must be yawning their remembrance day. Why you still persist in your outdated political philosophy? You have been screaming the most cliche Nations, Nationalities and Peoples for the last two decades. But no member of the TPLF can logically or semantically define these terminologies. On the one hand, you design a project (funded from the looted resource of the country) to escalate tension, terror and other inhuman acts in the country; on the other hand, you appear to be innocent, the only democrats gathering belly people or group who have no interest to safeguard the country from the targets of internal and external enemies. Anyways, the Weyane have no support nor will they come to power hereafter. The time of the de-facto “Federal Democratic Republic of Weyane” is gone. You have been trading in the name of federal state but proved to be nominal enough! Game over! The meeting is nothing but hot-air!
  With all its limitations, we support PM Abiy Ahmed’s government!!!!!!!!!!!!

  Avatar for Yisak Elias

  Yisak Elias
  December 6, 2019 at 1:58 am
  Reply

 8. I fear them. because all participants speak nervously. this shows something that is difficult to destroy. so democracy should start from individual and group. unless the future is only by negotiation.

  Avatar for Tonkolu Biltigina

  Tonkolu Biltigina
  December 6, 2019 at 5:30 am
  Reply

 9. ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት አደጋ ላይ ነው፤ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ተናግቷል እናድነው፤ ፌዴራላዊ ስርዓቱ ፈተና ላይ ነው ትሉናላችሁ ህውሃትና አጋሮቹ ከመቀሌ፡፡ ሰላም የለም፣ ሰው ወጥቶ መግባት አልቻለም፣ እየሞተ ነው፣ እየተፈናቀለ ነው የመሳሰሉት አስፈሪ እና ስር የሰደዱ ሁሉንም የኢትዮጵያ ክፍል ያካለለ መከራ መኖሩን ሁሉም ያምናል፡፡
  ይሄ ሁሉ መከራ በዚህ አገር ላይ እየዘነበ እያለ፣ በሲቃ፣ በሳግ ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ታዲያ ይህን ተማምነን ሳለን ዛሬውኑ ምርጫ ካልተካሄደ ሞተን እንገኛለን፣ ህገ መንግስቱ ተናደ ብሎ እዬዬ ማለት ምን ይሉታል፡፡ ከላይ የተማመንባቸውን ችግሮች በአፋጣኝ እንዴት እንፍታና ሰላም እናረጋግጥ ሳይሆን መፍትሄው ምርጫ ነው ማለት ሲበዛ ትዝብት ውስጥ ይጥላል፡፡
  ምርጫ ዛሬውኑ ካልተካሄደ የሚሉት ደግሞ በቅርብ ጊዜ ወደ አገር የገቡ፣ በቅርብ የተቋቋሙና በአዳራሽና ጭብጨባና ሙገሳ የሰከሩ ይመስለኛል፡፡ ህገመንግስቱን ማስከበር የፌዴራሉ መንግስት ብቻ ሳይሆን የክልል መንግስታትም ጭምር መሆኑ የተዘነጋና ማጥቂያነት እየተወሰደ ነው፡፡ ጥቂቶችን ከስልጣን እናወርዳለን፤ ወይም ወደ ስልጣን መንበር በዚህ ምርጫ እንወጣለን በሚል ግርግር የበዛበት፣ ተአማኒነት የሌለው ምርጫ ማካሄድ እንዘጭ እንቦጭ ነው ትርፉ፡፡
  በቅድሚያ ዜጋው በሰላም ወጥቶ፣ በራሱየሚተማመንበት ስርዓት እናረጋግጥለት፡፡ ተሸማቆ የልቡን ይመርጣል ብሎ ማሰብ ሲበዛ ውስጠ ወይራነት ነው፡፡

  Avatar for Nazrawi

  Nazrawi
  December 6, 2019 at 6:14 am
  Reply

 10. Fiseha little donkey
  is it your second nature to fart like a mare or a horse ? Why donot justify yourself and give reasons for your hate ? Insulting someone shows that he or she topped you and her or his sucess really bothers you. I mean you are in danger because of TPLF and Tigray peopl’s success.

  Avatar for donkey

  donkey'secondnature
  December 6, 2019 at 8:55 am
  Reply

 11. The Ferenj guy on the English part of this very website explained it better. There are now three kinds of TPLF. I thought TPLF would go after him in protest for exposing the second type with stealing billions of dollars. But not even one protested. It is just a fact they stole the money and are now have billions in USD.

  Four decades ago Ethiopians were furious when they found out Haile Selassie owned many cars but all of them were donated by foreign powers. They were also made believe he had 11 milliard dollars in a swiss bank. There is no ‘milliard’ in Amharic adopted counting but purposely done so that ‘milliard’ would be thought as trillion (after billion). Some level headed people figured there was no chance Haile Selassie could’ve stolen money that was not there since 1941 up to 1974.

  The late professor Fekade Shewakena who was kicked out (among the 41 professors that were kicked out) by Duri Mohammed and Meles Zenawi remembers Genet Zewde at AAU when WEYANE came to Addis very well. Genet was totally against WEYANE at frirst and then she is one of those people who claim they have royal blood when they have none and TPLF found out about that attitude and recruited her. She got 40 of her own students killed by WOYANE when she was education minister and she got rewarded for it.

  But Genet is only one of the hundreds who believe they have done so much for Ethiopia and everybody that opposes their master is ‘crazy’. And because they have done so much they have earned their ambassadorships and the commissions they took hooking up WEYANE businesses with Asians and Indians.

  I got to admit, WEYANE knows who to pick up to use as a tool

  Avatar for Irob

  Irob
  December 6, 2019 at 9:21 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.