“በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ የአማራ እና የሌሎችም ሕዝቦች ጥያቄዎች በህጋዊ እና በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ይሰራል እንጂ የሕዝብ እና የፓርቲውን መሠረታዊ አጀንዳዎች ልንተዋቸው አንችልም፡፡” አቶ ዮሐንስ ቧያለው

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

አማራውን ሆን ተብሎ በተዛባ ትርክት የሚፈርጁትን ሥርዓት ማስያዝ እንደሚገባ በሚኒሶታ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች እና የአማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያውያን ተናገሩ፡፡

የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በሚኒሶታ ከሚኖሩ የአማራ ተወላጆች እና የአማራ ጉዳይ ያገባናል ከሚሉ ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ ክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ዛሬ ተወያይተዋል፡፡ ውይይቱ በክልሉ ልማት፣ ኢንቨስትመንት እና በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ድጋፍ ላይም ያተኮረ ነበር፡፡ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ ናቸው ነዋሪዎቹን ያወያዩት፡፡ “የአማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ መልዕክት በተካሄደው ምክክር ምሁራን፣ ባለሀብቶች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች እና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡ ጥያቄ እና ምክረ ሀሳቦችንም አቅርበዋል፡፡

በክልሉ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ በትኩረት ይሰራበት፤ ለኢንቨስትመንት ምቹ አሰራሮች ሊፈጠሩ ይገባል፤ በኢንቨስትመንት የሚሰማሩ ባለሀብቶች የሚሰማሩባቸው ዘርፎች በአካባቢ ላይ ጉዳት አለማድረሳቸው ሊፈተሸ ይገባል፡-ለአብነትም የቆዳ ፋብሪካዎች የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ባለመካሄዱ በማኅበረሰቡ ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው፤ ዘር ተኮር ፖለቲካው አማራውን ለጥቃት እየዳረገው በመሆኑ ልትደርሱለት ይገባል ሲሉ ተሳታፊዎቹ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲዎች እየተስተዋለ ያለው ግጭት እንዲቆም መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባ እና አማራውን በተሳሳተ እና ሆን ተብሎ በተዛባ ትርክት መፈረጅ እንዲቆም ትክክለኛውን ታሪክ በማስገንዘብ እንዲሰራም ነው ተሳታፊዎቹ የጠየቁት፡፡ በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎችን እንዴት ለማስመለስ እንደታሰበ እና በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የነበረው የጸጥታ ሥጋት በዘላቂነት እንዲቀረፍ ምን መፍትሔ እንደተቀመጠም ማብራሪያ ጠይቀዋል፡፡ ሕዝብ እንዲደራጅ አዴፓ ሊያበረታታ እና ሊደግፍ ይገባል፤ ይህ ደግሞ ክልሉን በሁሉም መሥክ ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል የሚኒሶታ ነዋሪ የአማራ ተወላጆች፡፡

የሥራ ኃላፊዎችም ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የአልማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ በሰጡት ማብራሪያ በክልሉ አስተማማኝ ሰላም እና ጸጥታ የማስፈኑ ተግባር በተጠናከረ መልኩ እየተሰራበት እንደሆነ እና ለዘላቂነቱ ሁሉም በየዘርፉ መሥራት እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡ በክልሉ ለኢንቨስትመንት ስጋት የሚፈጥር ሁኔታ አለመኖሩን፣ በዚህም በርካታ ባለሀብቶች በክልሉ በዘርፉ እየተሰማሩ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ ይህንን በመገንዘብም ያለስጋት ወደ ክልሉ መጥተው እንዲያለሙ ነው ያስገነዘቡት፡፡

የአዴፓ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዮሐንስ ቧያለው በሰጡት ማብራሪያ ደግሞ “በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ የአማራ እና የሌሎችም ሕዝቦች ጥያቄዎች በህጋዊ እና በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ይሰራል እንጂ የሕዝብ እና የፓርቲውን መሠረታዊ አጀንዳዎች ልንተዋቸው አንችልም” ብለዋል፡፡ የተዛቡ ትርክቶች እንዲስተካከሉ መሥራት ፓርቲው ትኩረት ከሚያደርግባቸው አንኳር ጉዳዮች መካከል መሆኑን ያስገነዘቡት አቶ ዮሐንስ በየትኛውም አካባቢ የሚኖረውን የአማራ ሕዝብ ኅልውና የመጠበቁ ጉዳይም ትኩረት እንደሚደረግበት ነው የተናገሩት፡፡ በሕዝቡ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ፋብሪካዎች ሲገነቡ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ማድረግ ይገባል የሚለው ሀሳብም ተገቢነት ያለው እና መቀረፍ ያለበት እንደሆነ ነው የተናገሩት፤ ጉዳት እያደረሱ በሚገኙት ላይ ማስተካከያ ማድረግ ይገባል የተባለው ሀሳብም ተገቢ እንደሆነ አስረድዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት በተመለከተ ለቀረበው ማብራሪያም መፍትሔው ሁሉም ከየትኛውም አካባቢ የሚመደቡ ኢትዮጵውያን ወገኖቹን እንደልጆቹ ተንከባክቦ በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲተኩሩ ኃላፊነቱን መወጣት እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ ግጭቱ ግን የፖለቲካ ብልሽቱ ውጤት መሆኑን መረዳት እና መጠቀሚያ መሆን እንደማይገባ ነው አቶ ዮሐንስ የተናገሩት፡፡

አዴፓ ወደ ብልጽግና ፓርቲ ሲገባም ፓርቲው የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች በዕኩልነት እንደሚመልስ በመፈተሽ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

አብመድ ከሚኒሶታ

5 Responses to “በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ የአማራ እና የሌሎችም ሕዝቦች ጥያቄዎች በህጋዊ እና በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ይሰራል እንጂ የሕዝብ እና የፓርቲውን መሠረታዊ አጀንዳዎች ልንተዋቸው አንችልም፡፡” አቶ ዮሐንስ ቧያለው

 1. It’s just super-encouraging to see our PM Abiy to be keeping busy with important issues while in the midst of a chaotic chapter and times in current-Ethiopia. Viva, Abiy!

  amharic books
  December 14, 2019 at 12:54 pm
  Reply

 2. One of the main questions of Oromos not being addressed by EPRDF which we hope PROSPERITY will address it for us is , why are we Oromos displaced from Ogaden not being let back to Ogaden?

  Togasi
  December 14, 2019 at 3:14 pm
  Reply

 3. Amaras question of Wolqait , Raya and the Amara land Sudan got should be at the forefront of the ADP campaign speeches .

  Bireda
  December 14, 2019 at 8:21 pm
  Reply

 4. ዳያስፖራ አማራው መች ነው የአዴፓ አመራርን ማብጠልጠል የሚያቆመው? እንደ መላኩ ፈንታና ዮሀንስ ቧያለው ምሁር የአማራ መሪዎች ከግፈኛው ህውሀት ስርአት ሰለባ ሆነው በህይወት ተርፈው የአማራን ህዝብ አንገት ቀና እያደረጉ ነው:: ምን ምድራዊ ተአምር ይስሩ? በእነሱ ጫማ ውስጥ ገብቶ ይህ ሁሉ ጠያቂ ነፈዝ ምን የተሻለ ስራ ይሰራል? አማራ ሲተርት ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው ይላል! አሜሪካ ሆነው የአሜሪካን ህግ ጠንቅቀው የማያውቁ! ፖምፔኦ ለምን ጃዋራን አላሰረውም? መልሱ ሊያስረው አይችልም:: ዮሀንስ ቧያለው ምን ይፈይድ? የእውቀት ደካሞች! በአማራነቴ ያፈርኩበት ጊዜ:: ዛሬ አማራው ሌላውን አማራ በማብጠልጠል የሚጨምረው የአማራን ጠላት ህውሀትን ማጠናከር ብቻ ነው:: ዛሬ አብን አዴፓን የሚያግዝበት አዴፓ አብንን የሚደግፍበትና ተገን የሚሆንበት ወይንም መሆን የሚኖርበት የታሪክ አጋጣሚ ላይ ነን: አማራ የፖለቲካ ግንጦት ጫወታ ወቅት ላይ እይደለም:: ለህልውናው መሰባሰብ አለበት:: ክብር ከቤት ይወለዳል:: ዮሀንስ ቧያለው ቀጥትኛ የአማራ ልጅ አከብርሀለሁ:: በርታ
  የአለኝ የፖለቲካ ተሳትፎ ባይኖርም ቦንድ በመግዛት እረዳለሁ

  ተሰማ
  December 16, 2019 at 8:16 pm
  Reply

 5. Why should we rather not focus on grinding poverty 80% of the Ethiopian population is suffering from instead of talking about the blood flowing in our veins and labeling each other by the kind of languages our mothers spoke. We are all Ethiopians and let us focus on Ethiopia’s problems, i.e., the catastrophic economic effects of landlockedism, demographic explosion, inflation, unemployment, systemic corruption and negative balance of payment, to mention few. Kindly folks, let us talk about our real suffocating problems and the way out. I respect the cultural and linguistic rights of our diverse population which should be held as our strength and not weakness, asset and not liability provided that everyone’s human rights are respected. A poor person is poor whether/he speaks Amhara, Tigre, or Oromo language. Focus on real issues!

  Biftu
  December 19, 2019 at 10:20 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.