Home » Entries posted by ዘ-ሐበሻ
Entries posted by ዘ-ሐበሻ
የመለስ ዜናዊን ነቅለን ሳንጨርስ አብይ ተሰቀለ!

የመለስ ዜናዊን ነቅለን ሳንጨርስ አብይ ተሰቀለ!

ዛሬ በሃድያ ዞን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተደረገው አቀባበል ከወትሮው በተለየ በጣም ደማቅ ነበር ማለት ይቻላል። በዚህ ረገድ የዞኑ መስተዳድር እና የከተማዋ ነዋሪዎች ሊመሰገኑ ይገባል። እንዲህ ያለ ደማቅ አቀባበል ማድረግ ለዞኑ ገፅታ ግንባታ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ሆኖም ግን በዞኑ ጉብኝት ያደረገው ሌላ ሳይሆን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው። ከዞኑ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ማድረግ ሥራና ሃላፊነቱ ነው። በዚህ መሠረት […]

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸመው ግፍና መከራ እንዲቆም፣ ዛሬ ዕሁድ ብቻ ከሰላሳ በላይ በሚሆኑ የኢትዮጵያ ከተሞች ሰልፍ ተደረገ።የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ሰልፎቹን ተቀላቅሏል።ለንደንም ሰልፍ ነበር።(ከሃያ በላይ ፎቶዎች ይመልከቱ)

ጉዳያችን GUDAYACHN  መስከረም 11/2011 ዓም (ሴፕቴምበር 22/2019 ዓም) =================  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን እና አባቶች በቤተ ክርስቲያንና ምዕመኖቿ ላይ ግፍ የፈጸሙት አካላት በሕግ እንዲጠየቁ፣በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች እንዲቆሙ እና መንግስት ለችግሩ ትኩረት እንዲሰጥ በመጠየቅ  ከሰላሳ በላይ በሚሆኑ የኢትዮጵያ  ከተሞች ዛሬ  ሰልፎች ተካሂደዋል። በያዝነው ሳምንት አጋማሽ ላይ በዋሽንግተን የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን […]

Continue reading …
ሃይማኖት፤ እምነትና ፖለቲካ፤ ሕዝብ አደናጋሪ የዘመኑ ውዥንብር

በገ/ክርስቶስ ዓባይ መስከረም 10 ቀን 2012 ዓ/ም ሃይማኖት ለሰብአዊ ፍጡር የተሰጠ የሕልውና መገለጫ፤ የሕይወት ተስፋና ከአምላክ ጋር የሚያገናኝ፤ በዓይን የማይታይ ግን በመንፈስ የተዘረጋ ድልድይ ነው። ሃይማኖት ከአምላክ በሚሰጥ ልዩ ፀጋ በተለያዩ እምነቶች ይገለጻል። ጥንት፤ ዓለም እምነት አልባ (አረማዊ) በነበረችበት ዘመን፤ ኢትዮጵያውያን በሕገ ልቡና ፈጣሪ እንዳለ በመረዳት ከክፉ ሥራ በመራቅና በጎ ተግባርን በመሥራት ፈጣሪያቸውን ያመልኩ እንደነበር […]

Continue reading …
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዮች በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ አካሂደዋል

ባህር ዳር ወልዲያ ደባርቅ ራያ ቆቦ ደብረ ማርቆስ ላልይበላ ደብረ ብርሃን   ጎንደር በጎንደር ምህላ ተካሄዷል!! Posted by GondarTube/ጎንደር on Sunday, September 15, 2019

Continue reading …
“…አወቅሽ ።አወቅህ።”ሥንላቸው ፣መፅሐፍ እያጠቡ ያሉትን የሚያንጓልልን ከሆነ የመደመር ፍልስፍናን እንደግፋለን።  – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

 “አወቅሽ፣አውቅሽ ቢሏት የባሏን መፅሐፍ አጠበች” በድሮ ጊዜ ነው አሉ ፣ አንድ ያለማወቋን የማታውቅ ሆና  አውቃለሁ የምትል ሴት ነበረች።ይህቺ ሴት   ከሠፈሯ ካለው ምንጭ፣ ውሃ ለመቅዳት፣ የሚመጡትን  ሴቷች ሁሉ፣ከሰላምታ በፊት በወሬ ነበር  የምትቀበላቸው ።  ሥራ ፈት ሥለሆነችም ከምንጩ ዳር አትታጣም።  ውሃ ለመቅዳት የሚመጡትንም ሴቶች  በተለያየ ወሬ  እየነተርከች ታሥቸግራቸው ነበር።         አንድ ቀን ለመንደሩ እንግዳ […]

Continue reading …
የፖለቲከኞች አጀንዳ እና የሕዝብ አጀንዳ አዮ ሌላ ወዮ ሌላ – በገ/ክርስቶስ ዓባይ     

በገ/ክርስቶስ ዓባይ ጳጉሜን 3 ቀን 2011 ዓ/ም ዓለማችን በቴክኖሎጂ ጥበብ እጅግ እየተራቀቀች ቢሆንም ፖለቲካን (የሕዝብ አስተዳደርን) በተመለከተ ግን እጅግ ወደ ኋላ እየሄደች ትገኛለች። ለዚህም ብዙ ምክንያቶችን መደርደር ይቻላል። ይሁን እንጂ አሁን ለተነሳንበት ርዕስ፤ አንኳር አንኳር ከሆኑት ጥቂቶችን ብቻ መጥቀስ በቂ እንደሚሆን እንገምታለን። በጣም የሚደንቀው ነገር ግን በዓለም ብዙ የታወቁ ዩኒቨርስቲዎችና ፕሮፌሰሮች እንዲሁም ፈላስፎች ቢኖሩም፤ ለሰው […]

Continue reading …
የትውልደ ኢትዮጵያዊው ሚሊዬነር የአሟሟት እንቆቅልሽ!  (በታምሩ ገዳ)

በቅርቡ የበርካታ ሚሊዬን ዶላሮች አሸናፊ ለመሆን የበቁት እና በአገራችፕው ኢትዮጵያ ውስጥ የችግረኞችን ህይወት ለመቀየር ውጥን የነበራቸው ትውልደ ኢትዬጵያዊው ሰሞኑን በአገራቸው ኢትዬጵያ ውስጥ ሞተው የመገኘት ዜና ቤተሰቦቻቸውን በእጅጉ አስደንግጧል። በካናዳው ፣ቶሮንቶ ግዛት ውስጥ በአንድ የመገጣጠሚያ ፋብሪካ ውስጥ ይሰሩ የነበሩት የአርባ እንድ አመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ ሚካኤል ገብሩ የዛሬ ሁለት አመት(እኤአ ሰኔ 2017) የቆረጡት ሎተሪ ግፋ ቢል […]

Continue reading …
ጎሠኝነትና ይሉኝታና ሀፍረት  – ግርማ በላይ

ግርማ በላይ (gb5214@gmail.com) እኔንስ ኅሊና ደሳለኝን መሆን አያምረውም ያለው ማን ነው ? ባልቻና ደቻሣ – ሐጎስና ማንጁስ እየተባባሉ፤ ከአጥናፍ እስካጥናፍ መላ ኢትዮጵያን ሲግጧት አደሩ፡፡ እኔ ምን ቸገረኝ ግጥሙ ቢያምር ባያምር፤ ለግጥምማ ማማር አዝማሪ አለ አይደለምወይ፡፡ (ብለዋል የፍቅር እስከ መቃብሩ ፊታውራሪ መሸሻ)   ያዝ እንግዲህ!   ሞኙ አበበ፣ ደርግ ባስታቀፈው በሶ ላይ እንደተጎለተ ጩቤ የጨበጠው ጫላ […]

Continue reading …
ጠ/ሚ አብይ አህመድ ታላቁ ቤተ መንግስትን አስጎበኙ

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ታላቁ ቤተ መንግስትን አስጎበኙ

Continue reading …
ይቅርታ ማለትን ጠንቅቆ የሚያውቅ መሪ ብልህ ነው   (በታምሩገዳ)

አንዳንድ ጊዜ ሁሉም ነገር በእጃችን ነው (ባለጊዜዎች ነን)በማለት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የምናደርጋቸው፣የምንናገራቸው፣የምንጽፋቸው …ወዘተ ነገሮች ይዋል ይደር እንጂ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍሉናል ፣ሲያስከፍፈሉንም ይስተዋላሉ ። ከላይ ለተገለጸው አባባል ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑን ሰሞኑን ለሁለተኛ ዙር የምረጡኝ ዘመቻ የጀመሩት የካናዳ ጠ/ሚ/ር ጀስቲን ቱሩዲዬ ዋንኛ ተጠቃሽ ሲሆኑ ጠ/ሚ/ሩ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት እኤአ 2001 ቫንኩቨር ውስጥ ዌስት ፖይንት ግሬይ አካዳሚ […]

Continue reading …
አቶ አብይ አበራ በግሉ እስር ቤት አለው ተብሎ በ43 ክሶች የታሰረው ባለሃብት!

ነፃ ውይይት  የጉድ ሀገር ጉድ ሲጋለጥ! ” በግል መኖሪያ ቤቱ ውስጥ “የማሰቃያ እስር ቤት አለው” ተብሎ የተከሰሰውን ባለሃብት አስታወሳችሁት? ያ….እንኳን ሐምሌ 13/2009 ዓ.ም ጠዋት ላይ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (#FBC) “ለብዙ ወጣት ባለሃብቶች የአራጣ ብድር በመስጠት ለከፋ ድህነትና ችግር ዳርጓቸዋል” የተባለውና ከሰዓት በኋላ በቁጥጥር ስር የዋለው ሰውዬ ትዝ አይላችሁም። ከአምስት ቀናት በኋላ ሐምሌ 18/2009 ዓ.ም ፋና […]

Continue reading …
ከእጅ አይሻል ዶማ?!! – የአማራ ባለሙያዎች ማህበር (አምባ)

ከሐይለገብርኤል አያሌው በተለምዶ የተማረ ይግደለኝ ይላል የሃገራችን ሰው። ይህ ሲባል በደፈናው ፊደል ለቆጠረ ዲግሪ ለጫነና ምሁር የተባለውን አድርባይ ፈሪና ጥቅም አሳዳጁን ሳይሆን በእውቀትና በእውነታ ላይ የተመሰረተ ስብእና ያለውን ነው:: አርቆ አስተዋይነት፣ ሚዛናዊነት፣ ፍትሓዊነትን የተከተለ ህዝባዊ ወገንተኝነትንና ሰብኣዊ ርህራሄን ላነገበ ባሉባልታ የማይነዳ በማስረጃ የሚያምን በክርክርና በሃሳብ የበላይነት የሚመራን ምሁር ላቅ የሚያደርግና የሚያከብር ምሳሌዊ ጥቅስ ነው:: በሃገራችን […]

Continue reading …
ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ  በለውጥ ጎዳና  – ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ

ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ  ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ ብቁ መምህራንን በማፍራት በአገራችን በመምህራን ስልጠና እና በስፖርት ዘርፍ እድሜ ጠገብ የሆነ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነበር፡፡ ተቋሙ ከዚህ በፊት በሚታወቅበት በመምህራን ትምህርትና በስፖርት ዘርፉ ያለውን ዕውቅና አጠናክሮ መቀጠል ሲገባው በዘመኑ በነበሩ የፖለቲካ ሊሂቃን ውሳኔ ወደ አዲስ አበባ ት/ቢሮ ከዛም ወደ አዲስ አበባ መስተዳድር ሲሽከረከር ቆይቶ በ2012 ብሩህ ተስፋ የፈነጠቀለት […]

Continue reading …
አክራሪዎች ጋር በቋንቋ መግባባት በፍጹም አይቻልም – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ኦቦ በቀለ ገርባና አክቲቪስትና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በናሁ ቲቪ ያካሄዱትን ጭቅጭቅ (ውይይት ማለት ስለሚከብድ ነው) አሁን ከዩቲዩብ አውርጄ እያየሁ ነው፡፡አንድ ሰው በአግባቡ ተከራክሮ ማሸነፍ ሲያቅተው፣  ተፋላሚውን በሃሳብ መርታት የሚያስችለው ሚዛን የሚያነሣ የመከራከሪያ ነጥብ ሲያጥረው ወደምን እንደሚገባ ለማወቅ ይህን ዝግጅት ማየት ብቻውን በቂ ነው፡፡ ከስሜትና ከአሉቧልታ ውጭ ረብ ያለው ነገር ይዞ ወደ ክርክርና ውይይት የማይገባ ሰው […]

Continue reading …
በገጣሚ ህሊና ደሳለኝ ላይ የተጀመረው ዘመቻና  የ ኤል ቲቪ ነውረኛ ዉንጀላ – ከአበበ ጉልማ

በኢትዮጵያ  የሚተላለፈው LTV World የተሰኘው ቴለቪዥን ሰሞኑን የኦሮሞ መብት ተከራካሪ ነኝ ከሚሉት አቶ ግርማ ጉተማ ጋር ባደረገው ቃለመጥይቅ በገጣሚ ህሊና ደሳለኝ ላይ የተደረገ ስም ማጥፋትና በአደባባይ የተደረገ ዉንጀላ ነበር። LTV World በዮቲዩብ Sep 18, 2019  ባሰራጨው ቃለመጠይቁ (7፡18 አካባቢ ያለውን ያዳምጡ) ወጣቷን ገጣሚ ያላለችዉን ብላለች በማለትና፣ በኢትዮጵያ ቀርቶ በሌላዉም አለም ነዉር የሆነን የብልግና ቃል በአደባባይ […]

Continue reading …
አማራጭ የሌለው የሠላም ጎዳና    (ጆቢር ሔይኢ-ከሁስተን ቴክሳስ)

ኢትዮጵያ አገራችን የብዙ ብሔር ብሔርሰብ አገር ነች፡፡እያንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብም የራሱ ቋንቋ፤ባኅል፤እምነት፤ ታሪክና የምኖሪያ አካባቢ አለው።  ነገሥታቱ ሲያስከብሩ የቆዩት ኢኮኖሚያዊ ጥቅማቸውን፤ባኅል፤ ቋንቋና እምነታቸውን ነበር። ቤተ ክርስቲያን እንኳ ከሕዝቡ ከተወረሰው መሬት  የሲሶ መንግሥት ይዞታ ነበራት። ከዚህም የተነሳ የምሥራቅ፤የደቡብና የምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች፤  አብዛኛው በመደብ፤ በብሔርና፤ በሃይማኖት ጭቆና ሲማቅቁ ኑረዋል።ስለሆነም ሥርዓት ካስከተለባቸው ጭቆና ነጻ ወጥተው በእኩልነት መኖርን ይፈልጋሉ። በአንፃሩም  […]

Continue reading …
ሙትም ይወቀሳል! –  በላይነህ አባተ

ሙት አይወቀስም የሚሉት አባባል፣ የስንቱ ከሀዲ ወንጀል ሽፋን ሆኗል፡፡ እንኳንስ  በኮቢ እንኳን በሰው ልሳን፣ በቅዱስ መጻሕፍት ሙትም ይወቀሳል፡፡ በለስን የበሉት አዳምና ሄዋን፣ በኦሪት በሐዲስ ዛሬም ተወቅሰዋል፡፡ አቤልን የበላው ቃየል አረመኔው፣ ድህረ-ምጣትም ሲወቀስ ኗሪ ነው፡፡ ክርስቶስን ስሞ አሳልፎ ሰጪው፣ የጥንቱ ብአዴን ይሁዳ ከሀዲው፣ እስከ ዓለም ፍጣሜ ሲረገም ኗሪ ነው፡፡ የመሲህ ከሳሹ ከንቱው ፈሪሳዊው፣ በሐሰት ፈራጁ ጲላጦስ […]

Continue reading …
የሕዝብ ሀብትን ያለከልካይ መርጨት ካለእውቀት ማጨብጨብም ወንጀል ነው

በጀት ቁም ነገር ላይ የሚውለው መቼ ነው ? ባሳለፍነው አመት ብቻ በርካታ ገንዘቦች የባከኑባቸው ጭፈራዎችና ድግሶች በተለያየ ሰበብ ወጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩንና የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ጨምሮ በርካታ የመንግስት ሰዎች የምርጫ ቅስቀሳ በሚመስል መልኩ የራሳቸውን ገጽታ ለመገንባት የሃገሪቱን ገንዘብ ረጭተዋል። ሕዝቡም ካለእውቀት አጎንብሶ ያጨበጭባል፤ ቀና ብሎ መጠየቅን አልተካነበትም። የተለያዩ ባለስልጣናት ከፍተኛ ወጪ የወጡባቸው ድግሶችንና ስብሰባዊ ፋይዳቢስ […]

Continue reading …
ኢሕአዴግ ዛሬ እና ትላንት    (ፍትሕ መጽሔት ላይ የወጣ ጽሁፍ)

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ ‹ቲም ለማ›ን በመምራት፣ በኦሮ-ማራ ጥምረት በመንጠላጠል፣ ኢሕአዴግ ውስጥ የተፈጠረውን ስንጥቃት በመመርኮዝ የምንሊክ ቤት-መንግሥትን ከረገጡ 18 ወራት አስቆጥረዋል። በዚህ ዐውድ በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚንስትሩ (በመንግሥታቸው) የተስተዋሉ ተጻርዮሽ ንግግሮች (እርምጃዎች) በቀጣዩ አዲስ ዐመት እንዳይደገሙ የተወሰኑትን በማሳያነት ጠቅሰን እናሳስባለን። የርብ ግድብ በዐማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ‹በአራት ዐመት ተገንብቶ ያልቃል› ተብሎ የተጀመረው የ‹ርብ መስኖ ልማት […]

Continue reading …
አማራነትን ሣይሆን አማራዊነትን ያዙና ኢትዮጵያን አድኑ! – ሰሎሞን ንጉሡ

ሰሎሞን ንጉሡ (khartoum71@gmail.com) መንፈሴ በል ያለኝን እናገራለሁ፡፡ ኢትዮጵያችን ክፉኛ ታማለችና የሚመለከታችሁ ሁሉ ፈጥናችሁ እንድታድኗት በልጆቻችን ስም እማጸናችኋለሁ፡፡ እኔን መሰል የዕድሜ ባለጠጋ ከመናገርና ከመጻፍ ውጪ ሌላ ይህ ነው የሚባል አስተዋፅዖ እምብዝም የለውም፡፡ ኢትዮጵያን ከተደቀነባት አደጋ ለመታደግ ግን በተለይ ወጣቶችና በሳል ጤናማ ምሁራን ጉልኅ ሚና መጫወት ይችላሉና ጊዜው ብዙም ሳይመሽ ቢጥሩ መልካም ነው፡፡ ተሰሚነት ያላችሁና ማኅበራዊ ተፅዕኖ […]

Continue reading …
Page 1 of 894123Next ›Last »