Home » Archives by category » ስፖርት
የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ድባብ – ዋልያዎቹ ከሌሴቶ ያደርጉት ጨዋታ -ታርቆ ክንዴ

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ድባብ – ዋልያዎቹ ከሌሴቶ ያደርጉት ጨዋታ -ታርቆ ክንዴ

“90 ደቂቃ ያለእረፍት ከጎናችን በመሆን ያበረታንን ደጋፊ ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡” አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ “በቴክኒካል አቅሙ ከፍ ያለ እና ጥሩ ቡድን የገነባውን አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱን እንኳን ደስ አለህ ማለት እፈልጋለሁ፡፡” አሰልጣኝ ታቦ ሴኔንግ ለ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የሌሴቶ አቻውን በማስተናገድ የጀመረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ያለምንም ግብ […]

ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታውን ለማድረግ ዳሬ ሰላም ገብቷል

ቡድኑ ዳሬ ሰላም ሲደርስ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ እና ሌሎች አካላት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ በመሆን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው ፋሲል ከነማ የመጀመሪያውን የማጣሪያ ጨዋታ በባህርዳር አለማቀፍ ስታዲየም አዛምን 1ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡ ነሃሴ 18 የመልሱ ጨዋታ ዳሬ ሰላም ላይ ከአዛም ጋር የሚያደርገው ፋሲል ከነማ ለጨዋታው በአዲስ አበባና ባህርዳር ልምምድ ሲያደርግ […]

Continue reading …
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሞሮኮ እግር ኳስ ፕሬዝዳንትን ከሠሠ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ሦስተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት ፋውዚ ሌክጃ፤ በፊፋ እውቅና የተሠጠውን በዓምላክ ተሰማ (ዳኛ) ላይ ድብደባ በመፈጸማቸው ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ በሳለፍነው ሳምንት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን በግብፁ ዛማሌክ እና በሞሮኮው ቤርካኔ የእግር ኳስ ክለብ መካከል በተደረገው የፍፃሜ ዋንጫ ላይ በአምላክ ተሰማ የመሐል ዳኛ ሆነው በመሩበት ጨዋታ የግብፁ ዛማሌክ አሸናፊ ሆኖ […]

Continue reading …
ቅዱስ ጊዮርጊስ ለጥያቄዎቹ ምላሽ እስከሚያገኝ ከፕሪምየር ሊጉ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮቸ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ፡፡የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ የቅዱስ ጊዮርጊስን የሜዳ ተጠቃሚነት ለማሳጣት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ሊያደርገው የነበረን ጨዋታ በዝግ ወይም አዳማ  ተጫወቱ በማለት ሁለት ጊዜ እንዲቋረጥ […]

Continue reading …
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ምስጋና አቀረበ

በ2011 ዓ.ም እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ላይ እየተካፈለ የሚገኘው ክለባችሁ ግንቦት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በፋሲለደስ ስታዲየም ከወልዋሎ አ/ዩ ክለብ ጋር በነበረበት የ23ኛ ሳምንት ጨዋታ ፡- 1. ከውድድሩ 4 ቀን ቀደም ብሎ የክለቡ አመራሮች ወደ እንግዳው ክለብ አመራሮች ስልክ በመደወል የመረጃ ልውውጥ በማድረግ የማረፊያ ሆቴል ቅድመ […]

Continue reading …
ከጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር የተለያየው ዩጋንዳዊው አማካኝ ያሳር ሙጊርዋ በሰአታት ልዩነት ውስጥ የትግራዩን ሽሬ ከነማ እንደተቀላቀለ ተሰማ

ከጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር የተለያየው ዩጋንዳዊው አማካኝ ያሳር ሙጊርዋ በሰአታት ልዩነት ውስጥ የትግራዩን ሽሬ ከነማ እንደተቀላቀለ ተሰማ፡፡ የኡጋንዳው ካዎዎ ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው ተጨዋቹ ከአዲሱ ክለቡ ሽሬ ጋር ለአንድ አመት የሚቆይ ውል ተፈራርሟል፡፡ የውሉ መጠን በምስጢር እንዲያዝ የተወሰነ ቢሆንም ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ ለፊርማ ከ25 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ እንደተከፈለው ዘግቧል፡፡ ተጨዋቹ ከደቡብ አፍሪካው […]

Continue reading …
ሳሙኤል ተፈራ ለ22 ዓመታት ተይዞ የቆየውን  የ1,500 ሜትር  የቤት ውስጥ ሪኮርድ ሰበረ

እንግሊዝ በርኒንግሃም ውስጥ በተደረገው ሩጫ ውድድር አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ለ22 ዓመታት ተይዞ የቆየውን  የ1,500 ሜትር  የቤት ውስጥ ሪኮርድ ሰበረ:: በሌላ በኩል አትሌት አልማዝ ሳሙኤል በ3,000 ሜትር ተወዳድራ በጥሩ ሰዓት አንደኛ በመውጣቷ የ2019 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮን ለመሆን በቃች:: – ዛሬ በመቀሌ በተደረገው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ ባህርዳር ከነማን 1ለ0 አሸንፏል::  

Continue reading …
ናይጄሪያዊው አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ በመጨረሻም የጅማ አባጅፋር ንብረት ሆኗል

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ስኬታማ ጊዜ ካሳለፉ የውጭ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ናይጄሪያዊው አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን በ23 ግቦች ካጠናቀቀ በኃላ ውስብስብ በሆኑ አወዛጋቢ ጉዳዮች ታክለውበት ወደ ግብፁ ኢስማኤል ቢያመራም እምብዛም የመጫወት ዕድል ባለማግኘቱ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል፡፡ ዳግም ከተመለሰ በኋላ የቀድሞው ክለቡን በስፋት ይቀላቀላል ቢባልም በርካታ ክለቦች እሱን ፈላጊ […]

Continue reading …
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች  ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተደርገዋል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች  ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተደርገዋል:: በውጤቱም: መቐለ 70 እ. ፋሲል ከነማን 1ለ0 ሲያሸንፍ ጅማ አባ ጅፋር እና ድሬዳዋ ከተማ 3-3 ሲለያዩ ባህር ዳር ከተማ ስሑል ሽረን 2ለ0 አሸንፏል:: በትናንትናው ዕለት በተደረጉ ጨዋታዎች አዳማ ከተማ 0-0 ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲለያዩ  ደደቢት በሜዳውና በደጋፊው ፊት በመከላከያ 3ለ0 ተሸንፏል:: በአዲስ አበባ የተደረገው ወላይታ ድቻ እና […]

Continue reading …
ዛሬ በዱባይ በተካሄደው ማራቶን ኢትዮጵያዊያን ድል ቀናቸው፣ ጌታነህ ሞላ የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል

ዱባይ በተካሄደው የማራቶን ውድድር በወንዶች አትሌት ጌታነህ ሞላ 2 ሰአት ከ ደቂቃ ከ34 ሰከንድ የሆነ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ሲያሸነፍ፤ ሂርጳሳ ነጋሳ ሁለተኛ፤ እንዲሁም አሰፋ መንግስቱ ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡   ከ5 እስከ 9 ያለውን ደረጃም የያዙት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሆነዋል፡፡  በሴቶች በተካሄደው ውድድር ኬንያዊቷ ሩት በአንደኛ ስትወጣ እሷን በመከተል ወርቅነሽ ደገፋ ሁለተኛ፤ ወርቅነሽ ኢዶሳ ሶስተኛ፤ ዋጋነሽ መነካሻ […]

Continue reading …
ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አሳፍሮ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በማምራት ላይ ያለ አውቶብስ…

ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አሳፍሮ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በማምራት ላይ ያለ አውቶብስ ተገልብጦ በሰው ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል። የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎቹ ትናንት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት በባህርዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ መካከል ከተደረገው ጨዋታ በኃላ ወደ ጎንደር እየተመለሱ ጣራ ገዳም በሚባል አካባቢ ሲደርሱ ነው የመኪና አደጋው ያጋጠማቸው። በአደጋውም የሁለት ደጋፊዎች […]

Continue reading …
አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን አከባቢውን በመወከል የቦርድ አባል ሆና ተመረጠች

አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን አከባቢውን በመወከል የቦርድ አባል ሆና ተመረጠች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ደራርቱ ባዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን የቦርድ አባላት ምርጫ ም/ፕሬዝዳንት ሆና መመረጧን ከአትሌቲክስ ፌደሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Continue reading …
ፋሲል 1 ወልዋሎ 0

ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ላይ በትግራይ ስታድየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ፋሲል ወልዋሎን 1ለ0 አሸንፏል፡፡ ለፋሲል የማሸነፊያ ግቧን 57ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው ያሬድ ባየህ ነው፡፡ ፋሲል ከነማ ባለፈው እሁድም ሆነ ዛሬ በመቀሌ ያደረገው ጨዋታ በሰላም ተጠናቋል:: በስታዲየሙ የተገኙ የትግራይ ክለብ ደጋፊዎች ፋሲል ከነማም ኳስ ሲይዝ ሲያበረታቱ እንደነበር ከስፍራው የሚመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

Continue reading …
የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ከወልዋሎ ጋር ላለበት ጨዋታ መቀሌ ሲደርስ ደማቅ አቀባባበል አቀባበል ተደረገለት

የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ከወልዋሎ ጋር ላለበት ጨዋታ መቀሌ ሲደርስ ደማቅ አቀባባበል አቀባበል ተደረገለት::  የጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ከወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ጋር ለመጫዎት ከአንድ አመት በኅላ ነው ወደ መቀሌ  ያመራው:: ላለፈው አንድ ዓመት የአማራና የትግራይ ክልል ክለቦች የሚገናኙባቸው የፕሪምየርሊግ ጨዋታዎች በገለልተኛ ሜዳዎች ሲደረጉ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን የሁለቱ ክልሎች ክለቦች እርስ በ እርስ […]

Continue reading …
ትላንት በደጋፊዎች መሃከል በተነሳ ረብሻ የተቋረጠው የቅዱስ ጊዮርጊስና የሃዋሳ ከነማ ጨዋታ ዛሬ በዝግ ስታደየም ተደርጓል

  ትላንት በደጋፊዎች መሃከል በተነሳ ረብሻ የተቋረጠው የቅዱስ ጊዮርጊስና የሃዋሳ ከነማ ጨዋታ ዛሬ በዝግ ስታደየም ተደርጓል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው በዚህ ግጥሚያም ሁለቱም ክለቦች ምንም ጎል ሳያስቆጥሩ ዜሮ ለዜሮ ተለያይተዋል፡፡ ሀዋሳዎች አንጫወትም ብለው ወደሃዋሳ ጉዞ ጀምረው የነበረ ቢሆንም ፌዴሬሽኑ ካልተጫወቱ ፎርፌ እንደሚሰጥ በማስታወቁ ከዝዋይ ተመልሰው እንደተጫወቱ ለመረዳት ችለናል፡፡

Continue reading …
“በጨዋታው በርካታ ለጎል የሚሆኑ እድሎችን አግኝተን የነበረ ቢሆንም ተጨዋቾቼ አልተጠቀሙበትም”

ትላንት ጅማ አባ ጅፋርን 2 ለ ምንም ያሸነፈው የግብፁ አልሃሊ ክለብ አሰልጣኝ ሞሃመድ ዩሱፍ በርካታ ግቦችን ባለማግባታቸው መቆጨታቸውን ገለፁ፡፡ አህራም ኦንላይን እንደዘገበው ከጨዋታው በኋላ መግለጫ የሰጡት አሰልጣኙ ‹‹ያገኘነው ውጤት ጥሩ ቢሆንም ከቀጣዩ የመልሱ ግጥሚያ በፊት ማለፋችንን ለማረጋገጥ በርከት ያሉ ግቦችን እንደምናገባ ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹በጨዋታው በርካታ ለጎል የሚሆኑ እድሎችን አግኝተን የነበረ ቢሆንም ተጨዋቾቼ […]

Continue reading …
ጋናዊው የእግር ኳስ ተጨዋች በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እየተፈለገ ነው

ኪንግ ፋይሳል የተሰኘው የጋና ክለብ አጥቂ የነበረው ሞሪሰን ኦሲይ በተቃጠለ ቪዛ አገር ውስጥ በመቆየቱና በሆቴል እዳ በኢትዮጵያ ፖሊስ እየተፈለገ ነው፡፡ ራሱ ተጨዋቹ ለጋና ጋዜጦች እንዳስታወቀው ከኢትዮጵያ ቡና ክለብ ጋር የነበረው ኮንትራት ከተቋረጠ በኋላ ላለፉት ጥቂት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል፡፡ ሲናገርም ‹‹እኔ ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ኢትዮጵያ ቡና ክለብን ለመቀላቀል ነበር፡፡ ነገር ግን እኔን ያስፈረሙኝ ሰርቢያዊው አሰልጣኝ […]

Continue reading …
ድንገት ያረፉት የደደቢቱ ዋና አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ አስከሬን እየተመረመረ ነው

(ዘ-ሐበሻ) የደደቢቱ ዋና አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ትላንት ምሽት በገጠማቸው ድንገተኛ ህመም ማረፋቸውን ተከትሎ አስከሬናቸው በምኒልክ ሆስፒታል እየተመረመረ መሆኑ ታወቀ:: ምሽት 06:00 ገደማ ከጓደኞቸቻው ጋር በነበሩበት ሰአት በተሰማቸው የህመም ስሜት ወደ ጎፋ ጤና ጣብያ ተጉዘው ህክምና ካደረጉ በኋላ የህመም ስሜቱ ሲባባስ ለድጋሚ ህክምና ሀሌሉያ ሆስፒታል ሲደርሱ ህይወታቸው ማለፉን ከክለቡ የቅርብ ሰዎች ሰምተናል። የአሰልጣኙ አስከሬን ለምርመራ ምኒልክ […]

Continue reading …
አሰግድ ተስፋዬ እየታሰበ ነው

(ዘ-ሐበሻ)  የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ቡድን ተጫዋች የነበረው አሰግድ ተስፋዬ ልክ የዛሬ ዓመት በዛሬው ዕለት ከልምምድ መልስ በመታጠቢያ ቤት ውስጥ ወድቆ በአርባ ሰባት ዓመቱ በድንገት ሕይወቱ ያለፈው:: ሥርዓተ ቀብሩም በነጋታው በቅድስት ሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል:: አሰግድ ተስፋዬ በ1962 ዓ.ም. በድሬዳዋ ከተማ ነበር የተወለደው። እድገቱም በዚያው በድሬዳዋ ከተማ ልዩ ስሙ ደቻቶ […]

Continue reading …
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሊቨርፑል ደጋፊዎች ደረሰላቸው

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ውድድር ዛሬ ምሽት ሊቨርፑልና ሪያል ማድሪድ ኬቭ ላይ ይፋለማሉ፡፡ የቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜን ውድድር ለመከታተል ደጋፊዎች በዩክሬን ዋና ከተማ ኬቭ መከተማቸው ተነግሯል፡፡ የዘንድሮውን የቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ሪያል ማድሪድ የሚያነሳ ከሆነ ለአስራ ሶስተኛ ጊዜ ሲሆን፥ እንዲሁም ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ለማሸነፍ ነው የሚፋለመው፡፡ ሊቨርፑል ዋንጫውን የሚያነሳ ከሆነ ደግሞ በታሪኩ ለስድስተኛ ጊዜ ያነሳ ተብሎ ታሪክ […]

Continue reading …
Page 1 of 19123Next ›Last »